ዝክረ ቅዱሳ ዝርዝር
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Sep 01, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤3🥰3😍3😘3
•➢ ጳጉሜን ለምን እንጠመቃለን እና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል 👇👇👇
Sep 01, 2026•➢ ጳጉሜን ለምን እንጠመቃለን እና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል 👇👇👇
❤3🥰3😘3😍2
ነሐሴ ፳፮፦
Aug 31, 2026ነሐሴ ፳፮፦
✝ለሣራ ሰላም ለአብርሃም ብእሲቱ፤
ወለርብቃ ሰላም ለያዕቆብ ወላዲቱ፤
ኢየሱስ ሞዐ ወሀብተ ማርያም መጽሐፈ ዕልወት ዘአስተቱ፤
ሞይስስ ገዳማዊ ወሣራ እህቱ፤
ዘምስለ አጋቦስ ወቴክላ ጽዑራነ ዘሞቱ!
✝እንኳን አደረሰን !
🌷አርኬ (ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
🥰2
✝✝✝ ከግራ ወደ ቀኝ
Aug 31, 2026✝✝✝ ከግራ ወደ ቀኝ
#ቅዱስ_አብርሃም
#ብጽዕት_ሣራ
#ቅዱስ_ሙሴ ሊቀ ነቢያት:: ✝✝✝
✝ በረከታቸው ይብዛልን::
🥰1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 31, 2026በአንደኛውም ቀን አቡነ ሀብተ ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ሆነው ሲሄዱ ብዙ አጋንንት እየተደነባበሩ ወደ ታች ሲወርዱ ተመለከቱና አባታችን ሥራቸውን ለማየት ተከተሏቸው፡፡ አንዱንም ኃጥእ ይዘው ነፍሱን ከሥጋው ለዩዋትና ወደ ሲኦል አወረዷት…
Aug 31, 2026በአንደኛውም ቀን አቡነ ሀብተ ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ሆነው ሲሄዱ ብዙ አጋንንት እየተደነባበሩ ወደ ታች ሲወርዱ ተመለከቱና አባታችን ሥራቸውን ለማየት ተከተሏቸው፡፡ አንዱንም ኃጥእ ይዘው ነፍሱን ከሥጋው ለዩዋትና ወደ ሲኦል አወረዷት፡፡ አባታችንም ከሌሎቹ ቅዱሳን ጋር ሆነው ያችን ነፍስ ይምርላቸው ዘንድ ጌታችንን በጸሎት ማለዱት፡፡ ነገር ግን ‹‹ለጣዖት ስትሰግድ ስለኖረች ይህችን ነፍስ አልምራትምና አትድከሙ›› የሚል ቃል ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መጣላቸው፡፡ ቅዱሳኑም ‹‹ልመናችንን የማትቀበል ከሆነ በከንቱ ሰብስበኸናል›› ብለው ቢያዝኑ እግዚአብሔርም ‹‹ሕገ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ቅጣት እንድታዩ ነው›› አላቸው፡፡ እነርሱም ሕገ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ሲቀጣቸው ለደጋጎቹ ሰዎች ደግሞ መልካሙን ዋጋቸውን ሲሰጣቸው አይተው አንድ ሆነው አመስግነውታል፡፡
ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ራጉኤል አንዱን ሰው በመብረቅ ቀሰፈውና ቅዱስ ሚካኤል ሄዶ ቅዱስ ራጉኤልን ሲከራከረው አባታችን ተመለከቱ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹የእኔ አገልጋይ ነውና ለምን ገደልከው?›› ሲለው ቅዱስ ራጉኤልም ‹‹ሰንበት ሳይለይ ዝሙትን መሥራት የለመደ ሥራውም ዝሙት ስለሆነ በፈጣሪዬ ታዝዤ ነው የገደልኩት፡፡ ኃጥአንን ሊያጠፋ እንጂ ጻድቃንን ለመቅጣት መብረቅ እንዳይታዘዝ አንተስ ታውቅ የለም እንዴ?›› አለው፡፡ ይህንንም ተባብለው ከሥላሴ ፊት ሰግደው ቅዱስ ሚካኤል የተገባለትን ቃልኪዳን በማሳሰብ ምልጃውን አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም በጎና ክፉ ሥራዋን ባስመዘነ ጊዜ በጎ ሥራዋ ስለበለጠ ቅዱስ ሚካኤል ያችን ነፍስ ታቅፎ ወስዶ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠው፡፡ ሰባቱም ሊቃነ መላእክት እየተቀባበሉ ወስደው ከመስቀል ዘንድ አደረሷት፡፡ ለቅዱስ መስቀልም ካሰገዷት በኋላ አሳልመዋት በቅዱስ ሚኤካል አማላጅነት ወደ ገነት አስገቧት፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም ይህን በተመለከቱ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹መስቀል ታሳልሟት ዘንድ ያችን ነፍስ ወደ መስቀል ለምን ወሰዳችኋት?›› ብለው ጠየቁት፡፡ መልአኩም ‹‹በትልቅም በትንሽም ነገር ክርስቲያናዊትን ነፍስ የሚቃወም ቢመጣባት ድል የምትነሳበትን በመስቀል ፍርድ ይታይላታልና ስለዚህ ነው፡፡ የሚከራከራት ቢኖር ግን እንዳየኸው ወደ መስቀል ባደረሷት ጊዜ የሚቃወማት ሰይጣን ፈጥኖ ይርቅላታል ዳግመኛም ሊከራከራት አይችልም›› አላቸው፡፡
ከአቡነ ሀብተማርያም በረከት ለመቀበል ብዙ ቅዱሳን ከሮም፣ ከግብፅ፣ ከአስቄጥስና ከሲሐት ገዳም ወደ አባታችን ዘንድ ይመጡ ነበር፤ ከየሀገራቸውም በአንበሳ ተቀምጠው የሚመጡ አሉ፤ ክንፍ ተሰጥቷቸው እንደ ንስር የሚበሩም አሉ፤ ብፁዕ አቡነ ሀብተ ማርያምም የቅዱሳኑን ብቃት አይተው ‹‹ሥራችሁ እንዲህ እንዲህ ሲሆን ለምን ወደኔ መጣችሁ?›› ብለው ሲጠይቋቸው ቅዱሳኑም ‹‹በማንኛውም ሥራ እግዚአብሔርን በለመነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሚኖር እንደ ሙሴ ያለ ሀብተ ማርያም የሚባል ወዳጄ አለና ሁሉን ስለሚነግራችሁ ዘወትር እርሱን ጠይቁ ብሎ ስላዘዘን ወደ አንተ መጣን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ቅዱሳኑን ከባረኳቸውና ከእነርሱም ከተባረኩ በኋላ አባታችን ለቅዱሳኑ የሚመጣውን እንዳለፈ የሚደረገውንም እንደተደረገ አድርገው ይነግሯቸዋል፡፡ ቅዱሳኑም ከልጅነታቸው ጀምረው እስከዚያች ቀን ድረስ የሠሩትን ሥራ ሁሉ ይነግሯቸዋል፡፡ እነርሱም እጃቸውን እየሳሙ በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ እንደዚሁም አቡነ ሀብተ ማርያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየተራዱዋቸው ቀድሰው በሚያቆርቡ ጊዜ ተሰውረው የሚኖሩ 500 ስውራን ቅዱሳን መጥተው ሥጋ ወደሙን ከአባታችን እጅ ተቀበሉ፡፡ ቀድሰውም ወደበዓታቸው እንደገቡ እመቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹በነገውም ዕለት ቅዳሴዬን ቀድስ፣ ይህም ቅዳሴ መዓዛ ቅዳሴ ነውና፡፡ የዓለም መሠረት ማርያም ወደኔ ነይ ብለህ በጠራኸኝ ጊዜ ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትዬ መጥቼ እባርክሃለሁ›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በነገው ዕለት ሌላ ተረኛ ቄስ ይቀድሳልና ይህ እንዴት ይሆንልኛል?›› አሏት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ፈቃዴ ስለሆነ አንተ እንድትቀድስ አደርጋለሁ›› አለቻቸው፡፡ በነጋታው ተረኛው ቄስ ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ቸኩሎ እየተፋጠነ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገሰግስ ወድቆ ጥርሱ ደማና ስለ ሥጋ ወደሙ ቅዳሴ እጅግ ደንግጦ ወደ አባታችን መጥቶ ‹‹ቅዳሴው በእኔ ስም ከሚታጎል አንተ ቀድስልኝ›› አላቸው፡፡ አባታችንም አስቀድማ እመቤታችን የነገረቻቸውን ነገር አስበው እያደነቁ ሄደው ቀደሱ፡፡ እመቤታችንም ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትላ መጥታ ባረከቻቸው፡፡
† ነሐሴ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ብጽዕት ሣራ (የአብርሃም ሚስት)
2.ቅዱሳን አባ ሞይስስና እህቱ ሣራ (ሰማዕታት)
3.ቅዱሳን አጋቦስና ቴክላ (ሰማዕታት)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
🥰7❤2😍2😘2
መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም አባታችንን እንደ ጓደኛ ሆኖ ዘወትር ይጎበኛቸው ነበር፡፡ ቅዱሳን አባታቸንን ሊጎበኟቸው መጥተው ከደጅ ቆመው እንደሆነ ቅዱስ ሚካኤል አባታችንን ‹‹እከሌ ጉዳዩ እንዲህ ነው እንዲህ ብለህ ተናገረው…›› እያለ ያማክራ…
Aug 31, 2026መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም አባታችንን እንደ ጓደኛ ሆኖ ዘወትር ይጎበኛቸው ነበር፡፡ ቅዱሳን አባታቸንን ሊጎበኟቸው መጥተው ከደጅ ቆመው እንደሆነ ቅዱስ ሚካኤል አባታችንን ‹‹እከሌ ጉዳዩ እንዲህ ነው እንዲህ ብለህ ተናገረው…›› እያለ ያማክራቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ቅዱስ ሚካኤል ካዘዛቸው በቀር ምንም አይሠሩም ነበር፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንም ባነበቡ ጊዜ ኃይለ ቃሉን እየተረጎመ ምሥጢራትን ይነግራቸዋል፤ የተሰወረውንም ይገልጥላቸዋል፡፡ ከእንስሳት ጩኸት ጀምሮ ከዱር አራዊት ድምፅና እስከ አእዋፍ ቋንቋ ያለውን ያስረዳቸው ነበር፡፡
ይኸውም መልአክ አንድ ቀን አቡነ ሀብተ ማርያምን ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገብቷቸው ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ተዘጋጅተው ሳለ ወንጌል የሚነበብበት ሰዓት ሲደርስ ያልተማረ ቄስ የክርስቶስ ጌትነቱን የምትናገር ወንጌልን ሲያነብ ‹‹ወዮሴፍ ብእሲሃ ለማርያም ጻድቅ ውእቱ›› የሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ አባታችን ሲሰሙ እጅግ ደንግጠው ወንጌል ወደሚነበብበት ስፍራ ሄደው የሚያነበውን ቄስ ገሠጹት፡፡ ‹‹ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጻድቅ ውእቱ በል እንጂ ብእሲሃ አትበል›› ብለው መከሩት፡፡ ቄሱም አቡነ ሀብተ ማርያም እንዳዘዙት ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ይህን ጊዜ ጌታችን ለአባታችን ድጋሚ ተገልጦላቸው ‹‹ሀብተ ማርያም ሆይ ይህን ትምህርትህን ወድጄ አመሰገንኩህ፣ የእናቴን የድንግል ማርያምን የድንግልናዋን ንጽሕና ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ‹‹አሁንም ዮሴፍ ብእሲሃ ለማርያም የሚሉትን ሁሉ ለያቸው እንጂ አትተዋቸው፤ እንዲህ የሚል ጽሑፍም ብታገኝ እንዳይኖር እርሱን ፍቀህ ፈሃሪሃ ለማርያም የሚለውን ጻፍ›› ብሎ አባታችንን ካዘዛቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አባታችንም በዚህ ጊዜ ፊታቸው ላይ ብርሃን ስለተሳለባቸውና እንደ ፀሐይ ስላበራ ሰዎችም አይተው ባደነቁ ጊዜ ወደ በዓታቸው ገቡና ጌታችንን ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ በሰው ፊት ክብሬን አትግለጥብኝ ሰውርልኝ፣ በቸርነትህም አድነኝ›› ብለው ጸለዩ፡፡ እንዲህም ብለው በጸለዩ ጊዜ ፊታቸው መልኩ ተለውጦ እንደ ቀድሞው ሆነ፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባታችን ታመው ተኝተው ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ መጥተው ሥጋ ወደሙን አቀብለዋቸዋል፡፡፡ አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወደ ሰማይ ወስዶ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት፣ መንግስተ ሰማያትን እንዲሁም ኃጥአን የሚኖሩበትን ሲኦልን አሳያቸው፡፡ በገነት ያሉትንም ከአዳም ጀምሮ እሳቸው እስካሉበት ጊዜ እስከ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ድረስ ያሉትን ቅዱሳን አሳያቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆመው ሳለ ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመና ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ በሀብተ ማርያም ላይ እንደ ኢዮብ ብዙ መከራ አጸናበት ዘንድ ፍቀድልኝ›› ብሎ እየጮኾ ሲናገር አባታችን እጅግ ፈርተው አለቀሱ፡፡ እግዚአብሔር ግን በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ ‹‹በነፍሱም በሥጋውም መከራ ታጸናበት ዘንድ አልፈቅድም›› አለው፡፡ ‹‹እኔ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንጽሕናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሠራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ፤ በእርሱ ላይ ማሰልጠንስ ይቅርና በሀብተ ማርያም ጸሎት በተማጸነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሠለጥንህም›› አለው፡፡ ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከእርሳቸው በኋላ በመንበራቸው ከተሾሙት ከስምንቱ መምህራን ጋር ለሀብተማርያም ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ኤልሳዕ፣ ፊሊጶስ፣ ሕዝቅያስ፣ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ዮሐንስ ከማ፣ እንድርያስና መርሐ ክርስቶስ ናቸው፡፡ እነዚህም መልካቸው እንደ ፀሐይ ያበራ ልብሳቸው እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ልብሳቸው የእሳት ላንቃ የከበበው መልኩም ነጭ የሆነ የሚያስደንቅ ሆኖ ‹‹በቅድምና ለነበረ ለአብ በቅድምና ለነበረ ለወልድ በቅድምና ለነበረ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል›› እያለ ልብሳቸው በሰው አንደበት ያመሰግን ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም አቡነ ሀብተ ማርያምን ‹‹ልጄ ሀብተ ማርያም ሆይ! ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ›› አሏቸው፡፡
አቡነ ሀብተ ማርያምም ‹‹ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው?›› ሲሏቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ‹‹አባቴ ሆይ ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ?›› አሏቸው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው እነዚህም አንዱ መብረቅ ነው፤ ሁለተኛውም ቸነፈር ነው፤ ሦስተኛውም ረሃብ ነው፤ አራተኛውም ወረርሽኝ ነው፤ አምስተኛውም የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለች›› አሏቸው፡፡
አቡነ ሀብተ ማርያምም ‹‹ንዑድ ክቡድ የምትሆን አባቴ ሆይ ልዩ ክቡር በሚሆን በአንተ አጽም መቀበር ያልዳነች በእኔ አጽም መቀበር ድኅነት ታገኛለችን? ይህንስ ተወው›› ብለው በተከራከሯቸው ጊዜ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልሰው ‹‹ልጄ ሀብተ ማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው፡፡ ይልቁንስ እንዳልኩህ በተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበርልኝ ቃልኪዳን ግባልኝ›› ብለው ማለዷቸው፡፡ ይህንንም ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣላቸው፡- ‹‹ከወዳጄ ከሀብተ ማርያም አንደበት ይህ ቃልኪዳን አይወጣም፣ ዳግመኛም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ! እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለምና እኔ ከተቀበርኩበት እንድትቀበር ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው? እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ›› የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመኑናና እየሰገዱ ከሥላሴ ዙፋን ፊት ተንበረከኩ፡፡ ሦስተኛውም ‹‹ይሁን እንዳልከው ይቀበርልህ›› የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ዳግመኛም ‹‹በአንተም አጽም በሀብተ ማርያምም አጽም ቦታህ ከመቅሰፍታት ትዳንልህ፤ ልጆችህ ግን በቸነፈር ደዌ ቢሞቱ ከሰማዕትነት ተቆጥሮላቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ በራሴ ምዬ ቃልኪዳን ገብቼልሃለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት እጅግ ደስ ተሰኝተው ሦስት ጊዜ ሰገዱ፡፡
ከዚህም በኋላ መልአኩ ለአቡነ ሀብተ ማርያም ክብሯ እንደ ጽርሐ አርያም የሆነች አገርን አሳያቸው፡፡ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውም ቅዱሳን መላእክት በውስጧ ተድላ ደስታ ያደርጉባት ነበር፡፡ አባታችንም መልአኩን ‹‹ይህች ክብሯ ፍጹም የሆነችን አገር ማን ትባላለች በውስጧ ለመኖር በእጅጉ ወድጃለሁና›› ብለው ሲጠይቁት መልአኩም ‹‹ይህችማ አገር የአባትህ የተክለ ሃይማኖት አጽም ያረፈባት ደብረ ሊባኖስ ናት፤ ከእርሱም ጋር በክብር እስክትነሣ ድረስ በውስጧ ትቀበርባት ዘንድ ለአንተም ተሰጥታሃለችና ደስ ይበልህ፡፡ አባትህም እንደ ኢየሩሳሌም እንደትሆንለት ቃልኪዳን ተቀብሎባታል›› አላቸው፡፡
😘6🥰3😍3❤2🎉2
ከዕለታትም በአንደኛው ዕለት አባታቸን በጎችን ሲጠብቁ ሌሎች እረኞች በአመጻ ከሰው ሰርቀው ቆርጠው ያመጡትን እሸት ‹‹ና እንብላ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ከየት እንዳመጣቸሁት ምንም ስለማላውቅ አልበላም›› አሏቸው፡፡ እረኞቹም ሀብተ…
Aug 31, 2026ከዕለታትም በአንደኛው ዕለት አባታቸን በጎችን ሲጠብቁ ሌሎች እረኞች በአመጻ ከሰው ሰርቀው ቆርጠው ያመጡትን እሸት ‹‹ና እንብላ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ከየት እንዳመጣቸሁት ምንም ስለማላውቅ አልበላም›› አሏቸው፡፡ እረኞቹም ሀብተ ማርምን በቁጣ ዐይን እያዩአቸው ተቀምጠው ሲበሉ አባታችን ‹‹የማንችለው ዝናብ መጥቷልና ተነሡ በፍጥነት ወደቤታችን እንሂድ›› አሏቸው፡፡ እረኞቹም ‹‹ሰማዩ ብራ ነው ምንም ደመና የለውም፤ ነፋስም አይነፍስም፡፡ እኛ የማናየው አንተ ብቻ የምታየው ምን ነገር አለ?›› እያሉ በአባታችን ላይ ተዘባበቱባቸው፡፡ አባታችን ግን በጎቻቸውን እያስሮጡ በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሄዱ፡፡ ወዲያውም በጣም ኃይለኛ ዝናብ ዘነበ፡፡ የጥፋት ውኃው በላያቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ እነዚያን እረኞች ከቦታቸው አልተነቃነቁም ነበርና በጥፋቱ ውኃ አለቁ፡፡ በዚያችም ሌሊት አቡነ ሀብተ ማርያን ከሰማይ ሦስት ጊዜ ‹‹ሀብተ ማርያም ሀብተ ማርያም›› የሚል ድምፅ ጠራቸው፡፡ አባታችንም እንደ ሳሙኤል ‹‹ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር›› ሲሉ ጌታችን አናገራቸው፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ለሚሰሙህ ለመረጥኳቸው ቃሌን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔም ጋር በምሥጢር በባለሟልነት ትነጋገር ዘንድ መርጨሃለሁ›› አላቸው፡፡
ከጥቂት ቀንም በኋላ አባታችን በጎችን እየጠበቁ ሳሉ አንድ አመጸኛ መጣና በትራቸውን በኃይል ነጥቆ ወሰደባቸው፡፡ አቡነ ሐብተ ማርያምም ‹‹በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ እቋቋምህ ዘንድ ኃይል የለኝምና በትሬን መልስልኝ›› ቢሉት የትዕቢትን ቃል ተናገራቸው፡፡ አባታችንም ‹‹እምቢ ካልክስ እሺ የእግዚአብሔርን ኃይል ታያለህ›› አሉት፡፡ ወዲያም ያ አመጸኛ ላዩ ታች፣ ታቹ ላይ፣ ግራው ቀኝ፣ ቀኙ ግራ ሆኖ በአየር ላይ ተሰቅሎ ዋለና እየጮኸ አባታችንን ለመናቸው፡፡ አባታችንም ‹‹የቀጣህ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ›› ባሉት ጊዜ ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ፡፡ በዚያ የነበሩና ይህንን ተአምር ያዩ እረኞችም እጅግ ፈርተው ሄደው ለወላጆቻቸው ያዩትን ተናገሩ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ‹‹ቀድሞ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያለ ሲጸልይ ሲሰግድ አይተነዋል አሁንም ጠላቱን በነፋስ የሚቀጣ ይህ ልጅ ወደፊት ምን ይሆን!›› እያሉ አደቁ፡፡ ወላጆቻቸውም ይህን በሰሙ ጊዜ በግ ጠባቂነቱን አስተዋቸውና ወስደው ለመምህር ሰጧቸው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ በሚገባ ተማሩ፡፡
ከዚህም በኋላ አባታቸው ከሀገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አንዷን እጮኛ አጨላቸው፡፡ ነገር ግን አቡነ ሀብተ ማርያም ‹‹አባቴ ሆይ እኔ ራሴን ለክርስቶስ በድንግልና ለመኖር አጭቻለሁ፣ ተራክቦዬም ቃለ ወንጌልን መስማት እንጂ ሌላ አይደለምና ለምን እንዲህ ትለኛለህ?›› አሉት፡፡ አባታቸውም ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ ያለ አቡነ ሀብተ ማርያም ፈቃድ ሙሽራይቱን ለማምጣት ሄደ፡፡ አባታችን ግን ሀገር ጥለው ለመሰደድ ከቤት ተደብቀው ወጡ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በመብረቅ አምሳል አባታቸውን ገስጻቸውና በዚህ ድንጋጤ ምክንያት ከዚህ ኃላፊ ዓለም ዐረፈ፡፡
አባታችንም የአባታቸውን ዕረፍት ሳያዩ አፋር ወደምትባል ሀገር ሄደው አባ ሳሙኤል ከሚባል ደግ መነኩሴ ቦታ ገብተው መነኩሴውን እያገለገሉት ኖሩ፡፡ አንድ ቀን አባታችን እንስራ ተሸክመው ውኃ ይቀዱ ዘንድ ወደ ወንዝ ወረዱና ውኃውን ቀድተው ሲመለሱ ድንጋይ አደናቀፋቸውና እንስራው ከላያቸው ላይ ወደቀ፡፡ ነገር ግን መሬት ከመድረሱ በፊት አባታችን ፈጥነው የጌታችን ስም በጠሩ ጊዜ እንስራው ወድቆ ሳይሰበር ተመልሶ በትከሻቸው ላይ ተቀመጠ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይከተሏቸው ነበርና ይህን ጽኑ ተዓምር አይተው እጅግ አደነቁ፡፡
እንዲሁ ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበሩ ሳለ መብራቱ ከእጃቸው ላይ ወድቆ ጠፋ፡፡ መምህሩም አባ ሳሙኤል ቁጡ ነበረና ስለ መምህራቸው ቁጣ በጣም ደንግጠው ወድቆ የጠፋውነ መብራት ፈጥነው ባነሱት ጊዜ መብራቱ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በርቶ ታየ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይቶ እጹብ እጹብ በማለት ‹‹የዚህ ቅዱስ ልጅ መጨረሻ ምን ይሆን?›› ብሎ ካደነቀ በኋላ ‹‹የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል›› ሲል ትንቢት ተናገረላቸው፡፡ እመቤታችን ለአባ ሳሙኤል ተገልጣላቸው የአቡነ ሀብተ ማርያምን ክብር ነግራዋለች፡፡ አባታችንም አባ ሳሙኤልን 12 ዓመት ከትሕትና ጋር እየታዘዙ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ኖረው ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥተው ሄደው እለ አድባር በተባለ ገዳም መኖር ጀመሩ፡፡ ከቦታውም ደርሰው ጥቂት ከቆዩ በኋላ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበሉ፡፡ ይኸውም የሚዳው አቡነ መልኬጼዴቅ በደጃቸው የተቀበረውን ሰው አፈር የማያስበሉት ጻዲቅ ናቸው፡፡ ይህንንም የጻድቃኑን አባትና ልጅነታቸውን መሠረት በማድረግ የይሰበይ አቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ካህናት፣ መሪጌቶችና ዲያቆናት ግንቦት 4 ቀን ወደ ሚዳ መራቤቴ በመሄድ የአቡነ መልኬጼዴቅን በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ ያከብራሉ፡፡
አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንት አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡ አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡ በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ መዝሙረ ዳዊት፣ አራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡
ከዚህም በኋላ ወደ ምሥራቅ ሄደው ጎሐርብ ወደምትባል ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም በዓት አጽንተው ሲጸልዩ ጌታችን ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን›› አላቸው፡፡ ያን ጊዜ አባታችን ከፈጣሪአቸው ግርማ የተነሳ ደንግጠው ከመሬት ወድቀው እንደ በድን ሆኑ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አጸናቸውና ‹‹የመጣሁት ለጸናህ ነው ሰውነትህንም እንደ ንስር ላድሳት ነው እንጂ ላጠፋህ አይደለም፡፡ ድካምህና ገድልህ ሁሉ ለዘለዓለም መታሰቢያ ሊሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተጽፎልሃል ብዬ በእውነት እነግርሃለሁ፡፡ ለአንተ ለወደድኩህና ለመረጥኩህና ወዳጄ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ተጭነህ ወደምትሄድበት ቦታ የሚያደርስህ የብርሃን ሰረገላ ሰጥቼሃለሁ፡፡ እንደ አንተም ካሉ በዋሻ በመሬት ፍርኩታ ከሚኖሩ ከመረጥኳቸው ቅዱሳን ጋር ትገናኝ ዘንድ ወደ አራቱም አቅጣጫ ትበር ዘንድ የብርሃን ሠረገላ ሰጥቼሃልሁ፡፡ ዳግመኛም የሉቃስንና የዮሐንስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄድ ዘንድ የእሳት ሠረገላ ሰጥቼሃለሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ፡፡ አንተን ገድልህንና ቃል ኪዳንህን የናቀውን ያቃለለውን ሁሉ ፍጹም መበቀልን እበቀለዋለሁ፡፡ እንደ ወዳጄ እንደ ፊቅጦርም በእናቴ በማርያም ድንግል አተምኩህ›› ካላቸው በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸውና በታላቅ ግርማ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
አባታችንም ከጌታችን ይህን ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነፍሳቸውን ‹‹ነፍሴ ሆይ ከፈጣሪሽ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት አፍ ለአፍ ትነጋገሪ ዘንድ ደፍረሻልና በጎም ሥራ ሳይኖርሽ ከፈጣሪሽ ቃልኪዳን ተቀብለሻልና ከዛሬ ጀምሮ እንደ መላእክት ዘወትር አትተኝ›› እያሉ ተጋድሏቸውን አብዝተው ቀጠሉ፡፡
❤6🥰6😍2😘2
ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሠረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብፃዊ ጻድቅ ናቸው፡፡ ሐይቅን አባ ሰላማ ካልዕና ዐጼ ድል ነአድ በ862 ዓ.ም ነው የቆረቆሩት። ገዳሙን ካቀኑት በኋላ ‹‹የማንን ታቦት እ…
Aug 31, 2026ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሠረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብፃዊ ጻድቅ ናቸው፡፡ ሐይቅን አባ ሰላማ ካልዕና ዐጼ ድል ነአድ በ862 ዓ.ም ነው የቆረቆሩት። ገዳሙን ካቀኑት በኋላ ‹‹የማንን ታቦት እናስገባ?›› ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ የቅዱስ እስጢፋኖስንና የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ታቦት አገኙ፡፡ በላዩም ላይ ‹‹ይህንን ታቦት በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ታዘው የላኩት ነው›› የሚል ጽሑፍ አገኙ፡፡
ይህ ከሆነ ከ400 ዘመን በኋላ ነው አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ወደዚህ ቦታ የመጡት፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ለ52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ሥራቸውን እየሠሩ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ አባ ኢየሱስ ሞዐ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመገልበጥና በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ በዚሁ ገዳም ውስጥ የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ትምህርት ቤት በማቋቋም 800 መነኮሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ ሾመው በመላ ሀገራችን እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል፡፡
ከእነዚህም ተማሪዎቻቸው መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ደብረ ሊባኖስ)፣ አቡነ ኂሩተ አምላክ (ጣና ሐይቅ ዳጋ እስጢፋኖስ)፣ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቦረና)፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል (ቦረና)፣ አቡነ ገብረ እንድርያስ (ቦረና)፣ አቡነ ሕዝቅያስ (ቦረና)፣ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዳውንት)፣ አቡነ አሮን (መቄት- ጣራው ክፍት የሆነው)፣ አቡነ ተክለ ኢየሱስ ሞዐ (ሐይቅ)፣ አቡነ አላኒቆስ (ትግራይ)፣ አቡነ በግዑ (ሐይቅ)፣ አቡነ ሠረቀ ብርሃን (ሐይቅ)፣ አቡነ ብስጣውሮስ (ሐይቅ)፣ አቡነ ዮሴፍ (ላስታ) ዋና ዋናዎቹና በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ጻደቁን ንጉሥ ዐፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸውና ኮትኩተው ያሳደጉት ጻድቁ አባታችን ናቸው፡፡ እነዚህም ልጆቻቸው እያንዳንዳቸው እጅግ አስገራሚ ገድል ያላቸው የከበሩ ቅዱሳን ናቸው፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ ነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ እጅግ በጣም ብዙ መነኮሳትን አፍርተዋል፡፡ የመጀመሪያው መነኩሴ አባ እንጦንስ ነው፡፡ እንጦንስ መቃርስን፣ መቃርስ ጳጉሚስን፣ ጳጉሚስ ቴዎድሮስን፣ አቡነ አረጋዊንና 8ቱን ቅዱሳን አመነኮሱ፡፡ አቡነ አረጋዊም ወደ ኢትዮጵያ በ460 ዓ.ም መጥተው ክርስቶስ ቤዛን፣ አባ ክርስቶስ ቤዛም መስቀለ ሞዐን፣ መስቀለ ሞዐም አባ ዮሐኒን፣ አባ ዮሐኒም አባ ኢየሱስ ሞዐን፣ አባ ኢየሱም ሞዐም አቡነ ተክለ ሃይማኖትን አመነኮሱ፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ምን ያህል ቀደምትና ባለ ታሪክ አባት እንደሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡
በዮዲት ጉዲት እጅጉን ተጐድታ የነበረችው ሀገራችን ዳግም የወንጌሉ ብርሃን እንዲበራባት ሊቃውንት፣ እንዳይታጡባት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይቆነጻጸሉ፣ መነኮሳት አባቶች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወርደው ገዳማትን እንዲያስፋፉ ያደረጉት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ትልቅ ባለውለታ ናቸው፡፡ በተለይም በሐይቅ እስጢፋኖስ ያፈሯቸውን 800 ሊቃውንት በመላዋ ኢትዮጵያ በመሰማራታቸው ዛሬ የምናያቸውን አብዛኛዎቹን ገዳማትና ቅዱሳት መጻሕፍት አቆይተውልናል፡፡ አባታችን ለ45 ዓመታት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምን በአበ ምኔትነት እያስተዳደሩ ከቆዩ በኋላ ኅዳር 26 ቀን 1292 ዓ.ም በዕለተ እሑድ ዐርፈዋል፡፡ ባረፉበት ዕለትም በወቅቱ በቦታው የታየው ብርሃን ሀገሪቱን መልቶ ታይቷል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሀብተ_ማርያም
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ፅንሰታቸው ነው። አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፣ በትሩፋትና በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፉ በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ›› ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡
የአቡነ ሀብተ ማርያም እናት ቅድስት ዮስቴና ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ከመውለዷ በፊት ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል?›› የሚለውን የወንጌል ቃል አስባ መንና ወደ በረሃ የገባች ቢሆንም በበረሃ ውስጥ ከሰው ተለይቶ የሚኖር የበቃ ባሕታዊ በዋሻ ውስጥ አገኘችና ለምነና ወደ በረሃው እንደመጣች ነገረችው፡፡ ባሕታዊውም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ካመለከተ በኋላ ‹‹ምንኩስና ለአንቺ አልተፈቀደልሽም፣ ወደ ቤትሽ ግቢ፣ ከሕጋዊ ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም፣ ሰው ሁሉ የሚማፀነው፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም የሚነገርለት፣ በነፍስም በሥጋም የሚያማልድ፣ እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ የሚሰጠው በምድር ሆኖ መንበረ ጸባኦትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ›› በማለት ትንቢት ከነገራት በኋላ ቅድስት ዮስቴና ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ እርሷም ሀብተ ትንቢት እስከመሰጠት ድረስ የደረሰች በሃይማኖት በምግባር በትሩፋት ያጌጠች ሆነች፡፡
ቅድስት ዮስቴናም ወደ ቤቷ ከተመለሰች በኋላ አቡነ ሀብተ ማርያም ተወለዱና ወላጆቻቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጓቸው፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› እያሉ ሲጸልዩ ሰምተው በልቡናቸው ‹‹ይህች ጸሎት በጣም ጥሩ መልካም ጸሎት ናት፤ እኔ ይህችን ጸሎት መርጫታለሁ፤ በዚህ ጸሎት ዓለም ከአሳችነት ኅሊና በሚመጣውም ዓለም ከገሃነም እሳት እንድንድንባት አውቃለሁ›› አሉ፡፡ ይህችንም ጸሎት ማዘውተር ጀመሩ፡፡ እናትና አባታቸውም በተኙ ጊዜ ሌሊት ለጸሎት ተነሥተው በዚህ ጸሎት ፈጣሪአቸውን ያመሰግኑ ነበር፤ ስግደትን ይሰግዳሉ ነገር ግን እናትና አባታቸው ከእንቅልፋቸው በነቁ በጊዜ ሮጠው ወደ መኝታቸው ሄደው ይተኛሉ፡፡ የጽድቅ ሥራቸውንም ከአምላካቸው በቀር ማንም አያውቅባቸውም ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባታቸው ፍሬ ብሩክ የበግ ጠባቂ አደረጋቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ስውራን ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎች ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያ ቀን እስኪደርስ ድረስ ፈጣሪያችን አቡነ ሀብተ ማርያምን ይጠብቃቸው ነበር፡፡
❤6😍4😘3🕊2🥰1
#ነሐሴ_26
Aug 31, 2026#ነሐሴ_26
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች #ቅድስት_ሣራ መታሰቢያዋ ነው፣ የከበረ #አባ_ሞይስስና_እኅቱ_ሣራ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የከበሩ መነኰሳት #ቅዱሳን_አጋቦስና_ቴክላ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የከበሩ አባቶቻችን #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ እና #አቡነ_ሀብተ_ማርያም የተፀነሱበት ዕለት ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሣራ
ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች ሣራ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶች አዘዙ።
ይቺንም ክብርተ ማሕፀን የሆነች ጡቶቿም የተባረኩ ክብርት ሣራን የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ባል እንዳላት ሳያውቅ በወሰዳት ጊዜ እንዳይቀርባት እግዚአብሔር ገሠጸው በደዌም ቀሠፈው ባሏ አብርሃምም በጸለየለት ጊዜ ከደዌው ተፈወሰ ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘብ ጋራ ወደ ባሏ መለሳት።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ተገልጦ ወደ ቤቷ እንግድነት በመጣ ጊዜ ለአብርሃምም የይስሐቅን መወለድ በነገረው ጊዜ ሣራም በድንኳኑ ውስጥ ሳቀች እንዲህ ስትል እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል።
እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው ሣራን ለብቻዋ ምን አሳቃት እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል እኔም አሁን አርጅቻለሁ ብላ በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን። ከዚህም በኋላ ሣራ ፀንሳ እግዚአብሔር ባለው ወራት በርጅናዋ ለአብርሃም ወንድ ልጅን ወለደች።
ይስሐቅም በአደገ ጊዜ ልጅዋ ይስሐቅን ከእስማኤል ጋራ ሲጫወት አየችው። አብርሃምንም ሣራ እንዲህ አለችው ይቺን ባሪያ ከነልጅዋ አባራት የባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋራ አይወርስምና። ይህም ነገር ለአብርሃም ስለ ልጁ እስማኤል እጅግ ጭንቅ ሆነበት።
እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው የዚህ ልጅ የዚችም ባሪያ ነገር በፊትህ ጭንቅ አይሁንብህ የምትልህን ሁሉ ሣራን ስማት ከይስሐቅ ዘር ይተካልሃልና።
ይህም ነገር ታላቅ ምሥጢር አለው የተመሰገነ ጳውሎስ ቅድስት ሣራን የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጓታልና። ከዚህም በኋላ በበጎ እርጅና በአረፈች ጊዜ ከኬጢያዊ ኤሞር ልጆች በገዛው ቦታ ቀበራት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ሞይስስና_እህቱ_ሣራ
በዚህች ቀን የከበረ አባ ሞይስስና እኅቱ ሣራ በሰማዕትነት ሞቱ። የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው ደጎች እጅግም ባለጸጎች ናቸው። የከበረ ሞይስስ ወላጆቹ ከአረፉ በኋላ እኅቱ ሣራን ሊአጋባትና ወላጆቹ የተዉትን ገንዘብም ሊሰጣት እርሱም ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ አሰበ።
ይህን አሳቡንም በነገራት ጊዜ እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔን ልታጋባኝ ከወደድክ አስቀድሞ አንተ አግባ አርሱም እንዲህ አላት እኔ ብዙ ኃጢአት ሠርቻለሁ ስለዚህ ኃጢአቴን ለመደምሰስ እመነኵስ ዘንድ እሻለሁ ማግባት አይቻለኝም የነፍሴን መዳኛ አስባለሁ እንጂ ።
ሁለተኛም እንዲህ ብላ መለሰችለት አንተ ነፍስህን ስታድን እኔን በዓለም ወጥመድ ውስጥ እንዴት ትጥለኛለህ። እርሱም እንዲህ አላት ምንኵስና ከፈለግሽ ስለ ራስሽ የምታውቂ አንቺ ነሽ እኔም የወደድሺውን አደርግልሻለሁ።
እንዲህም አለችው ለነፍስህ የምታደርገውን ለኔም እንዲሁ አድርግ እኛ ሁለታችን ከአንድ ባሕርይ ከአንድ አባት ከአንዲት እናት የተገኘን ነንና የልቧንም ቆራጥነት አይቶ ወዲያውኑ ከእርሷ ጋራ ተነሣ ገንዘባቸውንም ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተኑ።
ከዚህም በኋላ እኅቱ ሣራን ወሰዳት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ወዳለ የደናግል ገዳም ውስጥ አስገባት እርሱም ከወንዶች ገዳም ገብቶ በዚያ ተጋድሎን ተጋደለ። እንዲሁ እኅቱም ጽኑዕ በሆነ ገድል ተጠምዳ እየተጋደለች ሁለቱም ሳይገናኙ ዐሥር ዓመት ኖሩ።
በሊቀ ጳጳሳት አባ ድሜጥሮስ የሹመት ዘመን ሳዊርያኖስ የሚባል ከሀዲ ተነሥቶ የክርስቲያንን ወገኖች ማሠቃየት ጀመረ። ከመነኰሳት ገዳማትም ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። አባ ሞይስስም ተነሣ ሊሰናበታትም ወደ እኅቱ ሣራ ላከ በሰማዕትነት መሞት እንደሚሻም ነገራት።
ሣራ እኅቱም በሰማች ጊዜ ወዲያውኑ ተነሣች ሒዳ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ እንድታሰናብታት እመ ምኔቷን ለመነቻት እመ ምኔቷም ጸለየለችላት ሰላምታም ሰጥታ አሰናበተቻት እርሷም ደናግሉን ሁሉ ተሰናበተቻቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ ወንድሟ ሔደች በጐዳናም አገኘችውና እርስ በርሳቸው ሰላም ተባባሉ ወደ እስክንድርያ ከተማም ገብተው በመኰንኑ ፊት ቁመው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሳቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#መነኰሳት_አጋቦስና_እህቱ_ቅድስት_ቴክላ
በዚህችም ቀን የከበሩ መነኰሳት አጋቦስና ቴክላ በሰማዕትነት ሞቱ። እሊህም ቅዱሳን በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን መከራ በመቀበል ተጋደሉ ። ከመኳንንቶቹም አንዱ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ። ሥቃያቸውም በአሰለቸው ጊዜ ለአንበሶች ጣላቸውና ገድላቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ
በዚህች ቀን አባታቻን አቡነ ኢየሱስ ሞዐ የተፀነሱበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱሱ አባት ሀገራቸው ጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ሲና ዳኅና በሚባል ቦታ ነሐሴ 26 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 26 ቀን 1210 ዓ.ም ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ተወለዱ። የተወለዱትም በቅዱስ ነአኲቶ ለአብ ዘመነ መንግስት ነው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የቆብ አባት ሲሆኑ ታላቁን ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገዳም የቆረቆሩ ደገኛ አባት ናቸው፡፡
ዕድሜያቸው 30 ዓመት እስከሚደርስ ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ1240 ዓ.ም ይህንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያጠኑ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ እጅ ምንኩስናን በ1247 ዓ.ም ተቀበሉ፡፡
አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ ‹‹የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ?›› በማለት መልአኩን ቢጠይቁት ‹‹ተነሥ! ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ›› አላቸው፡፡ አባ ኢየሱስ ሞዓ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበዓታቸው ተነሥተው ተከተሉት፡፡ የብዙ ወራት መንገድ የሆነውን ጐዳናም በስድስት ሰዓት አደረሳቸው፡፡ በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ፡፡ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ከመግባታቸው በፊት ለ6 ወራት ያህል በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡ ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፡፡ በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበውም ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ፡፡
😍6❤4🥰2🕊2😘2
⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
Aug 31, 2026⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
⚪️የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
🔴የዘንድሮው ጷግሜ ወር ስንት ቀን ነበር ⁉️
😘6❤3🥰1😍1
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Aug 31, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😍4❤1🥰1😘1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 31, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
😘5❤2🥰2😍2
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 31, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
😘5❤3🥰3😍3
ቅዱሳን (Saints)
Aug 30, 2026#ነሐሴ_25
Aug 30, 2026#ነሐሴ_25
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አምስት በዚች ቀን #ቅዱስ_እንድርያኖስ በሰማዕትነት ሞተ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሃያ አራቱ ባልንጀሮቹ በሰማዕትነት ሞቱ፣ ቅዱሱ አባት #አባ_ቢጻርዮን አረፈ።
#ቅዱስ_እንድርያኖስ
ነሐሴ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ቅዱስ እንድርያኖስ በሰማዕትነት ሞተ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሃያ አራቱ ባልንጀሮቹ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም እንድርያኖስ ከመክስምያኖስ መኳንንቶች አንዱ ነበር እርሱም የጐልማሶች አለቃ ነበረ። ለጣዖት መስገድን እምቤ ስለአሉ ንጉሡ ምእምናንን ሲአሠቃያቸው ቅዱስ እንድርያኖስ የሰማዕታትን የልባቸውን ቆራጥነትና በመከራቸው ላይ መታገሣቸውን ተመልክቶ አደነቀ።
እንዲህም አላቸው ይህን ያህል ስትታገሡ ምን ታገኛላችሁ ቅዱሳን ሰማዕታትም የሚጠብቀንን ተሰፋ ለመናገር አንደበታችን አይችልም አሉት ስለ ዓለም ድኅነትም ክርስቶስ መከራ እንደ ተቀበለ ከብሉይና ከሐዲስ መጽሐፍ ነገሩት።
እንድርያኖስም በሰማ ጊዜ ጽሕፈትን ወደ ሚያውቁ ብልሆች ሰዎች ሔደና እኔ ከዛሬ ጀምሮ ክርስቲያን ነኝ ስሜን ከገድለኞቹ ጋራ ጻፉ አላቸው።
ለንጉሥ መክስምያኖስም እንዲህ እንዳለ በነገሩት ጊዜ ጠርቶ እንድርያኖስ ሆይ አበድክን አለው እንድርያኖስም ከቀድሞው እብደቴ ተመለስኩ እንጂ እኔ አላበድኩም ብሎ መለሰለት።
ንጉሡም ሰምቶ ወደ ወህኒ ቤት ከንጹሐን ሰማዕታት ጋራ እንዲጨምሩት አዘዘ። ከአገልጋዮቹም አንዱ ሒዶ ለሚስቱ እንጣልያ ነገራት በስማችም ጊዜ ደስ እያላት ወደ ወህኒ ቤት ሔደች ሃያ አራቱ ቅዱሳን ሰማዕታት የታሠሩበትን ማሠሪያቸውን ሳመች በሥቃዩ እንዲታገሥ የባሏን ልብ ያጽናኑ ዘንድ ለመነቻቸው። እርሱንም እንዲህ አለችው ላህይህ ደምግባትህም ርስትህም ጥሪትህም አያስትህ ሁሉም ከንቱ ነውና ነገር ግን በእርሱ ዘንድ የማያልፍ መንግሥትን ትወርስ ዘንድ የክብር ንጉሥ ክርስቶስን ተከተለው ይህንንም ብላ ወደቤቷ ገባች።
ከዚህም በኃላ እንድርያኖስ ለፍርድ እንደ ሚአቀርቡት በአወቀ ጊዜ ሊሰናበታት ወደ ሚስቱ ሔደ መምጣቱንም ሰምታ የሸሸ መሰላት ደጇንም ዘግታ በውስጥ ሁና እንዲህ እያለች ዘለፈችው ትላንት ሰማዕት ተብለኽ ዛሬ ክርስቶስን ካድከውን እንድርያኖስም ሰምቶ የሃይማኖቷን ጽናት አደነቀ እንዲህም አላት እኅቴ ሆይ እንድስናበትሽ ክፈችልኝ አላት።
በሰማችም ጊዜ ከፈተችለት ከዚህም በኃላ ሁሉን እያነጋገራት እስከ በኃላ ሁሉን እያነጋገራት እስከ እሥር ቤት ወሰዳት እንጣልያም ከዚያ በደረሰች ጊዜ የታሠሩትን ቅዱሳን ተሳለመቻቸው ቅስላቸውንም አጠበች።
ከዚህም በኃላ ንጉሡ ቅዱሳኑን ከእሥር ቤት እንደአመጧቸው አዘዘ በመጡም ጊዜ ከሥቃይ ብዛት የተነሣ እንደደከሙ አያቸው። እንድርያኖስንም በፊቱ አቁሞ ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱሱም እርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ ንጉሡም የሆድ ዕቃው እስኪፈስስ ሆዱን እንዲደበድቡት አዘዘ በዚያን ጊዜም የእንድርያኖስ ዕድሜው ሃያ ስምንት ዓመት ነበር።
ከዚህም በኃላ እንድርያኖስን ከባልንጀሮቹ ሰማዕታት ጋራ ወደ እሥር ቤት መለሱት እንጣልያም መጥታ የቅዱሳንን ደማቸውን ጠራረገችላቸው። እሊህ ቅዱሳንም እንድርያኖስን እንዲህ ብለው ተሳለሙት እንድርያኖስ ሆይ ስምህ ተሳለሙት በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎአልና ደስ ይበልህ ።
ንጉሡም መሰፍ አምጥተው የቅዱሳኑን ሁሉ ጭናቸውን በድጅኖ ይሰብሩ ዘንድ አዘዘ እንጣልያም የእንድርያኖስን እጆቹንና እግሮቹን በመስፍ ላይ ለማኖር ቀደመች ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሰጠ ድረስ የእንድርያኖስን ዐጥንቶቹን ወታደሮች ቀጠቀጡ የቅዱሳኑንም ሁሉ ጭናቸውን ሰብረው ወደ እሳት ወረወሯቸው እሳቱ ግን ከቶ አልነካቸውም ።
ምእመናንም መጥተው በጭልታ ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱአቸው የመከራውም ወራት እስቲያልፍ ሠወሩአቸው። እንጣልያም የእንድርያኖስን የእጁን ቁራጭ ወስዳ በትርአሷ ውስጥ አኖረችው።
ከዚህም በኃላ የሀገሩ ገዥ እንጣልያን ሊአገባት ወደደ በአወቀችም ጊዜ የባሏን የእጅ ቁራጭ ይዛ በመርከብ ሸሸች የቅዱሳኑ ሥጋ ወዳለበትም ደርሶ ወደ እነርሱ ይቀበሏት ዘንድ ለመነች ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ አሳረፋት ከእነርሱም ጋራ ተቀበረች።
#ቅዱስ_አባ_ቢጻርዮን
በዚህችም ቀን ቅዱሱ አባት አባ ቢጻርዮን አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ነበሩ። በአደገም ጊዜ የምንኵስና ልብስን ለብሶ እግዚአብሔርን ሊአገለግል ወደደ ዓለምንም ንቆ ወደ አባ እንጦንስ ሔደ ለእርሱም ደቀ መዝሙር ሆኖ ብዙ ዘመናት አገለገለው።
ከዚህም በኃላ ወደ አባ መቃርስ ሒዶ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትንም አገለገላቸው። በአስቄጥስም ገዳም ይዘዋወር ነበር በቤት ውስጥም አያድርም ነበር። ምንጣፍና ልብስ እስኪአጣ ድረስ ምንም ምን ጥሪት አልነበረውም መነኰሳቱም የማቅ ጨርቅ ይሰጡት ነበር። ወገቡንም ታጥቆ በመነኰሳቱ መንደር ይዞር ነበር በቤቶቻቸውም ደጃፍ እያለቀሰ ይቀመጥ ነበር።
የማያውቀውም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ አባቴ ሆይ ምን ያስለቅስሃል ይለው ነበር። እርሱም ንብረቴን ስለዘረፉኝ እንዳልሞት ሸሸሁ ከወገኔም ክብር ተለይቼ በጉስቁልና ወደቅሁ ይለው ነበር። የቃሉንም ምልክት የማያውቅ የጠፋውን ገንዘብህን እግዚአብሔር ይመልስልህ ብሎ ካለው ይሰጠው ነበር። እርሱም ተቀብሎ ይሔድና ለሌለው ይሰጥ ነበር።
የቃሉን ምልክት የሚያውቅ ግን በፈቃደ ነፍስ የሚሠሩ ትሩፋትን ሰይጣን ከሰዎች የማረካቸው መሆኑን ልብ ብሎ ያስተውል ነበር። አባቶችም ጭንቅ የነበረ ተጋድሎውን ስለርሱ ይናገሩ ነበር። እርሱ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ከቶ ሳይተኛ ቁሞ ኖሮአልና ።
በምንኩስናውም ወራት ብዙ ጊዜ በየአርባ ቀን ጾመ እነሆ እንዲህ እየተጋደለ ድንቆችንም እያደረገ ኀምሳ ሰባት ዓመታት ኖረ። ቅዱሳን አባ ዱላስና አባ ዮሐንስም ከተአምራቱ ተናገሩ እነርሱ ከርሱ ጋር ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሔዱ። እጅግም በተጠሙ ጊዜ እንደተጠሙ አውቆ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መራራውንም ውኃ ጣፋጭ አድርጎላቸው ጠጥተዋል።
በሁለተኛም ጊዜ ወደ ፈሳሽ ውኃ ደርሶ መሸጋገሪያ አጣ ወደ ጌታችንም ጸለየ ያን ጊዜም እንደ የብስ በባሕሩ ላይ ሔደ። በአንዲት ቀንም የከበሩ አባቶች በጸሎታቸው ያድኑት ዘንድ ጋኔን ያደረበትን ሰው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሰዎች አመጡ አባቶችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ስለሚሸሽ ብንነግረው ይህን ጋኔን የያዘውን አያድነውም ።
አባ ቢጻርዮን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለጸሎት ወደሚቆምበት ቦታ ያንን ጋኔን ያደረበትን ሰው አስተኙት። አባ ቢጻርዮንም በገባ ጊዜ ያን ጋኔን ያደረበትን ሰው ተኝቶ አገኘውና ቀሰቀሰው እጁንም ይዞ ተነሥ አለው ያን ጊዜም ድኖ ተነሣ አእምሮውም ተመለሰ። ያዩትም እጅግ አደነቁ ለሚፈሩት ስለሚሰጠው ጸጋውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
የዚህም ቅዱስ ተአምራቶቹ ከነገርናችሁ የበዙ ናቸው እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።
† ነሐሴ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
2."24ቱ" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
3.ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ)
4.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ
5.ቅዱስ ኤልያኖስና እህቱ አውዶክስያ (ሰማዕታት)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)
❤8🥰3😍2💯2😘2
✝እንኳን አደረሰነ!
Aug 29, 2026✝እንኳን አደረሰነ!
❖ርዕሰ ርዑሳን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (መምህረ ትሩፋት)
❖እኅተ ጻድቃን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ርኅርኅተ ኅሊና)
❖ኮከበ መርዓስ ቅዱስ ቶማስ (ሐዋርያ ወሰማዕት)
❖አቡነ ተስፋ ሥሉስ ጻድቅ (ዘብሔረ ሸዋ)
❖አቡነ ጊዮርጊስ ሰማዕት (ዘመካነ ግሺ)
አርኬ፦
✝ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘይጥዕም እመዓር፤
ወእምነ ሐሊብ ዘዕጎልት ዘጣዕመ መዓዛሁ መንክር፤
ክርስቶስ ሠምራ ፍቅርቱ ለወልደ አምላክ ፍቁር፤
ተክለ ሃይማኖት አቡኪ ካህነ አርያም ሥሙር፤
ወቶማስ ዘመርዓስ ምስለ ዘለኪ ማኅበር!
🙏 ከደጋጉ ቅዱሳን በረከት አይለየነ!
🥰4❤3😘3😍2💯1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 29, 2026"በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድ…
Aug 29, 2026"በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔርንም ፈጽማ አመሰገነች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የክርስቶስ ምስክሩና ሐዋርያው የሆነ የመርዓስ ኤጲስቆጶስ ተጋዳይ ቅዱስ አባት ቶማስ አረፈ። የዚህንም አባት ትሩፋቱንና ገድሉን ሰው ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም እርሱ አስቀድሞ በጾም በጸሎት በስጊድ ቀንና ሌሊትም በመራራት ተጠምዶ የሚኖር ነው ። ከዚህም በኃላ መርዓስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መረጠው መንጋውንም እንደ ሐዋርያት ጠበቀ ። ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን ያሠቃያቸው ዘንድ ከመኳንቶቹ አንዱ ወደዚያች አገር ደረሰ እርሱም ቅዱስ ቶማስን ወደርሱ ያቀርቡት ዘንድ ጭፍሪቹን ላከ እነርሱም እየደበደቡ በምድር ላይ እየጎተቱ ወሰዱት ደሙም እንደውኃ ፈሰሰ ።
ከዚህም በኃላ መኮንኑ ቅዱስ ቶማስን ለአማልክት ስገድ አለው ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ ጣዖታት የሚሰግድ ሁሉ የተረገመ ነውና ።
መኰንኑም ተቆጥቶ እጅግ የበዛና ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው የነዳጅ ድፍድፍና አፍልተው በላዩ በአፉና በአፍንጫው ውስጥ ጨመሩ እንዲህም እያደረጉበት እስከ ብዙ ዘመናት ኖረ።
የእሊህ ከሀዲያን ልባቸው እንደ ድንጊያ የጸና ስለሆነ ቅዱስ ቶማስ ቶሎ እንዲሞት አልፈለጉም። ሌሎች ብዙዎች ሰዎችን ያሰፈሩአቸው ዘንድ የክብር ባለቤት ክርስቶስንም ይክዱት ዘንድ የሥቃዩን ዘመን አስረዘሙ እንጂ።
እርሱ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የጸና ነውና ማሠቃየቱን ከሀድያን በተቸነፉ ጊዜ ስለ ስሕተታቸውም ይዘልፋቸው ስለነበር ስለዚህ በጨለማ ቦታ ጣሉት በዚያም ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ።
ከሀድያንም በየዓመቱ ወደርሱ ገብተው ከሕዋሳቱ አንዱን ይቆርጣሉ። በዚያም ቦታ አፍንጫውን ከንፈሮቹን ጆሮዎቹን እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ መንጋዎቹም ያረፈ መስሏቸው በየዓመቱ መታሰቢያውን ሲያደርጉ ኖሩ። ነገር ግን አንዲት ክርስቲያናዊት ሴት በጣሉት ጊዜ ስለአየችው ቦታውን ታውቅ ነበር እርሷ በሌሊት ወደርሱ ተሠውራ በመሔድ ትመግበዋለች ። ጻድቅ ቁስጠንጢኖስም እስከ ነገሠና የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ክብር እስከ ገለጠ ድረስ እንዲህ ሲሠቃይ ኖረ።
ይህም ንጉሥ ክርስቶስን በመታመን የታሠሩ እሥረኞችን ሁሉ በሀገሮች ሁሉ በወህኒ ቤት ያሉትን ይፈቷቸው ዘንድ አዘዘ።
ይችም ሴት ሒዳ ስለ ቅዱስ ቶማስ ከእርሱ የሆነውን ሃያ ሁለት ዓመት ተጥሎ እንደኖረ ለካህናቱ ነገረቻቸው በውስጡ ወደሚኖርበትም ቦታ መራቻቸው። እነርሱም አንሥተው ተሸከሙት እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አደረሱት በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በወንበሩ ላይ አስቀመጡት ምእመናንም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ ከእርሱ ይባረኩና የተቆረጡ ሕዋሳቱን ይሳለሙ ነበር።
ንጉሥ ቂስጠንጢኖስም የከበሩ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳትን የአንድነት ጉባኤን በኒቅያ አገር በሰበሰበ ጊዜ ይህ የከበረ ቶማስ ከእሳቸው አንዱ ነው።
ንጉሡም ወደ እንርሱ ገብቶ ሰላምታ ሰጣቸውና ከእርሳቸውም ቡራኬ ተቀበለ። የዚህ የቅዱስ ቶማስን ተጋድሎውን በነገሩት ጊዜ ወደርሱ ቀርቦ ሰገደለት ሕዋሰቱም ከተቆረጡበት ላይ ተሳለመው አዝኖና እጅግም አድንቆ ሕዋሳቱን ዳሠሠው ፊቱንና ዐይኖቹን አሻሸው።
ከሀዲ አርዮስንም ተከራክረው ከረቱ በኃላ አውግዘው ለይተው ከወገኖቹ ጋር ከቤተ ክርስቲያን አሳደዱት። ከዚህም በኃላ መንፈስ ቅዱስ እንደ አስተማራቸውና እንደመራቸው የሃይማኖትን ትምህርት በአንደበታቸው ተናገሩ ሕግና ሥርዓትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ፍርድንም ሠሩ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቶማስ ወደ መንበረ ሢመቱ ሔደ ካህናቱንና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ አነበበላቸው እርሱንም እንዲአስተውሉት እንዲጠብቁትም በመጠበቅም እንዲጸኑ አዘዛቸው። ጥቂት ዘመናትም ከኖረ በኃላ በሰላም በፍቅር አረፈ የሹመቱም ዘመን አርባ ዓመት ነው በዚህም እግዚአብሔርን አገለገለው።
=>ነሐሴ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)
3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
4.አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
4."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
5.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ እና #ገድለ_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ)
🥰6😍3😘2❤1💯1
የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨ…
Aug 29, 2026የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው አስገቧት ...
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሳጥናኤል ምሕረት እንደለመነች፦ ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ዓርብ ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ስለሰው ልጆች ስትጸልይ ሣለ። ዓለሙ ሁሉ ከንቱ እንደሆነና የሰውም ልጅ ሕይወት እንደጥላ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ፈጽማ ተመለከተች። ነቢዩ ዳዊት "ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል ዘመኑ ወይም ሕይወቱ እንደጥላ ያልፋል" ሲል ተናግሯልና። ዳግመኛም "ሰው ክብር እንኳ ቢሆን ሊኖር አይችልም እንደሚጠፋ ወይም ማስተዋል እንደሌለው እንስሶች መሰለ... አለ ክቡር ዳዊት። ስለዚህም ሁሉ ነገር አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው መፃተኛዋ ባሪያህንም ኃጢአቷን አታስብባት እያለች ወደፈጣሪዋ መሪር ዕንባን አለቀሰች። ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ወደስዋ መጣ። በታላቅ ግርማ ሆኖ ባየችውም ጊዜ ደነገፀች ከእግሩ ሥርም ወደቀች። ከዚህ በኋላ ነውር በሌለባቸው ንዑዳት ክቡራንና ንጹሐን በሆነ እጆቹ አነሣት። ቀጥሎም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ አትደንግጭ ነገር ግን የልብሽን ሃሳብ ንገሪኝ" አላት። እስዋም "አቤቱ ባሪያህንስ በባለሟልነት ካሠለጠንካት አባታችን አዳምን በአርአያህና በአምሣልህ ስለምን ፈጠርከርው። በእንጨት መስቀልስ ላይ ለምን ተሰቀልክ ስለአዳምና ስለልጆቹ አይደለምን?" አለችው። "አዋን ስለነሱ ስል ተሰቅያለሁ" አላት። "እግዲያውስ መሰቀልህ ወይም የተሰቀልከው ስለነሱ ከሆነ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱን ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው" አለችው። "አንተ ቸር ይቅር ባይ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ ነህና ከአንተ ሌላ አምላክ የሌለ እውነተኛ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃልና የሚሣንህ ነገር ከቶ የለምና ዓለም በጠቅላላዋ በእፍኝህ አትሞላም" በማለት እያለቀሰች ለመነችው። በዚያ ጊዜ ጌታ መልሶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ አንቺ ራስሽ ፍረጅ አዳም ከነልጆቹ ከሠራው ኃጢአት እና እኔ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን በቀያፋና በሐና አደባባይ በዕለተ ዓርብ ከተቀበልኩት ሕማማተ መስቀል ቢመዘን የትኛው ይመዝን ይመስልሻል?" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ደነገጠችና ከመሬት ላይ ወደቀች። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት በሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣትና "እንግዲህ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩ ለማን ወይም በማን ምክንያት ይመስልሻል" አላት።
ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ የልብሽን ሃሳብ ወይም ፍላጐትሽን ንገሪኝ" አላት። በዚህን ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆች ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ። የኃጥእን መመለሱን እንጂ ጥፋቱን አትወድምና" አለችው። "የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እርሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት እንጂ። የነሱ ሥጋ ሥጋየ እንደሆመኑ መጠን የኔም ሥጋ ሥጋህ ነውና" አለችው። ይህንም ባለችው ጊዜ ጌታ ፍግግ ብሎ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ሌሎች ካንቺ በፊት የነበሩ ካንቺም በኋላ የሚነሱ የማያስቡትን እጅግ የሚያስደንቅ ልመና አቀረብሽ" አላት። ይህንም ካለ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ስትል ልመና አቅርባለችና እሺ ካላት ታወጣው በንድ ወደሲዖል ይዘሃት ሂድ" ብሎ አዘዘው። በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እሺ ብሎ ሰግዶ እጅ ነሥቶ ወደሲዖል ይዞአት ሄደ። አብረው በሚጓዙበትም ጊዜ "እንግዲህ ዲያብሎስ ከታረቀ ወይም ከተማረ የሰው ልጆች ሁሉ ያርፋሉ" እያለች ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ታሳስበው ነበር። ይህን አምላክነትን ሲሻ ከክብሩ የተዋረደ ዲያብሎስ ምሕረት ለማግኘት ይሻ መስሏት ነበርና።
ከሲዖል አፋፍ በደረሱም ጊዜ የተመለከተችው ሥቃይ ተነግሮ የማያልቅ ነው ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደውሻ ይናከሱ ነበር። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ምሕረት የሚፈልግ ከሆነ እስኪ በይ ዲያብሎስ ብለሽ ጥሪው" አላት። በዚህ ጊዜ በመላእክት ቋንቋ ሦስት ጊዜ "ሣጥናኤል ሣጥናኤል ሣጥናኤል" በማለት ጠራችው። ዲያብሎስም "ከዚህ በብዙ ሠራዊት ላይ ነግሼ ከምኖርበት አገር ማን ነው እሱ የሚጠራኝ" እያለ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ። ከዚህም በኋላ "ለብዙ ዘመን ስፈልግሽ ወይም ሳድንሽ ቆይቼ ነበር ዛሬ ግን ከምኖርበት ቤቴ ድረስ መጣሽን" አላት። እርሷም "ጌታ ይቅርታ አድርጓልሃልና ከዚህ ከሥቃይና ከመከራ ቦታ ከወገኖችህ ጋራ ና ፈጥነህ ውጣ" አለችው። ይህንም በለችው ጊዜ ልቡ እንደ እሳት ነደደ አፈፍ ብሎ ተረማምዶ በግራ እጁዋን ይዞ ከሲዖል ረግረግ ውስጥ ወረወራት። በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ ከኋላ ከኋላዋ ይከተላት ነበርና ይህን ምሕረት የሌለው ዕቡይ ዲያብሎስ በያዘው ሰይፍ ቢቀጣው የሲዖል ደጃፍ ተከፈተች። በዚህ ሰዓት ታላቅ ጨኸትና ውካታ ወይም መደበላለቅ ሆነ በሲዖል ያሉ የሰዎች ነፍሳት እንደንብ ከበቧት ወይም ሠፈሩባት። በዚያን ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና በስዋም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲዖል የወጡት ነፍሳት ቁጥር ዓሥር ሺህ ያህል ነበር። እነዚህ ከመከራ ያመለጡ ከሥቃይ የወጡ ነፍሳትን ባየች ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የእናቱን ጡት እየጠባ እንደሚዘል እምቦሳ ጥጃ በመካከላቸው ትዘል ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ "አቤቱ ፍርድህ ከቶ እንደዚህ ነውን?" እያለች አደነቀች። ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዲያብሎስን ድል አድርገሽ ጥቂት ምርኮን አገኘሽን" አላት። እስዋም "አዋ ጌታዬ በኃይልህና በቸርነትህ አገኘሁ" አለችው። ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "እሊህን ነፍሳት ዓለም ሳይፈጠር ወደ አዘጋጀሁላት ወደ ክርስቶስ ሠምራ መኖሪያ ቦታ ውሰዳቸው" አለው። በዚህ ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ የእኔ መኖሪያየ ወዴት ነው?" አለችው። ጌታም "መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋራ ነው እነሆ በትረ ማርያም ብየ ሰየምኩሽ መቀመጫሽን ወይም ደረጃሽን ከእርስዋ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ የባለሟልነት ግርማ አጐናጸፍኩሽ አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ፈጽማ ደስ ተሰኘች ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ብትመለከት ለዓይን የሚያንፀባርቁ ዓሥር አክሊላት አየች። በየአንዳንዳቸው አክሉል ላይ ዐራት ከዋክብት አሉባቸው የእሊህ ከዋክብት ቊጥራቸው ሲደመር አርባ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ከስዋ ጋራ የነበረውን መልአክ "እሊህ በላያቸው ብርሃናውያን ከዋክብት ያሉባቸው አክሊላት ለማን የተዘጋጁ ናቸው ሰውነቴ እጅግ አድርጋ ወዳቸዋለችና" አለችው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ላንቺ ቢሆን ደስ አይልሽምን?" አላት። እርስዋም "አዎን ጌታየ ለኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያስ ላንቺ የተዘጋጁ ናቸው" አላት።
🥰7😍4❤3💯1
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።
Aug 29, 2026ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።
መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።
አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ
በዚህች ቀን ደግሞ ኢትዮጵያዊት የሆነች ተጋዳይ የከበረች ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው፡፡ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።
በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማየ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።
ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት። ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።
ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።
ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም " ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።
ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ
❤3😘3🥰1😍1💯1
#ነሐሴ_24
Aug 29, 2026#ነሐሴ_24
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ አራት በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ #አባታችን_ተክለሃይማኖት አረፈ፣ የከበረች #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው፣ የክርስቶስ የመርዓስ ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_አባት_ቶማስ_አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት
ነሐሴ ሃያ አራት በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ።
በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶች ያደርጋቸዋል።
በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ።
ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት ባያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ።
እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ።
የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዙእ ኀረያ እንደሆነች አገኛት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው።
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው።
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱሱ ተፀንሶ በታኀሣሦ ወር በሃያ አራት ተወለደ በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ ቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው።
ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመነፈስ ቅዱስ ጸና።
ከዚህም በሗላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
ጐልማሳ በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።
ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርኩዙን ይዞ በሌሊት ወጣ።
ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሔዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣፆት የሚሠውበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ።
ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሔዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው እርሱ ግን በደኀና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው።
ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር።
ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኀነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመን ያጸናቸዋል።
ከዚህ በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር።
በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በሗላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔዶ ከእርሱም የምንኲስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሔዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ።
በዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ ከዚያም ግራርያ ወደ ሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው።
ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኲሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስበርሳቸውም አይተዋወቁም እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ሰለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እነደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም።
በዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በሗላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣ ኖረ።
❤6🥰4😍3💯1
✝ርዕሰ ሊቃውንት፡ መምህረ ወንጌል፡ ወሰማዕተ ጽድቅ የኔታ ወልደ አብ ወልደ ሚካኤል (ዘብሔረ ጎንደር)✝
Aug 28, 2026✝ርዕሰ ሊቃውንት፡ መምህረ ወንጌል፡ ወሰማዕተ ጽድቅ የኔታ ወልደ አብ ወልደ ሚካኤል (ዘብሔረ ጎንደር)✝
=>በዚህች ዕለት (ነሐሴ 23) በ1881 ድርቡሽ ጎንደርን ሲያጠፋ፥ ደገኛውን ሊቅም ከነተማሪዎቻቸው ገድሏቸዋል።
ድርቡሽ ደርሶ "ክርስቶስን ካድ" ይላቸዋል፡፡ ሊቁ ግን እዚያው የሚተረጉሙትን ጠቅሰው "በሰው ፊት የሚክደኝን ፡ እኔም በሰማዩ አባቴ ፊት እክደዋለሁ" መባሉን አልሰማህምን? ሲሉ መለሱለት ፡፡
#ሊቁ "ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም" ብለው መጽሐፍ እንደዘረጉ ተሰዉ፡፡ ምስጢሩን ከሐተታ ወደ ተግባር መለሱት፡፡
የመጨረሻ ቃላቸው "አነ ዘክርስቶስ/እኔ የክርስቶስ ነኝ" ነበር።
እርሳቸውና ስምንቱ ተማሪዎቻቸው "ሰማዕታተ ቅድስት ጉባዔ" ተብለዋል ፡፡
የንታ ወልደ አብ ወልደ ሚካኤል የደብረ መድኀኒት ዓቢየ እግዚእ ደብር አሰተዳዳሪ፥ በግምጃ ቤት የትርጓሜ ምስክር፥ ሊቅና ሰማዕት ናቸው፡፡
=>ከተሠዉ ፻፴፭/135 ዓመት ሆናቸው፡፡ ምሽት ላይ ከመምህራቸው ከሊቁ ወልደ አብ ወልደ ማርያም (ርዕሰ አበው) ጋር መታሰቢያቸውን እናደርጋለን፡፡ እናከብራቸዋለን፡፡
=>ከሰማዕቱ ሊቅ በረከት ያሳትፈን፡፡
አርኬ፦
✝ወልደ ሚካኤል ሰማዕት ለማርያም ፍቁራ፤
ዘተቀትለ በግፍዕ በእደ ደርቡሽ ጸራ፤
ወልደ አብ መምህር ለቤተ ክርስቲያን ዓቃቤ ዘውራ፤
እንዘ የሐትት ወይሜህር ለወንጌለ መንግሥት ምሥጢራ፤
እምደብረ መድኀኒት ነሥእዎ ዘሰማይ ሐራ!
https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
❤3😘3🥰2😍2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 28, 2026#ነሐሴ_23
Aug 28, 2026#ነሐሴ_23
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስክንድርያ አገር ከክርስቲያን ወንድሞቻችን ሠላሳ ሺህ ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ፣ ሰማዕቱ #ቅዱስ_ድምያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የግብፅ_ሰማዕታት
ነሐሴ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስክንድርያ አገር ከክርስቲያን ወንድሞቻችን ሠላሳ ሺህ ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ።
ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርትያኖስ አባታችን ዲዮስቆሮስን ወደ ደሴተ ጋግራ በአጋዘው ጊዜ ብዙ ዘመናት በእስክንድርያ አገር ሁከትና ብጥብጥ ሆነ።
መርትያኖስም በሞተ ጊዜ በርሱ ፈንታ ልዮን ነገሠ እርሱም አብሩታርዮስ የተባለውን መለካዊ ከሮማውያን ወገን ለእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሾመ ይህም መለካዊ በኬልቄዶን ጉባዔ የሚያምን ነው ስለዚህም ከጥቂት ግብዞች ሰዎች በቀር የእስክንድርያ ሰዎች አልተቀበሉትም።
ያልተቀበሉትም ሰዎች አስቀድሞ አባታችን ዲዮስቆሮስ ከሾማቸው ቀሳውስት ሥጋውንና ደሙን የሚቀበሉ ሆኑ። ከዚህም በኋላ በቃሉ ለሚያምኑ ባልንጀሮቹ ጉባኤ አደረገላቸውና የክርስቶስ መለኮቱ ከትስብእቱ ተቀላቀለ የሚል አውጣኪን አወገዘው ።
አብሩታርዮስም ይህን ማድረጉ የእስክንድርያን ሰዎች ሸንግሎ ወደ ከፋች እምነቱ ሊስባቸው ወዶ ነው እንጂ ስለዚህ ነገር አባ ዲዮስቆሮስ አውጣኪን አስቀድሞ አውግዞታል። የአባታችን የዲዮስቆሮስ ሃይማኖት እንደ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ እንደ ቅዱስ ቄርሎስ ቃል ከሥጋ ጋር ከተዋሐደ በኋላ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ ብለው እንደሚያምኑ የሚያምን ነውና።
ከጉባኤውም በኋላ የሰበሰባቸው የአብሩታርዮስ ተባባሪዎቹ ወደየቦታቸው ተመለሱ። እርሱም ራሱ አብሩታርዮስ በቤቱ ውስጥ ተገድሎ ተገኘ ለባልንጀሮቹም የአባታችን ዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት ወይም የአውጣኪ ባልንጀሮች ወይም ሌቦች ገንዘቡን ለመውሰድ የገደሉት መሰላቸው ይህም እውነት ይመስላል።
የአብሩታርዮስም ባልንጀሮች ወደ ንጉሥ እንዲህ ብለው መልእክትን ላኩ እነሆ የዲዮስቆሮስ ወገኖች የንጉሥን ትእዛዝ በማቃለል ደፍረው የሾምከውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት። በዚያንም ጊዜ ወንድሞቻችን የእስክንድርያ ሰዎች በላያቸው ጢሞቴዎስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
እሊህ መናፍቃንም ከዚህ በኋላ ሁለተኛ እንዲህ ብለው ወደ ንጉሥ መልእክትን ላኩ። እነሆ አብሩታርዮስን የገደሉት ሰዎች አሁንም ያለ ንጉሥ ፈቃድ ደፍረው ሊቀ ጳጳሳት ሾሙ።
ንጉሡም በሰማ ጊዜ ከሁለቱ መልእክቶች የተነሣ እጅግ ተቆጣ። ሰይጣንም በልቡ አድሮ ጭፍሮቹን ልኮ ሃይማኖታቸው ከቀና ወንድሞቻችን ክርስቲያኖች ታላላቆችና ታናናሾች ሠላሳ ሺህ ሰዎች ተገደሉ ጢሞቴዎስንም ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ሰባት ዓመት ኖረ።
ከአባታችን ዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት አንዱ የገደለውስ ቢሆን ስለ አንድ ሰው ፈንታ ሠላሳ ሺህ ሰው መግደል ይገባልን ስለዚህ ከሰይጣን ሥራ እንደሆነ ይታወቃል።
ከዚህ ከከፋ ዕልቂት በኋላም ወንድሞቻችን የሆኑ የዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት አብሩታርዮስን እንዳልገደሉት ንጉሡ ተረዳ እጅግም አዘነ ጢሞቴዎስንም ከተሰደደበት መልሶ በመንበረ ሢመቱ አኖረው ታላቅ ክብርንም አከበረው። መንጋውንም እያበረታ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ድምያኖስ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ድምያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ የአንጾኪያ አገር መኮንን ይዞ ብዙ አሠቃየው፡፡
በኋላ ቅዱስ ድምያኖስ በእምነቱ መጽናቱን ሲያውቅና ማሠቃየትም በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ቆረጠውናሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ የክብር አክሊንም ተቀዳጀ፡፡
† ነሐሴ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ሰላሳ ሺ የእስክንድርያ (ግብጽ) ሰማዕታት
2.ቅዱስ ድምያኖስ ሰማዕት
† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)
🥰4😍4😘3❤1
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
Aug 27, 2026⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
❤6🥰4😍3😘2
❤️🔔 ይሄን ሲቀላቀሉ፦ ❤️🌹
Aug 27, 2026❤️🔔 ይሄን ሲቀላቀሉ፦ ❤️🌹
🟢 መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን በተከታታይ ይማራሉ፤
🟡 በየዕለቱ የሚውሉ ቅዱሳንን በመዘከር በረከት ይሸምታሉ፤
🔵 የፈለጉትን ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ጠይቀው ያገኛሉ፤
🟣 በመንፈሳዊ የኪነ ጥበብ ሥራዎች የአምላክን ግሩም ጥበብ ያደንቃሉ፤
🟢 በበጎ አድራጎት ሥራዎች እርካታ ነፍሶን በሐሴት ይሞላሉ፤
🔴 መንፈሳዊ መጻሕፍትንና ጽሑፎችን በPdf እና Application በእጅዎ ያስገባሉ፤
🟡 የተለያዩ መምህራንን ስብከቶች እና ትምህርቶች ያገኛሉ፤
🔵 ባልዎት ጸጋ እግዚአብሔርን ያገለግላሉ፤
🔴 አዝናኝ በሆኑ ጥያቄዎች እየተማሩ ይሸለማሉ፤
ወ.ዘ.ተ ....
🥰4😍4😘4❤2
#ነሐሴ_22
Aug 27, 2026#ነሐሴ_22
#ነቢዩ_ሚክያስ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ታላቅ ነቢይ የሞራት ልጅ ሚክያስ አረፈ። ይህም ነቢይ በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት በመናገር አስተማረ።
ስለ ጌታችን መውረድም እንዲህ አለ። እነሆ እግዚአብሔር ከልዑል መንበሩ ወደዚህ ዓለም ይወርዳል ።
ሁለተኛም ሰለ ልደቱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የኤፍራታ ዕጣ የምትሆኚ አንቺም ቤተ ልሔም የእስራኤል ነገሥታት ከነገሡባቸው አገሮች አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና ።
ስለ ምኵራብ መቅረት፣ ስለ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ መታነፅ ትንቢት ተናግሯል። ዳግመኛም ስለ ሕገ ወንጌል መሠራት ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል አለ። የትንቢቱም ወራት ሲፈጸም ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ።
የትንቢቱም ዘመን ከጌታችን መምጣት በፊት በስምንት መቶ ዓመት ነው። ማርታ በምትባልም ቦታ ተቀበረ።
† ነሐሴ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ጳውሊ የዋህ
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)
❤5🥰4😍4😘3💯1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 27, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤5🥰2😍1😘1
✝ ንግሥተ ሳባ (ማክዳ) ✝
Aug 26, 2026✝ ንግሥተ ሳባ (ማክዳ) ✝
(እንኳን ተወለድሽልን)
" ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 12 : 42)
✿ከበረከተ ልደቷ ይክፈለን፡፡✿
🥰1
✝ ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
Aug 26, 2026✝ ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
-------------------------------
☞የታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ እናት ፡ የመስቀሉም ወዳጅ ናት፡፡ ዛሬ ነሐሴ21ደግሞ ልደቷ ነውና ከበረከቷ ይክፈለን፡፡
✿✨✿✨
❤1🥰1
አቡነ አብራንዮስ ቅዱስ መተርጉመ መጻሕፍት
Aug 26, 2026አቡነ አብራንዮስ ቅዱስ መተርጉመ መጻሕፍት
ዕረፍታቸው ነው።
በረከታቸው ይደርብን።
🥰1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 26, 2026#ነሐሴ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #ቅድስት_ኄራኒ ሰማዕትነት የተቀበለችበት፣ #የንግሥተ_ሳባ እና #ንግሥት_ዕሌኒ የተወለዱበት ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ …
Aug 26, 2026#ነሐሴ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #ቅድስት_ኄራኒ ሰማዕትነት የተቀበለችበት፣ #የንግሥተ_ሳባ እና #ንግሥት_ዕሌኒ የተወለዱበት ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ኄራኒ_ሰማዕት ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን ቅድስት ኄራኒ የስሟ ትርጓሜ ሰላም ፍቅር የሆነ ለንጉሥ ሉክያኖስ ልጁ ምስክር ሁና ሞተች ። እርሱም አባቷ ያማረ…
ከዚህ በኋላ ወደ ልጇ ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ነገረችው የከበረ መስቀል በመገኘቱ እጅግ ደስ አለው።
ይቺም ቅድስት በጎ ገድሏን ከፈጸመችና እግዚአብሔርንም ከአገለገለች በኋላ ስለ ካህናትም ልብስና ቀለብ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ብዙ ጉልቶችና ርስቶችን ለድኆችና ለምስኪኖችም እንዲሁ ከሠራችና ከተከለች በኋላ በሰላም ግንቦት ዘጠኝ ቀን አርፋለች መላ ዕድሜዋም ሰማንያ ሆነ።
† ነሐሴ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (6ኛ ቀን)
2.ቅድስት ኄራኒ ሐዋርያዊት (ሰማዕት)
3.ቡርክት ንግሥተ ሳባ (ልደቷ)
4.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት (ልደቷ)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_እና_ግንቦት_9)
😘4🥰3❤2😍1
#ነሐሴ_21
Aug 26, 2026#ነሐሴ_21
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #ቅድስት_ኄራኒ ሰማዕትነት የተቀበለችበት፣ #የንግሥተ_ሳባ እና #ንግሥት_ዕሌኒ የተወለዱበት ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ኄራኒ_ሰማዕት
ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን ቅድስት ኄራኒ የስሟ ትርጓሜ ሰላም ፍቅር የሆነ ለንጉሥ ሉክያኖስ ልጁ ምስክር ሁና ሞተች ። እርሱም አባቷ ያማረ አዳራሽን ሠራላት መስኮቶቹንም ስምንት አደረገ ቅጽሩንም በዙሪያው ዐሥራ ሁለት አደረገ ማዕድንም ሠራላት። የወርቅና የብር የሆኑ ሣህኖችና ጽዋዎችንም አዘጋጀላት የሚያስተምራትም አንድ ሽማግሌ ሰው አደረገላት።
ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አኖራት የሚያገለግሏትም ሦስት አገልጋዮችን በእርሷ ዘንድ አድርጎ ደጃፎችን በላይዋ ዘጋ መምህርዋም በውጭ ሆኖ ያስተምራታል።
ዕድሜዋም ሰባት ዓመት ሆናትና ያን ጊዜ ራእይን አየች በማዕዷ ላይ ርግብ ስትቀመጥ በአፍዋም የወይራ ቅጠል አለ ። በማዕዱም ላይ አኖረችው ሁለተኛም ንስር መጣ ከእርሱ ጋር አክሊል አለ በማዕዷ ላይም አኖረው ። ደግሞ ቊራ መጣ ከእርሱ ጋራ ከይሲ አለ በማዕዷ ላይም አኖረው ። ደነገጠችም ለመምህርዋም ነገረችው እርሱም እንዲህ ብሎ ተረጐመላት ርግብ የሕግ ምልክት ናት የዘይቱም ቅጠል የክርስትና ጥምቀት ናት፣ ንስርም ድል አድራጊነት ነው አክሊልም ለሰማዕታት የሚሰጥ ክብራቸው ነው ። ቊራ የንጉሥ ምሳሌ ነው ከይሲውም መከራ ነው አንቺም የክብር ባለቤት በሆነ ክርስቶስ ስለ ስሙ ትጋደዪ ዘንድ አለሽ አላት።
ከዚህም በኋላ ይጐበኛት ዘንድ አባቷ ወደርሷ መጣና ልጄ ሆይ ከመንግሥት ታላላቆች ለአንዱ ላጋባሽ እኔ እሻለሁ አላት እርሷ ግን ከልቡናዬ እስተምመክር ሦስት ቀኖችን አባቴ ሆይ ታገሠኝ ብላ መለሰችለት።
አባቷም በሔደ ጊዜ በጣዖታቱ መሠዊያ ፊት ተነሥታ ቆመችና ስለጋብቻ የሚሆነውን ይገልጡላት ዘንድ ለመነቻቸው እነርሱም ምንም ምን ከቶ አልመለሱላትም።
ከዚህም በኋላ ዐይኖቿን ወደ ሰማይ አቅንታ የክርስቲያን አምላክ ሆይ ወደምትፈቅደው ምራኝ ብላ ጸለየች ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንዲህ አላት። እነሆ ነገ ከጳውሎስ ደቀ መዛመርት አንዱ ወደዚች አገር ይመጣል እርሱም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቅሻል።
በማግሥቱም ያ ሐዋርያ መጥቶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃት። በሦስተኛውም ቀን እንደቀጠረቻቸው አባቷና እናቷ መጡ እርሷም እንዲህ አለቻቸው እኔ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ።
አባቷም ሰምቶ በእርሷ ላይ ተቆጣ ወደ ከተማው መካከልም አውጥተው በጐዳና ላይ እንዲጥሏትና በፈረሶች እግር እንዲአስረግጧት አዘዘ። ወታደሮችም ንጉሥ አባቷ እንዳዘዘ አደረጉባት ግን ምንም ምን ክፉ ነገር ከቶ አልደረሰባትም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አባቷና እናቷ በአዩ ጊዜ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ መንግሥታቸውንም ትተው ለርሷ ወደተሠራው አዳራሽ ሔደው በውስጡ ተቀመጡ።
በጐረቤታቸው ያለ ንጉሥም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ርሳቸው መጥቶ ወደ መንግሥታቸው እንዲመለሱ ተናገራቸው። እነርሱም አልፈለጉም እርሱም መንግሥታቸውን ያዘ ቅድስት ኄራኒንም ይዞ አሠቃያት ከዚያም አንበሶችን፣ እባቦችን በላይዋ ሰደደ ምንም አልቀረቧትም ። ሁለተኛም በመጋዝ መገዛት በአንገቷም ውስጥ ታላቅ ደንጊያ አሥሮ ከባሕር ጣላት የክብር ባለቤት ጌታችንም ከዚህ ሁሉ አድኖ ያለ ጥፋት በጤና አሥነሣት።
ከዚህም በኋላ እርሷን ያጠመቀ ሐዋርያን አባቷ ጠርቶ ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ ቊጥራቸውም ሦስት መቶ ሆነ ከዘመዶቹና ከሀገር ሰዎችም ብዙዎች ተጠመቁ።
ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ኑማርያኖስ የቅድስት ኄራኒን ዜናዋን ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ቀላኒካ ወደሚባል አገር ወሰዳት ። በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በበሬ አምሳል በተሠራ የነሐስ በርሜል ውስጥ ዘጋባት የክብር ባለቤት ጌታችንም ያንን በሬ ሰብሮ ቅድስት ኄራኒን ያለ ጥፋት በጤና አወጣት።
ከዚህም በኋላ ኑማርያኖስ ሙቶ በርሱ ፈንታ ሳፎር ነገሠ እርሱም የቅድስት ኄራኒን ዜና በሰማ ጊዜ ወደ ርሱ አስቀርቦ በእጁ ውስጥ በአለ በታላቅ ጦር ወጋትና ነፍሷን አሳለፈች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሞተ አስነሣት።
ንጉሥ ሳፎርም በአየ ጊዜ እጅግ አደነቀ ሰገደላትም በጌታችን ኢየሱስም አመነ ። ከእርሱም ጋራ ከሀገር ሰዎች ብዙ ወገኖች አመኑ ቁጥራቸውም ሠላሳ አንድ ሺህ ሆነ።
ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አባቷና እናቷ አረፉ እርሷን ግን አምላካዊት ኃይል ተሸከመቻት ወደ ኤፌሶን አገርም አድርሳት በዚያ ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገች።
በፋርስ ነገሥታት በመቄዶንያ፣ በቀላኒካና በቊስጥንጥንያ ነገሥታት ፊት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከመሰከረች በኋላ ወደ ወደደችው ክርስቶስ ሔደች ። የድልና የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ንግሥተ_ሳባ
ይህቺ ኢትዮዽያዊት ንግሥት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት። በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች።
ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች። ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ቀዳማዊ ምኒልክን ወልዳለች።
ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች። (ማቴ. 12፥42) በስምም ሳባ፣ አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች። ዛሬ ዕለተ ልደቷ ነው::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ዕሌኒ_ንግሥት
በዚህች ቀን የጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ቅድስት ዕሌኒ ተወለደች። ይቺም ቅድስት በፊት የአንድ ነጋዴ ሰው ሚስት ነበረች እርሱም በነገረ ሠሪ ንጽሕት ሁና ሳለች ወደ ባሕር ጣላት። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ፈቃድም ሮሐ ከሚባል አገር ደርሳ የበራንጥያ ንጉሥ ቊንስጣ አገኛት። ውበቷንና ደም ግባቷንም አይቶ አገባት። ለክርስቲያን ነገሥታት መጀመሪያቸው የሆነውን ቈስጠንጢኖስን ወለደችው ምግባርንና ሃይማኖትን በማስተማር በመልካም አሳደገችው።
ልጇም በነገሠ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሒደሽ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን መስቀል ግለጪ የከበሩ ቦታዎችንም ሥሪ የሚላትን በሕልሟ አይታ እንዴት እንዳየች ይህን ለልጇ ነገረችው እርሱም ከብዙ ሠራዊት ጋራ ሰደዳት። በደረሰችም ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን መስቀል መረመረች አዳኝ የሆነ መስቀሉንም ሁለቱ ወንበዴዎች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች ጋራ አገኘችው። የክብር ባለቤት የክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታውቅ ዘንድ በወደደች ጊዜ ከራሱ በላይ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል በእንጨት የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት።
ከዚህ በኋላ ከእርሱ ምልክት ታይ ዘንድ ፈለገች የሞተ ሰውም አግኝታ መስቀሎችን በበድኑ ላይ አኖረች አልተነሣም። ከዚህ በኋላ ሦስተኛውን መስቀል በላዩ አኖረች። ያን ጊዜ ምውት ተነሣ ሃይማኖቷም ጸና ደስታዋም በዛ።
ከዚህ በኋላም ዜናቸው በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት የተጻፈ በከበሩ ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ትሠራ ዘንድ ጀመረች። ለአባ መቃርስም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሠራ ብዙ ገንዘብ ሰጠችው።
❤1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 26, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😘2
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 26, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
🥰4😘4❤3😍2
💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
Aug 26, 2026💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
❤4🥰4😍1😘1
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Aug 26, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍5🥰3😘3❤2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 25, 2026#ነሐሴ_20
Aug 25, 2026#ነሐሴ_20
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ በዚች ቀን መጻሕፍትን የተረጐመ #አባ_ሰላማ አረፈ፣ በከሀዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ዘመን የነበሩ ከኤፌሶን ሀገር #ቅዱሳን_ሰባቱ_ደቂቅ አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሰላማ_ካልዕ (#መተርጉም)
ነሐሴ ሃያ በዚች ቀን መጻሕፍትን የተረጐመ አባ ሰላማ አረፈ።
እኒህ ታላቅ ደግ ሰው የነበሩት በሃገራችን ኢትዮዽያ ከ1340 እስከ 1380 ዓ/ም ነው:: በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም ለኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውለታን ውለዋል:: በዘመኑ ዻዻስ ሁነው ቢመጡም እንደ ሌሎቹ ዻዻሳት በቤተ መንግስት አካባቢ ሥራ ፈትተው መቀመጥን አልፈለጉም::
ወዲያው እንደ መጡ የግዕዝ ልሳንን ልቅም አድርገው ተማሩ:: ቀጥለው ኢትዮዽያውያን ሊቃውንትን ሰብስበው ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉሙ ገቡ:: አሥራው መጻሕፍትን (81ዱን) ጨምሮ ብዙ መሠረታዊ መጻሕፍትን መተርጐም ችለዋል::
ይህም ሥራ አድካሚ በመሆኑ ከ30 ዓመታት በላይ ጊዜን ወስዷል:: ከተረጐሟቸው መጻሕፍትም፦ #ስንክሳር፣ #ግብረ_ሕማማት፣ #ላሃ_ማርያም፣ #ፊልክስዩስ(መጽሐፈ መነኮሳት)፣ #መጽሐፈ_ግንዘት፣ድርሳን ዘቅዱስ #ያዕቆብ_ዘሥሩግ. . . ይጠቀሳሉ::
አቡነ ሰላማ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸውና በገዳማዊ ሕይወታቸው ይታወቁ ነበር:: በተጨማሪም በየቦታው እየዞሩ ይናዝዙ: ያጠምቁም ነበር:: በወቅቱ ልክ እንደ ስማቸው ሰላም እንዲሰፍን ይተጉ ነበር:: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን እያስታረቁ ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንዲቆሙ አድርገዋል::
ጻድቁ አቡነ ፊልዾስን ጨምሮ ቅዱሳንን ገንዘውም ቀብረዋል:: በቀደመ ስማቸው #አባ_ፊቅጦር የሚባሉት ካልዕ (2ኛው) ሰላማ በ1380 ዓ/ም ከ40 ዓመታት ትጋት በኋላ ዐርፈዋል:: ሲጠሩም:- #መተርጉም (መጻሕፍትን የተረጐሙ)፣ #ብርሃነ_አዜብ(የኢትዮዽያ ብርሃን)፣ #መጋቤ_ሃይማኖት ተብለው ነው::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ሰባቱ_ደቂቅ
በዚህችም ቀን በከሀዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ዘመን የነበሩ ከኤፌሶን ሀገር ሰባቱ ደቂቅ አረፉ። እሊህም ሰባቱ ደቂቅ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ውስጥ በመዛግብቱ ላይ የሾማቸው ነበሩ። አምልኮ ጣዖትንም በአወጀ ጊዜ ጣዖትን በማምለክ ሥራ አልተሳተፉም። እሊህንም ቅዱሳን በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ይዞም አሠራቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ለመሔድ በፈለገ ጊዜ እስከ ሚመለስ ድረስ ፈትቶ ለቀቃቸው ምናልባት ከምክራቸው ቢመለሱ ብሎ በልቡ አስቦ። ከዚህም በኋላ እሊህ ቅዱሳን ለረከሱ ጣዖታት እንዳይሰግዱ የጭፍራነት ሥራቸውን ትተው በተራራ ውስጥ ወደአለ ዋሻ ሒደው በዚያ ተሠወሩ።
የዋሻውን አፍ ዘጉ ከእሳቸውም ጋራ በንጉሥ ዳኬዎስ ስም የተቀረጸ ብር ነበር። ከእርሳቸውም አንዱም አንዱ በየተራቸው ወጥቶ ምግባቸውን ገዝቶ ወደእሳቸው ይመለስ ነበር። ዳኬዎስም ከሔደበት እንደተመለሰ በሰሙ ጊዜ የዋሻውን ደጃፍ ዘግተው ተኙ።
የእሊህንም ቦታቸውን የሚያውቅ አማኒ የሆነ ከጭፍሮች ውስጥ አንድ ሰው ነበረ ወደ ከተማ ሲወጡ ያገኛቸው ዘንድ ጠበቃቸው ባልመጡም ጊዜ ተነሥቶ ወደ ዋሻቸው ሔደ። ዋሻዋንም ከውስጥ እንደ ዘጓት ሁና አገኛት እነርሱም በረሀብ የሞቱ መሰለው ታላቅም የደንጊያ ሠሌዳ አምጥቶ ከእሳቸው የሆነውን ገድላቸውን ጽፎ በቀዳዳ ወደ ዋሻው ውስጥ አስገባው።እሊህም ቅዱሳን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዘመናት አንቀላፉ ዳኬዎስም ሙቶ እስከ ቴዎዶስዮስ ብዙ ነገሥታት ነገሡ።
በዚህም ምእመን ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዎች ተነሥተው ብዙዎች ተከተሏቸው። በዚያንም ጊዜ እሊህን ቅዱሳን ሰባቱን ደቂቅ እግዚአብሔር አነቃቸው ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ግልጽ ያደርግ ዘንድ።
ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው አንዱ ምግባቸውን ሊገዛ የከሀዲ ዳኪዎስንም ወሬ ይሰማ ዘንድ ብር ይዞ ወጣ ወደ ከተማም በገባ ጊዜ የከተማዋ ሁኔታ ተለወጠበት። በከተማውም በር መስቀሎችን አየ በየቅጽሮቿም የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ስሙን ያለ መፍራት ሲጠሩ ሰማ አንዱንም ሰው ይች አገር ኤፌሶን አይደለችምን ብሎ ጠየቀ እርሱም አዎን ናት አለው።
ያንንም ብር አውጥቶ ለባለ ሱቁ ሰጠው ምግባቸውን ይሸጥለት ዘንድ ባለ ሱቁም ያን ብር ተመለከተው የንጉሥ ዳኬዎስም ስም ተቀርጾበት አገኘውና ያንን ሰው ይዞ በአንተ ዘንድ የተሸሸገ መዝገብ አለ ይህ ምልክት ከአንተ ተገኝቷልና አለው።
እንዲህም ሲጣሉ ወደእርሳቸው ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እንዲህም ብለው ጠየቁት አንተ ከወዴት ነህ ከዚች አገር ነኝ አላቸው።ማንን ታውቃለህ አሉት እርሱም ዕገሌንና ዕገሌን አላቸው ከዘመን ብዛት የተነሣ የጠራቸውን ሰዎች የሚያውቃቸው የለም።ስለዚህም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ወደ ዳኞችና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ቴዎድሮስ ወደ ንጉሥ ቴዎዶስዮስም አቀረቡት።
ንጉሡና ኤጲስቆጶሱም ከአንተ የሆነውን እውነቱን ንገረን ከወዴት አገር ነህ አሉት። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው እኛ ሰባታችን የከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ነን እርሱም ወጥቶ ወደ ሌላ አገር በሔደ ጊዜ ከአንዷ ዋሻ ውስጥ ገብተን የዋሻዋን በር ዘግተን ተኛን። እነሆ ስንነቃ የምንመገበውን ምግብ እገዛ ዘንድ ላኩኝ።
ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ በሰሙ ጊዜ ተነሥተው ወደዚያ ዋሻ ከእርሱ ጋራ ሔዱ ከእርሳቸውም ጋራ ብዙ ሕዝቦች አሉ ቅዱሳኑንም ተቀምጠው አገኙአቸው። የዘመኑም ቁጥር በውስጡ የተጻፈበትን በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን የሆነውን ሠሌዳውን ወድቆ አገኙት ዘመኑም ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት እንደሆነ ታወቀ።
ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉትም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው ትንሣኤ ሙታን እንዳለ አመኑ። እሊህ ሰባቱ ደቂቅንም በጠየቋቸው ጊዜ ከእርሳቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩአቸው።
ከዚህም በኋላ ተመልሰው ተኙ። ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ንጉሥም የወርቅ ሣጥን ሠራላቸው በሐር ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው። ከሥጋቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
ስማቸውም:- መክሲማኖስ፣ ታሙኪሮስ፣ መርዳዲሞስ፣ ዮሐንስ፣ ቈስጠንጢኖስ፣ አዝሚና ዲዮናስዮ ነው።
† ነሐሴ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (5ኛ ቀን)
2.ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ
3.አቡነ ሰላማ ካልዕ (መተርጉም)
4.ቅድስት ሔዛዊ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የእሊህም ቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን!
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
😘10❤4🥰3💯2😍1
🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
Aug 25, 2026🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
😘4🥰3❤1😍1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 25, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
🥰5❤3😍3😘2
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Aug 25, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🥰5❤3😘3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Aug 25, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍7😘5🥰1
"✝" ከጎንደር 44ቱ አድባራት አንዱና ከተመሠረተ ከ600 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን #ጋናዮሐንስን ያቀኑት ታላቁ ሐዋርያዊ ጻድቅ አቡነ ዮሐንስ ዘጋና "✝"
Aug 24, 2026"✝" ከጎንደር 44ቱ አድባራት አንዱና ከተመሠረተ ከ600 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን #ጋናዮሐንስን ያቀኑት ታላቁ ሐዋርያዊ ጻድቅ አቡነ ዮሐንስ ዘጋና "✝"
☞ነሐሴ19 በዓለ ዕረፍታቸው ይከበራል፡፡
☞ በረከታቸው ይደርብን፡፡
❤6🥰4😍3😘3
#ነሐሴ_19 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን የታላቁ #አባ_መቃርስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ የደግነት የምጽዋት የፍቅር አባት የሆነው #ደጉ_አብርሃም ጣዖት የሰበረበት፣ የአልዓዛር ልጅ …
Aug 24, 2026#ነሐሴ_19 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን የታላቁ #አባ_መቃርስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ የደግነት የምጽዋት የፍቅር አባት የሆነው #ደጉ_አብርሃም ጣዖት የሰበረበት፣ የአልዓዛር ልጅ #የቅዱስ_ፊንሐስ መታሰቢያው ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ ነሐሴ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሳስዊር ከሚባል አገር ወደ አስቄጥስ ገዳም…
🥰9❤4😍3😘3
#ነሐሴ_19
Aug 24, 2026#ነሐሴ_19
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን የታላቁ #አባ_መቃርስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ የደግነት የምጽዋት የፍቅር አባት የሆነው #ደጉ_አብርሃም ጣዖት የሰበረበት፣ የአልዓዛር ልጅ #የቅዱስ_ፊንሐስ መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ
ነሐሴ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሳስዊር ከሚባል አገር ወደ አስቄጥስ ገዳም የታላቁ አባ መቃርስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።
ከዕረፍቱ በኋላ ከሀገሩ ከሳስዊር ሰዎች መጥተው ሥጋውን ሰርቀው ወደ ሀገራቸው ወሰዱት ቤተ ክርስቲያንም ሠርተውለት ሥጋውን በዚያ አኖሩት እስላሞች እስከ ነገሡበት ዘመንም በዚያ ኖረ።
ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ አፍልሰውት በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት። ለአባ መቃርስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ አባ ዮሐንስ እስከ ተሾመበት ዘመን ኖረ።
ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረች ጾመ አርብዓን ሊጾም ወደ አባ መቃርስ ገዳም በወጣ ጊዜ ፈጽሞ አለቀሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ። ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የከበረ የአባ መቃርስ ሥጋ በዚህ ገዳም በመካከላችን ይሆን ዘንድ እንድትረዳኝ እመኛለሁ።
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ አባ ሚካኤል ሔደ ከእርሱ ጋራም ስለ ገዳሙ አገልግሎት አረጋውያን መነኰሳት አሉ ልቦናቸውም በመንፈሳዊ ሁከት ተነሣሥቶ ያመጡት ዘንድ የአባ መቃርስ ሥጋ ወደ አለበት ቦታ ደረሱ።
የአገር ሰዎችም በአዩአቸው ጊዜ በትሮቻቸውንና ሰይፎቻቸውን በመያዝ ከመኰንናቸው ጋራ ተሰብስበው ከለከሏቸው። በዚያቺም ሌሊት በልባቸው ፈጽሞ እያዘኑ አደሩ። አባ መቃርስም በዚያች ሌሊት ለመኰንኑ በራእይ ተገለጠለትና ከልጆቼ ጋራ መሔድን ለምን ትከለክለኛለህ እንግዲህስ ተወኝ ከእሳቸው ጋራ ወደ ቦታዬ ልሒድ አለው።
ያ መኰንንም በጥዋት ተነሣ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ የከበሩ አረጋውያን መነኰሳትን ጠርቶ የከበረ የአባ መቃርስን ሥጋ ሰጣቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው ተቀበሉት በመርከብም ተሳፍረው ተርኑጥ ወደሚባል አገር ደረሱ ከእርሳቸውም ጋራ የሚሸኙአቸው ከየአገሩ የመጡ ብዙ ሕዝቦች ነበሩ። በዚያችም ሌሊት በዚያ አደሩ ጸሎትንም አደረጉ ቀድሰውም ለሕዝቡ ሥጋውንና ደሙን አቀበሉ።
ከዚህም በኋላ ተሸክመው ወደ ገዳም ተጓዙ ሲጓዙም ከበረሀው እኵሌታ ደርሰው ከድካማቸው ጥቂት ሊአርፉ ወደዱ። አባ ሚካኤልም የከበረ የአባታችን የአባ መቃርስን ሥጋ የምናሳርፍበትን እግዚአብሔር እስከ ገለጠልን ድረስ እንደማናርፍ ሕያው እግዚአብሔርን ብሎ ማለ።
ከዚህም በኋላ የከበረ የአባ መቃርስን ሥጋ የተሸከመ ገመል ወደ አንድ ቦታ ደርሶ በዚያ በረክ አለ። የከበረ የአባ መቃርስ ሥጋ ያለበትንም ሣጥን ይጥል ዘንድ በራሱ ወዲያና ወዲህ ይዞር ጀመረ። አረጋውያን መነኰሳትም እግዚአብሔር የፈቀደው ያ ቦታ እንደሆነ አወቁ እጅግም አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ያም ቦታ እስከ ዛሬ የታወቀ ነው።
ወደ ገዳሙም በቀረቡ ጊዜ መነኰሳቱ ሁሉም ወጡ ወንጌልና መስቀሎችን ይዘው መብራቶችን እያበሩ እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እስከ አስገቡት ድረስ በታላቅ ክብር በራሳቸው ተሸክመው ወሰዱት።
እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት ተአምራትን አደረገ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አበ_ብዙሃን_ቅዱስ_አብርሃም
በዚህችም ቀን የሃይማኖት የደግነት የምጽዋት የፍቅር አባት የሆነው ደጉ አብርሃም ጣዖት የሰበረበት እለት ይታሠባል።
በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የአብርሃም አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር። ሽጦ ገንዘብ የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር። በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ ገብቶ ነበር። አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ። "አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ። መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን አልጠይቀውም" በሚል አናገረው።
"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት ሔደዋል:: ከገበያ ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ አብርሃም እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው።
ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው:: ይህ የተደረገው ከ2,000 ዓመታት በፊት በዚህች ቀን ነው። የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ የእግዚአብሔር ወዳጅ አባታችን አብርሃም በመጨረሻው በውሃ፣ በነፋስ፣ በእሳትና በፀሐይ ተመራምሮ ፈጣሪውን አግኝቷል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ፊንሐስ_ካህን
በዚህች ቀን የአልዓዛር ልጅ የፊንሐስ መታሰቢያው ነው። ካህኑ ፊንሐስ የብሉይ ኪዳን ዘመን አገልጋይ: ከነገደ ሌዊ: የሊቀ ካህናቱ የአሮን የልጅ ልጅ ነው:: አባቱም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ነው:: ፊንሐስ እሥራኤል ከግብጽ ሲወጡ ሕጻን የነበረ ሲሆን አድጐ በመጀመሪያ ካህን፤ አባቱ አልዓዛርና አያቱ አሮን ሲያርፉ ደግሞ ሊቀ ካህንነትን ተሹሟል::
አንድ ቀን በጠንቅዋዩ በበለዓም ክፉ ምክር እሥራኤላውያን ከሞዐብ ሴቶች ጋር በኃጢአት በመሳተፋቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበር:: ያጠፋቸው ዘንድም መቅሰፍት ተጀምሮ ሳለ ፊንሐስ ወንድና ሴት: በደብተራ ኦሪቱ አንጻር የማይገባውን ሲሠሩ አያቸው::
ለፈጣሪው ቀንቶ በአንድ ጦር ሁለቱንም በአንድ ላይ ጥሏቸዋል:: ያን ጊዜ ጌታ "አስተንፈስካ ለነፍስየ" ብሎታል:: መቅሰፍቱም ተከልክሏል:: በዚህም ምክንያት ካህኑ ፊንሐስ የ300 ዓመት ዕድሜ ተጨምሮለት: እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: (ዘኁ. 25፥7, መዝ. 105፥30)
† ነሐሴ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (4ኛ ቀን)
2.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ፍልሠቱ)
3.አባታችን ቅዱስ አብርሃም (ጣዖቱን የሰበረበት)
4.ቅዱስ ፊንሐስ ካህን (ወልደ አልዓዛር)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
🥰11😍4❤2😘2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 24, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😍8🥰3❤2
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 24, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤8😍2😘2🥰1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 23, 2026#ነሐሴ_18
Aug 23, 2026#ነሐሴ_18
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_እለእስክንድሮስ አረፈ፣ የከበረና የተመሰገነ ሐዋርያ #ቅዱስ_እንድራኒቆስ መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_እለእስክንድሮስ
ነሐሴ ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን ቁጥሩ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ አረፈ። ይህም አባት ከአርዮስ ወገኖች ብዙ ችግር ደርሶበታል እርሱ ከወገኖቹ ጋር ሁኖ አርዮስን አውግዞ ከቤተክርስቲያን አሳዶት ነበርና።
በታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘመን በኒቅያ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ሊቃውንት አርዮስን በጉባኤ አውግዘው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው በአሳደዱት ጊዜ ወደ ንጉሡ ቈስጠንጢኖስ ጓደኞቹን ይዞ ገብቶ በእለእስክንድሮስና በአትናቴዎስ ላይ ነገር ሠራ ሁለተኛም እለእስክንድሮስ ከካህናቱ ጋር ይቀበለው ዘንድ እንዲያዝለት ንጉሡን ለመነው።
ንጉሡም ልመናውን ተቀብሎ መልእክተኞችን ልኮ አባት እለእስክንድሮስን አስመጥቶ እንዲህ አለው "አትናቴዎስ ትእዛዛችንን በመተላለፍ አርዮስን አልቀበልም ብሏል፤ እኛም አንተን እንዳከበርንህ አንተ ታውቃለህ አሁንም ትእዛዛችንን አትተላለፍ አርዮስንም ከውግዘቱ ፈትተህ ልባችንን ደስ አሰኝ" አለው ።
ቅዱስ እለእስክንድሮስም ለንጉሥ እንዲህ ብሎ መለሰለት "አርዮስን እኮን ቤተክርስቲያን አልተቀበለችውም። ልዩ ሦስትነትን አያመልክምና" ንጉሡም "አይደለም እርሱ በሥሉስ ቅዱስ ያምናል እንጂ" አለው ቅዱስ እለእስክንድሮስም "ወልድ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ትክክል እንደሆነ የሚያምን ከሆነ በእጁ ይጻፍ" ብሎ መለሰለት።
ንጉሥም አርዮስን አስቀርቦ "ትክክለኛ ሃይማኖትህን ጻፍ" አለው አርዮስም በልቡ ሳያምን 'ወልድ ከአብ ጋራ በመለኮቱ ትክክል ነው' ብሎ ጻፈ በሐሰትም የከበረ ወንጌልን ይዞ ማለ። ንጉሡም ቅዱስ እለእስክንድሮስን "አሁን በአርዮስ ላይ ምክንያት አልቀረህም ትክክለኛ ሃይማኖቱን ጽፎአልና በከበረ ወንጌልም ምሎአልና" አለው ።
አባ እለእስክንድሮስም ንጉሡን እንዲህ አለው "በአባትህ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እጅ የተጻፈ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ አባቶች በእጆቻቸው የጻፉትን እርሱንና ወገኖቹን ከቤተ ክርስቲያን እንዳሳደዷቸው የአርዮስን ክህደቱንና ውግዘቱን አትናቴዎስ አንብቦታል። ነገር ግን አንድ ሱባዔ በእኔ ላይ ታገሥ በዚህ ሱባዔ በአርዮስ ላይ አንዳች ነገር ካልደረሰ ይህ ካልሆነ ሃይማኖቱ መሐላውም እውነት ነው እኔም ተቀብዬ ከካህናቱ ጋር እቀላቅለዋለሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ከእሳቸው ጋራ አንድ ይሆናል።"
ንጉሡም አባት እለእስክንድሮስን እንዲህ አለው "እወቅ እኔ ስምንቱን ቀኖች እታገሥሃለሁ አርዮስን ካልተቀበልከው በአንተ ላይ የፈለግሁትን አደርጋለሁ።" ከዚህም በኋላ ከንጉሡ ዘንድ ወጥቶ ወደ ማደሪያው ሔደ ቤተክርስቲያንን ከአርዮስ መርዝ ያድናት ዘንድ በዚያ ሱባዔ እየጾመና እየጸለየ ወደ እግዚአብሔር ሲለምን ሰነበተ።
ከዚያም ሱባዔ በኋላ አርዮስ መልካም ልብስን ለበሰ ወደ ቤተክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ከካህናቱ ጋራ ተቀመጠ። ከዚህም በኋላ አባ እለእስክንድሮስ እያዘነና እየተከዘ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ የሚሠራውን አላወቀም የቅዳሴውንም ሥርዓት ሊጀምር ቆመ። ያን ጊዜ የአርዮስ ሆዱ ተበጠበጠና ወጥቼ ልመለስ አለ ይህንንም ብሎ ወደ መጸዳጃ ቦታ ወጣ። ሊጸዳዳም በተቀመጠ ጊዜ አንጀቱና የሆድ ዕቃው ሁሉ ወጣ በዚያውም ላይ ሞተ።
በዘገየም ጊዜ ሊፈልጉት ወጡ በመጸዳጃውም ቦታ ሬሳውን ወድቆ አገኙት። ለዚህም ለአባት እለእስክንድሮስ ነገሩት እርሱም አደነቀ የከበረች ቤተክርስቲያኑን ያልጣላት ምስጉን የሆነ ክርስቶስንም አመሰገነው።
ንጉሡም በሰማ ጊዜ አደነቀ ከሀዲ አርዮስም በሐሰት እንደማለና በሽንገላ እንደጻፈ አወቀ። የዚህንም አባት የእለእስክንድሮስን ቅድስናውን ዕውነተኛነቱ ሃይማኖቱም የቀናች መሆኗን የአርዮስንም ሐሰተኛነቱንና ከሀዲነቱን ተረዳ።
አንድ የሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስንም አመሰገነው መለኮታቸውም አንድ እንደሆነ ታመነ።
ይህም አባት በበጎ ሥራ ጸንቶ ኖረ ለምለም ወደ ሆነ እርግናም ደርሶ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ የሕይወት አክሊልንም አገኘ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_እንድራኒቆስ
በዚህችም ቀን የከበረና የተመሰገነ ሐዋርያ እንድራኒቆስ መታሰቢያው ነው። ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።
በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው።
ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ።
ከዚህ በኋላ ሐዋርያ እንድራኒቆስ ታመመና ግንቦት ሃያ ሁለት ቀን አረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው።
=>ነሐሴ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (3ኛ ቀን)
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ዲያቆን
4.አባ ዘክርስቶስ ዘወሎ (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴና_ዘወርኀ_ግንቦት)
❤11😘4😍2💯2
† ነሐሴ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
Aug 22, 2026† ነሐሴ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል
2.ቅዱስ እንጣዎስ አሞራዊ (ሰማዕት)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ግብጻዊ (ሰማዕት)
4.ቅዱስ አክራጥስ ሰማዕት
5.አባ እለእስክንድሮስ ዘቁስጥንጥንያ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)
✝ማርያም ድንግል ለእንጣዎስ ባላሒቱ፤
ምስለ እኁኁ አክራጥስ ጊዜ ኮነንዎ ሎቱ፤
ለሄሬኔዎስ ዘኤዶም ስነ ኂሩቱ ወመዓዛ ድርሰቱ፤
ለያዕቆብ ግብጻዊ ለእግዚአብሔር ሰማዕቱ፤
ወለጸጋ ዘአብ ካህን ማርያም ሠርጎ ትርሲቱ!
🌷አርኬ (ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
🥰11😍5❤4😘3
"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"
Aug 22, 2026"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"
☞ (ነሐሴ 17) የታላቁ ሐዋርያዊ ጻድቅ የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት፡ ደገኛው ካህን ቅዱስ ጸጋዘአብ ዐረፈ፡፡
☞እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን፡፡ በረከቱም ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ጸንታ ትኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
😘11🥰3😍3❤2
"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"
Aug 22, 2026"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"
☞ታላቁን ሊቅ፡ ሰማዕትና ጸረ መናፍቃን የነበረውን የኤዶሙን (ሊዮን-ፈረንሳይ) ጳጳስ፡ ቅዱስ #ሄሬኔዎስን ( Irenaeus) ነሐሴ 17 እናከብራለን፡፡
☞በ130 ዓ/ም በቱርኳ ሰርሚኔስ (አሁን ኢዝሚር) የተወለደው ሊቁ የታላቁ ሐዋርያዊ ጳጳስ ወሰማዕት ቅዱስ #ፖሊካርፐስ (Polycarp) ደቀ መዝሙር ነበር፡፡
☞ያረፈው በ202 ዓ/ም በ72 ዓመቱ ሲሆን ከድንቅ ትምህርቶቹ መካከል የተወሰነው በቤተክርስቲያን ሃይማኖተ አበው ላይ ይገኛል፡፡
✝️ በረከቱ ይደርብን፡፡
🥰12😍5😘3
ቅዱሳን (Saints)
Aug 22, 2026#ነሐሴ_17
Aug 22, 2026#ነሐሴ_17
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አሞራዊ #ቅዱስ_እንጣዎስ በሰማዕትነት አረፈ፣ ከደቡብ ግብጽ አቡስ ከሚባል አውራጃ መኑፍ ከሚባል ታናሽ መንደር #ቅዱስ_ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_እንጣዎስ_አሞራዊ
ነሐሴ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አሞራዊ ቅዱስ እንጣዎስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ክርስቶስን የካደ ነበር ገንዘብ ለማከማቸትም የሚተጋ ነበር።
በአንዲትም ዕለት ወደ ደማስቆ ከተማ ሔደ የበዓላቸው ቀን ነበርና ሕዝቡ ተሰብስበው ሳሉ ወደ ምሥራቃዊው ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ ገብቶም ዕቃዎችን ማቃጠል ጀመረ መስቀልንም ሰበረ።
ከዚህም በኋላ በሰማይ ውስጥ የእሳት ፍላፃዎችን ይዘው ከሀዲዎችን ሲነድፏቸው አየ እርሱንም የቀኝ ጐኑን አንዲት ፍላፃ ነደፈችው። ያን ጊዜም ተጨንቆ ላቡ ተንጠፈጠፈ ከጥልቅ ልቡም እንዲህ ብሎ ጮኸ የቅዱስ ቴዎድሮስ አምላክ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አመንኩብህ ከእንግዲህ ዳግመኛ ሌላ አምላክ እንዳያመልክ በልቡናው ቃል ገባ።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችም በእርሱ ላይ የሆነውን አላወቁም ነገር ግን ጩኸቱንና የሚናገረውን ሰምተው አደነቁ እምነታቸውም ጠነከረ እጅግም ጸና። እንጣዎስም ኤልያስ ወደ ሚባል ጳጳስ ሒዶ በርሱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገረው የክርስትና ጥምቀትንም ያጠምቀው ዘንድ ለመነው።
ጳጳሱም በውኃው ላይ በጸለየ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ እንደ ቀስተ ደመና ሁኖ ሕዝቡ ሁሉ እያዩት ወረደ ቅዱስ እንጣዎስም ተጠመቀ። ከእርሱም ጋራ ከአይሁድና ከአረሚ ዐሥር ሽህ ሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ያህል ሰዎች ተጠመቁ። ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ።
ቅዱስ እንጣዎስም እንዲህ አለ እነሆ ይህን እያደነቅሁ ሳለ በእንቅልፌ ሕልምን አየሁ። ብርሃንን የለበሰች ሴት እጄን ያዘችኝ ወስዳም ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰችኝ ወደ መሠዊያውም አቀረበችኝ እኔም ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል ተዘጋጀሁ በመሠዊያውም ውስጥ ነጭ በግን አየሁ ካህኑም በዕርፈ መስቀል በሠዋው ጊዜ ደሙ ጽዋው ውስጥ ተጨመረ ከእርሱም የክርስቶስን ሥጋና ደም በተቀበልሁ ጊዜ ሥጋው ንጹሕ ኅብስት ደሙም ጥሩ ወይን ሆነ።
ከዚህም በኋላ በደማስቆ ጐዳና ሲጓዝ አስቀድሞ የሚያውቁት ያዙት ወደ ንጉሡም ወሰዱት ንጉሡም ክርስቶስን በማመን እንደጸና አይቶ ጥርሶቹ እስቲበተኑ አፉን በበሎታ እንዲመቱት አዘዘ አፉም ደምን ተመላ። ከዚህም በኋላ እህል ውኃን ሳይሰጡ በተበሳ ግንድ ውስጥ ሰባት ቀን ያህል አሠሩት ከዚያም አውጥተው ዲን፣ ሙጫ፣ ዝፍት ከስብ ጋራ ባፈሉበት እሳት ውስጥ ጨመሩት ከእርሱም የመልካም መዓዛ ሽታ ወጣ።
ወታደሮችም ከእሳት ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ አገኙት። እሳቱም አልነካውም ወደ ንጉሥም ወሰዱት ንጉሡም የሥራይን ኃይል መቼ ተማርክ አለው ቅዱስ እንጣዎስም ንጉሡን እንዲህ አለው ሥራይንስ አላውቅም ነገር ግን ክብር ይግባውና በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አሳፍርሃለሁ።
ንጉሡም ቁጣን ተመልቶ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ እንጣዎስ ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ቆመ እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን ወደ እግዚአብሔር አማፀነ ሲጸልይም ወደርሱ እንዲህ የሚል ቃል መጣ ከእስጢፋኖስና ከጊዮርጊስ ጋራ ታርፍ ዘንድ አገልጋዬ በሰላም ና። ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ራሱን ቆረጡት ምስክርነቱንም ፈጸመ ከሥጋውም ቁጥር የሌላቸው ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ግብጻዊ
በዚህችም ቀን ከደቡብ ግብጽ አቡስ ከሚባል አውራጃ መኑፍ ከሚባል ታናሽ መንደር ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት ሞተ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ክርስቲያኖች ነበሩ ከእርሱ መወለድም በፊት ሦስት ሴቶች ልጆችን ወልደው ነበር።
ጥቂትም በአደጉ ጊዜ እንዲያስተምሩአቸውና በፈሪሀ እግዚአብሔር እንዲአሳድጓቸው በገዳም ለሚኖሩ ደናግል ሰጧቸው። የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትንም ተማሩ። ወላጆቻቸውም ሊወስዷቸው በወደዱ ጊዜ እነርሱ ከደናግል ገዳም መውጣትን አልወደዱም። ነገር ግን ለድንግል ማርያምና ለልጅዋ ለክርስቶስ ሙሽሮች ይሆኑ ዘንድ መረጡ ወላጆቻቸውም ከእርሳቸው በመለየታቸው አዘኑ።
መሐሪ ይቅር ባይ እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ ያዕቆብ መወለድ አጽናናቸው። ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ዐውሎ ወደ ሚባል አገር ጥበብን ይማር ዘንድ ላከው ትምህርትንም ተምሮ በትምህርት ሁሉ ፍጹም ሆነ።
አባቱም ለገንዘቡና ለጥሪቱ ለእንስሶቹም ሁሉ ተቈጣጣሪ አደረገው በዚያም አንድ በሥውር ብዙ ትሩፋትን የሚሠራ የበጎች ጠባቂ ነበረ በክረምትም በበጋም ብዙ ጊዜ ወደ ውኃ ጒድጓድ እየወረደ መላዋን ሌሊት ሲጸልይ ያድር ነበር።
ቅዱስ ያዕቆብም ሽማግሌው የበግ ጠባቂ በሚያደርገው አምሳል እያደረገ በዚህ ሥራ ብዙ ዘመን ኖረ። ከዚህም በኋላ ሰይጣን በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራን አስነሣ ብዙዎች ክርስቲያኖችም በሰማዕትነት ሞቱ።
በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት ይሞት ዘንድ ከዚያ ሽማግሌ ጋራ ተስማማ ቅዱስ ያዕቆብም ከሽማግሌው ጋራ ሒዶ ይመለስ ዘንድ አባቱን ፈቃድ ጠየቀ እርሱም ሒድ አለው።
በሔዱም ጊዜ በላይኛው ግብጽ የንጉሥ ልጅ ቅዱስ ዮስጦስን መኰንኑ ሲአሠቃየው አገኙት ሽማግሌውም ልጄ ሆይ ይህ የንጉሥ ልጅ መንግሥቱን ትቶ እውነተኛውን ንጉሥ ክርስቶስን እንደ ተከተለ ከሚስቱና ከልጆቹም እንደተለየ ተመልከት። እኛ ድኆች ስንሆን ለምን ችላ እንላለን ልጄ ሆይ እንግዲህ ተጽናና ከወላጆችህም በመለየትህ አትዘን አለው።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ የረከሱ አማልክቶቹንም ረገሙ ያን ጊዜም መኰንኑ አስቀድሞ ሽማግሌውን ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ራሱንም በሰይፍ ፈጥኖ አስቆረጠው ምስክርነቱንም ፈጸመ።
ቅዱስ ያዕቆብን ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ከገመድ በተሠራ ጅራፍ ገረፈው ድንጋይም በእሳት አግለው በሆዱ ላይ አኖሩ። ዐይኖቹንም አቅንቶ ክብር ይግባውና ወደ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ጸለየ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከዚህ መከራ ርዳኝ አጽናኝም ያን ጊዜም ያለ ምንም ጉዳት አስነሣው።
ከዚህም በኋላ በማቅ ውስጥ አስጠቅልሎ በባሕር ውስጥ አስጣለው የእግዚአብሔርም መልአክ አውጥቶ ያለ ጉዳት በመኰንኑ ፊት አቆመው። መኰንኑንም አሳፈረው የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመ።
ከዚህም በኋላ ፈርማ ወደሚባል አገር ላከው በዚያም የፈርማ መኰንን ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ምላሱን ቆረጠው፣ ዐይኖቹንና ቅንድቦቹንም አወጣ፣ በመንኰራኩርም ውሰጥ አኬዱት፣ በመጋዝም መገዙት፣ ሕዋሳቱ ሁሉም ተሠነጣጠቁ። ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ የእግዚአብሔር መልአክ ሱርያል ወርዶ ቊስሎቹን አዳነለት።
መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሠለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘና ቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። ከገምኑዲ ሀገር የሆኑ አብርሃምና ዮሐንስም ከእርሱ ጋራ ሰማዕታት ሆነው አረፉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
🥰12❤4😍3😘3
✝እንኳን አደረሳችሁ !✝
Aug 21, 2026✝እንኳን አደረሳችሁ !✝
✝ሰላም ለዕርገተ ሥጋኪ ኀበ ሀሎ ርእስ፤
እንዘ ይሴብሑኪ መባርቅት ወዓውሎ ነፋስ፤
ማርያም ድንግል ንጽሕተ ሥጋ ወነፍስ፤
በፍልሠትኪ ዮም ወደሰኪ ጊዮርጊስ፤
ወለጊጋር መተሮ መዓትም ሔሮድስ!
ከጣዕመ ረድኤቷ ያድለን!
😘7😍5❤2🥰1
✝የልዳ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ
Aug 21, 2026✝የልዳ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ
✝ነሐሴ 16 በዓለ ፍልሠቱ ይከበራል።
✝የሰማዕቱ በረከቱ ይደርብን በአማላጅነቱ ሀገራችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ይጠብቅልን::
❤6😘4🥰2😍2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 21, 2026🌹#ነሐሴ_16
Aug 21, 2026🌹#ነሐሴ_16
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ፣ የሰማዕታት አለቃ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥጋው የፈለሰበት ነው፣ #ቅዱስ_ጊጋር በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
🌹#ዕርገተ_ማርያም🌹
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ ።
የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።
የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።
አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።
ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።
ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ።
በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው ። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።
በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ።
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
🌹#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ፍልሰተ_አጽሙ
በዚህችም ዕለት የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሆኗል ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያወቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
🌹#ቅዱስ_ጊጋር_ሰማዕት
በዚህችም ቀን የሶሪያ መስፍን ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ። ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኄሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዳገኟቸው አሸሻቸው።
ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ።
=>ነሐሴ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም (ፍልሠቷ:
ትንሳኤዋና ዕርገቷ)
2.ቅዱሳን ሐዋርያት
3.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ፍልሠቱ)
4.ቅዱስ ጊጋር ሶርያዊ (ሰማዕት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/
ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
❤7🥰3😘3🕊2😍2
✝ ቅድስት ጌቴሴማኒ ✝
Aug 20, 2026✝ ቅድስት ጌቴሴማኒ ✝
"ለመቃብርኪ ሶቤ ለጌቴሴማኒ በመርሕባ::
ጌቴሴማኒሰ ለሥጋኪ ምስካባ::
እግዝእትየ ስሂነ ሳባ::
በሰጊድ ሰላም!!!"
(ያንቺስ መቃብር በጌቴሴማኒ በአውዷ ነውና::
ጌቴሴማኒም የሥጋሽ ማረፊያ ነበረችና::
እመቤቴ ማርያም መዓዛሽ እንደ ሳባ ሽቱ ይመስጣልና፡፡
ስግደትና ሰላምታ ይገባሻል!!!)
"✝' እንኩዋን አደረሰን "✝
@zetewahidosnksar
❤11🥰3❤🔥2😍2😘2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 20, 2026ሠላሳ ሺህ ዐሥራ ሁለት ሰዎች አምነው በሰማዐትነት ሞቱ ከሀዲው መኰንን ድዮስም በድንገት ሞተ።
Aug 20, 2026ሠላሳ ሺህ ዐሥራ ሁለት ሰዎች አምነው በሰማዐትነት ሞቱ ከሀዲው መኰንን ድዮስም በድንገት ሞተ።
ሦስተኛም መኰንን መጣ የከበረች ክርስጢናንም ይዞ ለአማልክት ትሠዋ ዘንድ አባበለት እርሷም እንዲህ አለችው። አንተና አማልክቶችህ ለዘላለም ወደማ ይጠፋ የገሀነም እሳት ትወርዳላችሁ። እጅግም ተቆጥቶ ወደ እሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨምርዋት አዘዘ ምንም የነካት የለም።
ዳግመኛም ለአራዊት ይጥሏት ዘንድ አዘዘ እነርሱም የእግርዋን ትቢያ ላሱ እባቦችንም የሚያጠምደውን ነከሱትና ወዲያውኑ ሞተ።
ሁለተኛም ምላሷንና ጡቶቿን ቆረጡ የምላሷንም ቁራጭ አንሥታ ከመኰንኑ ዐይኖች ላይ ጣለችውና ዐይኖቹን አሳወረችው ። ቁጣውንም ተመልቶ ለእባቦች እንዲጥሏት አዘዘ አንዲቷም እባብ ልቧን ነደፈቻት አንዲቱ ደግሞ ጐኗን እንዲህም የምስክርነቷን ተጋድሎ ፈጸመች ነፍሷንም አሳልፋ የድል አክሊልን ተቀዳጀች ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ለውረንዮስ_ሰማዕት
በዚህችም ዕለት በንጉሥ ዳስዮስ ቄሣር ዘመን ቅዱስ ለውረንዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ በሃይማኖት የጸና ነው የክብር ባለቤት ስለ ሆነ ስለ ክርስቶስ ሃይማኖት ሊቀ ዲቁና ተሹሞ የሊቀ ጵጵስናውን ገንዘብ ይጠብቅ ነበር።
ንጉሥ ስለርሱ ሰምቶ አምጥተው ከወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ በአስገቡትም ጊዜ በዚያ ዕውር ሰውን አገኘና አይኖችህ ይገለጡ ዘንድ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ አምነህ በስሙ ትጠመቃለህን አለው ዕውሩም አዎን ጌታዬ አለ።
ያን ጊዜም በውኃው ላይ ጸልዮ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀው ያን ጊዜም አይኖቹ ተገለጠ። እንዲህም ብሎ ጮኸ በአገልጋዩ ለውረንዮስ ጸሎት ዐይኖቼን የገለጠ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመስገን ብሎ ጮኸ።ይህንንም ድንቅ አይተው ብዙዎች አመኑ።
ንጉሡም በሰማ ጊዜ የከበረ ለውረንዮስን ወደርሱ ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ በአቀረቡትም ጊዜ ለአማልክት እንዲሰዋ አግባባው እምቢ ባለውም ጊዜ ጥርሶቹን በደንጊያ ሰበሩ ልብሶቹንም ገፈው በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ሥጋው እስከሚቀልጥ ከበታቹ እሳትን አነደዱ።
እርሱም ነፍሱን እስከአሳለፈ ድረስ ወደ ፈጣሪው ይጸልይ ነበር። መላእክትም ሃሌ ሉያ እያሉ ተቀብለው ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አስገቡት።
✞ ነሐሴ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት እንባ መሪና ገዳማዊት
2.ቅድስት ክርስጢና ሰማዕት
3.ቅዱስ ለውረንዮስ ሰማዕት
4.ሰላሳ ሺ ሰማዕታት (የቅድስት ክርስቲና ማኅበር)
5.አበው ቅዱሳን ሐዋርያት (ወላዲተ አምላክን ለመገነዝ በዚህ ዕለት ተሠብስበዋል::)
✞ ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
🥰9😘4❤3😍3
#ነሐሴ_15
Aug 20, 2026#ነሐሴ_15
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን አምላክን ስለወለደች #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋን ስለመገነዝ የሐዋርያት ስብሰባ ሆነ፣ #ቅድስት_እንባ_መሪና አረፈች፣ #ቅድስት_ክርስጢና በሰማዕትነት ሞተች፣ #ቅዱስ_ለውረንዮስ በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_እንባ_መሪና_ገዳማዊት
በዚህች ቀን የአንድ ክርስቲያናዊ ባለጸጋ ሰው ልጅ ቅድስት እንባመሪና አረፈች። የዚችም ቅድስት የእናቷ ስም ማርያም ይባላል ሕፃንም ሁና ሳለች እናቷ ሞተች አባቷም አድጋ አካለ መጠን እስከምታደርስ መልካም ትምህርትን እያስተማረ አሳደጋት።
አባቷም እሷን አጋብቶ እርሱ ወደ አንድ ገዳም ሒዶ ይመነኲስ ዘንድ ወደደ ። እርሷም አባቷን ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ታጠፋለህን አለችው። እርሱም ስለ አንቺ እንዴት አደርጋለሁ ከገዳም ውስጥ ሴትን አይቀበሉምና አላት እርሷም እንዲህ አለችው አባቴ ሆይ የሴቶችን ልብስ ከላዬ አስወግደህ የወንዶችን ልብስ አልብሰኝና ከአንተ ጋራ ውሰደኝ።
የልቧንም ጽናት አይቶ የወንድ ልብስ አልብሶ ከእርሱ ጋር ወሰዳት የቀድሞ ስሟ መሪና ነበር እርሱ ግን ስሟን ለውጦ እንባመሪና ብሎ ጠራት ገንዘቡንም ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች በተነ ልጁንም በወንድ ስም እየጠራ ከእርሱ ጋራ ወስዳት ወደ አንድ የመነኰሳት ገዳምም ደርሰው በዚያ እየተጋደሉ ኖሩ።
ከዚህም በኋላ አባቷ ታመመ ለሞትም በቀረበ ጊዜ አበ ምኔቱን ጠርቶ እርሷን ልጁን አደራ ሰጠው ስለ ገዳም አገልግሎት ከገዳም እንዳትወጣ ከዚያም በኋላ አረፈና ቀበሩት።
የከበረች እንባመሪናም ከአባቷ ተለይታ ብቻዋን ቀረች በጾም በጸሎት በስግደት ከቀድሞዋ ዕጥፍ አድርጋ ተጋድሎ ጀመረች።
ከዚህም በኋላ የገዳሙ መነኰሳት ይህ ወጣት መነኰስ ከእኛ ጋራ ለገዳሙ አገልግሎት ለምን አይወጣም ብለው ተቃወሟት እንዲህም አበምኔቱን በአሰጨነቁት ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ ሰደዳት።
ለመነኰሳቱ ቀልብ የሚሆነውን የገዳሙን እህል የሚሰበስብ አንድ ሰው አለ መነኰሳቱም በሚወጡ ጊዜ ከእርሱ ዘንድ አድረው እህላቸውን ይጭናሉ የእንግዳ መቀበያ ቤትም
አለው በዚያ ያድራሉ።
በዚያችም ዕለት ከጐረቤቱ አንድ ጐልማሳ ሰው መጥቶ በዚህ ሰው ቤት አድሮ የልጅን ድንግልና አጠፋ ። እንድህም አላት አባትሽ ማን ደፈረሽ ብሎ የጠየቀሽ እንደሆነ አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኰሴ ደፈረኝ በይው።
በፀነሰችም ጊዜ አባቷ አወቀ ማነው የደፈረሽ ብሎ ጠየቃት እርሷም እንዲህ ብላ ረለሰችለት አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኵሴ ደፈረኝ።
ያን ጊዜም ተነሥቶ ወደዚያ ገዳም ሒዶ መነኰሳቱን ይረግማቸው ጀመረ። አበምኔቱም ሰምቶ ወጣና መነኰሳቱን ለምን ትረግማቸዋለህ እግዚአብሔርን አትፈራውምን አለው እርሱም በልጁ ላይ የሆነውን ነገረው አንዲህም አለው አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኰሴ የልጄን ድንግልና ስለደፈረ ነው አለው።
አበ ምኔቱም በሰማ ጊዜ እውነት መሰለውና እጅግ አዘነ ሰውየውንም እንዲህ ብሎ ለመነው በአንድ ሰው በደል ንጹሐን የሆኑ መነኰሳትን በሕዝባውያን ፊት አታዋርዳቸው ይህንንም ነገር ሠውር።
ከዚህም በኋላ ቅድስት እንባመሪናን ጠርቶ ይገሥጻትና ይረግማት ጀመረ እርሷም ስለምን እንደሚረግማት አላወቀችም ነበር በአወቀችም ጊዜ ከእግሩ በታች ወደቃ እኔ ወጣት ነኝና በደሌን ይቅር በለኝ ብላ ለመነችው እርሱም አጅግ ተቆጥቶ ከገዳሙ አባረራት እርሷም ከገዳም ውጭ ሁና እየተጋደለች ኖረች።
ያቺም ልጅ በወለደች ጊዜ የልጅቷ አባት ሕፃኑን አምጥቶ ለቅድስት እንባመሪና ሰጣት እርሷም እግዚአብሔርን እያመሰገነች ተቀበለችው በላሞችና በበጎች ጠባቂዎች ዘንድ ለሕፃኑ ወተትን እየለመነች መዞርን ጀመረች እንደዚህም አድርጋ ሕፃኑን አሳደገችው።
ከሦስት ዓመትም በኋላ መነኰሳቱ ተሰብስበው አባ ምኔቱን ለመኑት አባ እንባመሪናን ይቅርታ አድርጎለት ወደ ገዳሙ ይመልሰው ዘንድ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከመነኰሳቱ ጋራ ቀላቀላት ይኸውም ከባድ ቀኖና ከሰጣት በኋላ ነው።
ከዚህም በኋላ ጭንቅ የሆኑ ሥራዎችን ትሠራ ጀመረች የመነኰሳቱንም ቤቶች ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳሙ ውጭ ትጥለዋለች ውኃንም ቀድታ ታጠጣቸዋለች ምግባቸውንም ታዘጋጃለች።
ያም ሕፃን አደገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ መነኰሰ።
አርባ ዓመትም ሲፈጸም ሦስት ቀኖች ያህል ታማ በሰላም አረፈች ደወልንም ደውለው መነኰሳቱ ሁሉ ተሰበሰቡ ሊገንዙም ገብተው ልብሶቿን በገለጡ ጊዜ እርሷ ሴት እንደ ሆነች አግኝተዋት ደነገጡ መሪር እንባንም አለቀሱ አበ ምኔቱም በጣም ጊዜ ያለ በደሏ ከባድ ንስሐ ቀኖና ስለ ሰጣትና በእርሷ ላይ ስለ አደረገው ተግሣጽ መሪር ዕንባን አለቀሰ።
ከዚህም በኋላ መልእክተኞችን ልኮ የዚያችን የሐሰተኛ ልጅ አባቷን አስመጥቶ እንባመሪና ሴት እንደሆነች ነገረው ።
ከዚህም በኋላ በድኗን ተሸክመው ይቅር ይበለን የሚል ቃል ከበድኗ እስከ ሰሙ ድረስ አቤቱ ክርስቶስ ማረን እያሉ ጸለዩ ከዚያም በኋላ በዝማሬና በማኅሌት ከብዙ ልቅሶ ጋር ገነዟት ከሥጋዋም ተባርከው ቀበሩዋት።
እነሆ እግዚአብሔር ክፉ ሰይጣንን አዝዞት ያቺን ሐሰተኛ ሴት ልጅና ድንግልናዋን የደፈረውን ጉልማሳ ያዛቸው እያጓተተም አሠቃይቶ ይቀጣቸው ጀመረ ወደ ቅድስት እንባመሪና መቃብር ሔደው ኃጢአታቸውን በሕዝቡ ሁሉ ፊት እስከሚአምኑ እጅግ አሠቃያቸው ።
ከመቃብርዋም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ክርስጢና
በዚህች ቀን የመኰንን ርባኖስ ልጅ ቅድስት ክርስጢና በሰማዕትነት ሞተች። አባቷ ጣዖታትን የሚያመልክ ነው። እርሷም አባቷ እንደ አስተማራት ታጥናቸው ነበር።
በአንዲት ዕለትም አስባ ተመራመረች በልቧም እግዚአብሔርን መፍራት አደረ ተነሥታም ፊቷን ወደ ምሥራቅ መልሳ ቆመች የምትጓዝበትንም የሕይወት መንገድ ይመራት ዘንድ ጸለየች መንፈስ ቅዱስም አንድነቱንና ሦስትነቱን ገለጠላት።
አባቷም በመጣ ጊዜ ልጄ እንዴት አለሽ አላት በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሕይወት አለሁ አለችው። አባቷም ሰምቶ ደነገጠ ልብሽን ምን ለወጠው አላት እርሷም ከሰማይ አምላክ ተማረኩ አለችው። ከዚህም በኋላ አባቷ እያዘነ ሔደ።
እርሷም ተነሥታ ወደ እዚአብሔር ጸለየች ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንዲህ አላት በርቺ ከሦስት መኳንንት ትሠቃዪ ዘንድ አለሽ አዳኝ በሆነ በጌታችን ክርስቶስ መስቀልም አተማት ሰማያዊ ኅብስትንም ሰጣት።
ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጣዖታቱ ወደ አሉበት ቤት ገብታ ቀጠቀጠቻቸው ።አባቷም አይቶ እጅግ ተቆጣ ልጁንም ይገርፏት ዘንድ አዘዘ ከሥጋዋም ስለ ደም ፈንታ ማር ወጣ። ሁለተኛም በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታችዋ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ እርሷን የነካት የለም ግን ከአረማውያን ብዙዎችን አቃጠለ።
ዳግመኛም በታንኳ አድርገው ወደ ባሕር ይጥሏት ዘንድ አዘዘ በጸለየችንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክት ጋራ መጥቶ ራሱ አጠመቃት ሚካኤልም በእሳት ጉጠት የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሥጋና ደም አቀበላት ከጣዖታት እድፍም አነጻት በዚያችም ሌሊት አባቷ ርባኖስ ሞተ ። ስሙ ድዮስ የሚባል ሌላ መኰንን መጣ ቅድስት ክርስጢናን አምጥተው ራቁቷን ሰቅለው ከበታችዋ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ ። ሴቶችም ራቁትነቷን አይተው መኰንኑን ረገሙት እነርሱም በሰይፍ አስቆረጣቸው እርሷን ግን ምንም ምን አልነካትም ሕዝቡም ይህን ተአምር አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
😘11🥰3😍3❤🔥2❤2
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
Aug 20, 2026⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
🔐ከስር ክፈት የሚለውን
በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
................💚💛❤️...............
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
...............💚💛❤️................
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
🥰2😘2😍1
አባ ስምዖን እና አባ ዮሐንስ St. Simeon the Holy Fool and St. John the Ascetic
Aug 19, 2026አባ ስምዖን እና አባ ዮሐንስ St. Simeon the Holy Fool and St. John the Ascetic
🥰6❤3😘3😍2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 19, 2026ከዚያም በማግስቱ አበ ምኔቱ የምንኲስናን ልብስ አለበሳቸው በቀን እንደሚተያዩ በሌሊትም እርስበርሳቸው የሚተያዩ እስቲሆኑ በፊታቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን በራ ሁለተኛም በዚህ መነኵስ ላይ እንደሰዩ በራሶቻቸው ላይ የብርሃን አክሊል አ…
Aug 19, 2026ከዚያም በማግስቱ አበ ምኔቱ የምንኲስናን ልብስ አለበሳቸው በቀን እንደሚተያዩ በሌሊትም እርስበርሳቸው የሚተያዩ እስቲሆኑ በፊታቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን በራ ሁለተኛም በዚህ መነኵስ ላይ እንደሰዩ በራሶቻቸው ላይ የብርሃን አክሊል አዩ።
ከዚህም በኋላ ከመነኰሳቱ መካከል ተለይተው ወደ በረሀ ይገቡ ዘንድ ኀሳብ መጣባቸው። በዚያችም ሌሊት ብርሃንን የለበሰ ሰው ለአበ ምኔቱ ተገልጾ የክርስቶስ በጎች እንዲወጡ የገዳሙን በር ክፈት አለው በነቃም ጊዜ ወደ በሩ ሒዶ ተከፍቶ አግኝቶት እያዘነና እየተከዘ ሳለ ሊወጡ ፈለገው እሊህ ቅዱሳን መጡ በፊታቸውም በትረ መንግስትን አየ።
በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት ተገናኛቸው እነርሱም በልባቸው ያሰቡትን ነግረውት እንዲጸልይላቸው ለመኑት ለረጅም ጊዜም አለቀሰ ከዚህም በኋላ ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ በቀኙና በግራው አቆማቸው እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ጸሎት አድርጎ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠበቃቸው።ከዚያም በፍቅር አሰናበታቸው።
ከዚህም በኋላ አርጋኖን ወደ ምባል ወንዝ ሔዱ በዚያም አንድ ገዳማዊ በዚያን ወራት ያረፈ በውስጡ የኖረበትን በዓት አገኙ በውስጡም ያ ሽማግሌ ገዳማዊ ሲመገበው የነበረ ለምግባቸው የሚያስፈልጋቸውን የእህል ፍሬዎችን አገኙ ምግባቸውን በአዘጋጀላቸው በእግዚአብሔርም እጅግ ደስ አላቸው።
በድንግያ ውርወራ ርቀት መጠን አንዱ ከሁለተኛው የተራራቁ ሁነው ሰፊ በሆነ ተጋድሎ ቡዙ ዘመናት ኖሩ። ሰይጣንም ቡዙ ጊዜ ይፈታተናቸው ነበር ግን አባታቸው ቅዱስ ኒቅዮስ በራእይ ወደ እሳቸው መጥቶ ስለ እነርሱ ይጸልያል ተኝተውም ሳሉ የዳዊትን መዝሙር ያስተምራችዋል በነቁም ጊዜ ያስተማራቸውን ሁሉ በትክክል ያነቡታል እጅግም ደስ ይላቸዋል።
አምላካዊ ራእይም ተሰጣቸው ተአምራትንም ያደርጋሉ በዚያችም በረሀ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ኃይል ሰይጣንን ድል እስከ አደረጉት ድረስ የቀኑን ሐሩር የሌሊቱን ቊር ታግሠው ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነሩ።
ከዚህም በኋላ ስምዖን ወንድሙ ዮሐንስ እንዲህ አለው በዚህ በረሀ በመኖራችን ምን እንጠቃማለን ና ወደ አለም ወጥተን ሌሎችን እንጥቀማቸው እናድናቸውም ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለው ወንድሜ ሆይ ይህ ኀሳብ ከሰይጣን ቅናት የተነሣ ይመስለኛል።
ስምዖን እንዲህ አለው ከሰይጣን አይደለም በዓለም ላይ እንድዘበትበት እግዚአብሔር አዞኛልና ነገር ግን ና እንጸልይ ያን ጊዜም በአንድነት ጸለዩ ልብሳቸውንም እስከ አራሱት ድረስ እርስበርሳቸው ተቃቅፈው አለቀሱ። ከዚህም በኋላ ስምዖን እስከሚሞትባት ቀን ሥራውን ይሠውርለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ጎዳናውን ተጓዘ።
ወደ ዓለምም ገብቶ ራሱን እንደ እብድ አደረገ እብዶችንም የፈወሰበት ጊዜ አለ እሳትን በእጁ የሚጨብጥበትም ጊዜ አለ። ከዚህም በኋላ ከከተማው በር የሞተ ውሻ አግኝቶ በመታጠቂያውም አሥሮ እየጐተተ እንደሚጫወት ሆነ ሰዎች እስከሚሰድቡትና እስከሚጸፉት ድረስ።
በአንዲት ቀን እሑድ ከቅዳሴ በፊት የኮክ ፍሬ ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ መቅረዞችንም ሰበረ።ሴቶችንም መትቶ ከእርሳቸው ጋራ እንደሚተኛ ጐተታቸው ባሎቻቸውም ደበደቡት።
ዕረፍቱም ሲቀርብ የእግዚአብሔር መልአክ የእርሱንም የወንድሙ የዮሐንስንም የዕረፍታቸውን ጊዜ ነገረው ወደ ወይን ሐረግ ሥር ገብቶ ከወንድሙ ዮሐንስ ጋራ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ባስሊቆስ
በዚህችም ቀን ቅዱስ ባስሊቆስ በሰማዕትነት ሞተ። በእሥር ቤትም እርሱ ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት እንዲህ አለው የምስክርነትህ ፍጻሜ ደርሷልና ሒደህ ዘመዶችህን ተሰናበታቸው።
ከዚህም በኋላ ወታደሮችን ከእርሱ ጋራ ወደ ቤቱ ይሔዱ ዘንድ ለመናቸው ሒደውም ወደ ቤቱ ገቡ እናቱንና ዘመዶቹንም ተሰናበታቸው። በማግሥቱም የከበረ ባስሊቆስን ወደ ፍርድ ሸንጎ አቀረቡትና በሁለት ምሰሶዎች መካከልም አሥረው ሲደበድቡት ዋሉ በእግሮቹም ችንካሮችን አደረጉበት ደሙም በምድር ላይ ፈሰሰ ያየው ሁሉ አለቀሰለት።
ከዚህም በኋላ ከደረቀ ዕንጨት ላይ አሠሩት ዕንጨቱም በቀለና ቅርንጫፍና ቅጠሎችን አወጣ።ሰዎችም የልብሱን ጫፍ ለመንካት የሚጋፉ ሆኑ በበሽተኞችና በዚህ ዕንጨት ላይ ያደረገውን ተአምር አይተዋልና።
ከዚህም በኋላ ዋርሲኖስ ወደሚባል አገር በመርከብ ወሰዱት ወታደሮችም እንዳትሞት እህልን ብላ አሉት እርሱም እኔ ከሰማያዊ መብል የጠገብኩ ነኝ ምድራዊ መብልን አልመርጥም አላቸው።
ወደ መኰንኑም በአቀረቡት ጊዜ ለአማልክት መሥዋዕትን አቅርብ አለው የከበረ በስሊቆስም እኔ አንድ ለሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የምስጋና መሥዋዕትን አቀርባለሁ አለው።
ሁለተኛም ወደ ጣዖታቱ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ እርሱም ቁሞ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ያን ጊዜ እሳት ወርዶ ጣዖታቱን አቃጠላቸው መኰንኑም ፈርቶ ሸሽቶ ወደውጭ ወጣ። ቁጣንም ተመልቶ ይገድሉት ዘንድ ያ መኰንን አዘዘ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስሊቆስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መከራውን ይሳተፍ ዘንድ ስለ አደለውም አመሰገነው።
ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ብዙዎችም መላእክት ነፍሱን ሲያሳርጓት አዩዋት ጌታችን ኢየሱስም ወዳጄ ባስሊቆስ ወደ እኔ ና እኔ የምዋሽ አይደለሁም ተስፋ ያስደረግሁህን እፈጽምልሃለሁ ብሎ ጠራው። እንዲህም ተጋድሎውን ፈጸመ።
✞ ነሐሴ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ
2.ጻድቃን ቅዱሳን (አባ ስምዖንና አባ ዮሐንስ)
3.ቅዱስ ባስሊቆስ (ኃያል ሰማዕት)
4.ቅዱስ ድምጥያና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
✞ ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
6.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
❤5🕊2😍2😘2🥰1
#ነሐሴ_14
Aug 19, 2026#ነሐሴ_14
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በእስክንድርያ ሀገር ድንቅ ተአምርን አደረገ፣ #የአባ_ስምዖንና የወዳጁ #የአባ_የዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ፣ #ቅዱስ_ባስሊቆስ በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መስቀለ_ክርስቶስ
ነሐሴ ዐሥራ አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእስክንድርያ ሀገር ድንቅ ተአምርን አደረገ። ስለርሱም ከአይሁድ ብዙዎች አምነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ቴዎፍሎስ እጅ ተጠመቁ እርሱም ለቅዱስ ቄርሎስ የእናቱ ወንድም ነው። ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ አገር ስሙ ፈለስኪኖስ የሚባል አይሁዳዊ ባለጸጋ ሰው ይኖር ነበር እርሱም እንደ አባቶቹ የኦሪትን ሕግ የሚጠብቅና እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው።
ዳግመኛም ሙያተኛዎች ሁለት ድኃዎች ክርስቲያኖች አሉ በአንደኛውም ላይ ሰይጣን የስድብ መንፈስ አሳድሮበት ጓደኛውን ወንድሜ ሆይ ክርስቶስን ለምን እናመልከዋለን እኛ ዶኆች ነን ይህ ክርስቶስን የማያመልክ አይሁዳዊ ፈለስኪኖስ ግን እጅግ ባለጸጋ ነው አለው።
ጓደኛውም እንዲህ ብሎ መለሰለት ዕወቅ አስተውል የዚህ ዓለም ገንዘብ ከእግዚአብሔር የሆነ አይደለም ምንም አይጠቅምም ጥቅም ቢኖረው ጣዖትን ለሚያመልኩ ለአመንዝራዎች ለነፍሰ ገዳዮች ለዐመፀኞች ሁሉ ባልሰጣቸውም ነበር።
አስተውል የከበሩ ነቢያት ድኆች ችግረኞችም እንደነበሩ ሐዋርያትም እንደርሳቸው ችግረኞች እንደነበሩ። ጌታችንም ድኆችን ወንድሞቼ ይላቸው እንደነበረ። ሰይጣን ግን የጓደኛውን ምክር እንዲቀበል ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ለውጦ ነፍሱን እስከማጥፋት ድረስ አነሣሣው ቀሰቀሰው እንጂ።
ከዚህም በኋላ ወደ ፈለስኪኖስ ሒዶ በአንተ ዘንድ እንዳገለግል ተቀበለኝ አለው። ፈለስኪኖስም እንዲህ ብሎ መለሰለት በሃይማኖቴ የማታምን አንተ ልታገለግለኝ አይገባም ከቤተ ሰቦቼም ጋራ የማትተባበር ልቀበልህ አይገባኝም። ሁለተኛም ይህ ጐስቋላ ወዳንተ ተቀበለኝ እኔም ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ ያዘዝከኝንም ሁሉ አደርጋለሁ አለው።
አይሁዳዊው ባለጸጋም ከመምህሬ ጋር እስከምማከር ጥቂት ታገሠኝ ብሎ ከዚያም ወደ መምህሩ ሒዶ ድኃው ክርስቲያናዊ ያለውን ሁሉ ነገረው መምህሩም ክርስቶስን የሚክድ ከሆነ ግረዘውና ተቀበለው አለው።
አይሁዳዊውም ተመልሶ መምህሩ የነገረውን ለዚያ ድኃ ነገረው ያም ምስኪን የምታዙኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ። ከዚህም በኋላ ወደ ምኵራባቸው ወሰደው የምኵራቡም አለቃ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ጠየቀው። ንጉሥህ ክርስቶስን ክደህ አይሁዳዊ ትሆናለህን እርሱም አዎን እክደዋለሁ አለ።
የምኵራቡም አለቃ መስቀል ሠርተው በላዩ የክርስቶስን ሥዕል እንዲአደርጉ መጻጻንም የተመላች ሰፍነግ በዘንግ ላይ አሥረው ከጦር ጋራ እንዲሰጡት አዘዘ ከዚያም ከተሰቀለው ላይ ምራቅህን ትፋ መጻጻውንም አቅርብለት ክርስቶስ ሆይ ወጋሁህ እያልህ ውጋው አሉት።
ሁሉንም እንዳዘዙት አድርጎ በወጋው ጊዜ ብዙ ውኃና ደም ፈሰሰ ለረጂም ጊዜም በምድር እየፈሰሰ ነበር በዚያን ጊዜም ያ ከሀዲ ደርቆ እንደ ደንጊያ ሆነ። በአይሁድ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ወደቀባቸው በእውነት የአብርሃም ፈጣሪ ስለእኛ ተሰቅሏል እኛም ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደሆነ አመንበት እያሉ ጮኹ።
ከዚህም በኋላ አለቃቸው ከዚያ ደም ወስዶ የአንድ ዕውር ዐይኖችን አስነካው ወዲያውኑ አየ ሁሉም አመኑ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ሒደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ ተነሣ አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋራ አለ። ወደ አይሁድ ምኵራብም ሒዶ ውኃና ደም ከእርሱ ሲፈስ መስቀሉን አገኘው ከዚያም ደም ወስዶ በግንባሩ ላይ ቀብቶ በረከትን ተቀበለ ሕዝቡንም ሁሉ ግንባራቸውን በመቀባት ባረካቸው።
ያንንም መስቀል አክብረው ተሸክመው እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደው ያኖሩት ዘንድ አዘዘ። ደም የፈሰሰበትንም ምድር አፈሩን አስጠርጎ ለበረከትና ለበሽተኞች ፈውስ ሊሆን በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኖረው።
ከዚህም በኋላ ፈለስኪኖስ ከቤተ ሰቦቹ ሁሉ ጋራ ሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስን ተከተለው ከአይሁድም ብዙዎቹ የቀደሙ አባቶቻቸው በሰቀሉት የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ከእርሱ ጋራ አንድ አደረጋቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ ለዘላለሙ ክብር ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደየቤታቸው ገቡ። እኛንም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን በመስቀሉ ኃይል ያድነን አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አባ_ስምዖንና_አባ_ዮሐንስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የአባ ስምዖንና የወዳጁ የዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ። እሊህ ቅዱሳንም በአማኒው ዮስጦንስ ዘመን መንግሥት የነበሩ ናቸው እሊህም ወንድሞች የከበሩ ክርስቲያን ናቸው።
ከዚህ በኋላ ለከበረ መስቀል በዓል ቅዱሳት መካናትን ሊሳለሙ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ ሥራቸውንም አከናውነው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ ኢያሪኮ ቀረቡ።
ዮሐንስም በዮርዳኖስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳም አይቶ ወንድሙ ስምፆንን ወንድሜ ሆይ ለእሊህ ገዳማት እኮ የእግዚአብሔር መላእክት ይኖራሉ አለው ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋራ ከሆን አወን ልናያቸው እንችላለን አለው።
ከዚያም ከፈረሶቻቸውን ወርደው ለሰዎቻቸው ሰጥተው እስከምናገኛችሁ በየጥቂቱ ተጓዙ ብለው እንደሚጸዳዱ መስለው ወደ ዱር ገቡ።
የዮርዳኖስንም ጐዳና ተጒዘው ከሰዎቻቸው በራቁ ጊዜ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ ጸሎት እናድርግ ከእኛም አንዳንችን ወደ መነኰሳቱ ገዳም በምታደርስ ጐዳና ቁመን ዕጣ እንጣጣል እግዚአብሔር ከፈቀደ ዕጣችን ወደ ወጣበት እንሔዳለን።
ከዚህም በኋላ ስምፆን በዮርዳኖስ ጐዳና ቆመ ዮሐንስም ወደ ሀገራቸው በሚወስድ ጐዳና ላይ ቆመ ዕጣውንም በአወጡበት ጊዜ ዮርዳኖስ ጐዳና ላይ ወጣ እጅግም ደስ አላቸውና ስለ ደስታቸው ብዛት እርስ በእርሳቸው ተያይዘው ተሳሳሙ።
አንዱም አንዱ ወደኋላ እንዳይመለስ ስለጓደኛው ይጠራጠርና ይፈራ ነበር አንዱም ሁለተኛውን ይመክረውና ለበጎ ሥራ ያተጋው ነበር።
ዮሐንስ ስለ ስምፆን ይፈራ ነበር ስለ ወለላጆቹ ፍቅር አንዳይመለስ ስምፆንም ስለ ዮሐንስ ይፈራ ነበር እርሱ በዚያ ወራት መልከ መልካም የሆነች ሚስት አግብቶ ነበርና።
ከዚህም በኋላ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ እንዲህም አሉ በውስጧ እንመነከኵስ ዘንድ ለኛ የተመረጠች ገዳም ደጃፍዋ ክፍት ሆኖ ብናገኝ ምለክት ይሆናል።
የገዳሙም አለቃ ኒቆን የሚሉት በተሩፋት ፍጽም የሆነ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርግ ሀብተ ትንቢት የተሰጠጠው ሲሆን በዚያች ሌሊት በጎቼ ይገቡ ዘንድ የገዳሙን በር ክፈተት የሚለውን ራእይ አየ።
ወደርሱም በደረሱ ጊዜ የክርቶስ በጎች ሆይ መምጣታችሁ መልካም ነው አላቸውና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተላኩ ሰዎች አድርጎ ተቀበላቸው።
ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱን የምንኵስናን ልብስ ያለብሳቸው ዘንድ ለመኑት እነርሱ በቆቡ ላይ የብርሃን አክሊል አድርጎ መላእክትም ከበውት አንዱን መነኰስ አይተዋልና ሰለዚህም ፈጥነው ይመነኵሱ ዘንድ ተጉ።
😍7😘5🥰2🕊2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 19, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😘4😍3❤1
🥖 ስለ ቡሄ እና የቡሄ መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር ባለው link ይቀላቀሉ 🥖
Aug 18, 2026🥖 ስለ ቡሄ እና የቡሄ መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር ባለው link ይቀላቀሉ 🥖
🥰9❤3😘2😍1
🌷እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ
Aug 18, 2026🌷እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ
✨ደብረ ታቦር (የታቦር ተራራ)
✨ደብረ ምስጢር (የምስጢር ተራራ)
✨ወደብረ በረከት (የበረከት ተራራ)
✨ደብር ርጉዕ (ጽኑዕ ተራራ)
✨ወደብር ጥሉል (የለመለመ ተራራ)
✝ ከበረከቱ ከብርሃኑ ከጸጋው ከሃብቱ ያካፍለን፡፡
❤4😍4🥰2😘2💯1
💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
Aug 18, 2026💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹የአበባ ምልክቱን ሲጫኑ ከታች ያሉትን ጠቃሚ ነገሮች ያገኛሉ ይቀላቀሉ 👇👇
😍6😘4❤1🥰1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 18, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤4🥰4😍2😘2
✝በደብረ ታቦር ብረሃነ መለኮቱን ያየ ቅዱስ ሙሴ የዋህ ነብይ ነሐሴ13 ልደቱ ነው።
Aug 18, 2026✝በደብረ ታቦር ብረሃነ መለኮቱን ያየ ቅዱስ ሙሴ የዋህ ነብይ ነሐሴ13 ልደቱ ነው።
ከበዓለ ልደቱ በረከት ያድለን።
@zetewahidosnksar
❤15😍3🥰2😘2
✝እንኳን አደረሳችሁ!
Aug 18, 2026✝እንኳን አደረሳችሁ!
✝በደብረ ታቦር ተገብረ ዘኢተገብረ ቅድመ፤
እስመ ተከሥተ ምሥጢረ ሥላሴ በኀበ እግዚእነ ቆመ፤
እንዘ ይትናገር አብ ግብረ እደዊሁ አርመመ፤
ወመንፈስ ቅዱስ ወሀበ ለሐዋርያቲሁ ሰላመ፤
አሜሃ ሙሴ አንከረ ወኤልያስ ተደመ፤
ጋልዮን ወዓቢየ እግዚእ ወፈሩ ገዳመ!
🌷አርኬ (ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
😘11❤4🥰4😍3
#ነሐሴ_13 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን #በደብረ_ታቦር የገለጠበት ዕለት ነው፣ #የቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት ልደቱ ነው፣ ተጋዳይ #አ…
Aug 18, 2026#ነሐሴ_13 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን #በደብረ_ታቦር የገለጠበት ዕለት ነው፣ #የቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት ልደቱ ነው፣ ተጋዳይ #አባ_ጋልዩን አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ደብረ_ታቦር ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል…
😍11❤5😘3🥰2💯2
#አባ_ጋልዮን_መስተጋድል
Aug 18, 2026#አባ_ጋልዮን_መስተጋድል
በዚችም ቀን ዳግመኛ ተጋዳይ አባ ጋልዩን አረፈ። ይህም በቀንና በሌሊት ለጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጭ አልወጣም ከማኅበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።
ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት። እኛ ተሠውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋራ ልንወስድህ ወደን ወዳንተ መጣን ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሮአቸው ሔደ።
ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህ በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጹለት። እነርሱም የዳዊትን መዝሙር ያነቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁት በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእሳቸው ጋራ አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።
ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው ወዴት ነበርክ አለው እርሱም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገረው።
ከዚህም በኃላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ በሰላም አረፈ መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት።
=>ነሐሴ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ደብረ ታቦር / ደብረ ምሥጢር / ደብረ በረከት
2.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
4.ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
5.አባ ጋልዮን መስተጋድል
6.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ልደታቸው)
7.ቅድስት ኦፍራ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
😘9❤4🥰3😍3❤🔥2
#ነሐሴ_13
Aug 18, 2026#ነሐሴ_13
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ሦስት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን #በደብረ_ታቦር የገለጠበት ዕለት ነው፣ #የቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት ልደቱ ነው፣ ተጋዳይ #አባ_ጋልዩን አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ደብረ_ታቦር
ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።
በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።
በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።
ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።
የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት።
ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።
ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።
ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት
በዚችም ቀን የቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ልደቱ ነው።
ዓለም በተፈጠረ በ3,600 ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት ያዕቆብ ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ215 ዓመታት ተከብረው ለ215 ዓመታት ደግሞ በባርነት በድምሩ ለ430 ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል። በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ 2 ከተሞችን (ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን) በደም ገንብተዋል። ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ። ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ። ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል።
ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ ዮካብድና እንበረም ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው፡፡ ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል። ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይገደሉ ነበር። ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል።
በተወለደ በ3 ወሩ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት (የፈርኦን ልጅ) ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: ሙሴ ያለችውም እርሷ ናት። 'ዕጓለ ማይ (ከውሃ የተገኘ) ለማለት ነው። ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል። ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና።
ቅዱስ ሙሴ 5 ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ። ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና። (ዕብ. 11÷24)
አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ። በዚያም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ። ልጆንም አፈራ። 80 ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው። ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው፡፡ ሙሴም ከወንድሙ ጋር ግብጻውያንን በ9 መቅሰፍት በ10ኛ ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ፡፡
ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፦ እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል፣ ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል፣ ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል፣ ውሃን ከጨንጫ (ከዓለት) ላይ አፍልቁዋል፣ በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል፣ በ7 ደመና ጋርዷቸዋል፣ ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል፣ ቅዱስ ሙሴ ለ40 ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ570 ጊዜ ተነጋግሯል።
ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር። ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል፡፡ ቅዱስ ክቡር ታላቅ ጻድቅ ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ120 ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል። መቃብሩንም ሠውረዋል። (ይሁዳ 1÷9)
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
😘10😍5❤3💯2🥰1
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 18, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😍8😘2🥰1
⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
Aug 18, 2026⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
የሁሉንም አባቶች ትምህርት ይፈልጋሉ❓️
--------------------------------------------------
😘5🥰3❤2😍2
✝ሰላም ለቆስጠንጢኖስ ዘአስተራትአ ሃይማኖተ፤
Aug 17, 2026✝ሰላም ለቆስጠንጢኖስ ዘአስተራትአ ሃይማኖተ፤
ሚካኤል መልአክ እንዘ ይከውኖ ረድኤተ፤
ወዘነግሠ በሮሜ ድኅረ አንኃለ ጣዖተ፤
እግዚእ ኃረያ ዘጼሐት ለተክለ ሃይማኖት ፍኖተ፤
በጊዜ ፍልሠታ ለማርያም ረከበት ዕረፍተ!
🌷አርኬ (ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
✞ ነሐሴ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
2.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
✞ ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
🥰9😍6❤🔥2❤1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 17, 2026#ነሐሴ_12
Aug 17, 2026#ነሐሴ_12
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ #ቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ነገሠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት
ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስከ አሸነፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።
ስለዚህም አባቶቻችን የቤተክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እናደርግ ዘንድ አዘዙን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ንጉሥ_ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ
በዚህችም ቀን ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ነገሠ።
(ዜናውም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ተጽፏል።)
የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ቍንስጣ የእናቱ ስም ዕሌኒ ነው ቊንስጣም በራንጥያ ለሚባል አገር ንጉሥ ነው መክስምያኖስም በሮሜ በአንጾኪያና በግብጽ ላይ ነግሦ ነበር።
ይህም ቍስጣ አረማዊ ነበር ግን በጎ ሥራ ያለው እውነትን የሚወድ በልቡናውም ይቅርታና ርኃራኄን የተመላ ክፋት የሌለበት ነው። ወደሮሐ ከተማ በሔደ ጊዜ ዕሌኒን አይቶ ሚስት ልትሆነው አገባት እርሷም ክርስቲያናዊት ናት። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስንም ፀንሳ ወለደችው ስሙንም ቈስጠንጢኖስ ብላ ጠራቸው ይህም ዝንጉርጒር ማለት ነው።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቊንስጣ ዕሌኒን በዚያው ትቷት ወደ በራንጥያ ከተማ ተመለሰ። እርሷም ልጇን እያሳደገች በዚያው ኖረች የክርስትናን ትምህርት አስተማረችው ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው ትዘራበት ነበር። እርሷ ክርስቲያን ስትሆን የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ አልደፈረችም መንፈሳዊ ዕውቀትን ሁሉ በማስተማር አሳደገችው ዳግመኛም ለመንግሥት ልጆች የሚገባውንም ሁሉ።
ከዚያም በኋላ ወደ አባቱ ሰደደችው አባቱም በአየው ጊዜ ደስ ተሰኘበት ዕውቀትን የተመላ ሁኖ ፈረስ በመጋለብም ብርቱና የጸና ሆኖ አግኝቶታልና በበታቹም መስፍን አድርጎ ሹሞ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ሁሉ ሥልጣን ሰጠው።
ከሁለት ዓመትም በኋላ አባቱ አረፈ ቈስጠንጢኖስም መንግሥቱን ሁሉ ተረከበ የቀና ፍርድንም የሚፈርድ ሆነ ከእርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ አስወገደ። አሕዛብም ሁሉ ታዘዙለት ወደዱትም የአገዛዙ ቅንነትና የፍርዱ ትክክለኛነት በአገሮች ሁሉ እስቲሰማ ተገዙለት።
የሮሜ ሰዎች ታላላቆች መልእክትን ወደርሱ ላኩ ከከሀዲ መክስምያኖስ ጽኑ አገዛዝ እንዲያድናቸው እየለመኑ እርሱ አሠቃይቷቸው ነበርና። ነመልእክታቸውንም በአነበቡ ጊዜ ስለ ደረሰባቸው መከራ እጅግ አዘነ ያድናቸውም ዘንድ ምን እደሚያደርግ በዐደባባይ ተቀምጦ እያሰበ ሲያዝን እነሆ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በቀትር ጊዜ ኅብሩ እንደ ከዋክብት የሆነ መስቀል ታየው በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጹሑፍ አለ ትርጓሜውም በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ ማለት ነው።
የመስቀሉም ብርሃን የፀሐይን ብርሃን ሲሸፍነው በአየ ጊዜ አደነቀ። በላዩ ስለተጻፈውም አስቦ ለጭፍሮቹ አለቆችና ለመንግሥቱ ታላላቅ ባለሥልጣኖች አሳያቸው። እነርሱም ቢሆኑ ይህ መስቀል ስለምን እንደተገለጠ አላወቁም።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ለቈስጠንጢኖስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው በቀኑ እኩሌታ በቀትር በአየኸው በዚያ መስቀል አምሳል ላንተ ምልክት አድርግ በርሱም ጠላትህን ድል ታደርጋለህ አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው መኳንንቱንና ወታደሮቹን ጭፍሮቹን ሁሉ መስቀል ሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ።
ይህም የሆነው በበራንጥያ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ ነው። የሮሜን ሰዎች ከሥቃያቸው ሊያድናቸው ሠራዊቱን ሰብስቦ ተነሥቶ ወጣ። መክስምያኖስም ሰምቶ በታላቅ ወንዝ ላይም ታላቅ ድልድይ ሠርቶ ወደ ቈስጠንጢኖስም ተሻግሮ ከእርሱ ጋራ ተዋጋ።
የመስቀሉም ምልክት ቀድሞ በታየ ጊዜ የመክስምያኖስ ሠራዊት ድል ይሆኑ ነበር የቈስጠንጢኖስም ሠራዊት ከመክስምያኖስ ሰራዊት ብዙ ሰው ገደሉ። የቀሩትም ሸሽተው ሲሔዱ ከመክስምያኖስ ጋር ሊሻገሩና ወደ ሮሜ ሊገቡ ድልድይ ላይ ወጡ ድልድዩም ፈርሶ ፈርዖን ከሠራዊቱ ጋራ እንደ ሠጠመ እንዲሁ መክስምያኖስ ከሠራዊቱ ጋራ ሠጠመ።
ቈስጠንጢኖስም ወደ ሮሜ ከተማ ሲገባ የሮሜ ሰዎች ከካህናት ጋራ መብራቶች ይዘው በእንቍ የተሸለሙ አክሊሎችን ደፍተው እምቢልታ እየነፉ ተቀበሉት የተማሩ ሊቃውንትም የከበረ መስቀልን ሲያመሰግኑት የሀገራችን መዳኛ ይሉት ነበር ለከበረ መስቀልም ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።
ቈስጠንጢኖስም ዳግመኛ በሮሜ ነገሠ ከሀዲዎች የሆኑ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ስለ ክብር ባለቤት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ያሠሩአቸውን እሥረኞች ሁሉንም ፈታቸው ደግሞ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ ብሎ ዓዋጅ አስነገረ።
ዳግመኛም ክርስቲያኖችን እንዲአከብሩአቸው እንጂ እንዳያዋርዱአቸው የጣዖታቱንም ገንዘብና ምድራቸውን ለካህናት እንዲሰጧቸው አዘዘ ክርስቲያኖች በአረማውያን ላይ እንዲሾሙ አደረገ። ዳግመኛም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ ማንም ሰው በሰሙነ ሕማማት ሥራ እንዳይሠራ አዘዘ።
በነገሠ በሥስራ አንድ ዓመት በሮሜ ሊቀ ጳጳሳት በሶል ጴጥሮስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። ሠራዊቱም ሁሉ። ይህም የከበረ መስቀል ከተገለጠለት በኋላ በአራት ዓመት ነው።
ከዚህ በኋላም በእርሱ ርዳታና ድል ያገኘበትን የሚያድን ስለ ሆነ ስለ ጌታችን መስቀል ትመረምር ዘንድ እናቱ ዕሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት። እርሷም ዐመፀኞች አይሁድ ቀብረው ከደፈኑት ቦታ አወጣችው።
በዘመኑ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ጳጳሳት የአንድነት ስብሰባ በኒቅያ ስለ አርዮስ ተደረገ። ለክርስቲያኖች መመሪያ በበጎ አሠራር ክርስቲያናዊት ሥርዓት ተሰራች።
ከዚህም በኋላ በበራንጥያ ታላቅ ከተማ ሊሠራ አሰበ እንደ አሰበውም ታላቅ ከተማ ሠርቶ በስሙ ቍስጥንጥንያ ብሎ ጠራት። በውስጧም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአግያና በሶፍያም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሠራ መንፈሳዊ በሆነ በመልካም ጌጥ ሁሉ አስጌጣት። በውስጥዋ ከሐዋርያት የብዙዎቹን ዓፅም ከሰማዕታትና ከቅዱሳን ጻድቃን ሥጋቸውን ስለሚሰበስብ።
የክብር ባለቤት ጌታችንን ደስ አሰኝቶ መልካም ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በኒቆምድያ ከተማ ጥቂት ታሞ መጋቢት ሃያ ስምንት አረፈ።
ገንዘውም በወርቅ ሣጥን አድርገው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ አደረሱት የጳጳሳት አለቆችና ካህናቱ ከሁሉ ሕዝብ ጋር ወጥተው ተቀበሉት በብዙ ጸሎት በመዘመርና በማኅሌት በምስጋና ወደ ከበሩ ሐዋርያት ቤተ መቅደስ አስገብተው በክብር አኖሩት።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_እና_መጋቢት)
😍4❤3🥰3😘3🕊1
የቡሄ |ደብረ ታቦር መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
Aug 17, 2026የቡሄ |ደብረ ታቦር መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
🎶 ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
🎶 ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ
🎶 አምላካችን ናና በዓምደ ደመና
🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
🎶 ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው
🎶 ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ.....
🎶 እንደ ጸሐይ ፊቱ ሲያበራ
🎶 የታቦር ተራራ ምንኛ ታደለች
🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
🎶 እንዲህ አለው ጴጥሮስ
🎶 በክብር ተገለጠ በታቦር
🎶 በደብረ ታቦር /፬/ ለሙሴ
እነዚህን ለማጥናት Join አድርጉ
join join join
Join join join
😍6❤3😘3🥰1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 17, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤4😘4😍3🥰1
#ነሐሴ_11 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን #አባ_ሞይስስ አረፈ፣ #የቅዱስ_ፋሲለደስ_ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ሞቱ፣ #ቅዱስ_አብጥልማዎስ በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞…
Aug 16, 2026#ነሐሴ_11 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን #አባ_ሞይስስ አረፈ፣ #የቅዱስ_ፋሲለደስ_ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ሞቱ፣ #ቅዱስ_አብጥልማዎስ በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ኤጲስቆጶስ_አባ_ሞይስስ ነሐሴ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን የአውሲም አገር ኤጲስቆጶስ አባ ሞይስስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም…
🥰11❤3😍3😘3
#ነሐሴ_11
Aug 16, 2026#ነሐሴ_11
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን #አባ_ሞይስስ አረፈ፣ #የቅዱስ_ፋሲለደስ_ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ሞቱ፣ #ቅዱስ_አብጥልማዎስ በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ኤጲስቆጶስ_አባ_ሞይስስ
ነሐሴ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን የአውሲም አገር ኤጲስቆጶስ አባ ሞይስስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም ነበረ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ ተምሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባ። በአንድ ጻድቅ ሰው ዘንድም መነኰሰ በዚያም እያገለገለ በጠባብዋ መንገድም ተጠምዶ ያለመብልና መጠጥ ያለእንቅልፍም እየተጋደለ ዐሥራ ስምንት ዓመት ኖረ።
ከብዙ ፍቅርና ትሕትና ጋር ዘወትር በጾምና በጸሎት ይተጋ ነበር። ትሩፋቱም በበዛ ጊዜ ከአባ ገሞስ በኋላ በአውሲም ከተማ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። ይህም አባ ሞይስስ በተሾመ ጊዜ ትሩፋት መሥራትን አብዝቶ ጨመረ ስለ እነርሱም በጸሎት እየተጋ መንጋዎቹን ነጣቂዎች ከሆኑ ከዲያብሎስ ተኲላዎች ጠበቀ።
በሕይወቱም ዘመን ሁሉ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ የሚሰበስብ አልነበረም። አባ ሚካኤልም በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜና ደሙ ሳይፈስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ ይህ አባ ሞይስስ በእሥር ቤት ከእርሱ ጋር ነበር ብዙ ስለገረፉት እግሮቹንም ለረጅም ጊዜ በእግር ብረት አሥረው ስለ አሠቃዩት ብዙ መከራ ደረሰበት።
በዚህ አባት ሞይስስ እጅም እግዚአብሔር ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ የሚያውቁትም በተአምራቶቹ ደግነቱንና ትሩፋቱን ተረዱ። ዳግመኛም ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ከመሆኑም በፊት ብዙ ነገርን ተናገረ እንደተናገረውም ይሆን ነበር። የምስር ኤጲስቆጶስ ስለሆነው ስለ አባ ቴዎድሮስ ከሔደበት እንደማይመለስ ትንቢት ተናግሮበት እንዲሁ ተፈጸመበት።
ዳግመኛም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ነበር። ብዙዎች ሕሙማንንም ፈወሳቸው። ገድሉንም በመልካም ሽምግልና ፈጸመ። እግዘአብሔርንም አገልግሎ ጥቂት ታመመ የሚያርፍበትንም ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና ባረካቸው በቀናች ሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አረፈ። አለቀሱ ለትም ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ በዝማሬና በማኀሌት በታላቅ ክብር ገንዘው ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም የሚሆን ፈውስ ተገለጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ፋሲለደስ_ማኅበርተኞች
በህች ቀን በአንጾኪያ ከተማ የሠራዊት አለቃ ከነበረው ከቅዱስ ፋሲለደስ ጋራ ሦስት መቶ ሰዎች በማዕትነት ሞቱ።
ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በሚገዛበት አገር ሁሉ ክርስቶስን ያልካዱትን ምእመናን ማስገደልና ማሳደድ ጀመረ፡፡ ብዙ ሰማዕታትም ወደ ንጉሡ የሰማዕትነት አዳባባይ እየመጡ በጌታችን ስም ደማቸውን አፈሰሱ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደጌታችን ይጸልይ ጀመር፡፡ በመኝታም ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታዞ ወደ እርሱ መጥቶ ሰላምታ ሰጠውና ‹‹በምድር አለቃ ሆነህ ሆነህ ሁሉን እንደምታዝ በሰማይም የክርስቶስ ወታደሮቹ የሆኑ የሰማዕታት አለቃ ሆነሃልና ደስ ይበልህ›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹ወደ ጌታህ ዘንድ አደርስህ ዘንድ ተነሥ›› አለውና በክንፎቹ ተሸክሞ ወደ ሰማይ አሳረገውና በጌታችን ፊት አቆመው፡፡ ጌታችንም ለቅዱስ ፋሲለደስ ሰላምታ ከሰጠው በኋላ ስለ ስሙ ይቀበል ዘንድ ስላለው መከራና በሰማይም ስለሚያገኘው ክብር ነገረው፡፡ ሰማዕታት ይሆኑ ያላቸውንም ሁሉን ስማቸውን እየጠራ ነገረው፡፡ አባድርና እኅቱ ኢራኒ፣ የህርማኖስ ልጅ ፊቅጦር፣ ምሥራዊ ቴዎድሮስ፣ ገላውዴዮስ፣ አራቱም ልጆቹ አውሳብዮስና መቃርስ እንዲሁም ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ፣ የንጉሡ ልጅ ዮስጦስና አቦሊ ሚስቱም ታውክልያ… እነዚህንና ሌሎቹንም ሁሉ ስማቸውን እየጠራ ጌታችን ሰማዕት እንደሚሆኑ ለቅዱስ ፋሲለደስ ነገረው፡፡ እርሱ ግን ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ሰማዕት እንደሚሆን ነገረው፡፡ በሌሎቹ ሰማዕታትም ሆነ በእርሱ ላይ የሚደረስበትን መከራ እና በኋላም የሚያገኙትን ክብር ሁሉ በዝርዝር ነገረው፡፡ ብዙ ቃልኪዳንም ገባለት፡፡ የሰማዕታትንና የቅዱሳንን መኖሪያ ካሳየው በኋላ ሰማዕትነቱን ሲፈጽም የሚያገኘውን ክብር መሆኑን ነግሮት በገነት ውኃ በምለአኩ እጅ እንዲጠመቅ ካደረገው በኋላ ወደ ምድር መለሰው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ብዙዎቹን ታላላቅ ሰማዕታት እጅግ አሠቃይቶ ሁሉንም በየተራ ገደላቸው፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት አፍሪካ ላኩት፡፡ በዚያም ብዙ እጅግ አሠቃቂ ሥቃዮችን አደረሱበት፡፡ ከእርሱ ጋር ያመኑ ከ7 ሺህ በላይ ክርስቲያኖችን ሰየፏቸው፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስንም ሰውነቱን በመንኰራኩር ፈጭተው በመጋዝ ሰነጣጥቀው ገደሉት፡፡ ነገር ግን ጌታችን ከሞት አስነሣው፡፡ እጅግ ብዙ አሕዛብም በአምላከ ፋሲለደስ አመኑ፡፡ ጣዖቶቻቸውንም ረገሙባቸው፡፡ በዚህም ወቅት 14ሺህ 737 ሰዎችን አንገታቸውን በሰይፍ ቆረጧቸው፡፡ ሰማዕትነታቸውንም ፈጸሙ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስን ዳግመኛ በምጣድ ላይ አስተኝተው እሳት አነደደዱበት፡፡ በተራራ ላይ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በዚያ ቀበሩት፡፡ አሁንም ጌታችን ከሞት አስነሥቶት በመኰንኑ ፊት እንዲቆም አደረገው፡፡ ንጉሡንም ‹‹አምላኬ ፍጹም ጤነኛ አድርጎ አስነሥቶኛልና እፈር፣ የረከሱ ጣዖቶችህም ይፈሩ›› አለው፡፡ ሕዝቡም ይህን ተአምር ባዩ ጊዜ በጌታችን አምነው አንገታቸውን ተሰይፈው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ ቁጥራቸውም 2300 ነበሩ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስንም ደግመኛ ሰውነቱን በመንኰራኩር ከፈጩት በኋላ በብረት ምጣድ ላይ አስተኝተው ከሥሩ እሳት አነደዱበት፡፡ ጌታችንም ከቁስሉ ፈውሶት ትልቅ ቃልኪዳን ሰጠውና ሰማዕትነቱን በትዕግስት እንዲፈጽም ነገረው፡፡ ንጉሡም አማካሪዎቹን ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያማክራቸው ‹‹ፋሲለደስን ምንም ብናሠቃየው ሊሞት አልቻለም በእርሱም ምክንያት የሀገሩ ሰዎች ሁሉ አልቀዋልና ራሱን ቆርጠን ብንጥለው ይሻላል›› አሉት፡፡ መኰንኑም ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘና ቅዱስ ፋሲለደስ መስከረም 11 ቀን ሰማዕትነቱን ፈጸመ፡፡ የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበርተኞች ቁጥራቸው 2 ሺህ ሰባት ሰዎች መስከረም 7 ቀን ዐረፉ፡፡ እንዲሁም መስከረም 9 ቀን ቁጥራቸው 14 ሺህ 737 ማኅበርተኞቹ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አብጥልማዎስ_ሰማዕት
በዚችም ቀን ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ቅዱስ አብጥልማዎስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህንንም ቅዱስ ክርስቲያን እንደሆነ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት።
መኰንኑም በአስቀረበው ጊዜ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃይቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
† ነሐሴ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ሞይስስ
2.ቅዱስ አብጥልማዎስ
3.ሦስት መቶ ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበር)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
🥰9😍5😘4❤2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 15, 2026መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን አላቸው እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን አሉት። መኰንኑም ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ አላቸው።
Aug 15, 2026መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን አላቸው እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን አሉት። መኰንኑም ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ አላቸው።
ቅዱሳኑም እንዲህ ብለው መለሱለት እኛስ ለረከሱና ለተናቁ አማልክት አንሠዋም ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከጌታችን ኢየሱስ በቀር። መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ምስክርነታቸውንም እስከፈጸሙ ድረስ አሠቃያቸው።
ቅዱስ ቢካቦስን ግን ከአሠቃየው በኋላ አሠረውና ከመንኰራኲር ውስጥ ጨመረው ዘቅዝቆም ሰቀለው ሕዋሳቱንም ቆራረጠው ጌታችንም ያስታግሠውና ያበረታው ነበር ያለ ጉዳትም ጤናማ አድርጎ አስነሳው።
ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ከብዙዎች ሰማዕታት ጋራ ላከው በመርከብም ውስጥ እህልና ውኃ ሳይቀምሱ ሃያ ስድስት ቀኖች ኖሩ። በርሙን ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይተው በምሳር ቆረጡት የምስክርነቱንም ተጋድሎ ፈጸመ መንግሥተ ሰማያትም አክሊልን ተቀበለ።
ከሀገረ በርሙን ሹማምንቶችም አንድ ባለ ጸጋ ሰው መጥቶ የቅዱስ ቢካቦስን ሥጋ ወስዶ በአማሩ ልብሶች ገነዘው ወደ አገሩ እስሙናይንም ላከው። በመከራውም ወራት ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ ከእርሱም ጋራ የተገደሉ ዘጠና አምስት ሰዎች ናቸው።
ከዚህም በኋላ ለቅዱሱ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ።
† ነሐሴ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዓቢየ እግዚእ ኢትዮጵያዊ (ተአምራትን ያደረጉበት)
2.ቅዱስ መጥራ ሰማዕት
3.ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ሰማዕት
4.ሰላሳ ሺ ሰማዕታት (የሐርስጥፎሮስ ማኅበር)
5.ቅዱሳን ቢካቦስና ዮሐንስ (ሰማዕታት)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
7.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
🥰8😍6❤3😘3🕊2
#ነሐሴ_10
Aug 15, 2026#ነሐሴ_10
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥር በዚህች ቀን የታላቁ ጻድቅና ገዳማዊ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ ዓመታዊ የተአምር በዓል ነው፣ #ቅዱስ_መጥራ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የከበሩ #ቅዱሳን_ቢካቦስና_ዮሐንስ በሰማዕትነት ሞቱ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ዓቢየ_እግዚእ_ኢትዮዽያዊ
ነሐሴ ዐሥር በዚህች ቀን የታላቁ ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ ዓመታዊ የተአምር በዓል ነው። አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው። የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ። አጥምቀው "ዓቢየ እግዚእ" ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ጳጳስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው። ትርጉሙም 'በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው' ማለት ነው።
ዓቢየ እግዚእ በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ። ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ (ደብረ በንኮል) ሔደው መንኩሰዋል።
በገዳሙ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል። በጊዜው በአርባ ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር።
ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል። ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ። ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው።
አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ዐሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።
ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ዐሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል።
ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ። ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች። ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር።
በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት። ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ። በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም። በሰማይም እሳትን አያዩም። ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም።" ብሏቸው አርጓል።
አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው ሦስት ሙታንን አስነስተው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው በመቶ አርባ ዓመታቸው ግንቦት ዐሥራ ዘጠኝ ቀን አርፈዋል። የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እናስባቸው።
ይህች ዕለት ባሕረ ተከዜን ከፍለው ሕዝቡን ያሻገሩባት አሕዛብንም ያጠመቁባት ናትና በገዳማቸው ጐንደር ውስጥ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያናቸውም ይከበራል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መጥራ
በዚህች ቀን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ ዲሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መንግሥት ቅዱስ መጥራ በሰማዕትነት ሞተ።
ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው።
የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኃ ኋቸው አለው።
መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው።
ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት።
በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ
በዚህችም ቀን ዳግመኛ በከሀዲ መክስምያኖስ እጅ ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ በሰማዕትነት ሞተ። በንጉሥ መክስምያኖስ ፊት በአቆሙት ጊዜ ለአማልክት ሠዋ አለው። የከበረ ሐርስጥፎሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ። ንጉሡም ተቆጥቶ ሥጋው ተቆራርጦ በምድር ላይ እስቲወድቅ በበትር ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።
ከዚህም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት ጣሉት በላህያቸውም እንዲአስቱት ሁለት ሴቶችን ንጉሡ ወደርሱ ላከ ቅዱሱ ግን የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራቸው የዛሬ የሆነ የዚህንም ዓለም ኃላፊነት አስገነዘባቸው ወደ መክስምያኖስም በተመለሱ ጊዜ እንዴት አደረጋችሁ አላቸው።
እነርሱም እንዲህ አሉት በከበረ ሐርስጥፎሮስ አምላክ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ እኛ እናምናለን ንጉሡም ሰምቶ አንዲቱን በዕንጨት ላይ ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ሁለተኛዋን በአንገቷ ደንጊያ አንጠልጥለው ቊልቊል እንዲሰቅሏት አዘዘና ምስክርነታቸውን እንዲህ ፈጸሙ።
ከዚህም በኋላ ዕንጨቶችን ሰብስበው በማንደጃው ውስጥ አድርገው አነደዱ የከበረ ሐርስጥፎሮስን እጅና እግሩ እንደ ታሠረ ከውስጡ ጨመሩት ያን ጊዜም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አለ እሳቱ ከቶ ምንም አልነካውም። ሕዝቡም ይህን አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ዐሥር ሺህ ያህል ሰዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
ሁለተኛም የብረት ሠሌዳዎችን በእሳት አግለው አመጡ ቅዱሱንም በላያቸው በአስተኙት ጊዜ ምንም ምን የነካው የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰዎችና አርባ ሕፃናት አምነው ምስክር ሁነው ሞቱ።
ንጉሥ መክስምያኖስም አይቶ እጅግ ተቆጣ የቅዱስ ሐርስጥፎሮስንም ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።ከንጉሡም ዘንድ በወጣ ጊዜ ጸሎትን አደረገ ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ ከዚህም በኋላ ምስክርነቱን ፈጸመ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ቢካቦስና_ዮሐንስ
በዚህችም ቀን እስሙናይን ከሚባል አገር የከበሩ ቢካቦስና ዮሐንስ ሌሎችም ከእሳቸው ጋራ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም ቅዱስ ቢካቦስ ክርስቲያን ሲሆን በሥውር ወታደር ሆነ። አንጥያኮስ ለሚባል መኰንንም ስለ ዮሐንስና ስለ ኤጲስቆጶስ አባ አክሎግ ከተርሴስ አገር ስለ ናሕር ስለ አባ ፊልጶስም እነርሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው።
❤8😘3🥰2🕊2😍1
#ነሐሴ_9
Aug 14, 2026#ነሐሴ_9
#አባ_ኦሪ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዘጠኝ በዚች ቀን ስጥኑፍ ከሚባል አገር የከበረ ቄስ አባ ኦሪ ምስክር ሁኖ ሞተ። ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት።
ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ለአማልክት ዕጣን አቅርብ አለው እርሱም ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም ብሎ እምቢ አለው።
መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ።
ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ።
† ነሐሴ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ (ሰማዕት)
2.አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት
† ወርኀዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ)
3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
🥰8😍4❤3😘3🕊2
ቡሄ ፣ ጅራፍ ፣ ችቦ ፣ ሙልሙል ዳ❗️ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው ⁉️
Aug 13, 2026ቡሄ ፣ ጅራፍ ፣ ችቦ ፣ ሙልሙል ዳ❗️ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው ⁉️
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
❤7🥰6😘1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 13, 2026#ነሐሴ_8
Aug 13, 2026#ነሐሴ_8
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ስምንት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን ከሚስቱ እና ልጆቹ ጋር በሰማዕትነት ሞቱ፣ ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ #ጻድቅ_አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡
#ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን
ነሐሴ ስምንት በዚች ቀን አልዓዛርና ሚስቱ ሰሎሜ አንኤም አንጦኒኃስ ዖዝያ አልዓዛር አስዮና ስሙና መርካሎስ የሚባሉ ልጆቻቸውም ሰባቱ በሰማዕትነት ሞቱ።
ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት።
የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው።
ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኮል እንዲገባ አደረጉት።
በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ።
#አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና
ዳግመኛም በዚህች ቀን ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ኂሩተ አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡
የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ ‹‹ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ›› ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ ‹‹ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት/ገንፎ›› ብለው በመናገር ማላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን ‹‹ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል›› ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ ‹‹የጌታችንን መስቀል ያስመጡ›› ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
† ነሐሴ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (ሰማዕት)
2.ቅድስት ሰሎሜ ሰማዕት (ሚስቱ)
3."7ቱ" ቅዱሳን ሰማዕታት (ልጆቹ)
4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4🥰3😍2😘2💯1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 13, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤4🥰4😍2😘2
✝እንኳን አደረሳችሁ!
Aug 13, 2026✝እንኳን አደረሳችሁ!
•ማር #ዘርዓ_ያዕቆብ
•ማር #ናዖድ
•ማር #ልብነ_ድንግል
•ማር #ገላውዴዎስ
✞ዘኃረይኪዮ ለናዖድ ገብርኪ፤
ባርክኒ እግዝእትየ በእዴኪ!
❤4😘4🥰2😍2💯2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 13, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
የቡሄ |ደብረ ታቦር መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
Aug 13, 2026የቡሄ |ደብረ ታቦር መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
🎶 ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
🎶 ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ
🎶 አምላካችን ናና በዓምደ ደመና
🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
🎶 ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው
🎶 ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ.....
🎶 እንደ ጸሐይ ፊቱ ሲያበራ
🎶 የታቦር ተራራ ምንኛ ታደለች
🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
🎶 እንዲህ አለው ጴጥሮስ
🎶 በክብር ተገለጠ በታቦር
🎶 በደብረ ታቦር /፬/ ለሙሴ
እነዚህን ለማጥናት Join አድርጉ
join join join
Join join join
✨ሊቀ_ሐዋርያት
Aug 12, 2026✨ሊቀ_ሐዋርያት
✨በዓለ_መርኆ (የቁልፉ ባለቤት)
✨አርሳይሮስ (ሊቀ ዻዻሳት)
✨ኮኩሐ_ሃይማኖት (ዓለት)
✨መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን
✨ተልሚድ (ደቀ መዝሙር - ፈጥኖ ንስሃ የገባ)
✨ወተአማኒ_በማዕከለ_አርድዕት . . .
✨ቅዱስ_ዼጥሮስ ሊቅ_ሐዋርያ ✝
✝✝ ጌታ ከቅዱሱ በረከትን ይክፈለን . . . አሜን
🌿 እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።
🥰10❤5😘3😍2
#ነሐሴ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሰባት በዚች አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን ፅንስቷ ነው፣ የሐዋርያት አለቃ የከበረ #ሐዋርያው_ጴጥሮስ በዓል ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳ…
Aug 12, 2026#ነሐሴ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሰባት በዚች አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን ፅንስቷ ነው፣ የሐዋርያት አለቃ የከበረ #ሐዋርያው_ጴጥሮስ በዓል ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ጢሞቴዎስ አረፈ፣ የራኄል ልጅ #ቅዱስ_ዮሴፍ ተወለደ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #በዓለ_ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር…
😘10❤5🥰3😍3💯2
የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እ…
Aug 12, 2026የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ የግብፅ ሰዎችም 70 ቀን አለቀሱለት፡፡ ዮሴፍም አባቱን ባዘዘው ቦታ በእነ አብርሃም መቃብር ከቀበረው በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ፡፡
የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ‹‹ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፣ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል›› ብለው ፈርተው ወደ ዮሴፍ መልዕክት ልከው ‹‹አባትህ ገና ሳይሞት ‹ዮሴፍን እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፣ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፤ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል› ብሎሃል›› ብለው ላኩለት፡፡ ወንድሞቹም መጥው በፊቱም ሰግደው ‹‹እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን፣ በአባቶችህ አምላክ ባሮችህን ኃጢአታችንን ይቅር በለን›› አሉት፡፡ ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ፡፡ እርሱም ‹‹ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ስለሆነ አይዟችሁ አትፍሩ›› እያለ እንዳይፈሩ አጽናናቸው፤ደስም አሰኛቸው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ተቀምጦ 110 ዓመት ኖረ፡፡
የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ካየ በኋላ ወንድሞቹን ጠርቶ ‹‹እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፣ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ብሎ አማላቸው፡፡ ዮሴፍም በ110 ዕድሜው በሰላም ዐረፈ፡፡ በሽቱ አሽተው በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ዮሴፍም ‹‹እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ማለቱ አንድም ከግብፅ ምድር እንደሚወጡና የአባቶቻቸውን ርስት ከነዓንን እንደሚወርሱ ሲነግራቸው ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ግብፅ የመቃብር ከነዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም ግብፅ የገሃነም ከነዓን የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ያዕቆብም እንዲሁ ብሏልና ዮሴፍም እንዲህ ያለ ስለምን ነው ቢሉ አባቶቻችን እንዲህ ማለታቸው መውጣታችንን ቢያውቁ ነው ብለው እንዲነቁ፣ እንዲተጉ፣ አንድም ለማጸየፍ ነው፣ ‹‹አባቶቻችን አጥንታችን እንኳን ከዚህ አይቅር›› ብለዋል ብለው እንውጣ እንዲሉ ነው፡፡
† ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር
4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ)
7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት
† ወርኀዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘8❤3🥰2😍2💯2
አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው፡፡ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፡፡ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአ…
Aug 12, 2026አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው፡፡ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፡፡ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡ ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን ስላገኘ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው፡፡ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው፤ የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ፡፡ ጲጥፋራም ያለውን ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ የጌታችን፣ ወንድሞቹ ደግሞ የአይሁድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ዮሴፍ ምግባቸውን ይዞላቸው ቢሄድ ከበው እንደደበደቡት ሁሉ ጌታችንም ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ…›› እያለ የነፍሳቸውን ምግብ ቢያስተምራቸው አይሁድ ጠልተውት ገድለውታል፡፡ ዮሴፍ እንዲሸጥ ሀሳብ ያመጣው ይሁዳም ጌታችንን የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በግብፅ ሕያው በከነዓን ግን ምውት እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በትስብእቱ ግን ምውት ሆኗል፡፡
ወንድሞቹም የዮሴፍን ቀሚስ ወስደው የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነክረው ወደ አባታቸው ሄደው ‹‹ይህንን አገኘን፣ ይህ የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው›› አሉት፡፡ ያቆዕብም ‹‹ይህ የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል›› ካለ በኋላ ልብሱን ቀዶ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ጊዜ አምርሮ ስላለቀሰ ዐይኑ ጠፋ፡፡
ዮሴፍም ጌታውን በቅንነት እያገለገለ ሲኖር የጌታው ሚስት ባሏ በሌለበት ጠብቃ በዮሴፍ ላይ የዝሙት ዐይኗን ጣለችበትና ‹‹ከእኔ ጋር ተኛ›› አለችው፡፡ ዮሴፍም ‹‹እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፣ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል፤ ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?›› አላት፡፡ እርሷ ግን ስለዚህ ነገር በየጊዜው ትጨቀጭቀው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በቤት ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም ስላልነበረ ወደ እርሱ ገብታ ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሽቶ ወደ ውጭ ወጥቶ ሄደ፡፡ የጲጥፋራ ሚስት ግን የቤቷን ሰዎች ጠርታ ‹‹እዩ ዕብራዊው ሰው ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፣ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ›› ብላ በሐሰት ከሰሰችው፡፡ ባሏም ሲመጣ እንዲሁ ብላ ነገረችው፡፡ ባሏም የእርሷን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፡፡ ዮሴፍን ይዞ እስር ቤት ጣለው፡፡ እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው፡፡ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር፡፡
የጲጥፋራ ሚስት የኃጢአት ምሳሌ ስትሆን ዮሴፍ የንጽሕና ምሳሌ ነው፡፡ ኃጢአት ደርሳ ሥሩኝ ሥሩኝ ስትላችሁ የንጽሕናን የቅድስናን ነገር አስባችሁ ፈጥናችሁ ከእርሷ ተለዩ ሲል ነው፡፡ ንጽሕናችሁን በኃጢአት አታቆሽሹ አለ፡፡ አንድም የጲጥፋራ ሚስት የዚህ ዓለም ዮሴፍ የመናንያን ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍን የጲጥፋራ ሚስት ሽንገላ ሳያታልለው ጥሏት እንደሸሸ ሁሉ መናንያንም የዚህ ዓለም ሀብት፣ ንብረት፣ ቤት፣ ልጅ፣ ባል፣ ሚስት… ሳያታልላቸው የዓለምን ጣዕም ሸሽተው ገዳም ይገባሉና ነው፡፡
ዮሴፍ ከታሰረ ከሁለት ዓመት በኋላ ንጉሡ ፈርዖን ሕልም አየ፡፡ በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታውካ የግብፅን ሕልም ተርጓሚዎችና ጠቢባንን ሁሉ ሰብስቦ እንዲተረጉሙለት ሕልሙን በዝርዝር ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ሊተረጉሙለት አልቻሉም ነበር፡፡ የንጉሡም የጠጅ አሳላፊ አስቀድም ከዮሴፍ ጋር ታስሮ ሳለ እርሱ ያየውን ሕልም ዮሴፍ ተርጉሞለት እንደነገረው ሆኖለት ስለነበር በዚህ ጊዜ የጠጅ አሳላፈው ለንጉሡ ስለ የሴፍ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን አስመጥቶ ሕልሙን ነግሮት ተረጎመለት፡፡ በፈርዖንም ሕልም መሠረት ሰባት ዓመታት ጥጋብ እንደሚሆንና ከዚያም በኋላ ሰባት የርኃብ ዓመታት እንደሚመጡ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን ‹‹እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ›› ብሎ በቤቱና በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው፡፡ ቀለበቱንም አውጥቶ አሰረለት፡፡ ይህም የሆነው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ዮሴፍ በእናት በባቱ ቤት 17 ዓመት፣ በጲጥፋራ ቤት 10 ዓመት፣ በእስር ቤት ሁለት ዓመት ተቀምጦ ባጠቃላይ ልክ 30 ዓመት ሲሆነው በፈርዖን ፊት ለሹመት ቆመ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በ30 ዘመኑ ለሹመት በፈርዖን ፊት እንደቆመ ሁሉ ጌታችን መድኃኔዓም ክርስቶስም በጲላጦስ ፊት ለፍርድ የቆመው በ30 ዘመኑ ነው፡፡
ዮሴፍም በግብፅ ምድር ዞሮ የሰባቱን ዓመት እጅግ ብዙ እህል ሰበሰበ፡፡ ሰባቱም የጥጋብ ዘመን ሲያልፍ ሰባቱ የርኃብ ዘመን በጀመረ ጊዜ በሀገሩ ሁሉ ታላቅ ርኃብ ሆነ ነገር ግን በግብፅ ምድር ብቻ እህል ነበር፡፡ ንጉሡም ከየሀገሩ ሁሉ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ዮሴፍ እየላካቸው ዮሴፍም እህል ከጎተራ እያወጣ ይሸጥላቸው ነበር፡፡ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ ልጆቹን እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው፡፡ ነገር ግን ክፉ እንዳያገኘው ብሎ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ከእነርሱ ጋር አላከውም ነበር፡፡ ዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ ከሕዝቡ ጋር ገብተው ሲሰግዱለት አይቶ ዐወቃቸው፣ እነርሱ ግን የሰገዱለት የሀገሩ ገዥ ስለነበረ ነው እንጂ ወንድማቸው እንደሆነ ዐላወቁትም ነበር፡፡ ዮሴፍም በልጅነቱ ከእነርሱ ጋር ሳለ ያየውን ሕልም አሰበ፡፡ እነርሱም ስለራሳቸው በነገሩት ጊዜ ‹‹እቤት የቀረውን ወንድማችሁን አምጡ›› ብሎ ለርኃባቸው እህሉን ሰጥቶ አንዱን (ስምዖንን) ለይቶ አስቀርቶ ዘጠኙን ስንቃቸውን ጭኑ ወደ አባታቸው ቤት ወደ ከነዓን ላካቸው፡፡ ሄደውም የሆነውን ለያዕቆብ ነገሩት፡፡
እርሱም ከወንድማቸው ጋር ድጋሚ ወደ ግብፅ ላካቸውና ድጋሚ በዮሴፍ ፊት ሰግደው ሰላምታ አቅርበው እጅ መንሻን አመጡለት፡፡ ዮሴፍም የእናቱን ልጅ ብንያምን ባየው ጊዜ ወደ ውስጥ ገብቶ አለቀሰ፡፡ ዮሴፍ ቆይቶ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ ያደረጉበትንም ነገራቸው፡፡ የርኃቡም ዘመን ገና 5 ዓመት ይቀረው ነበርና ዮሴፍ ወንድሞቹን ‹‹ስለሸጣችሁኝ አትዘኑ እነሆ ሕይወታችሁን ለማዳን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእናንተ በፊት ወደ ግብፅ ልኮኛል›› አላቸው፡፡ አባቱንም ወደ እርሱ እንዲያመጡት ላካቸው፡፡ ያዕቆብም ከነቤተሰቡ ንብረቱንም ሁሉ ሰብስቦ ወደ ግብፅ ወረደ፡፡ ልጁን ዮሴፍንም ባየው ጊዜ እያለቀሰ አቅፎ ከሳመው በኋላ ሞቱን ተመኘ፡፡
በግብፅ የያዕቆብ የልጅ ልጆቹ ቁጥር 66 ሆነ፡፡ ከዮሴፍም ልጆች ጋር አንድ ላይ 70 ሆኑ፡፡ ያዕቆብም ፈርዖንን ገብቶ ከባረከው በኋላ በግብፅ ጌሤም ምድር 17 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ዘመኑም 140 በሆነ ጊዜ በሞት ማረፉን ዐውቆ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ በአባቶቹ መቃብር ቤት ውስዶ እንዲቀብረው ነገረው፡፡ የዮሴፍንም ሁለቱን ልጆች ምናሴንና ኤፍሬምን ባረካቸው፡፡ ‹‹አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፣ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ›› ብሎ ባረካቸው፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ ወደፊት
❤10😘4😍3🥰2💯2
#ነሐሴ_7
Aug 12, 2026#ነሐሴ_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሰባት በዚች አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን ፅንስቷ ነው፣ የሐዋርያት አለቃ የከበረ #ሐዋርያው_ጴጥሮስ በዓል ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ጢሞቴዎስ አረፈ፣ የራኄል ልጅ #ቅዱስ_ዮሴፍ ተወለደ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#በዓለ_ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ማርያም
ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።
ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ።
የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች።
በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሐዋርያ
በዚህችም ቀን የሐዋርያት አለቃ የከበረ ሐዋርያ ጴጥሮስ በዓል ነው። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና።
በከበረ ወንጌል እንደተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኲላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን።
ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ስለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጭ አወጣቸው። ከእርሳቸውም ኤልያስ እንደሆነ የሚአስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ። ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ አላቸው።
ስለዚህም የጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጭ አወጣቸው። እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት። ጴጥሮስ ግን አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በእውነት ምስክርን ሆነ።
ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ። ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስቆጶሳት የቀሳውስትና የዲያቆናት ሹመት ተሰጠ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ጢሞቴዎስ_ሊቀ_ዻዻሳት
በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ስድስተኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጢሞቴዎስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መርጦት ተጋዳይ የነበረ አባ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ ከአረፈ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ።
ይህም አባት ጢሞቴዎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል። ንጉሥ መርቅያን ለእስክንድርያ አገር ሌላ መናፍቅ ሊቀ ጳጳሳት ሹሞ አባት ጢሞቴዎስን አስቀድሞ አባ ዲዮስቆሮስ ተሰዶባት ወደ ነበረች ደሴተ ጋግራ አጋዘው። መርቅያንም ከሞተ በኋላ የእስክንድርያ ሰዎች ተነሥተው መርቅያን የሾመውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት አባት ዲዮስቆሮስ እንዳዘዘ አባ ጢሞቴዎስን መልሰው ሾሙት።
ከዚህም በኋላ የመርቅያን ልጅ ልዮን ነገሠ ያን ጊዜ አባ ጢሞቴዎስን ሁለተኛ ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ዐሥር ዓመት ኖረ ልዮን እስከ ሞተ ድረስ ከእርሱም ኋላ ዘይኑን ነገሠ። ያን ጊዜም አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበረ ሢመቱ በታላቅ ክብር መለሰው ሕዝቡንም እያስተማራቸውና እየመከራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ኖረ።
በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ
በዚህችም ቀን የራኄል ልጅ ዮሴፍ ተወለደ። አባቱ ያዕቆብ እናቱ ራኄል ይባላሉ፡፡ ለአባቱ 11ኛ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ያዕቆብ የወንድሙን የኤሳውን በረከት ከአባቱ ከወሰደ በኋላ ከኤሳው ሸሽቶ ወደ አጎቱ ላባ ዘንድ ተሰዶ 14 ዓመት ለላባ ተገዝቶ ራሄልንና ርብቃን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወለደ፡፡ ሀብት ንብረትም ካፈራ ከ21 ዓመት በኋላ ወደ አባቱ አገር ተመልሶ ከወንድሙ ጋር ታረቀ፡፡ ያዕቆብም በምድረ በዳ አቅራቢያ ባለች አብርሃም ይቀመጥባት ከነበረ አገር ከአባቱ ከይስሐቅ ዘንድ ደረሰ፡፡ ይህችውም በከነዓን ያለችው ኬብሮን ናት፡፡ አባቱ ይስሐቅ አብርሃም ይቀመጥባት በነበረችው የወይራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘው፡፡ ከዚህም በኋላ ይስሐቅ አርጅቶ ዘመኑን ጨርሶ ሞተ፡፡ ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ ይኖርባት በነበረች አገር ኖረ፡፡ ያንጊዜም ልጁ ዮሴፍ 17 ዓመት ሆኖት ነበር፡፡ እርሱም ከአባቱ ከያዕቆብ ሚስቶች ከዘለፋ ልጆችና ከባላ ልጆች ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ያዕቆብም በእርጅናው ዘመን ወልዶታልና አብልጦ ይወደው ነበር፡፡
ወንድሞቹም በዚህ ምክንያት ጠሉት፡፡ ዮሴፍም ሕልም አልሞ ሕልሙን ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ዮሴፍም ያየው ሕልም 11ዱ ወንድሞቹና አባቱም ጭምር ለዮሴፍ እንደሚገዙለትና እንደሚሰግዱለት የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህንንም ሕልሙን ሲሰሙ ወንድሞቹ ይበልጥ ጠሉት፡፡
የዮሴፍም ወንድሞች የአባታቸውን በጎች ይዘው ወደ ሴኬም ጎዳና ሄዱ፡፡ አባቱም ዮሴፍን ‹‹ወንድሞችህን አይተሃቸው ና›› ብሎ ስንቃቸውን ቋጥሮ ወደ ቆላው ላከው፡፡ ሴኬምም እንደደረሰ አንድ ሰው ወንድሞቹ ያሉበትን አሳይቶት ወደ ዶታይን ወረደ፤ በዶታይንም አገኛቸው፡፡ እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩትና ወደ እነርሱ ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡ ‹‹እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፡፡ ክፉ አውሬም በላው እንላለን›› ብለው ሲመካከሩ ከእነርሱ ውስጥ ሮቤል ይህን ሲሰማ ‹‹ሕይወቱን አናጥፋ፣ ደም አታፍስሱ፤ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፣ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት›› አላቸው፡፡ ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው፡፡ ዮሴፍንም ቀሚሱን ገፈው ወስደው ወደ ቀበሮ ጕድጓድ ጣሉት፡፡ ጉድጓዱንም በድንጋይ ገጥመው በላይ ተቀምጠው ዮሴፍ ያመጣላቸውን እንጀራ እየተመገቡ ሳለ የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ ሲመጡ አይተው በይሁዳ ምክር ወንድማቸውን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሀያ ብር ሸጡት፤ እስማኤላውያንም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት፡፡ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም
😍8🥰4❤3🏆3
🎼 መዝሙሮችን እንደየ ጊዜያቸው ከግጥምና ዜማቸው ጋር እና የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርት ነክ ነገር ያገኙበታል 👇
Aug 12, 2026🎼 መዝሙሮችን እንደየ ጊዜያቸው ከግጥምና ዜማቸው ጋር እና የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርት ነክ ነገር ያገኙበታል 👇
🎧በዕለቱ ታስበው የሚሉ በዓላት
🎧የጾመ ፍልሠታ መዝሙሮችን
🎧በቅርብ ቀን 👇👇👇👇
🎧የደብረ ታቦር መዝሙሮችን
🎧የአዲስ ዓመት መዝሙሮችን
🎧የመስቀል በዓል መዝሙሮችን
🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎
😍6😘3🥰2❤1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 12, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 12, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
😍5❤3🥰2😘2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 12, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
Aug 11, 2026⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
🔐ከስር ክፈት የሚለውን
በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
................💚💛❤️...............
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
...............💚💛❤️................
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
🥰5😍2😘2❤1
✝ኢየሉጣ ሰማዕት እግዚአብሔር ዘሐወጻ፤
Aug 11, 2026✝ኢየሉጣ ሰማዕት እግዚአብሔር ዘሐወጻ፤
ወረድአ ሲኖዳ ዐቢይ ዘስሙ ዊጻ፤
ኢዮስያስ ለወንጌል ዘአፍቀረ ተግሣጻ፤
ማርያም መግደላዊት ለጎልጎታ በአንቀጻ፤
ወማርያም እግዝእት ዘእደ አምላክ ሐነጻ!
✝እንኳን አደረሰን !
😍11❤3🥰2🕊2😘2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 11, 2026#ነሐሴ_6
Aug 11, 2026#ነሐሴ_6
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች #ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም አረፈች፣ ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር የከበረች #ቅድስት_ኢየሉጣ ምስክር ሁና አረፈተች ፣ታላቁ አባት #አቡነ_ኢዮስያስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው
#ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም
ነሐሴ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች መግደላዊት ማርያም አረፈች። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች።
በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል አላቸው ።
ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው።
ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች።
ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም በፍቅር አረፈች።
#ቅድስት_ኢየሉጣ_ዘቂሳርያ
በዚህች ቀን ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር የከበረች ኢየሉጣ ምስክር ሁና ሞተች። ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብን ወረሰች ከታጋዮችም አንዱ በግፍ በላይዋ ተነሥቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿንም ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት።
ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት። በልቧም እንዲህ አለች የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም።
ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች።
ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል።
#አቡነ_ኢዮስያስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቁ አባት አቡነ ኢዮስያስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው። ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጥር 6 ቀን ሲወለዱ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡ የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በመመነን በመጀመሪያ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ገቡ፡፡ አቡነ ኢዮስያስ በሐይቅ ገዳም ለ14 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኮሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አጠናቀው ተምረዋል፡፡ በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ትግራይ ደብረ በንኮል ገዳም ሄዱ፡፡ በደብረ በንኮልም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ መነኮሱ፡፡ ቆብ የተቀበሉት ግን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡
አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩአቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ወደ አዱዋ አውራጃ ዛሬ በስማቸው ወደተጠራው ገዳም ሄደው በቦታው ላይ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ገዳሙንም ከገደሙት በኋላ በርካታ መነኮሳትን አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ ያፈለቁት ጠበል በፈዋሽነቱ የታወቀ ነው፡፡ በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ነሐሴ 6 ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ በየዓመቱ ነሐሴ 6 ቀን በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡
አቡነ ኢዮስያስን ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን ቢያስቸግሯቸው ጻድቁም በጸሎት ቢያመለክቱ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ የንብ መንጋ መጥቶ አረማውያኑን አንጥፍቶላቸዋል፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡ ጻድቁን እንደ ረድእ ሆኖ የሚያገለግላቸው አንበሳ ነበራቸው፡፡ ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የተሰመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡
=>ነሐሴ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ማርያም መግደላዊት (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት)
2.ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት (ዘቂሣርያ)
3.አባ ዊጻ (የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
😍8❤4🥰3🕊3
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Aug 11, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🥰4😍4❤3😘1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 11, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 11, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
😘6😍3❤2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 11, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😍5❤4🥰3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Aug 11, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍4❤3🥰2😘2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 10, 2026ከጥቂት ወራትም በኋላ እኅቱ ያለችበትን አባ አብርሃም ሰማ ሰዎችም እንዳያውቁት የምንኩስናውን ልብስ ለውጦ ፊቱንም ተከናንቦ የወታደር ልብስ ለብሶ በፈረስ ተቀምጦ ወዳአለችበት አገር ሔደ ከዚያም ደርሶ ማርያ ወዳለችበት ገባ የመሸተኛንም …
Aug 10, 2026ከጥቂት ወራትም በኋላ እኅቱ ያለችበትን አባ አብርሃም ሰማ ሰዎችም እንዳያውቁት የምንኩስናውን ልብስ ለውጦ ፊቱንም ተከናንቦ የወታደር ልብስ ለብሶ በፈረስ ተቀምጦ ወዳአለችበት አገር ሔደ ከዚያም ደርሶ ማርያ ወዳለችበት ገባ የመሸተኛንም ልብስ ለብሳ በአያት ጊዜ እጅግ አዘነ ነገር ግን እንዳትሸሸው እንድታውቀው አልሆነም።
ከዚህም በኋላ ለሚያገለግላት አሽከር ከማርያ ጋር የሚደሰትበት መብልና መጠጥ እንዲያዘጋጅ የወርቅ ዲናር ሰጠው ለርካሽ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ይመስላት ዘንድ።
ከራት በኋላም ወደ ውስጠኛው ቤት አስገባት በሩንም ዘጋ እጇንም ይዞ ራሱን ገለጠላት በአወቀችውም ጊዜ ደንግጣ እንደ በድን ሆነች ልጄ ሆይ አይዞሽ ከእግዚአብሔር በቀር ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ የለም ነገር ግን ወደ ንስሐ ተመለሺ ወደቦታሽም ገብተሽ የቀድሞ ሥርዓትሽን ያዢ አላት እርሷም እሺ አለች።
በነጋም ጊዜም ወስዶ በፈረሱ አስቀመጣትና ደስ እያለው ተመለሰ እኅቱን ከሰይጣን እጅ ማርኳልና ወደቦታውም በደረሰ ጊዜ የቤቷን ደጅ ዘግቶላት ማቅ በመልበስ እየተጸጸተች የተጋድሎንም ሥራ እየተማረች በብርታቷና በተጋድሎዋ ያዩ ሁሉ እስቲአደንቁ ጸንታ ኖረች ።
እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ ሰው እጆች ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ አጋንንትን በማስወጣት በሽተኞችን በማዳን ከአንዲት ዓመትም በኋላ የማርያን ንስሓዋን አይቶ በሰባ ዘመኑ የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ አረፈ።
ማርያ እኅቱም ከለቅሶ ጋር ትርኅምትን በማብዛት ቀንና ሌሊት እየተጋደለች ሌሎች አምስት ዓመታትን ኖረች ከዚያም በኋላ አረፈች ያዩዋትም በፊቷ ውስጥ ሰለአለው ብርሃን እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ
በዚህችም ቀን የከበረ ተጋዳይ ወታደር ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው እርሱም በከሀዲ በዑልያኖስ ሠራዊት ውስጥ ወታደር ሆነ። ንጉሡም ከባልንጀሮቹ ወታደሮች ጋራ ላከው የክርስቲያን ወገኖችንም በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዛቸው።
እርሱም ለባልንጀሮች ጭፍሮች ክርስቲያኖችን እጅግ እንደሚጠላቸውና እንደሚጣላቸው ይገልጽላቸዋል በጭልታም ገብቶ በጎ ነገርን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል ያጽናናቸዋልም። ሁል ጊዜም ይጸልያል ይጾማል ይመጸውታልም የቅዱሳንንም አኗኗር ኖረ ምስጉን እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
=>ነሐሴ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.ቅድስት ማርያ እህቱ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ
4.አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4😍4🕊1😘1
#ነሐሴ_5
Aug 10, 2026#ነሐሴ_5
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ አምስት በዚህች ቀን የደብረ ቢዘን #አባ_ፊልጶስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አባ_አብርሃም ገዳማዊ አረፈ፣ የከበረ ተጋዳይ ወታደር #ቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ፊልጶስ_ዘደብረ_ቢዘን
ነሐሴ አምስት በዚህች ቀን የደብረ ቢዘን አባ ፊልጶስ አረፈ። አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን እንደ ነቢዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ የተመረጡና እንደተወለዱ ነው ሰማንያ አንዱን የብሉይ መጻሕፍትን አጠናቀው ያወቁት ናቸው፡፡ በ12 ዓመታቸውም ለመመንኮስና ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብቺኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘውና ደብረ ጸራቢ ወደሚባለው ገዳም ገቡ፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስም የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ ከባድ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢመክሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነገሯቸው፡፡ ከብዙ ፈተናም በኋላ አመነኮሷቸው፡፡
በገዳሙም እንጨት እየለቀሙና እየፈለጡ፣ ውኃ እየቀዱ፣ የክርስቶስን ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ በጾምና ጸሎት ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ነገራቸውና ሽሬ አደያቦ ወደሚባለው ስፍራ ሄዱ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገሩ ዞረው ሰበኩ፡፡ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእርሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡ 16 ደጋግ መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ፡፡ ይኸውም በኤርትራ ክፍለ ሀገር በሐማሴን አውራጃ ከአሥመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው አስደናቂው ገዳም ነው፡፡
ጻድቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባሕር በተአምራት ያቃጠሉት አባት ናቸው፡፡ በንጉሡ በዐፄ ዳዊት ዘመን ሰንበትን አንድ ብቻ ናት እያሉ በአንደኛዋ ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ጻድቁ አቡነ ፊልጶስ ይህን ሰምተው አንዲት ሰንበት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው፡፡ ከግብፅ የመጡት ጳጳስም ቀደም ብሎ ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሁንም ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ ዐፄ ዳዊት አከራክረዋቸው ጳጳሱም በክርክሩ ተረቱ፡፡ ክፉዎችም በአቡነ ፊሊጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው፡፡ በአቁማዳ ጠቅልለው ሐይቅ ባሕር ውስጥ ጣሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባሕር በእሳት ተቃጥሎ ጽድቃቸውን መስክሮላቸዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባሕር ዳርቻ ላይ የተቃጠለው ድንጋይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ በወቅቱ የንጉሡ ሚስት በዋናተኛ አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አስወጣቻቸው፡፡ እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው፡፡ ወዲያውም ‹‹ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል›› ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው አለመግባባትና ክፉዎችም በባሕር ውስጥ ስለጣሏቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያው ታርቀዋል፡፡ በዘመናቸውም ርኃብ ስለነተሳ ጻድቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማክረዋቸዋል፡፡ አቡነ ፊልጶስም ‹‹የጌታችንን መስቀል ያስመጡ›› ብለው መከሯቸው፡፡
ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም በአቡን ፊልጶስ ምክር መሰረት ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዓሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊልጶስ ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_አብርሃም_ገዳማዊ
በዚህች ቀን ሌላው አብርሃም አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ባለጸጎች ናቸው በተግሣጽና ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት ። በአደገ ጊዜም ያለ ፈቃዱ አጋቡት እግዚአብሔርም ወደሚፈቅደው ይመራው ዘንድ ሲለምን ኖረ።
በሰባተኛውም ቀን በዐልጋው ላይ ሳለ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሳሥቶት ከጫጉላ ቤቱ ወጣ ብርሃን እየመራው ሒዶ ባዶ ቤት አግኝቶ በውስጡ ገብቶ ኖረ ምግቡን ከሚቀበልባት ከጥቂት መስኮት በቀር መዝጊያ ሠርቶ ደጁን ዘጋ።
ዓለምን ከተወ በዓሥረኛው ዓመት አባትና እናቱ ብዙ ጥሪት ትተውለት ሞቱ እርሱ ግን ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ በጾምና በጸሎት ተወስኖ እየተጋደለ ኖረ ከአንድ ዐጽፍና ሰሌን በቀር ምንም ምን ጥሪት አላኖረም እንዲህም ሆኖ ዐሥር ዓመት ተጋደለ።
እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አየ በአንዲት አገርም አረማውያን ነበሩ ከታናሾቻቸው እስከ ታላላቆቻቸው ወደ ሃይማኖት ሊመልሳቸው የሚችል የሌለ። በአንዲት ቀንም አባ አብርሃምን ጳጳሱ አሰበው ብርታቱንና ብልህነቱንም አይቶ ቄስ እንዲሆንና እነዚያን አረማውያን እንዲመልሳቸው አስገደደው በግድ አስጨንቆም ቅስና ሾመው ። ወደዚያም ቦታ ደርሶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ እነዚያን አረማውያን እርሱን ፈጣሪያቸውን ወደ ማወቅ ይመልሳቸው ዘንድ በውስጧ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
በአነዲት ቀንም ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ገባ ያን ጊዜ ጣዖታቱን ከመቀመጫቸው ጣላቸው የአገር ሰዎችም በአዩ ጊዜ ቁጣን ተመልተው አብዝተው ደበደቡትና ከአገር አበረሩት በጥዋትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲጸልይ አገኙት።
ሁለተኛም በገመድ አሥረው ወደ ከተማው ውጭ ጐትተው በላዩም አፈር ቆልለው እንዳይሞት ጥቂት መተንፈሻ ትተው አልፈው ከዚያ ሔዱ። በእግዚአብሔርም ኃያል ተነሥቶ ሔደ ስለ መመለሳቸውም ሲጸልይ አገኙት በእንዲህ ያለ ሥራም እየተጋደለ ዐሥር ዓመት ኖረ።
የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ልባቸውን መለሰ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከታናናሾች እስከ ታላላቆች ድረስ ሁሉንም አጠመቃቸው
የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትም ጸኑ።
ከዚህም በኋላ በሃይማኖታቸው መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ከንቱ ውዳሴ እንዳያመጣበት ፈርቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አገሪቱንም በመስቀል ምልክት አማተበባትና ማንም ሳያውቅ ወጥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ ።
ሰይጣንም በሚያስፈራው በብዙ ሥራ ይፈታተነው ነበር ቅዱሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኃይል አሸነፈው ። ጽኑ በሆነ ተጋድሎም ኖረ ያለ ዕንባም ሰዓት አላለፈችውም በጥርሶቹም አልሳቀም በከንፈሮቹም ፈገግ አላለም ስጋውን ቅባት አልነካውም ስጋውንና ደሙን ከሚቀበልበት ጊዜ በቀር ፊቱንና እግሩን አልታጠበም ።
እናትና አባቱ በስድስት ዓመቷ ትተዋት የሞቱ እኅት ነበረችው ስሟም ማርያ ይባላል ዘመዶቿም ወደ አብርሃም አምጥተዋት ፈሪሀ እግዚአብሔር ሃያ ዓመት ሆናት ድረስ ትሕትናንም እያስተማራት በእርሱ ዘንድ አደገች።
ከዚህም በኋላ ሰይጣን ቀንቶባት ከአንድ መነኩሴ ጋር አፋቀራት ድንግልናዋንም አጠፉች ልብሷንና አስኬማዋን ለውጣ ወደ ሌላ አገር ሔደች።
አባ አብርሃምም በዚያች ሌሊት ታላቅ ከይሲ ርግቢቱን ሲውጣትና ጥቂት ቆይቶ ከእግሩ በታች ሲተፋት ራእይን አየ። በማግሥቱም ማርያ ከቦታዋ ታጣች አባ አብረሃምም ደነገጠ ወደ እግዚአብሔርም ከብዙ ዕንባ ጋር ጸለየ እርሷን ያገናኘው ዘንድ።
😍5🥰3😘3❤2🕊1
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 10, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
🥰8😘3😍2
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 10, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
😘6❤4🥰1😍1
💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
Aug 10, 2026💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
❤6🥰4😍2😘1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 10, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤7🥰3😍3😘2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 09, 2026#ነሐሴ_4
Aug 09, 2026#ነሐሴ_4
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አራት በዚህች ቀን ከዳዊት ዘር የሆነ የአካዝ ልጅ #ቅዱስ_ሕዝቅያስ ንጉሥ አረፈ፣ እንደ በግ የጸጒር ልብስ ለብሶ በበረሃ የሚኖር #አባ_ማቴዎስ አረፈ።
#ቅዱስ_ሕዝቅያስ_ጻድቅ (ንጉሠ ይሁዳ)
ነሐሴ አራት በዚህች ቀን ከዳዊት ዘር የሆነ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ ንጉሥ አረፈ። ከጻድቁ ንጉሥ ከዳዊት በኋላ እንደ ሕዝቅያስ ያለ በእስራኤል ውስጥ አልተሾመም ከዚህ ጻድቅ ንጉሥ በቀር ሁሉም ጣዖትን አምልከዋልና መሠዊያም ሠርተዋልና።
እርሱም በነገሠ ጊዜ ጣዖታትን ሰበረ መሠዊያቸውንም አፈረሰ ከነሐስ የተሠራውንም እባብ ቆራረጠ የእስራኤል ልጆች አምልከውት ነበርና እግዚአብሔርም ዘመነ መንግሥቱን እጅግ አሳመረለት በጎ ነገርንም ሁሉ ሰጠው ።
ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዘመን የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በዘመኑ እንደርሱ ያለ የሌለ ኃይለኛ ብርቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ የፈሩትና የታዘዙለት ነው ። ሕዝቅያስም ከእርሱ ግርማ የተነሣ ፈርቶ አገሩን እንዳያጠፋ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ላከለት ሰናክሬምም ደስ ብሎት ምንም ምን አልተቀበለም በእርሱ ላይና በልዑል እግዚአብሔር ላይ ተቆጥቶ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ አይችልም በማለት የስድብን ቃል ላከ እንጂ ።
ሁለተኛም በልዑል ስም ላይ ስድብና ቍጣ የተጻፈበትን ደብዳቤ ላከ ሕዝቅያስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ ለበሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ ። አቤቱ የእስራኤል አምላክ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ አንተም ብቻህን በዓለም መንግሥታት ላይ ንጉሥ የሆንክ አንተም ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ልመናዬን አድምጥ ። ዐይኖችህን ገልጠህ ተመልከት ሕያው እግዚአብሔር አንተን እያቃለለ ሰናክሬም የላከውን ቃሉን ስማ ።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም የተናገውን እንዲነግሩትና ስለርሱና ስለ ሕዝቡ ይጸልይ ዘንድ ወደ ኢሳይያስ መልእክተኞችን ላከ ። ኢሳይያስም ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ እንዲህ ብሎ መለሰለት ልብህን አጽና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ ሊሠራ እግዚአብሔር አለውና ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ የለኪሶም ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አገኙ የተረፉትም ከንጉሣቸው ጋራ ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ ። ሰናክሬምም ሊጸልይ ወደጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ልጆቹ አድራማሌክና ሶርሶር በሰይፍ መትተው ገደሉት ። ሕዝቅያስምከሰናክሬም እጅ ድኖ የተመሰገነ እግዚአብሔርን አመሰገነ ።
በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ ለሞትም ደረሰ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስም ወደረሱ መጥቶ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ትሞታለህ እንጂ አትድንምና ቤትህን ሥራ አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ እያመሰገነውም እንዲህ አለ አቤቱ በቀና ልቡና በዕውነት ሥራ በፊትህ ጸንቼ እንደኖርኩ ፈቃድህንም እንደፈጸምሁ አስብ ብሎ ሕዝቅያስ ፈጽሞ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰ ።
ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ዐፀድ ደረሰ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው ሒደህ ለወገኖቼ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ያባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በለው ። ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ እስከ ሦስት ቀንም ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ ።
በዘመኖችህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይቺንም አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ። ሕዝቅያስም ኢሳይያስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር እንደሚያድነኝና እስከ ሦስት ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመውጣቴ ምልክቱ ምንድ ነው ።
ኢሳይያስም እንዲህ አለው የተናገረውን ቃል ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምልክቱ ይህ ነው እነሆ ጥላው ወደ ዐሥረኛው እርከን ቢመለስ ምልክቱ ይህ ነው ። ሕዝቅያስም እንዲህ አይደለም የጥላው ወደ ዐሥረኛ እርከን መመለስ ቀላል ነው ። መመለስስ ከሆነ ፀሐይ ወደ ዐሥረኛው እርከን ይመለስ አለ ። ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፀሐይም ዐሥሩን እርከን ተመለሰ ።
ሕዝቅያስንም የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና ። በመንበረ መንግሥቱም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነግሦ ኖረ ። እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ ።
#አባ_ማቴዎስ_ገዳማዊ
በዚችም ቀን እንደ በግ የጸጒር ልብስ ለብሶ በበረሃ የሚኖር አባ ማቴዎስ አረፈ። ይኸውም አባ ማቴዎስ የአቶሩን ንጉሥ በተአምሩ ከነቤተሰቡ ያሳመነው ነው፡፡ በእርሱም ትምህርት በሀገሪቱ ብዙ ሰማዕታት ተገኝተዋል፡፡ ቅድስት ሣራና ወንድሟ መርምህናም አባታቸው የአቶር ንጉሥ ሲሆን እርሱም የተቀረጹ ጣዖታን ያመልክ ነበር፡፡ እናታቸው ግን አማኝ ክርስቲያን ነበረች፡፡ አባቱን ለምኖና አስፈቅዶ ወደ ዱር ሄዶ አራዊትን ለማደን በወጣ ጊዜ እናቱ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር በላዩ በረከትን ያሳድርበት ዘንድ ከጸለየችለት በኋላ ሸኘችው፡፡
መርምህናም ከአርባ ፈረሰኛ አገልጋዮቹ ጋር ወጥቶ ሄደ፡፡ ወደ አንድ ተራራም ወጥቶ በዚያ አደረ፡፡ በሌሊትም የታዘዘ መልአክ ጠራውና ‹‹መርምህናም ሆይ ተነሥተህ ወደዚህ ተራራ ጫፍ ላይ ውጣ፣ ስሙ ማቴዎስ የሚባል ቅዱስ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱም የሕይወትን ነገር ይነግርሃል›› አለው፡፡
ሲነጋም ወደ ተራራው ጫፍ ላይ ወጣና የበግ ጠጉር ለብሶ አባ ማቴዎስን ባገኘው ጊዜ እጅግ ፈራ፡፡ አባ ማቴዎስም ‹‹አይዞህ አትራ እኔም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነኝና አትፍራ›› ብለው አበረቱት፡፡ መርምህናም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠሩ ሲሰማ ‹‹አባቴ ከአማልክቶች በቀር አምላክ አለን?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ አባታችንም የሃይማኖትን ነገር ሁሉንም አስተማሩት፡፡ መርምህናም ‹‹ከራስ ጠጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ በለምጽ የተመታች እኅት አለችኝና እርሷን የአምላክህን ስም ጠርተህ ካዳንክልኝ በእውነት በአምላክህ አምናለሁ›› አላቸው፡፡ ተያይዘውም ከተራራው ወርደው ወደ ንጉሡ ቤት ሄደው መርምህናም ለእናቱ ያጋጠመውን ነገር ነገራትና በለምጽ የተመታችውን እኅቱን ሣራን በሥውር ወደ አቡነ ማቴዎስ ዘንድ ወሰዳት፡፡ አቡነ ማቴዎስም መሬቱን ባርከው ውኃ አፍልቀው አጠመቋትና ከለምጹዋ ፈወሷት፡፡ አርባው ጭፍራዎችም አምነው በአባታችን እጅ ተጠመቁ፡፡
አባታችንም ሰማዕትነትን እንደሚቀበሉ ትንቢት ነግረዋቸው ባርከው መርቀው አሰናበቷቸው፡፡ የአቶሩም ንጉሥ ልጆቹንና ያመኑትን አርባውን ጭፍራዎቹን በሰይፍ ገደላቸው፡፡ ሰይጣንም በአቶሩ ንጉሥ አድሮ አሳበደው፡፡ እንደ እሪያም መጮህ ጀመረ፡፡
ክርስቲያን የሆነችው የቅዱስ መርምህናምና የቅደስት ሣራ እናታቸው ወደ አባ ማቴዎስ ሄዳ ንጉሡ በልጆቹ ላይ ያደረገውንና በእርሱም ላይ የተፈጸመበትን ነገር ነገረቻቸው፡፡ አባ ማቴዎስም ንጉሡን ዘይት ቀብተው ጸልየው ፈወሱት፡፡ በውስጡ አድሮበት የነበረውንም ሰይጣን በእሪያ መልክ ከንጉሡ ውስጥ አስወጡት፡፡
ንጉሡም ወደ ልቡ ሲመለስ በአቡነ ማቴዎስ ትምህርት በጌታችን አመነ፡፡ በሚገዛቸው አገሮች ሁሉ ያሉትን ሰዎች ይዞ ከነቤተሰቡ ተጠመቀ፡፡ አቡነ ማቴዎስም እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ኖረው በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፉ፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
😍6😘5🥰4🕊1
(Saint Simeon The Stylite=Syria)
Aug 08, 2026(Saint Simeon The Stylite=Syria)
❖በሶርያ የእርስ በርስ ግጭት ጉዳት የደረሰበት የታላቁ አባት ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ቤተ ክርስቲያን (ሶርያ)
በሃገራችን በዓለ ዕረፍቱ ዛሬ ይታሰባል።
ለብዙዎች ከተረፈ በረከቱ አምላኩ ያድለን።
🥰10😍4❤3😘3🕊2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 08, 2026ነሐሴ 3
Aug 08, 2026ነሐሴ 3
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሦስት በዚህች ቀን በገድል የተጠመደ መስተጋድል የከበረ #አባ_ስምዖን_ዘዓምድ አረፈ፣ ከመንግሥት ወገን የሆነች #ቅድስት_ሶፍያ አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_አባ_ስምዖን_ዘዓምድ
ነሐሴ ሦስት በዚህች ቀን በገድል የተጠመደ መስተጋድል የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ ስድስት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎቹ ጠባቂ አደረገው። ወደ ቤተ ክርስቲያንም በመሔድ ሁል ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይሰማ ነበር የእግዚአብሔርም ቸርነት አነሳሥቶት ወደ አንድ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ሲጋደልና ሰውነቱን ሲያስጨንቅ ኖረ።
ከዚህም በኋላ ገመዱ ሥጋውን ቆርጦ እስቲገባ ድረስ በወገቡ ላይ ገመድን አሠረ። ሥጋውም ተልቶ ከእርሱ ክፉ ሽታ ይወጣ ነበር ስለ ክፉ ሽታውም መነኰሳቱ አዘኑ ተጸየፉትም ወደ አበ ምኔቱም ተሰብስበው ይህን መነኰስ ስምዖንን ከእኛ ዘንድ ካላወጣኸው አለዚያ አንተን ትተን ወደሌላ እንሔዳለን አሉት እርሱም ምን አደረገ አላቸው እነርሱም ጥራውና አንተ ራስህ እይ አሉት።
ጠርቶትም መጥቶ በፊቱ በቆመ ጊዜ ደም ከመግል ጋራ በእግሮቹ ላይ ሲፈስ አየ አበ ምኔቱንም እጅግ አስጨነቀው። ልብሶቹንም ገልጦ በሥጋው ውስጥ የገባውን ያንን ገመድ አየው አበ ምኔቱም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ ይህን ታደርግ ዘንድ እንዴት ደፈርክ አለው በታላቅ ድካምም ያንን ገመድ ከሥጋው ውስጥ አወጡት ቍስሉም እስከሚድን መድኃኒት እያደረጉለት ኃምሳ ቀኖች ያህል ኖረ።
ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ እንዲህ አለው ልጄ ስምዖን ሆይ እንግዲህስ ወደ ፈለግኸው ቦታ ሒድ ከዚያም ወጥቶ ሔደ በደረቅ ጕድጓድ ውስጥም ገብቶ ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ኖረ።
ከዚህም በኋላ አገልጋዩ ስምዖንን ለምን ሰደድከው አሁንም ፈልገህ መልሰው በፍርድ ቀን እርሱ ከአንተ ይሻላልና ብሎ ሲገሥጸው አበ ምኔቱ ራእይን አየ። አባ ስምዖንንም ከገዳሙ ስለመውጣቱ ገሠጸው።
በነጋም ጊዜ አበ ምኔቱ ራእይን እንዳየ ስለ አባ ስምዖንም እንደገሠጸው ለመነኰሳቱ ነገራቸው ወንድሞችም ደንግጠው እጅግ አዘኑ እስከምታገኙትም ሔዳችሁ በቦታው ሁሉ ፈልጉት አላቸው ሔደውም ፈለጉት ግን አላገኙትም። ከዚህም በኋላ መብራትን አብርተው ወደ ጕድጓድ ውስጥ ገቡ ያለ መብልና መጠጥም ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ተቀምጦ አዩት።
ገመድም አውረዱለትና ከዚያ አወጡት በፊቱም ሰግደው በአንተ ላይ ያደረግነውን በደላችንን ይቅር በለን አሉት እኔንም ስለ አሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ገዳማቸው ወሰዱት በብዙ ገድልም ተጠምዶ ሲያገለግል ኖረ።
ከዚህም በኋላ ከዚያ ገዳም በሥውር ወጥቶ ወደ አንዲት ዐለት ቋጥኝ ደረሰ። በእርስዋም ላይ ሳያረፍና ሳይተኛ ስልሳ ቀን ቆመ። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ ብዙ ሰዎች ድኅነት እግዚአብሔር እንደ ጠራው ነገረው። ከዚያም ሔዶ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ የሚሆን የድንጋይ ምሰሶ አገኘ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ በሽተኞችንም እየፈወሰ ወደርሱ የሚመጡትንም እያስተማረ ዐሥራ ሁለት ዓመት በድንጋይ ምሰሶው ላይ ቆመ።
አባቱም ፍልጎት ነበር ግን ሳያየው ሞተ እናቱ ግን ወሬውን ሰምታ ከብዙ ዘመናት በኋላ ወደርሱ መጣች በድንጋይ ምሰሶውም ላይ ቁሞ አገኘችው አይታውም አለቀሰች ከድንጋይ ምሰሶውም በታች ተኛች። ቅዱስ ስምዖንም ጌታችን በጎ ነገርን ያደርግላት ዘንድ ስለርሷ ለመነ ያን ጊዜም እንደተኛች አረፈችና ከደንጊያው ምሰሶ በታች ቀበሩዋት።
ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ እግሩን መታው ከእግሩ ትል እየወደቀ በአንዲት እግሩ ብዙ ዓመታት ኖረ። ከዚህም በኋላ የሽፍቶች አለቃ ወደርሱ መጥቶ ንስሐ ገባ ጥቂት ቀኖችም ኑሮ አረፈ በጸሎቱም ሕይወትን ወረሰ። ወደርሱ ስለሚመጡ ብዙ ሕዝቦችም የውኃ ጥማት እንዳያስጨንቃቸው ወደ እግዚአብሔር ለምኖ ከድንጋይ ምሰሶው በታች ውኃን አፈለቀላቸው።
ዳግመኛም ወደ ሌላ ምሰሶ ተዛወረ በእርሱም ላይ እየተጋደለ ሠላሳ ዓመት ኖረ። ብዙዎች አረማውያንንና ከሀድያንን ካስተማራቸውና ወደ ፈጠራቸው እግዚአብሔር ከመለሳቸው በኋላ ክብር ይግባውና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ በሰላምም አርፎ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።
ከዚህም በኋላ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን እንዳረፈ በሰማ ጊዜ ካህናትን ዲያቆናትንና የአገሩን መኳንንቶች ከእርሱ ጋራ ይዞ የቅዱስ አባ ስምዖን ሥጋው ወዳለበት ደረሰ በታላቅ ክብርም ተሸክመው እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ እስክንድርያ አድርሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ታላቅ ፈውስም ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሶፍያ_ቡርክትና_ደናግል_ልጆቿ
በዚችም ቀን ከመንግሥት ወገን የሆነች ሶፍያ አረፈች። ለዚችም ቅድስት ብዙ ሀብትና ብዙ ጥሪት ነበራት ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር የክርስቶስን መከራ መስቀል አንሥታ ትሸከም ዘንድ ከሦስት ሴቶች ልጆቿ ጋራ ወደ ሮም ከተማ ሔደች።
ንጉሥ እንድርያሰኖስም ክርስቲያን እንደ ሆነች አውቆ ከልጆቹ ጋራ ወደ አደባባይ አስቀረባትና ስለ ሀገርዋና ስለ ስሟ ጠየቃት እርሷም የሚቀደመው ስሜ ክርስቲያን ነኝ ወላጆቼ ያውጡልኝ ስም ሶፊያ ነው እኔም በኢጣልያ ባለ ብዙ ወገን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ፈቃድም ልጆቼን መሥዋዕት አድርጌ ላቀርብ ወደ አገርህ መጣሁ አለችው። ከዚህም በኋላ የከዳተኛው ንጉሥ ሥቃዩ እንዳያስፈራቸው ልጆቿን አበረታቻቸው።
ምስክርነታቸውንም ፈጽመው ከሞቱ በኋላ ገንዛ ከሮሜ ከተማ ውጭ ቀበረቻቸው።
በሦስተኛውም ቀን መታሰቢያቸውን ታደርግ ዘንድ ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ከብዙዎች ከከተማው ሴቶች ጋራ ሔደች እንዲህ ብላም ጸለየች አክሊላትን የተቀዳጃችሁ የምታምሩ ፍጹማት የሆናችሁ ልጆቼ ሆይ እኔንም ከእናንተ ጋራ ውሰዱኝ ይህንንም እንዳለች ወዲያውኑ አረፈች ከልጆቿም ጋር ተቀበረች።
† ነሐሴ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ አባ ስምዖን ዘዓምድ
2.ቅድስት ሶፍያ ቡርክትና ደናግል ልጆቿ
† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
7.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
🥰8😍6😘3❤2🕊2
#ነሐሴ_2 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሁለት በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር #ቅድስት_አትናስያ አረፈች፣ ከነገሥታት ወገን የሆነች #ቅድስት_ኢዮጰራቅስያ አረፈች። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞…
Aug 07, 2026#ነሐሴ_2 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሁለት በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር #ቅድስት_አትናስያ አረፈች፣ ከነገሥታት ወገን የሆነች #ቅድስት_ኢዮጰራቅስያ አረፈች። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_አትናስያ_ቡርክት ነሐሴ ሁለት በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር ቅድስት አትናስያ አረፈች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ ቤቷን…
😘7❤3💯3🥰2😍2
#ነሐሴ_2
Aug 07, 2026#ነሐሴ_2
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሁለት በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር #ቅድስት_አትናስያ አረፈች፣ ከነገሥታት ወገን የሆነች #ቅድስት_ኢዮጰራቅስያ አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_አትናስያ_ቡርክት
ነሐሴ ሁለት በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር ቅድስት አትናስያ አረፈች።
የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ ቤቷን ለእንግዳ ማደሪያ ታደርግ ዘንድ በጎ ኃሳብ አሰበች ወደርሷም የሚመጡትን እንግዶች ሁሉ ትቀበላቸው ነበር። በገዳም ለሚኖሩ መነኰሳትም የሚያስፈልጓቸውን ትሰጣቸው ነበር ስለ በጎ ሥራዋም ይወዷት ነበር።
ከዚህም በኋላ ግብራቸው የከፋ ክፉዎች ሰዎች ወደርሷ ተሰብስበው ኃሳቧን ወደ ኃጢአት ሥራ መለሱትና ኃጢአትን አብዝታ ትሠራ ጀመር። በአስቄጥስ ገዳም በሚኖሩ አረጋውያን ቅዱሳን ዘንድም ወሬዋ ተሰማ ስለእርሷም እጅግ አዘኑ አባ ዮሐንስ ሐጺርንም ጠርተው ስለርሷ የሆነውን ነገሩት አስቀድማም ከእነርሱ ጋራ በጎ ስለ ሠራች ወደ እርስዋ ይሔድ ዘንድ ነፍስዋንም ለማዳን ይወድ ዘንድ ለመኑት።
እርሱም ትእዛዛቸውን ተቀበለ በጸሎታቸውም እንዲረዱት ለመናቸው ያን ጊዜም አባ ዮሐንስ ሐጺር ተነሥቶ ሔደ አትናስያ ወዳለችበት ቦታ ደረሰ ለበረኛዋም ለእመቤትሽ ስለእኔ ንገሪ አላት። በነገረቻትም ጊዜ ለረከሰ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ሁሉ የመጣ መሰላትና አጊጣ በዐልጋዋ ላይ ሁና ጠራችው። ወደርሷም ገባ እርሱም እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር በሞት ጥላ ውስጥ ብሔድም እንኳ ክፉን አልፈራውም አንተ ከእኔ ጋራ ነህና።
ከእርሷ ጋራም አስቀመጠችው ያን ጊዜም ራሱን ዘንበል አድርጎ አለቀሰ ለምን ታለቅሳለህ አለችው እርሱም ሰይጣናትን በላይሽ ሲጫወቱ አየኋቸው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን አሳዘንሺው የቀድሞ በጎ ሥራሽን ትተሽ ወደ ጥፋት ሥራ ተመልሰሻልና አላት።
ቃሉንም ሰምታ ደነገጠችና ተንቀጠቀጠች ምን ይሻለኛል አለችው ንስሐ ግቢ አላት እርሷም እግዚአብሔር ይቀበለኛልን አለችው እርሱም አዎን አላት እርሷም ወደምትሔድበት ከአንተ ጋራ ውሰደኝ አለችው እርሱም ነዪ ተከተይኝ አላት።
ያን ጊዜም ፈጥና ተነሥታ በኋላው ተከተለችው ከገንዘቧም ምንም ምን አልያዘችም። በመሸም ጊዜ ለማደር ወደ ጫካ ውስጥ ገቡ በዚያም ለእርስዋ ቦታ አዘጋጅቶ እስኪነጋ በዚህ አረፍ ብለሽ ተኚ እኔም ወደዚያ እሆናለሁ አላት። ይህንንም ብሎ ከእርሷ ጥቂት ተገልሎ እየጸለየ ብቻውን ተቀመጠ።
በሌሊቱ እኩሌታም ሊጸልይ ተነሣ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ አየ የእግዚአብሔርም መላእክት የከበረች ነፍስን ተሸክመው ሲወጡ አይቶ አደነቀ። በነጋም ጊዜ ወደ ርሷ ሔደ ሙታም አገኛት እጅግም አዘነ ስለ ርሷም ያስረዳው ዘንድ እየሰገደ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።
ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ከቤቷ በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ንስሓዋን ተቀብሎ ኃጢአትሽ ተሠረየልሽ ብሎአታል። ከዚህም በኋላ ሒዶ ለአረጋውያን የሆነውን ሁሉ ነገራቸው እነርሱም እርሱ እንዳያት ማየታቸውን ነገሩት የኃጢአተኛን ወደ ንስሐ መመለሱን እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ኢዮዸራቅስያ_ድንግል
በዚህችም ቀን ከነገሥታት ወገን የሆነች ቅድስት ኢዮጰራቅስያ አረፈች። የእርስዋም የአባቷ ስም ኢጣጎኖስ ነው የንጉሥም አማካሪ ነበር የእናቷም ስም ኢዮጰራቅስያ ነው እነርሱም ደጎች ነበሩ ጾምና ጸሎትንም ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ነበሩ። ይችንም ቅድስት በወለዷት ጊዜ በእናቷ ስም ኢዮጰራቅስያ ብለዉ ጠሩዋት።
ከጥቂት ጊዜ በኋላም አባቷ አረፈ ዕድሜዋም ስድስት ዓመት በሆነ ጊዜ እናቷ ወደ ደናግል ገዳም ከእርሷ ጋር ወሰደቻት ይህችም ቅድስት ደናግሉ ሲያገለግሉ አይታ ስለ ምን እንዲህ ደክማችሁ ትሠራላችሁ አለቻቸው እነርሱም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ነው ብለው መለሱላት ወደ ዲያቆናዊትም ሒዳ ያመነኲሷት ዘንድ ለመነች እነርሱም ለእናቷ ነገሩዋት እናቷም ለዲያቆናዊተዋ ሰጠቻት በደናግሉም ሁሉ ዘንድ አደራ ሰጠቻት ከጥቂትም ቀኖች በኋላ እናቷ አረፈችና ቀበሩዋት።
ከዚህም በኋላ ቅድስት ኢዮጰራቅስያ የምንኲስና ልብስን ለበሰች በጾም በጸሎትና በሰጊድ ተጋድሎ ጀመረች በየሰባት ቀንም ትጾም ነበር ሰይጠንም በእርሷ ላይ ቀንቶ ሊፈትናት ጀመረ ወደ ውኃ ውስጥ እርስዋን የሚጥልበት ጊዜ ነበር እንጨትም ስትፈልጥ በምሳር የሚአቊስልበት ጊዜ ነበር። የፈላ ውኃም በላይዋ የሚያፈሰበት ጊዜ ነበር ነገር ግን ምንም ምን የጐዳት የለም።
ለደነግሎችም ስታገለግል ብዙ ዘመናት ኖረች ምንም አትታክትም ነበር በምድርም ላይ አትተኛም መላዋን ሌሊት ቁማ በጸሎት ታድር ነበር እንጂ ከገድሏ ጽናትም የተነሣ ደናግሉ እስከሚያደንቁ ድረስ አርባ ቀን ቁማ ትፈጽም ነበር።
ከዚህም በኋላ ጌታችን በሽተኞችን በማዳን አጋንንትን በማስወጣት የዕውሮችን ዐይን በመግለጥ የአንካሶችንም እግር በማስተካከል ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቿ ገለጠ።
ዲያቆናዊት ኢዮኤልያም ለኢዮጰራቅስያ መጸሐፍትንና የምንኵስናንም ሥርዓት አስተማረቻት በሥራም ሁሉ ትሳተፋት ነበር እጅግም ይፋቀሩ ነበር እርሷም ሰማያዊ ሙሽራ ወደአለበት የመንግሥት አዳራሽ የማያልቅ ተድላ ደስታም ወደአለበት ኢዮጵራቅስያን ሲያወጧት ራእይን አየች።
በነቃችም ጊዜ ለደናግል ነገረቻቸው ወደርሷ ሲሔዱም በትኩሳት በሽታ ታማ አገኟት ስለእነርሱም እንድትጸልይ ለመኑዋት እርሷም ደግሞ በጸሎታቸው እንዲአስቧት ለመነቻቸው ያን ጊዜም ጸሎት አድርጋ መረቀቻቸውና በሰላም አረፈች በእናቷም መቃብር ውስጥ ቀበሩዋት።
ወዳጅዋ ኢዮኤልያም ወደ መቃብርዋ ሒዳ ጸለየችና በሦስተኛው ቀን አረፈች ከእርሷም ጋር ተቀበረች።
🗓 ነሐሴ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት አትናስያ ቡርክት
2.ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ድንግል
3.ቅዱስ ዴሚና ሰማዕት
🗓 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
🥰8❤4💯3😍2😘2
ስለ ፍልሰታ እና ለፍልሰታ የተዘመሩ መዝሙሮች
Aug 07, 2026ስለ ፍልሰታ እና ለፍልሰታ የተዘመሩ መዝሙሮች
❤2
† "በጽዮን መለከትን ንፉ። ጾምንም ቀድሱ። ጉባዔውንም አውጁ። ሕዝቡንም አከማቹ። ማሕበሩንም ቀድሱ። ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ። ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ። ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።" †††
Aug 06, 2026† "በጽዮን መለከትን ንፉ። ጾምንም ቀድሱ። ጉባዔውንም አውጁ። ሕዝቡንም አከማቹ። ማሕበሩንም ቀድሱ። ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ። ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ። ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።" †††
(ኢዩ. 2:15)
እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †
❤4🕊3😍3😘3🥰2
⚠️ ጥቆማዎች ለጾመ ፍልሰታ 5 የመጻሕፍት
Aug 06, 2026⚠️ ጥቆማዎች ለጾመ ፍልሰታ 5 የመጻሕፍት
❤3🥰3😍3😘1
✝️ መልክ0 ፍልሰታ
Aug 06, 2026✝️ መልክ0 ፍልሰታ
❤7😘4🥰3😍3
#ነሐሴ_1 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አንድ በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም እናቷ #የቅድስት_ሐና መታሰቢያዋ ነው፣ የዮስጦስ ልጅ #ቅዱስ_አቦሊ በሰማዕትነት አረፈ፣ የከበ…
Aug 06, 2026#ነሐሴ_1 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አንድ በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም እናቷ #የቅድስት_ሐና መታሰቢያዋ ነው፣ የዮስጦስ ልጅ #ቅዱስ_አቦሊ በሰማዕትነት አረፈ፣ የከበሩ ሰዎች #ቅዱሳን_የዮሴፍና_የኒቆዲሞስ መታሰቢያቸው ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ሐና (የእመ ብርሃን እናት) ነሐሴ አንድ በዚህች ቀን አምላክን…
❤7😘5😍3🥰2🕊2
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ አቦሊ ተገለጠለት እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው። በመከራ ውስጥ ያለ ሰው በስምህ ርዳታ ቢለምን እኔ እሰማዋለሁ ልመናውን ፍላጎቱንም እፈጽምለታለሁ። በስምህ ቤተ ክርስቲያን …
Aug 06, 2026ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ አቦሊ ተገለጠለት እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው። በመከራ ውስጥ ያለ ሰው በስምህ ርዳታ ቢለምን እኔ እሰማዋለሁ ልመናውን ፍላጎቱንም እፈጽምለታለሁ። በስምህ ቤተ ክርስቲያን ለሠራም እኔ በሰማያት ብርሃናዊ ማደሪያ ቤት እሠራለታለሁ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን ወይም የሚሰማውን እኔ በኪሩቤል ክንፎች ላይ ስሙን እጽፉለሁ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍም አሳርፈዋለሁ ተድላ ደስታ ካለባት ከገነት ፍሬዎችም እመግበዋለሁ።
ብዙ ኃጢአትን ሠርቶ የበደለውንም በስምህ ወደኔ እየለመነ ንስሐ ቢገባ በደሉን ሁሉ ይቅር እለዋለሁ። ከጻድቃንም ጋርም እቈጥረዋለሁ ሰላሜም ካንተ ጋራ ይሁን ይህንንም ብሎ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።
መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ሥጋውም ከምስር ከተማ ውጭ ሕንቅ በሚባል ገዳም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አበው_ሐዋርያት_ዮሴፍና_ኒቆዲሞስ
በዚህችም ቀን ለአምላካዊት ምሥጢር አገልጋዮች ሊሆኑ የተገባቸው የከበሩ ሰዎች የዮሴፍና የኒቆዲሞስ መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶች አዘዙ።
በፈቃዱ መከራ ተቀብሎ ስለ ደኅንነታችን በሞተ ጊዜ የደኅንነታችንንም ምሥጢር በፈጸመ ጊዜ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ እነርሱ ከመስቀል ላይ አውርደዋልና። የአይሁድም መገርመም ከጲላጦስ ዘንድ የመድኃኒታችንን ሥጋ እስከ ለመኑ ድረስ አላስፈራቸውም።
ጴላጦስም በፈቀደላቸው ጊዜ የእጆቹንና የእግሮቹን ችንካሮች ነቅለው ከመስቀል አውርደው በትክሻቸው ተሸከሙት ሲገንዙትም እንዲህ የሚል ቃል ከበድኑ ሰሙ። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በዮርዳኖስ የተጠመቀ በእንጨት መስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ በክብር ወደ ሰማያት ያረገ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ የሚመጣ አቤቱ ይቅር በለን።
ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን አሜን ይሁን ይሁን። ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ይቅር በለን።
ይህንንም በሰሙ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖታቸው ጸናች። ዮሴፍም በፍታ ኒቆዲሞስም ሽቶዎችን አምጥተው ጌታችንን ገነዙት በአዲስ መቃብር ውስጥም ቀበሩት።
ይህ ዮሴፍም ለሰማዕታት መጀመሪያ ለእስጢፋኖስ ዘመድ ለሆነው ለቀለዮጳ ወንድሙ ለኒቆዲሞስ ዘመዱ ነው ኒቆዲሞስም የአይሁድ አለቃ ፈሪሳዊ ነበር እርሱም ወደ ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ በሌሊት የሔደና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣ ያመነ ነበር። ጌታችንም ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንደማይችል የነገረው ነው።
ይህ ኒቆዲሞስም የጌታችንን ቃል በሚአቃልሉ ጊዜ አይሁድን ይገሥጻቸው ነበር። ከተነሣ በኋላም በኢማሁስ መንገድ ሲሔድ ጌታችን ኢየሱስ የተገናኛቸው እሊህ ኒቆዲሞስና ቀለዮጳ ናቸው። እነርሱም ሳያውቁት በእርሱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገሩት። እርሱም ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ አስተማራቸው።
ከዘህም በኋላ እርሱ መሆኑን ባወቁት ጊዜ ተሠወራቸው እነርሱም ተመልሰው ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩ። ክብር ይግባውና የጌታችንን ሥጋ ስለ ቀበረ ሊገድሉት ፈልገው አይሁድ ዮሴፍን በወህኒ ቤት አሠሩት። የወህኒ ቤቱም በር በሊቃነ ካህናቱና በጲላጦስ ማኅተም ተቆልፎ ሳለ ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ዮሴፍ ወደ አለበት ገባ ከእርሱ ጋርም እልፍ አእላፋት መላእክት ነበሩ። ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው በፊቱ ያጥናሉ በቀኝ በኩል ተሰቅሎ የነበረ ወንበዴውም ብሩህ ልብስ ለብሶ በቀኝ ቁሞአል ባለሟልነትን በልዑል ፊት አግኝቶአልና ስለ ኃጢአተኞች ይማልድ ነበር።
የወህኒ ቤት ጠባቂዎችም በአዩ ጊዜ ደነገጡ ፈርተውም መንቀጥቀጥ ያዛቸው ጌታችንም ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው ከአይሁድ ግርማ የተነሣ አትፍራ ከማሠሪያህ ልፈታሕ እኔ መጣሁ አንተ መከራዬን የተሳተፍከኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ አኔ ጌታህና የዓለሙ ሁሉ ጌታ እንደሆንሁ ፈጽመህ ታውቅ ዘንድ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን የተወጋ ጐኔንም እይ።
ከዚያም ዮሴፍን ነጥቆ ወደ አገሩ አርማትያስ ወሰደው። የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎችም ሔደው ጌታችን ያደረገውን ሁሉ ዮሴፍንም ይዞ ከእርሱ ጋር እንደወሰደው ለካህናት አለቆች ነገሩ። የካህናት አለቆችም በሔዱ ጊዜ የወህኒ ቤቱ በር ተቆልፎ አገኙ እሽጉም አልተለወጠም ነበር። እሊህ ቅዱሳንም ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን እየሰበኩ ኖሩ ብዙ መከራም አገኛቸው። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፉ።
† ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
😍7🥰3❤2🕊2😘2
#ነሐሴ_1
Aug 06, 2026#ነሐሴ_1
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ አንድ በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም እናቷ #የቅድስት_ሐና መታሰቢያዋ ነው፣ የዮስጦስ ልጅ #ቅዱስ_አቦሊ በሰማዕትነት አረፈ፣ የከበሩ ሰዎች #ቅዱሳን_የዮሴፍና_የኒቆዲሞስ መታሰቢያቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
ነሐሴ አንድ በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም እናቷ የሐና መታሰቢያዋ ነው። ይህችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት (ጣ ጠብቆ ይነበብ) ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።
ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧት። (ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።)
ቅድስት ሐና ኢያቄምን አግብታ ስትኖር የቴክታና እና የጴጥሪቃ ምክነት በዘር ወርዶ መክና በመኖሯ የዐይኗ ማረፊያ የልቧ ተስፋ የሚሆን ልጅ እንዲስጣት ፈጣሪዋን ስትማጸን ኖራለች።
የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ልመናዋን ሰምቶ ሐምሌ ፴ ራእይ አየች። ራእዩንም ከባሏ ከኢያቄም ጋር ተወያየተው ምንጣፍ ለይተው ሱባኤ ገቡ።
ከአንድ ሱባኤ በኋላ ነሐሴ ፯ ቀን ጌታ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ እንደሚወልዱ አበሠራቸው። ከዚያም እመቤታችን ጸንሳ ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርጋለች። ሳምናስን ከሞት አስነስታለች። በርሴባን ዐይኗን አብርታለች። ከዚያም በአይሁድ ተንኮልና አሳዳጅነት ወደ ሊባኖስ ተራራ ተሰዳ ድንግል ማርያምን ወልዳለች። በመውለዷም ሕዳሴ አካል አግኝታ ከኖረች በኋላ ዐርፋለች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አቦሊ
በዚህችም ቀን የዮስጦስ ልጅ ቅዱስ አቦሊ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ አቦሊ ከመንግሥት ልጆች ውስጥ ነበር ዐላውያንን ወግቶ በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ አገኘው።
ያም አቦሊና አባቱ ዮስጦስ ሌሎችም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን ሊያጠፉትና መንግሥትን ከእርሱ ሊወስዱ ችሎታ ሲኖራቸው የማታልፍ ሰማያዊት መንግሥትን አሰቡ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ አቦሊ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አብዝቶ አባበለው። እንዲሁም አባቱ ዮስጦስንና የከበረች እናቱ ታውክልያን አባበላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም ልባቸው በመድኅን ክርስቶስ ፍቅር ተነድፏልና። ንጉሡም እነርሱን በዚያ ማሠቃየትን ፈራ ስለዚህም ከመልእክት ደብዳቤ ጋር ወደግብጽ ስሙ ኄርሜኔዎስ ወደሚባል የእስክንድርያ ገዥ ላካቸው በመልእክቱም እንዲህ አለው ዮስጦስና ሚስቱ ታውክልያ ልጃቸው አቦሊም ወደአንተ በሚደርሱ ጊዜ አባብላቸው አለዚያም እየአንዳንዳቸውን ለያያቸው።
በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዮስጦስና ለሚስቱ ታውክልያ ለልጃቸው አቦሊም ተገልጦላቸው አጽናናቸው ከእነርሱም የሚሆነውን ነገራቸው የጸና ቃል ኪዳንም ሰጣቸው።
ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስም በደረሱ ጊዜ ስለእነርሱ እጅግ አደነቀ እነርሱ መንግሥታቸውን ትተዋልና ክፋ ነገርንም ሊናገራቸው አልደፈረም ከምክራቸው ይመለሱ ዘንድ በለሰለሰ ቃል ሸነገላቸው እንጂ ነገር ግን አልሰሙትም።
ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለእየብቻቸው ለያያቸው ቅዱስ ዮስጦስን ወደ እንዴናው ከተማ ሚስቱን ታውክሊያን ፃ ወደ ሚባል አገር ልጃቸው አቦሊንም ብስጣ ወደ ሚባል አገር ሰደዳቸው ለእያንዳንዳቸውም የሚአገለግላቸው አንዳንድ አገልጋይ ሰጣቸው። ቅዱስ አቦሊም ወደ ሀገር ብስጣ በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፉት ታመነ። መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን በእሳት ቃጠሎና በመንኰራኵር አሰቃየው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ለአንበሶች ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ከሥቃዩ ሁሉ አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አነሣው።
ብዙዎች ሰዎችም ስቃዩንና ዳግመኛ መዳኑን በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው ሰማዕታት ሆኑ።
መኰንኑ ግን እጅግ ተቆጥቶ የቅዱስ አቦሊን ቆዳውን እንዲገፍፉትና ጨውና መጻጻን በማቅ አምጥጠው ቍስሉን እንዲያሹ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት።
ከዚህም በኋላ ቆዳውን አሸክመው በከተማ ውስጥ ሁሉ አዞሩት ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ጸለየ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጣ ሁለመናውንም ዳስሶ አዳነው።
መኰንኑም በእርሱ ላይ የሚያደርገውን እስኪያስብ ከእሥር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ። ቅዱስ አቦሊም ቁሞ ጸለየ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና የመረጥኩህ አቦሊ ሰላም ለአንተ ይሁን እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ አለው ጌታችንንም በአየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው ክብር ይግባውና ለጌታችንም ሰገደለት።
ስሙ አብስኪሮን የሚባል አንድ ባለ ጸጋ ነበር የቤቱንም ግድግዳ አፍርሰው አዲስ ይሠሩለት ዘንድ ሠራተኞችን አመጣ ሥራቸውንም እስኪጨርሱ ከዚያ ይቆሙ ዘንድ ሁለቱን ልጆቹን አዘዛቸው።
ከግርግዳውም ላይ በወጡ ጊዜ ግርግዳው ተደርምሶ ዐሥራ ስድስት ሰዎችና ሁለቱ ልጆቹ ሞቱ። ባለጸጋውም የሆነውን በአየ ጊዜ ልብሱን ቀደደ ጩኾም አለቀሰ ወደ ቅዱስ አቦሊም ሒዶ ከእግሩ በታች ሰገደለት እንዲህም አለው ራራልኝ ሁለቱ ልጆቼ ሙተዋልና ከእነርሱም ጋራ ዐሥራ ስድስት ሰዎች ሞቱ። ከሞትም ብታሥነሣቸው እኔ በአምላክህ አምናለሁ።
ያን ጊዜም ቅዱስ አቦሊ ተነሣ እንዲህ ብሎ ጸለየ ስለ ቅዱስ ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ የመረጥከኝ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኒህ በሞቱ ሰዎች ላይ ኃይልህን ግለጥ። እኒህ ሰዎች ሁሉ እንዲአምኑ ያለ አንተም ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ከሞት አንሣቸው። ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
ከዚህም በኋላ የተገፈፈ ቆዳውን ወስዶ በሞቱት ሰዎች ላይም ዘረጋውና በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሞት ተነሡ አለ። ወዲያውም ሁሉም ድነው ተነሡ በዚያ ያሉ ሕዝብም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ የክርስቲያን አምላክ የቅዱስ አቦሊም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው እኛም እናምንበታለን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለምና እያሉ ጮኹ።
ባለ ጸጋው አብስኪሮንም መጥቶ ለቅዱስ አቦሊ እንዲህ እያለ ሰገደ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ዛሬ አወቅሁ እኔም አምንበታለሁ። ከቤተሰቦቹም ሁሉ ጋር አመኑ መኰንኑም አፈረ።
❤7😘3🕊2😍1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 06, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😘5❤2😍2🥰1
❤️🔔 ይሄን ሲቀላቀሉ፦ ❤️🌹
Aug 06, 2026❤️🔔 ይሄን ሲቀላቀሉ፦ ❤️🌹
🟢 መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን በተከታታይ ይማራሉ፤
🟡 በየዕለቱ የሚውሉ ቅዱሳንን በመዘከር በረከት ይሸምታሉ፤
🔵 የፈለጉትን ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ጠይቀው ያገኛሉ፤
🟣 በመንፈሳዊ የኪነ ጥበብ ሥራዎች የአምላክን ግሩም ጥበብ ያደንቃሉ፤
🟢 በበጎ አድራጎት ሥራዎች እርካታ ነፍሶን በሐሴት ይሞላሉ፤
🔴 መንፈሳዊ መጻሕፍትንና ጽሑፎችን በPdf እና Application በእጅዎ ያስገባሉ፤
🟡 የተለያዩ መምህራንን ስብከቶች እና ትምህርቶች ያገኛሉ፤
🔵 ባልዎት ጸጋ እግዚአብሔርን ያገለግላሉ፤
🔴 አዝናኝ በሆኑ ጥያቄዎች እየተማሩ ይሸለማሉ፤
ወ.ዘ.ተ ....
❤1🥰1😍1
⏰ ከ60 second በኋላ ይጠፋል! 🎬 ምን አይነት የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?
Aug 06, 2026⏰ ከ60 second በኋላ ይጠፋል! 🎬 ምን አይነት የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?
❤6🥰3😘3😍2
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Aug 06, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
❤4😘4🥰1
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Aug 06, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
🥰4😍3😘3❤1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 06, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
😘5🥰4😍3❤2
ስለ ፍልሰታ እና ለፍልሰታ የተዘመሩ መዝሙሮች
Aug 06, 2026ስለ ፍልሰታ እና ለፍልሰታ የተዘመሩ መዝሙሮች
😍4😘4🥰3❤2
📖 ስለ ፍልሰታ
Aug 05, 2026📖 ስለ ፍልሰታ
ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው❓
የፍልሰታን ጾም ለምን እንጾማለን❓
ጾም ማለት ምን ማለት ነው❓ ጾም ለምን እንጾማለን❓
🥰7❤4😘2😍1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Aug 05, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
😍5❤3😘3
"ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት"
Aug 05, 2026"ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት"
ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::
በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብን ያሳራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::
በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::
የይቅርታ ጌታ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወን፣ አይጣለን።
🥰4😍3😘3❤2💯1
ቅዱሳን (Saints)
Aug 05, 2026እኒያ ሐዋርያትም የሚሆነውን ያዩ ዘንድ ወጥተው በሀገሩ ጎዳና ዳር ተቀመጡ የከተማው ሰዎችም እነደ ልማዳቸው የሚበሉትን ከእሥረኘች ውስጥ ሊአመጡ መጡ የእሥር ቤቱን ደጅ ክፍት ሆኖ አገኙ እሥረኞችም አልነበሩም ደነግጠውም በእኛ የደረሰብን …
Aug 05, 2026እኒያ ሐዋርያትም የሚሆነውን ያዩ ዘንድ ወጥተው በሀገሩ ጎዳና ዳር ተቀመጡ የከተማው ሰዎችም እነደ ልማዳቸው የሚበሉትን ከእሥረኘች ውስጥ ሊአመጡ መጡ የእሥር ቤቱን ደጅ ክፍት ሆኖ አገኙ እሥረኞችም አልነበሩም ደነግጠውም በእኛ የደረሰብን ምንድነው ወዮልን አሉ ያን ጊዜም ሰይጣን በሰው መስሎ ሐዋርያት ይህን እንዳደረጉ ነገራቸው የአሉበትንም አመለከታቸው የከተማው ሰዎችም በመቀዳደም ሮጡ እንድርያስንና ማትያስንም ይዘው በከተማው ጥጋጥግ አስጎተቱአቸው በሌሊትም በእሥር ቤት ያሳድሩአቸው ነበር ሦስት ቀናትም እንዲህ አደረጉባቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ።
ከዚህም በሗላ ሰለ ከተማዋ ሰዎች ድኀነት ወደ እግዚአብሔር ጸለዪ ጸሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ በላዩ ምስል ወደአለበት የዕብነ በረድ ምሶሶ ቀርበው በመስቀልመ ምልክት አመተቡት እንዲህም አሉት አንተ ምሶሶ ፍራ ከበታችህም እንደ ጥፋት ውኃ ያለ ብዙ ውኃን በዚች ከተማ ላይና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ላይ አውጣ ያን ጊዜም ከምሶሶው ሥር ብዙ ውኃ መነጨ የከተማው ሰዎችንም ያሠጥማቸው ዘንድ ገነፈለ ሰዎችም ከከተማው ወጥተው ሊሸሹ ወድደው ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ያዙ ውኃውም በዝቶ ከበባቸው ማምለጥም አልቻላቸውም ውኃውም እስከ እስከ አንገታቸው ደረሰ ያን ጊዜም አለቀሱ እንዲህም አሉ ወዮልን ይህ ሁሉ በእኛ ላይ የመጣው በእነዚህ በተመረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር አገልጋዮች ምክንያት ነው እኛም በአምላካቸው እናምናለን። እንድርያስም የዕብነ በረደ ምሰሶ እንግዲህስ በቃህ እነሆ የጥፋት ጊዜ አለፈ ያን ጊዜም ውኃው ተገታ ውኃውም እንደተገታ የከተማው ሰው አይተው ወደ ሐዋርያት ሔዱ ስለዚያች ከተማ ሰዎች ድኅነትም ቁመው እጆቻቸውን ዘርግተው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ አገኙአቸው ሐዋርያትን ይቅር በሉን ብለው ለመኑአቸው። ሐዋርያትም በሕያው እግዚአብሔር እመኑ እንጂ አትፍሩ አሏቸው ሐዋርያትም ሁለተኛ ጸለዩ በውኃ ስጥመት የሞቱትንም ሙታን አስነሡአቸው በዚያም ውኃ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበሏቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው። ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተምረው በቀናች ሃይማኖት አጸኑአቸው እንዲህም አሏቸው ያዘዝናችሁን ጠብቁ ከእናንተ በኃላ ለሚነሡ ልጆቻችሁም አስተምሯቸው።
ከዚህም በኃላ የአራዊትን ጠባይ ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት ክብር ይግባውና ጌታችንም ይህን የአራዊት ጠባይ አራቀላቸው። ሰዎች የሚመገቡትንም የሚመገቡ የዋሆች ሆኑ። አባቶቻችን ሐዋርያትም ብዙ ተአምራትን አደረጉ በሽተኞችን ሁሉ ፈወሱ ከዚህም በኃላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ግሪክ አገር ተመለሰ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#እናታችን_ማርያም_ክብራ
በዚህችም ቀን የንጉሥ ናዖድ ሚስት ንግሥት ማርያም ክብራ አረፈች። እርሷም መንፈሳዊ የሆነ በጎ ተግባርን ሁሉ የጠበቀች ትሩፋትንና መጋደልንም በጾምና በጸሎት የፈጸመች ነበረች በደብረ ሊባኖስም ተቀበረች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልና በመነኮሳት በቅዱሳን መላእክትም በተመረጡ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት በቀሳውስትና በዲያቆናት ሃይማኖታቸው በቀና በአእሩግና ሕፃናት በእነዚህ ሁሉ ጸሎት ይማረን።
=>ሐምሌ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ (ከቤተሰቡ ጋር)
3.ቅዱስ ሱርያል (እሥራልዩ) ሊቀ መላእክት
4.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም (ሰማዕታት)
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት (ፍልሠቱ)
6.እናታችን ማርያም ክብራ ኢትዮዽያዊት (የዐፄ ናዖድ ሚስት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ በሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት እንዲሁም በሁላችን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘6😍5💯1
#ሐምሌ_30
Aug 05, 2026#ሐምሌ_30
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሠላሳ በዚች ቀን ቅዱሳን የገሊላ ሰዎች #ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ኤፍሬም በሰማዕትነት አረፈ፣ ክብርንና ብልጽግናን ንቆ የተወ #ቅዱስ_ጳውሎስ_መናኒ አረፈ፣ #ቅዱስ_ሐዋርያ እንድርያስ ተአምራትን አደረገ፣ የንጉሥ ናዖድ ሚስት #ንግሥት_ማርያም_ክብራ አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ኤፍሬም (ሰማዕታት)
ሐምሌ ሠላሳ በዚች ቀን ቅዱሳን የገሊላ ሰዎች መርቆሬዎስና ኤፍሬም በሰማዕትነት አረፈ። እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንደማሞች በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደሉ በገዳሙ ውስጥ ሃያ ዓመት ያህል ኖሩ።
ከዚህም በኃላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕትን ሊሠው ወደ ኦርቶዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተኑት።
እንዲህም አሏቸው በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም። ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንምገረፏቸው ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖርዋቸው ከእነሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዻውሎስ_መናኒ
በዚህችም ቀን ክብርንና ብልጽግናን ንቆ የተወ ጳውሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ባለጸጋ ነበር። ደግ የሆነች ሚስትና የተባረኩ ልጆችም ነበሩት። መነኮስ ሊሆን ወደደ ሚስቱንና ልጆቹንም ጠርቶ እነሆ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር እሸጣችሁ ዘንድ ወደ ዱኩ አላቸው እነርሱም አሳዳሪያቸን ነህና የወደድከውን አድርግ አሉት።
ከዚህም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ሚስቱንም ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት እመምኔቷንም ጠራትና እንዲህ አላት ለገዳምሽ አገልጋይ ትሆን ዘንድ ሚስቴን ልሸጥልሽ እወዳለሁ እርሷም እሺ አለችው የመሸጫዋንም ደብዳቤ ጻፈ የሺያጭዋን ዋጋ ተቀብሎ ለድኆች ሰጠ ልጆቹንም ወደ አበ ምኔቱ ወስዶ እንደ እናታቸው ሸጣቸው ለአበ ምኔቱም አሳልፎ ሰጣቸው።
ከዚህም በኃላ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ ራሱንም ለገዳሙ አለቃ ሸጠ አለቃውንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ብቻዬን ልገባ እሻለሁ አለው በገባም ጊዜ በሩን በላዩ ዘጋ። እጆቹንም ዘርግቶ ቆመ በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብሎ ጮኸ አቤቱ በፍጹም ልቡናዬ ወዳንተ እንደ መጣሁ አንተ ታውቃለህ።
ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ሀሳብህን ሁሉ አውቅሁ በፍጹም ልቤም ተቀበልኩህ። ከዚህም በኃላ መነኮስ አስጨናቂ የሆኑ የገዳሙን ሥራዎች ሁሉ እንደ ባሪያ እየሠራ ኖረ ራሱንም ከሁሉ እጅግ አዋረደ ነገር ግን ስለ መዋረዱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው። ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከዚህም በኃላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_እንድርያስ_ሐዋርያ
በዚችም ቀን ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስ ተአምራትን አደረገ። እንድርያስ በጽርዕ አገር እያለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ እንዲህ አለው ማትያስን ከእሥር ቤት ታወጣው ዘንድ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሒድ የዚያች አገር ሰዎች ከሦስት ቀን በኃላ ሊበሉት ያወጡታልና ።
እንድርያስም ጌታችንን እንዲህ አለው የቀረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ ነገር ግን ፈጥኖ የሚያወጣውን ከመላእክት አንድ ላክ እንጂ።
ጌታችንም ለእንድርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት ስማ ሀገሪቱን ወደዚህ ነዪ ከልዃት በውስጧ ከሚኖሩ ሁሉ ጋር ትመጣለች አንተና ደቀ መዘሙሮችህ ግን ጠዋት በሆነ ጊዜ ተነሥታችሁ ወደ ባሕር ሒዱ የተዘጋጀ መርከብንም ታገኛላችሁ እርሱም ያደርስሃል ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ በክብር ዐረገ። በነጋ ጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተነሥቶ ወደ ወደብ ደረሰ ጥሩ መርከብንም አየ ጌታችንንም በሊቀ ሐመር አምሳል አየው ጌታችን እንደሆነ አላወቀም ሊቀ ሐመር ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አለው ጌታም የእግዚእብሔር ሰላም ይደርብህ አለው እንደርያስም ደግሞ በዚህ መርከብ ወዴት ትሔዳለህ አለው ሰውን ወደ ሚበሉ ሰዎች አገር እሔዳለሁ አለው እንድርያስም ሊቀ ሐመሩን ወንድሜ ሆይ ከአንተ ጋር ትጭነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው ሊቀ ሐመሩም እሺ ብሎ ወደ መርከቡ አወጣቸው። በባሕሩ ላይም ሲጏዙ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ ብሎ ጠየቀው ጌታህ ምን ኃይል አደረገ እንድርያስም ጌታችን ከአደረጋቸው ተአምራቶች ለነግረው ጀመረ ጌታችን እንደሆነ አላወቀም ነበርና።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ሐመሩ እነደሚአንቀላፋ ሰው ሆነ ያንጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተኛ በዚያን ጊዜም ጌታችን እንድርያስንና ሁለቱን አርድእቱን ይሸክሙአቸው ዘንድ መላእክትን አዘዛቸውና ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አኖሩዋቸው። እንድርያስም ከእነቅልፍ በነቃ ጊዜ መረከብን አላገኘም እጅግም አደገቀ ለደቀ መዛሙርቱም እንድህ አላቸው ልጆቼ ሆይ በመርከብ ውስጥ ከጌታችን ጋር ነበርን ግን አላወቅንም።
ከዚህም በኋላ እንድርያስ ተነስቶ ጸለየ ክብር ይግባውና ጌታችንም በመልካም ጎልማሳ አምሳል ተገለጸለት እንዲህም።
አለው ወዳጄ እንድርያስ አትፍራ እኔ ይህን አድርጌአለሁና አንተ በሦስት ቀን አልደርስም ብለህ ነበር ስለዚህ በፍጥረት ሁሉ ላይ ኃይል እንዳለኝ የሚሳነኝምእንደሌለ ተውቅ ዘንድ እንግድህም ወደ ከተማው ገብተህ ማትያስን ከእሥር ቤት አውጣው ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሁሉ።
ከዚህም በኋላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተነሥቶ ወደ ከተማ ገባ ማትያስ ወዳለበትም እስር ቤት ሔደ። በደረሰም ግዜ የወሀኒ ቤቱ ደጀ ራስዋ ተከፈተች በገባ ጊዜም ማትያስን ተቀምጦ ስዘምር አገኘው እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሳጣጡ እንድርያስም ማትያስን ከሁለት ቀን ቡኋላ አውጥተው እንደ እንስሳ አርደው ይበሉኛል አልክ አንተ በጌታችን ዘንድ ያየናትን ያቺን ምሥጥር ረሰሃትን በምንናገረት ጊዜ ሰማይና ምድርን ይናወጣሉ አለው። ማትያስም ወንድሜ ሆይ እንሆ ይህን አወቅሁ ነገር ግን በዚች ከተማ ውስጥ ሥራዬን እንድፈጽም የጌታችን ፍቃድ እንደ ሆነ እኔ እናገራሎህ እርሱ ራሱ እንሆ እኔ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እንኳችኃሎህ ብሏልና ወደ ዝህም እሥር ቤት በጨመሩኝ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ጠራሁት እርሱም ሃያ ሰባት ቀን ሲፈጸም ወንድምህ እንድርያስን ወዳንተ እልከዋሎህ እርሱም ከእሥር ቤት ያወጣሃል ከአንተ ጋራ ያሉትን ሁሉ ያወጣችዋል ብሎ ገለጠልኝ እንሆም ደርሰሃል የምትሠራውን አስተውል አለው።
እንድርያስም ወደ እስረኞች በተመለከተ ጊዜ እንደ እንስሳ ሥር ሲበሉ አይቶ አዘነ አለቀሰም ሰይጣንንም ከሠራዊቱ ጋር አሥረው ከዝህ በኃላ አንድርያስና ማትያስ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ማለዱ እጆቻቸውንም በእሥረኞች ሁሉ ላይ ጫኑ አእምሮአቸውም ተመለሰ ከከተማው ውጭ ወጥተው በዝያ በአንድነት እንድቀመጡ አዘዙአቸው።
😘5❤3😍3🥰2💯1
1. ማማተብ ማለት ምን ማለት ነው ❓
Aug 05, 20261. ማማተብ ማለት ምን ማለት ነው ❓
2. ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ማማተብ እንዴት አይነት ነው ❓
3. ወደ ላይ፣ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝና ወደ ግራ የምናማትብበት ሚስጢሩ ምንድን ነው❓
4. በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምናማትበው መቼ መቼ ነው ❓
5. በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓተ ቤተክርስቲያን መሰረት ካማተብን በኋላ የራሳችንን እጅ መሳም ተገቢ ነውን ❓
የሚሉትን ጥያቄዎች ??? ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ መልስ ለማግኘት ቻናላችንን JOIN በማድረግ ይቀላቀሉ 👇👇👇
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 05, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤5🥰4😘3
💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
Aug 05, 2026💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
😍4❤3🥰3😘3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Aug 05, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍1
²⁹ሐምሌ ²⁹
Aug 04, 2026²⁹ሐምሌ ²⁹
ደብረ ጉንድ (ጎንድ) ተክለሃይማኖት (መካነ ጸሎቱ ለእጨጌ ዮሐንስ ጻድቅ፡፡)
☞ገዳሙ የተመሠረተው በጻድቁ አባ ዮሐንስ ሲሆን በለሳን ርስት አድርጎ የሰጣቸው ጻድቅ ንጉሥ አፄ ዘርዓያዕቆብ በ1442 ዓ/ም ነበር፡፡
☞ይህ ከሆነ ከ18 ዓመት በሁዋላ (በ1460) ጻድቁ ከነበሩበት ደብረ ኤጎራ ወደስፍራው መጥተው ገድመውታል፡፡
☞7 ገዳማትን ገድመው፡ 10 ትውልድ የሚያስምር ቃልኪዳንን ተቀብለው በ500 ዓመታቸው (በ1611 ዓ/ም) ዐርፈው በዚሁ ገዳም ተቀብረዋል፡፡
☞ዛሬ የደገኛው ጻድቅ በዓል በገዳሙ ይከበራልና ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
❖🥀❖🥀❖
🥰6😍4😘4❤2💯1
#ሐምሌ_29 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን #አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፣ #የቅዱስ_ሐዋርያ_ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ #ቅዱስ_ወርስኖፋ በሰማዕትነት አረፈ። ✞✞✞✞✞✞…
Aug 04, 2026#ሐምሌ_29 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን #አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፣ #የቅዱስ_ሐዋርያ_ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ #ቅዱስ_ወርስኖፋ በሰማዕትነት አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #እጨጌ_አባ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ (ዘጐንድ) ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም…
😍7❤5😘3🥰2💯2
በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም …
Aug 04, 2026በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ታዴዎስ_ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
በዚህችም ቀን ከሶሪያ አገር ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም የሆነ ክርስቶስን የሚወድ ጻድቅ ቁስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ነበር። በሱ ትእዛዝም የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስን ሥጋ አፈለሱ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ።
በዚችም ቀን አከበሩዋት ከእርሱም ብዙ የሆኑ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዋርስኖፋ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ቅዱስ ወርስኖፋ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅድስ አዋቂ ሃይማኖቱ የቀና የዋህና በገድል የተጠመደ ሰው ነበረ። ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በፈለጉት ጊዜ ከእርሳቸው ሸሸ ወደ አንዲት አገርም ደርሶ እግዚአብሔርን በሚወዱ ሁለት መነኰሳት ዘንድ አደረ።
በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲ ታመን የሰማዕትነትንም አክሊል እንዲቀበል አዘዘው። በነቃም ጊዜ ለእኒህ ለሁለቱ ወንድሞች ያየውን ነገራቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ተስማሙ። ከዚህም በኃላ መኰንኑ ወደ አለበት ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃያቸው ከዚያም ሰንዑር ወደሚባል አገር እስከሚሔድ ድረስ በወህኒ ቤት ጨመራቸው።
የሚሔድበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወሰዳቸው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው በሚያሠቃያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ያጸናቸውና ቁስላቸውን ይፈውስ ነበር።
ከዚህም በኃላ ፃ ወደሚባል አገር ወሰዳቸው። በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙዎች አማንያንንም ሰብስቦ ስለ አምልኮ ጣዖት የሚያዝዝ የከሃዲውን ንጉሥ ደብዳቤ አነበበላቸው። ይህም ቅዱስ ወርስኖፋ ተነሥቶ ያቺን ደብዳቤ ከአንባቢው እጅ ነጥቆ ቀደዳት መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እሳትንም እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ። ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን በእሳቱ እቶን ውስጥ ፈጸመ።
እነዚህንም ሁለት ወንድሞች ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዝዞ ቆረጧቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
† ሐምሌ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት
3.እጨጌ አባ ዮሐንስ (ዘጐንድ)
† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4😍4😘4🥰2🕊2
#ሐምሌ_29
Aug 04, 2026#ሐምሌ_29
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን #አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፣ #የቅዱስ_ሐዋርያ_ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ #ቅዱስ_ወርስኖፋ በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#እጨጌ_አባ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ (ዘጐንድ)
ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ ‹‹በምን አውቀኸኝ ነው?›› ብላ አቅፋ ሳመችውና ‹‹ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ…›› ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡
ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በድብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡
ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡
አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡ ከዚኽም በኋላ ‹‹ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸው?›› ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም ‹‹አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?›› አሏት እርሷም ‹‹አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው ‹‹በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ›› ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ ‹‹የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣ የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ›› ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡
አቡነ ዩሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም መቋሚያቸው በመዳበስ በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዩሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15 ነቢያት፣ ከ12 ሐዋሪያት፣ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ‹‹ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡ በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…›› የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኃላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ቅዱስ አባታችንም በ500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡
አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው ‹‹በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም›› አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ134 ዓመት በኃላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡
ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ግማሽ ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው አርባ ሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል-ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ ነበር፡፡
😘5❤3🥰2🕊2😍2
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Aug 04, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
🥰1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Aug 04, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤4😍4🥰3😘3
💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
Aug 04, 2026💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹የአበባ ምልክቱን ሲጫኑ ከታች ያሉትን ጠቃሚ ነገሮች ያገኛሉ ይቀላቀሉ 👇👇
😘7❤3😍3🥰2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Aug 04, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😍5😘3🥰2❤1
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
Aug 04, 2026⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
🔐ከስር ክፈት የሚለውን
በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
................💚💛❤️...............
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
...............💚💛❤️................
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
❤5🥰3😍2😘2
😍❤️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ልዩ መንፈሳዊ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ።
Aug 03, 2026😍❤️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ልዩ መንፈሳዊ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ።
❤️ እዚህ ሲቀላቀሉ፦👇
❤️ ሁሉን በአንድ የያዘ ፤
✅ ሁላችንንም የሚያሳትፍ ፤
😍 በቤተ ክርስቲያን ልጆች የተከፈተ
🤩 የኦርቶዶክሳዊያን ኅብረት ፥
🗣 የቃለ እግዚአብሔር ጉባኤ፤
📣 ወዳጆችዎንም በመጋበዝ
ክርስቲያናዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ።🙏
💠❤️ ኑ እውነትን በፍቅር እንማር! ❤️💠
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+4spyK-uT0MkyZmZk
https://t.me/+4spyK-uT0MkyZmZk
❤️❤️❤️💠💠💠❤️❤️❤️
😍5❤3😘3🥰2
#ሐምሌ_28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ #አቡነ_ፊሊጶስ ዕረፍታቸው ነው፣ ክርስቶስን የሚወዱ #የቅዱስ_እንድራኒቆስና የሚስቱ #የቅድስት_አትናስያ መታሰቢያቸው ነ…
Aug 03, 2026#ሐምሌ_28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ #አቡነ_ፊሊጶስ ዕረፍታቸው ነው፣ ክርስቶስን የሚወዱ #የቅዱስ_እንድራኒቆስና የሚስቱ #የቅድስት_አትናስያ መታሰቢያቸው ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ፊልዾስ_ጻድቅ (ዘደብረ ሊባኖስ) ሐምሌ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሊጶስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የደብረ…
🥰10😍5😘4❤3
ነበር፡፡ አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነፅርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፡- ‹‹እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣…
Aug 03, 2026ነበር፡፡ አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነፅርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፡- ‹‹እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣ ሐሰተኞችና ዋዛ ፈዛዛ የሚወዱትን ደጋጎች የሚያደርጉ ሰዎች ይመጣሉ፡፡
በመጨረሻው ዘመን ኃጥአን በጻድቃን ይመሰላሉ፣ ጻድቃንን ኃጢአተኞች ያደርጓቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን እውነተኛዎቹ መምህራን አይሾሙም፣ ኃጢአተኞች መማለጃ ሰጥተው ወሬ እያቀበሉ ይሾማሉ፣ እንደ እባብ ክፉ ነገርን ለማድረግ ፍላፃቸውን ያሾሉ ደጋግ ሰዎችን በነገር ያጠፏቸው ዘንድ በእውነት ንጹሕ የሆኑትን ሰዎች አመፅን በተመላ አንደበታቸው ሹመትን ከመውደድ የተነሣ በቅናት ያጠፏቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን መጻሕፍትን የሚያውቁ አይሾሙም፣ ነገርን የሚያመላልሱና የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቁ ከመኳንንትና ከነገሥታት ዘንድ ሔደው ነገርን የሚሠሩ ሰውን የሚያጣሉ በአመፅ ሹመትን የሚያገኙ ብቻቸውን ይሾማሉ እንጂ ደጋጎች አይሾሙም፡፡ በሚመረጡበትም ጊዜ ከአባታቸው ከሰይጣን ጋር ሆነው ‹እገሌ መጻሕፍትን ያውቃል፣ የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቅ ይሾም› ይላሉ፡፡ ያንጊዜም አመፅ ይበዛል፣ ፍቅርም ትጎድላለች፡፡ ከእኔ በኋላ የሚሆነውን እነሆ ነገርኳችሁ ይህንንም አውቃችሁ በልቡናችሁ ያዙ፡፡››
ጌታችን ለአቡነ ፊሊጶስ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- ‹‹ገድልህንና ስለ እኔ የታገስከካቸውን መከራዎችህን የጻፈውን ከሁላቸው ከቅዱሳንና ከሰማዕታት ጋር በሰማያዊት ኢየሩሳሌም በወርቀ ቀለም ለዘለዓለሙ ስሙን እጽፍልሃለሁ፡፡ ሥጋህ ከተቀበረበት ቦታ ይቅርታዬንና ቸርነቴን አደርጋለሁ፡፡ መቃብርህ የበረከት ቦታ ትሆናለች፡፡››
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ጻድቃን_እንድራኒቆስና_አትናስያ
በዚህች ቀን ክርስቶስን የሚወዱ የእንድራኒቆስና የሚስቱ የአትናስያ መታሰቢያቸው ነው። እነርሱም ከአንጾኪያ ከተማ ነበሩ። በወርቅና በብርም የከበሩ ባለጸጎች ነበሩ ከገንዘባቸውም ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር።
ከዚህም በኃላ አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅን ወለዱ ወንዱን ዮሐንስ ሴቲቱንም ማርያም ብለው ሰየሟቸው ልጆችም አደጉ እንዱራኒቅስና ሚስቱም እንግዳ በመቀበል ለድኆችና ለምስኪኖች በመመጽወት በጎ ሥራን አበዙ እነርሱም መገናኘትን ትተው ሰውነታቸውን በንጽሕና ጠበቁ።
ልጆቻቸውም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆናቸው ጊዜ የሆድ ዝማ በሽታ ታመው በአንዲት ቀንም ሞቱ እንዲራኒቆስም አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ራሱን ጥሎ እንዲህ ብሎ አለቀሰ ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ወጣሁ ወደ እግዚአብሔርም ራቁቴን እሔዳለሁ እርሱም ሰጠ እርሱም ወሰደ የእግዚአብሔር የጌትነቱ ስም የተባረከ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
እናታቸውም ለሞት እስከምትደርስ እጅግ አዘነች ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ወደ ዐፀደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ከኀዘንዋም ብዛት የተነሳ አንቀላፋች በእንቅልፏም ውስጥ በልጆችሽ ሞተ አታልቅሺ እነርሱ ግን በሰማያት ደስ እያላቸው ናቸው እያለ በመነኰስ አምሳል ሲነግራት አየች። ይህንንም ሰምታ ሒዳ ለባሏ ነገረችው።
ከዚህም በኃላ ይህን ዓለም ይተዉ ዘንድ ተስማሙ ገንዘባቸውንም ሁሉ ምንም ሳያስቀሩ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጡ በሌሊትም ወጥተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ደረሱ ሚስቱንም በዚያ ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ። ከዚያም ተመልሶ ሚስቱ አትናስያን ወደ ሴቶች ደናግል ገዳም ወሰዳት በዚያም ተዋት።
ከዐሥራ ሁለት ዓመትም በኃላ እንድራኒቆስ ከቅዱሳት መካናት ይባረክ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ አባ ዳንኤልን ለመነው ፈቀደለትም በመድኃኒታችንም ቸርነት ሚስቱ አትናስያ በወንድ አምሳል በጉዞ ላይ ተገናኘችው ሚስቱ እንደሆነችም አለወቀም እርሷ ግን አወቀችው ነገር ግን ሚስቱ እንደሆነች አልገለጠችለትም።
ወደ ቅዱሳት መካናትም በደረሱ ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አባ ዳንኤል በአንድነት ተመለሱ። አባ ዳንኤልም ሚስቱ እንደሆነች በመንፈስ ቅዱስ አውቆ እንድራኒቆስን ባልንጀራ ካደረግኸው ከዚህ መነኰስ ጋራ በአንድ ቦታ ኑሩ እርሱ ቅዱስ ነውና አለው። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በአንድነት ኖሩ ማንም የአወቀ አልነበረም።
አባ ዳንኤልም ይጎበኛቸውና ስለ ነፍሳቸው ጥቅም ያስተምራቸው ነበር። ከዚህም በኃላ አትናስያ በታመመች ጊዜ ለእንድራኒቆስ አባታችንን አባ ዳንኤልን ጥራልኝ አለችው ሒዶም ለአባ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ነገረው ባልንጀራዬ ታሞ ለመሞት ተቃርቧልና ትጎበኘው ዘንድ ና። በደረሰም ጊዜ በታላቅ ሕመም ላይ አገኛት እርሷም ታቆርበኝ ዘንድ እሻለሁ አለችው ያን ጊዜም ተፋጠነና ሥጋውንና ደሙን አቀበላት ከዚህም በኃላ አረፈች በሚገንዟትም ጊዜ ሴት እንደሆነች አገኙ ዳግመኛም ታሪኳንና ለባሏ የረወቻቸውን ምልክቶች አገኙ።
እንድራኒቆስም በአነበበ ጊዜ እርሷ ሚስቱ እንደሆነች አወቀ ደንግጦም ልቡ ተሠወረ ፊቱንም እየጻፈ ጮኸ ያለቅስ ጀመረ።ከጥቂት ቀን በኃላም ታመመ አረጋውያንም መጥተው በረከቱን ተቀበሉ ሥጋውንና ደሙንም ተቀበሉ በሰላም አረፈ።
=>ሐምሌ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ጻድቃን እንድራኒቆስና አትናስያ
2.አቡነ ፊልዾስ ጻድቅ (ዘደብረ ሊባኖስ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
🥰9❤3😘3😍2💯2
#ሐምሌ_28
Aug 03, 2026#ሐምሌ_28
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ #አቡነ_ፊሊጶስ ዕረፍታቸው ነው፣ ክርስቶስን የሚወዱ #የቅዱስ_እንድራኒቆስና የሚስቱ #የቅድስት_አትናስያ መታሰቢያቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ፊልዾስ_ጻድቅ (ዘደብረ ሊባኖስ)
ሐምሌ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሊጶስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሊጶስ፡- በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኩሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡
አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- ‹‹ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ ‹ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?› አሉት፡፡ እርሱም ‹ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ› አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ ‹አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ› አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡
አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም ‹ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?› አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም ‹ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት ‹ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል› ብሎኛል› ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር፡፡››
ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኮሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ ‹‹ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኩስና ይገባዋል›› አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኩስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡ በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡
አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ ‹‹ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች›› ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 አንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡
የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ ‹ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት› ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን ‹‹ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው›› ብለው መክረውት ‹‹እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት›› ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡
በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው ‹‹ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም›› ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ ‹‹ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ›› ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡
አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ ሰላማን በአቃሊት ቅበረኝ ብለዋቸው በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ አቃሊት ወሰዷቸው፤ እዚያም ሐምሌ 28 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ አጽማቸውም ከተቀበረ ከ140 ዓመት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ በክብር መጥቶ ዐርፏል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰባት አክሊላት አቀዳጅቷቸዋል፡፡
ስለ አሁኑ ዘመን የአቡነ ፊሊጶስ ትንቢት!፡- በወቅቱ የነበሩት ጳጳስ አባ ያዕቆብ በብዙ ልመናና ምክር አቡነ ፊሊጶስን ጳጳሱ ራሱ የሚለብሰውን የክብር ልብስ አልብሶ በሸዋ አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው፡፡ ከተሾሙም በኋላ አቡነ ፊሊጶስን ‹ሌሎችን ሹምልን› የሚሉ በርካቶች ሲያስቸግሯቸው እሳቸው የሰጡት ምላሽ ‹‹በሥልጣን ፍለጋ ምክንያት ይህችን የትርህምትና የፅሙናን ቦታ (ደብረ ሊባኖስን) የጨዋታ የተድላ ቦታ እናደርጋታለን›› በማለት በወቅቱ ማንንም አልሾምም ብለው
😘7😍4❤3🥰2🕊2
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Aug 03, 2026✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
💒 የኦርቶዶክስ ቻናል
❤4🥰3😘3
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
Aug 03, 2026💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤6🥰3😍2😘2
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Aug 03, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😘5🥰4❤3😍1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Aug 03, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😍5❤3🥰2😘2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 02, 2026#ሐምሌ_27
Aug 02, 2026#ሐምሌ_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አሞን በሰማዕትነት ዐረፈ፣ ኢትዮጵያዊቷ #ቅድስት_መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፣ የአዳም ልጅ #ቅዱስ_ሴት ዕረፍቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_አሞን
ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ አሞን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ተርኑጥ ከሚባል አገር የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡ ወደ ላይኛው ግብጽ በሄደ ጊዜ የእንዴናው ገዥ ሰማዕታትን ይዞ በጽኑ ሲያሠቃያቸው ተመለከተ፡፡ እርሱም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው፡፡ ሥጋውን ሁሉ ሰነጣጥቆ ከጣለው በኋላ ዳግመኛ በትላልቅ ችንካሮች ቸነከረው፡፡ ነገር ግን ጌታችን አጽናንቶ ከቁስሉ ፈውሶ ጤነኛ አደርጎ አስነሣው፡፡
መኮንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ቅዱስ አሞንን ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው፡፡ በዚያም ሳለ ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራና ገድሉን ለሚጽፍ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃልከዳን ከገባለት በኋላ ሰማዕትነቱን በድል እንዲፈጽም ነገረው፡፡
ወዲያውም ይዘው ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ሥቃዮች አሠቃዩት፡፡ ጌታችንም ከመከራው እያዳነው ልዩ ልዩ ተአምራትን ስላደረገለት ይህንን ያዩ ብዙዎች ‹‹በቅዱስ አሞን አምላክ አምነናል›› እያሉ በመመስከር ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡ እነርሱም ውስጥ ቲዮጲላ የምትባል ድንግል ነበረች፡፡ እርሷም ወደ መኮንኑ ዘንድ በመሄድ በጌታችን ታመነች፡፡ መኮንኑም እቶን እሳት ውስጥ ከተታት ነገር ግን እሳቱ አላቃጠላትም፡፡ በመጨረሻም ራሷን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች፡፡
ከዚህም በኋላ አባለ ዘሩንና አካሉን ሁሉ በሰይፍ እየቆረጡ ቅዱስ አሞንን እጅግ ካሠቃዩት በኋላ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_መስቀል_ክብራ
በዚህችም ቀን ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው፡፡ የታላቁ ጻድቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ሚስት ናት፡፡ ከእርሱም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች፡፡ ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡
ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡
ቅድስት መስቀል ክብራን ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡
ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡
ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሴት_ነቢይ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የአዳም ልጅ ሴት ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፡፡ ሔኖስንም ወለደው፡፡ ሔኖስንም ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፡፡ መላ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡
† ሐምሌ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሴት ነቢይ (ወልደ አዳም)
2.ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ቅዳሴ ቤቱ)
4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት
† ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘4❤3😍3🕊2🥰1
ሐምሌ 26 እንኳን ለጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ በዓለ እረፍቱ አደረሳችሁ።
Aug 01, 2026ሐምሌ 26 እንኳን ለጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ በዓለ እረፍቱ አደረሳችሁ።
ቅዱስ ዮሴፍ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአይኖቹ አየው በእጆቹም አቀፈው በትከሻውም ተሸከመው በከንፈሮቹም ሳመው በምድርም እንደ አባት አሳደገው በእጁ ሥራው መገበው ስለ እርሱ ስደትን ርሀብን ጥማትን ተቀበለ። ነቢያት እርሱ ያየውን አላዩም ሐዋርያት ከጌታ ቢማሩም ታቅፈው ለማሳደግ አልቻሉም.......ኦ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ክብርህ እንደምን ታላቅ ነው። ጸሎቱ በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
😍6❤3💯3😘3🥰2
ቅዱሳን (Saints)
Aug 01, 2026ለመንግሥተ ሰማያትም ያልታጨ ሰው በዚህ ገዳም ገብቶ አይቀበርም፡፡ ጻድቁ ከዛፉ ላይ ወድቀው ሳለ ጌታችንን እጨብጣለሁ ብለው የዘረጓት እጃቸው እያበራች ኖራለች፡፡ እንደ መብረቅም እየጮኸች ለገዳሙ እንደ ደወል ታገለግል ነበር፡፡ በመጨረሻም…
Aug 01, 2026ለመንግሥተ ሰማያትም ያልታጨ ሰው በዚህ ገዳም ገብቶ አይቀበርም፡፡ ጻድቁ ከዛፉ ላይ ወድቀው ሳለ ጌታችንን እጨብጣለሁ ብለው የዘረጓት እጃቸው እያበራች ኖራለች፡፡ እንደ መብረቅም እየጮኸች ለገዳሙ እንደ ደወል ታገለግል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸውን ሰብስበው ባርከዋቸዋል፡፡ ያ አቡነ ሳሙኤል የባረኩበት ቡራኬም በመጽሐፈ ግንዘት ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሰው ሲሞት ‹‹ቡራኬ ዘአቡነ ሳሙኤል›› ብሎ ካህኑ ይደግማል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በከተማ አካባቢ ግን እየተደረገ አይደለም፡፡ አቡነ ሳሙኤል ብዙዎችን ያመነኮሱ ሲሆን እንደነ አቡነ ተጠምቀ መድኅን፣ አቡነ ዘኢየሱስ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ያሉ ሌሎችንም በርካታ መነኮሳትን አፍርተዋል፡፡
አባታችንን ያመነኮሷቸው አባት አቡነ እንጦንዮስ ሊጠይቋቸው ወደ ደብረ ሃሌሉያ ሄደው ሲመለሱ እንዲላላካቸው አንድ ትንሽ ልጅ ትተውላቸው ተመለሱ፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በጥበብ መንፈሳዊ ኮትኩተው አሳደጉት፡፡
አንድ ቀን ምግባቸው የሚሆን የእንጨት ፍሬዎችን ለመልቀም ከበዓታቸው ሲወጡ ልጃቸው እንዳይደክምባቸው በማሰብ በገዳማቸው ትተውት ለመሄድ አሰቡ፡፡ ብቻውን ስለሆነ አስፈሪ አራዊት እንዳያስደነግጡት በማሰብ ጉድጓድ ቆፍረው በዚያ አኑረውት ሄዱ፡፡ ርቀው ሄደው የእንጨቶችን ፍሬ ሲለቅሙ በጫካው እሳት ተስቶ ገዳማቸውንም ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡ ጻድቁ ስለ ልጃቸው ወደ ፈጣሪያቸው ጸልየው ካበቁ በኋላ ወደ ገዳማቸው ቢሄዱ የልጃቸው የራስ ፀጉር እንኳን ሳትቃጠል በሰላም አገኝተውታል፡፡ ያ ልጅም በኋላ አቡነ ገብረ መስቀል የተባለው ገድለኛ አባት ነው፡፡
† ሐምሌ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ (የድንግል ማርያም ጠባቂ)
3.ቅዱስ አባ ጢሞቴዎስ (ዘአልቦ ጥሪት)
4.አባ ሮዲስ
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😍4😘4❤3🥰2🕊1
#ሐምሌ_26
Aug 01, 2026#ሐምሌ_26
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ስድስት በዚች ቀን የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን የተገባው #ጻድቁ_ዮሴፍ አረፈ፣ ለኢትዮጵያ ሀገር ብርሃንን የገለጠ ቅዱስ አባት #አባ_ሰላማ አረፈ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ጢሞቴዎስ አረፈ፣ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቁ_ዮሴፍ
ሐምሌ ሃያ ስድስት በዚች ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ጻድቁ ዮሴፍ አረፈ።
እርሱም እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ጠርቶ ተሰናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ።
በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት። ዕረፍቱም ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ በዐሥራ ስድስት ዓመት ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ሰላማ_ከሳቴ_ብርሃን
በዚችም ቀን ለኢትዮጵያ ሀገር ብርሃንን የገለጠ ቅዱስ አባት አባ ሰላማ አረፈ። ዜናውም እንዲህ ነው ስሙ ሜሮጵዮስ የሚባል የጥበበኞች አለቃ አንድ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ ከእርሱም ጋራ ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ። በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ።
ከዚህም በኃላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኙዋቸው ወደ ንጉሥም ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት ንጉሡም ተቀበላቸው።
ከጥቂት ቀኖች በኃላም ንጉሡ ኤዴስዮስን በፊቱ የሚቆም ጋሻ ዣግሬ አድርጎ ሾመው ፍሬምናጦስን ግን በገንዘቡ ሁሉ ላይ በጅሮንድ አድርጎ ሾመው ይህም ንጉሥ የአብርሀና የአጽብሐ አባታቸው ስሙ አይዛና የተባለው ነበር። እነርሱ ሕፃናት ሳሉም አረፈ። እኒህም አካለ መጠን እስከሚያደርሱ ድረስ የንጉሡን ልጆች እያሳደጉ ኖሩ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ማመንንም አስተማሩዋቸው።
የንጉሡም ልጆች አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ ፍሬምናጦስ ግን ወደ ግብጽ ሔደ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ደረሰ። የደረሰብትንም ሁሉ ነገረው።ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ ግድ አለው። ጵጵስነትንም ሾመ ከታላቅ አክብሮት ጋራ ላከው በአብርሀና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥትም ወደ ኢትዮጵያ በደረሰ ጊዜ በክብር ተቀበሉት።
በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ ስለዚህም ብርሃንን ገላጭ ሰላማ ተባለ ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጢሞቴዎስ
በዚችም ቀን ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ቁጥር ውስጥ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጢሞቴዎስ አረፈ። በተሾመ ጊዜም የክርስቶስን መንጋዎች ከአርዮስ ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ተኩላዎች ጠበቀ።
ይህም አባት በተሾመ በስድስተኛው ዓመት ለክርስቲያን ወገኖች ደግ የሆነ ቴዎዶስዮስ ነገሠ በዚያችም ዓመት ክብር ይግባውና መንፈስ ቅዱስን ስለ ካደው ስለ መቅዶንዮስ በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡ የመቶ ሃምሳ ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ተደረገ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ሊቀ ጉባኤ ሆኖ መቅዶንዮስንና ሰባልዮስን አቡሊናርዮስንም ተከራከራቸው። ረትቶም አሳፈራቸው። እነሆ የክህደታቸውንና የክርክራቸውንም ነገር የካቲት አንድ ቀን ላይ ጽፈናል።
ከዚህም በኃላ ይህ አባት በሹመቱ ዘመን አብያተ ክርስቲያናትን በማነፅና በሚገባውም ሥራ ሁሉ በእድሳታቸውም አሰበ። ለመጻተኞችም ቤቶችን ሠራላቸው።
መንጋዎቹንም ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር በመልካም እውቀቱና በትምህርቱ ጣዕም ሁልጊዜም በማስረዳቱ በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከአርዮስና ከመቅዶንዮስ ወገኖችም ብዙዎቹን መልሶ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።
በወንጌላዊው ማርቆስ መንበርም ላይ ዘጠኝ ዓመት ተኩል ኖረ ከዚያም በኃላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ
በዚህችም ቀን አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ሃሌሉያ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ተንቤን ነው፡፡ አባታቸው ይስሐለነ እግዚእ እናታቸው ትቀድሰነ ማርያም ይባላሉ፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ አጎታቸው ናቸው፡፡ እናታቸው እሳቸውን ፀንሳ ሳለ ቡራኬ ለመቀበል ወደ ወንድሟ ስትሄድ አቡነ አቢየ እግዚእ መሬት ላይ ወድቀው ሰግደውላታል፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ‹‹ለዚህች ሴት እንዴት ሰገዱላት?›› ብለው ቢጠይቋቸው አቡነ አቢየ እግዚእ ስለ አቡነ ሳሙኤል ክብርና ጽድቅ ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡
አቡነ ሳሙኤል ሲወለዱ እናታቸው ለአቡነ አቢየ እግዚእ ሰጠቻቸው፣ እርሳቸውም በሃይማኖት በመግባር ኮትኩተው ሁሉን አስተምረው አሳደጓቸው፡፡ አባታችን የጻድቃንና የሰማዕታትን ታሪክ እያነበቡ ያዝኑና ያለቅሱ ነበር፡፡ እንደ እነርሱ በሆንኩም እያሉ ይመኙ ነበር፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ ሀሳባቸውን በመንፈስ ተረድተውላቸው ነበርና መርቀው ባርከው አሰናበቷቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በሕፃንነታቸው መንነው ወደ አቡነ እንጦንዮስ ገዳም ገብተው በ14 ዓመታቸው መነኮሱ፡፡
ከየት እንደመጣ የማይታወቅና መላ አካሉ እንደበረዶ ነጭ የሆነ አንበሳ መጥቶ እየመራቸው አሁን ደብረ ሃሌሉያ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳማቸው ሄደው በዓታቸውን አጽንተው ገዳሙን መሠረቱት፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘሀለሎም እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
ጻድቁ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ነበር፡፡ እንዲሁ አድርገው ዛፍ ላይ ራሳቸውን ሰቅለው 40 ቀንና 40 ሌሊት ሲጸልዩ በመጨረሻ የታሠሩበት ፀጉራቸው ተነቅሎ ከመሬት ላይ ወደቁ፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን አስከትሎ ተገልጦላቸው እጃቸውን ይዞ አንሥቷቸዋል፡፡ ‹‹ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› ቢላቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ይልቁንም በዚህ በቆረቆሩት ገዳማቸው የሚኖሩትን ልጆቻቸውን እንዲጠብቅላቸው ለመኑት፡፡ ጌታችንም በገዳማቸው ውስጥ በፍጹም ሕማም፣ ደዌና ተስቦ በሽታ እንደማይገባ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
❤6🥰4😘3😍2🕊1
✝እንኳን አደረሰን!
Jul 31, 2026✝እንኳን አደረሰን!
✨በዓለ ልደቱ ወቅዳሴ ቤቱ
ለማር መርቆሬዎስ፤ መፍቀሬ አብ።
✨ሰላም ለኅሊናከ ዘኢየአምር ቅያሜ፤
....
ኦ! በኅሊናህ ቂም በቀል የሌለብህ!
መዓዛህ እንደ ጣፋጭ ሽቱ የሆነ!
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ (ከሃዲዎች) እንደ ደመና የበተኑህ!
የተጋድሎ ምስክርነትን የፈጸምህ!
ኦ! መርቆሬዎስ ዘሮሜ! (አርኬ)
(በከመ ልማድከ ፍጡነ ተራድአነ) እንደልማድህ ፈጥነህ እርዳን!
❤5🥰4😘3😍2
✝እንኳን አደረሳችሁ !
Jul 31, 2026✝እንኳን አደረሳችሁ !
✝ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ መርቆሬዎስ ዘሮሜ፤
ዱማድዮስ ወአበከረዙን በመቅደሰ አምላክ ቀዋሜ፤
ሕጻን ሞዐ ወሄኖክ በዓለ ረቂቅ ትርጓሜ፤
ይስሐቅ ወእንዲኒና ዘዝብጠትክሙ ማሕመሜ፤
ሙጊ ወኢላርያ ብእሲተ ፍቅር ወሱላሜ፤
ወቴክላ ለጣዕመ ዜናኪ ዘአልቦ ፍጻሜ!
(አርኬ ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
🥰4❤2😍2😘2🕊1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 31, 2026በሲኦል ያየችውን ሁሉ ነገረቻቸው ከጭፍሮቹ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት ነፍስ ነበር።
Jul 31, 2026በሲኦል ያየችውን ሁሉ ነገረቻቸው ከጭፍሮቹ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት ነፍስ ነበር።
ከዚህ በኋላ አባ አበከረዙንን ወደ እስክንድርያ ሰደደው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ዳግመኛ ወደ ገምኑዲ ላኩት በዚያም በብረት በትሮች ደብድበው የጀርባውን አጥንት ሰበሩት እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ዳነ።
መኰንኑም ማሰቃየት በደከመ ጊዜ ዳግመኛ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ወደ እስክንድርያም በሚያዚያ ወር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና አጽናናው ገድሉንም በዚያ እንደሚፈጽም ነገረው።
ስሙን ለሚጠራ ሁሉ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ኃጥያቱን እንደሚያስተሠርይለት ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኃላ ራሱን ቆረጡት ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።
የእግዚአብሔር መልአክም መኑፍ ከሚባል አገር ለአንድ ቄስ ተገልጦ የቅዱስ አበከረዙን ሥጋ ያለበትን ቦታ ነገረውና እንዲወስደው አዘዘ። እርሱም ወስዶ ባማሩ ልብሶች ገነዘው የመከራውም ወራት እስከሚፈጸም በመልካም ቤት አኖረው ከዚህም በኋላ ቦታ ክርስቲያን ሰርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሰማዕት_ዱማድዮስ
ዳግመኛም በዚች ቀን የሶርያ ሰው ቅዱስ ሰማዕት ዱማድዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ በፋርስ አገር አደገ የከዋክትን ምግብን ጥበብ ተማረ ከዚህም በኋላ ክርስርስቲያን ሊሆን ወደደ ከፋርስ ሰዎችም ስሙ አጋሊዮስ የሚባል ቄስ በገበያ ውስጥ አገኘ እርሱም ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ሃይማኖትን አስተማረው እጅግ ደስ ብሎት ቤተሰቦቹን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ያስተምራቸው ጀመረ አሳመናቸውም።
ከዚህም በኋላ በሶሪያና በሮም መካከል ወዳለች አገር ሔደ በዚያም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቆ መነኮሰ ታላቅ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ መነኰሳቱም ታላቅ የሆነ ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ በእርሱ ላይ ቀንተው ከገዳም ሊያሳድዱት ወደዱ።
በአወቀም ጊዜም ወጥቶ ወደ ቅዱስ ሰርጊዮስ ገዳም ሔደ በዚያም በአንድ ባህታዊ ቄስ ዘንድ ተቀመጠ ከዚህም በኋላ ዲቁና እንዲሾመውና ከእርሱ ጋር በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል ቅዱስ ዲማድዮስን አስገደደው ትዛዙንም መተላለፍ ባልተቻለው ጊዜ ዲቁና ተሾመ።
አረጋዊው ቄስ በመሰዊያው ላይ በሚሰየም ጊዜ በቅዳሴው እኩሌታ በምሥዋቱ ላይ ርግብ ስትወርድ ቀዱስ ዱማድዮስ ያያት ነበር እርሱም ሥጋዊት ርግብ እንደሆነች ያስብ ነበር ሽማግሌው ግን አያያትም ነበር የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ባሕታዊው ቄስ እንዲህ ብሎ ጠየቀው በቅዳሴ ጊዜ የምትደነግጥ እጅህንም ወደ መሥዋቱ የምትዘረጋው ምን ሆነህ ነው እርሱም ርግቧን እንዳያት ነገረው ከእንግዲህ ስታያት ንገረኝ አለው።
ከዚያም በኋላ በአያት ጊዜ አባቴ ሆይ ያቺ ርግብ መጣች ብሎ ነገረው ሽማግሌው ግን አላያትምእጅግም አዝኖበእግዚአብሔር ፊት ሰገደ ያቺንም ርግብ እስከሚያያት ድረስ ፈጽሞ ይጸልይና ይማልድ ነበር ያቺ ርግብ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና ለዲያቆን አባ ዱማድዮስም ልቡ እንዳይታበይ አልነገረውም።
ከዚህ በኃላም ሽማግሌው ቄስ ወደ ኤጲስቆጶስ ሒዶ ዱማድዮስን የቅስና መዐረግ ይሾምለት ዘንድ ለመነው ልመናውንም ተቀብሎ ያለ ውዴታው ቅስናን ሾመው።
ሊቀ ጳጳሳቱም ዜናውንና ገድሉን በሰማ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወገኖቹን ወሰደ ከወገኖቹ ጋራም ወደርሱ ሔዶ በረከቱን ሊቀበል ወደደ። ቅዱስ ዱማድዮስ ግን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ከዚያ ተሠውሮ ሔደ ወደ ሰማዕቱ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ደረሰ ከዚያም ወደ በረሀ ሔዶ በዚያ ሣር እየበላ ኖረ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ይሸሽ ነበረና።
እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆችንና ተአምራቶችን ያደርግ ነበር። በአንዲት ቀንም ውኃ ሊቀዳ ወደ ወንዝ ሔደ ውኃ የሚቀዱ ሴቶችም አይተውት በመጠቃቀስ በእርሱ ላይ ተዘባበቱ በልቡም እያዘነ ውኃ ሳይቀዳ ተመለሰ ያን ጊዜም ወንዙ ደረቀ።
ሰዎችም ቅዱስ ዱማድዮስ እንዳደረቀው በአወቁ ጊዜ ሴቶችና ወንዶች ሁሉ ወጥተው በብዙ ለቅሶ ለመኑት ልቅሶአቸውንም አይቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው የወንዙንም ውኃ እንደ ቀድሞው መለሰላቸው።
ሰዎችም ሲያከብሩት በአየ ጊዜ ከዚያ መጠለያ ከሰማይ በታች ያለውን የበጋውን ቃጠሎና የክረምቱን ቅዝቃዜ ታግሦ እየተጋደለ ዓመት ሙሉ ኖረ በብዙ ድካምም አስገድደው ትንሽ ጎጆ ሠርተው በውስጧ አስገብት።
ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከእነርሱም አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ ሰው ነበረ ከእርሱም በተባረከ ጊዜ ዐይኑ ድና አየች እንደ ሁለተኛዋም ሆነች ሁለተኛም ጉባጣ ሰው ወደርሱ አመጡ በውኃና በዘይትም ላይ ጸልዮ የመጻጉዑን ሥጋ አጥቦ አዳነው ዲዳውንም እንዲሁ አዳነው።
ከዚህም በኃላ ባልና መካን ሚስቱ መጡ ስለ እነርሱም ይጸልይ ዘንድ ለመኑት እርሱም ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ለምኖላቸው ልጆችን ሰጣቸው ወደርሱም ልጆቻቸውን አምጥተው ባረካቸው። ከዚህም የሚበዛ ብዙ ተአምራትን አደረገ።
በከሀዲው በዋሊጦስ ዘመንም የአምላክ ወዳጅ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ያሠራቸውን አብያተ ክርስቲያናት ጭፍሮቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው አፈረሱ። ከዚህም በኃላ የፋርስ ሰዎች ጦርነት ሊገጥሙት መጡ ሲጓዙም ወደ ቅዱስ ዱማድዮስ ማደሪያ ደረሱ ስለ ርሱም ለመኵንኑ ነገሩት እርሱም ይወግሩት ዘንድ አዘዘ ከረድኡም ጋራ በድንጊያ ወገሩት። የጣሉባቸው ድንጋይም በበዐታቸው ላይ ታላቅ ኮረብታ ሆነ። እርሱና ረድኡም እንዲህ በሆነ ድርጊት አረፉ።
ከአንድ ዓመትም በኃላ ለአንድ መንገደኛ ነጋዴ ሰው ገለጠለት።ገመልም ጭኖ ነበር። እርሱም ሲያልፍ ገመሉ ከምድር በታች በጉድጓድ ውስጥ ወደቀ። ሰዎችም ገመሉን ሊያወጡት በመጡ ጊዜ የቅዱስ ዱማድዮስ በዐት ተገለጠ። ቆፍረውም የቅዱስ ዱማድዮስንና የረድኡን ሥጋ በክብር አወጡ ይኸውም በአረፈበት በሐምሌ ሃያ አምስት ቀን ነበር። ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው የእርሱን ሥጋና የረድኡን ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ጌታችንም ከእርሱ ብዙዎች ተአምራትን ገለጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቅዱስ_ኄኖክ_ነቢይ
በዚችም ቀን አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ በሞት ፋንታ የተሰውረው ነቢዩ ቅዱስ ሄኖክ የዕርገቱ መታሰቢያ በዚህች ዕለት ሆነ፡፡ ዘፍ 5፡21፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም "ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ መስክሮለታልና" በማለት ገልጾታል፡፡ ዕብ 11፡5፡፡
ነቢዩ ሄኖክ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢራትን ያየ ነው፡፡ ስለጌታችንም እንዲህ ብሎ ትንቢትን ተናገረ፡- ‹‹የዘመናት አለቃ ወደሆነው የሰው ልጅ ተጠራ፣ ዓለም ከመፍጠሩ አስቀድሞ የነበረ ሆነ፣ ሁለተኛም ለጻድቃን የጽድቅ በትር ለአሕዛብም ብርሃን ተስፋ ለሌላቸውም አለኝታ ይሆናል›› አለ፡፡ ዳግመኛም ስለምኩራብ ሲናገር ‹‹ያንን አሮጌ ቤት እስኪያሳንሰው ድረስ አየሁ፣ ምሰሶዎቹንም ከውስጡ አውጣ፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ጌታ አዲስ የበጎች ቤት አምጥቶ ሲሠራ አየሁ፣ ከቀድሞውም የበለጠ ነው፣ በጎችም ሁሉ በውስጧ ይሰማራሉ›› አለ፡፡ ስለ ምእመናንም ‹‹የእነዚህ በጎች ፀጉራቸው ንጹሕ ነጭ ነው፣ የተበተኑትም ከአራዊት ጋራ ይሰማራሉ፤ ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ገራሞች ሆነዋል›› አለ፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤4😘3🥰1😍1💯1
በዚህችም ቀን ደግሞ ይስሐቅ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ሳምሳ ከምባል አገር ነበር እሱም የአታክልት ቦታዎች ጠባቅ ነበረ ደግ የዋህና ፁሙድ አገልጋይ ነበረ ሰጋም አይበላም ነበር ወይንም አይጠጣም ነበር በየሁለት ቀን ይፆም ነበረ ቅጠ…
Jul 31, 2026በዚህችም ቀን ደግሞ ይስሐቅ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ሳምሳ ከምባል አገር ነበር እሱም የአታክልት ቦታዎች ጠባቅ ነበረ ደግ የዋህና ፁሙድ አገልጋይ ነበረ ሰጋም አይበላም ነበር ወይንም አይጠጣም ነበር በየሁለት ቀን ይፆም ነበረ ቅጠልም ይበላ ነበረ ድሆችንና ችግረኞችንም ይጎበኛቸው ነበረ ከደመዙም የምተርፈውም ይሰጣቸዋል።
ክብር ይግባውና ጌታችንም በራእይ ተገለጠለትና ወደ መኩንኑም ሒዶ በቅዱስ ስሙ እንዲታመን አዘዘው ከዝህም ቡኃላ ብዙ ቃል ክዳን ሰጠው ያዘጋጀለትንም የደስታ አክልሎችን ተስፍ አስደረገው።
በነቃ ግዜም እጅግ ደስ አለው ተነሥቶም ከእርሱ ያለውን ገንዘብ ለድሆች ሰጠ ከዝያም ቡኃላ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወደ መኩንኑም ደርሶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኩንኑም ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ሰቀለው በመንኩራኲርም አበራየው ጌታችንም ያጸናውና ይፈውሰው ነበር ከመሠቃየቱም የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክልሊ በመንግስተ ሰማያት ተቀበለ።
ከዚህም በኃላ ምእመናን ሰዎች ከሀገሩ ሳምሳ መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችንም ገንዘው የመከራው ዘመን እስክፈጸም ድረስ በመልካም ቦታ አኖሩትከዝያም ቡኃላ ውብ የሆነች ቤተክርስትያን ሠሩለት ሥጋውን በዝያ አኖሩት ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ኢላርያ
ዳግመኛም በዚች ቀን በድሜራ አቅራብያ ድምድል ከሚባል አገር ቅድስት ኢላርያ በሰማዕትነት ሞተች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ደጎች ምእመናን ነበሩ እርሷዋም በስጋዋና በነፍሷ የነጻች ነበረች ሁሉ ጊዜም ተጻምና ትጸልይ ነበረች።
አሥራ አንድ አመትም በሆናት ጊዜ እርሷ ቆማ ስትጸልይ ጌታችን ታላቅ። ብርሃንን ገለጠላት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፍኤልም ተገልጦ እንድህ አላት ተጋድሎ ተዘርግቶ ሳለ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ለምጋደሉም አክልሎች ተዘጋጅተው ሳሉ አንቺ ለምን ከዝህ ተቀምጣሻል አላት።
ይህንንም በሰማች ግዜ ደስ አላት ገንዘቧዋንም ሁሉ ለድኖችና ለችግረኞች ሰጥታ ጣው ወደ ምባል አገር ሔደች ከዝያም ስርስና ወደ ምባል አገር ሒዳ በመኩንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰም ታመነች ጌታችንም ሳኑሲ ለሚባል ሰው ለዝች ቅድስት ከእርሷ የሚሆነውን ነገረው።
ባያትም ጊዜ በእርሷ ደስ አለው አረጋጋት ልቧንም አጸናናት መኩንኑም ታላቅ ሥቃይን አሰቃያት ሥጋዋን ሁሉ ሠነጣጠቀ በእሳት ያጋሏቸውንም የብረት ችንካሮች በሥጋዋ ውስጥ ቸነከሩ።
ከዝህም ቡኃላ ከአምስት መቶ ባልንጀራሞች ሰማዕታት ጋራ አሠራት በመርከቦችም ከእርሱ ጋራ ወስዳቸው እነርሱም በመርከብ ስጓዙ አንበሪ መጥቶ ከእናቱ እቅፍ አንዱን ሕፃን ልጅ ነጥቆ ወሰደ እናቱም ከእርሱ በቀር ሌላ ስለሌላት እጅግ አዝና አለቀሰች ይች ቅድስትም አይታ ራራችላት ስለእርስዋም ጌታችንን ለመነችው ጌታችንም አንበርውን አዘዘውና ሕፃኑን ደኅና እንደሆነ ወደ እናቱ መለሰው ምንም ጥፋት አላገኘውም።
ከዚህም በኃላ ሕዋሳቷን ቆራረጡ የእጆቿንና የእግሮቿን ጥፍሮች ነቀሉ ምላሷንም ቆረጡ እግሮቿንም በብረት ችንካሮች ቸነከሩ። በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው ከበታችዋ እሳትን አነደዱ። ነገር ግን ምንም ምን ጥፋት አልደረሰባትም ክብር ይግባውና ጌታችን አድኗታልና።
መኮንኑም እርሷን ከማሠቃየት የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳት_ቴክላና_ሙጊ
በዚችም ቀን ከእስክንድርያና ከባሕያራ አውራጃ ቀራቁስ ከሚባል መንደር የከበሩ ቴክላና ሙጊ ሰማዕታት ሆኑ። እሊህም ቅዱሳት ቀራቁስ በሚባል መንደር በአንዲት እግዚአብሔርን በምትፈራ አማኒት ሴት ዘንድ አደጉ።
ወደ ባሕር ዳርቻ በአለፉ ጊዜም የክርስቲያን ወገኖችን ሲአሠቃያቸው መኰንኑን አዩት። እነዚያም ደናግል ስለ ልቡ ደንዳናነት አደነቁ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠላቸው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም መከራን ለሚታገሡ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጀውን ክብራቸውን አሳያቸውና አጽናናቸው።
ከዚህም በኃላ በመርከብ ተጭነው ወደ እስክንድርያ ተጓዙ። እመቤታችን ማርያምም አልቃሾች በሆኑ በሁለት ሴቶች አምሳል ከኤልሳቤጥ ጋራ ተገለጸችላቸው ከእርሳቸውም ጋራ ወደ ከተማው በደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመኮንኑ ፊት ታመኑ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው።
ከዚህም በኃላ የቅድስት ሙጊን ራስ በሰይፍ ቆረጠ ተጋድሎዋንም ፈጸመች። ቅድስት ቴክላን ግን ድሙጢ ወደሚባል አገር ላካት በዚያ ሰማዕት ሆነች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አበከረዙን
በዚችም ቀን ዳግመኛ ባንዋን ከሚባል አገር ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ወንበዴ ነበር ሌሎችም ሁለት ወንበዴዎች ነበሩ ገንዘቡን ሊሰርቁ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አንድ መነኩስ በአንድነት ሔዱ በጸሎትም እየተጋ አገኙት ጸሎቱን ጨርሶ እስቲተኛ ድረስ ጠበቁት እርሱ ግን ከቶ አልተኛም በልቡናቸውም ፍርሀት አደረባቸውና ደነገጡ።
በነጋ ጊዜም ያ ሽማግሌ መነኰስ ወደ ሽፍቶቹ ወጣ ባዩትም ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገዱ ሰይፎቻቸውንም በፊቱ ጥለው ደቀ መዝሙሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ለመኑት በርሱም ዘንድ መነኰሱ። ቅዱስ አባ አበከረዙንም በሥጋውም በመንፈሱም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። አንድ አረጋዊም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ እንዳለው ነገረው።
ከሰባት ዓመት በኃላም ሰይጣን በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራን አመጣ አባ አበከረዙንም ተነሥቶ መንፈሳዊ አባቱን እጅ ነሥቶ ከእርሱም ቡራኬ ተቀብሎ ኒቅዮስ ወደሚባል አገር ሔደ ንጉሥ መክስምያኖስንም አገኘው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም በፊቱ ታመነ መኰንኑም በጽኑ ስቃይ አሰቃየው በብረት መጋዝም ስጋውን መገዘው ቁስሉንም በመጣጣና በጨው አሸው።
ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሲወስዱት አምስት ጊዜ በመርከብ ምሰሶ ላይ ሰቀሉት ገመዶችም ተበጠሱ ከማስ በተሠራ ጋን ውስጥም አድርገው በባሕር ጣሉት ከእግዚአብሔርም የተላከ መላክ ከባሕር አውጥቶ ወደ ገምኑዲ ከተመሰ እንዲሔድ አዘዘው ብንውም ወደሚባል አገር ደረሰ ስለ አባ አበከረዙንም ጠየቀ እነርሱም አላወቁትም ነበርና ከብዙ ጊዚያትም ጀምሮ ከዚህ ሔዷል ወዴት እንዳለም አናውቅም ወሬውንም አልሰማንም አሉት።
አንዲት ብላቴና ግን አስተውላ አወቀችው ፈራችም ከፍርሀቷም ብዛት የተነሣ ወደቀችና እንስራዋ ተሰበረ እርሷም ሰዎች ይህ አባ አበከረዙን ነው አለቻቸው የአገሩ ሰዋችም ሁሉም ፈጥነው መጥተው ከእርሱ ተባረኩ ደዌ ያለባቸውም ወደርሱ ይመጡ ነበር እርሱም በዘይት ላይ ጸልዮ ሲቀባቸው ወዲያውኑ ይድኑ ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ ገመኑዲ ከተማ ሔደ ከወታደሮቹም አንዱን እኔ ክርስቲያን ነኝና በዚች ከተማ ውስጥ አሥረህ ጎትተኝ አለው እርሱም ወደ መኰንኑ እስከሚአደርሰው እንደ አዘዘው አደረገ መኰንኑም በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው በአፍንጫውና በአፋም ብዙ ደምእየፈሰሰ ዐሥር ቀኖች ኖረ አባ አበከረዙንም የጭፍራ አለቃውን ልጅ ረገማትና ወዲያውኑ ሞተች በመቃብርም ዐሥራ ሁለት ቀኖች ኖረች። ስለ እርሷም አባ አበከረዙንን ለመኑት ክብር ይግባውና ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ያንጊዜም ከሙታን ተለይታ ተነሥታ
🥰7😘4❤1
የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገ…
Jul 31, 2026የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሕጻን_ሞዐ_ዘደብረ_ሊባኖስ
በዚህችም ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ አረፈ። በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡
ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡
ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ቴክላ
በዚህችም ቀን ከኒቆምድያ አገር ሐዋርያዊት ቅድስት ቴክላ አረፈች። ይህችም ቅድስት በቅዱስ ሐዋርያ በጳውሎስ ዘመን ሐዋርያዊት ሆነች። ቅዱስ ጳውሎስም ከአንጾኪያ ከተማ በወጣ ጊዜ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ሔደ በዚያም ስሙ ሰፋሮስ የሚባል ምእመን ሰው ነበረ ቅዱስ ጳውሎስን ወስዶ በቤቱ አኖረው ብዙ አሕዛብም የሐዋርያው የጳውሎስን ትምህርት ይሰሙ ዘንድ በእርሱ ዘንድ ይሰበሰቡ ነበር። ይህች ቅድስት ቴክላም በቤቷ መስኮት ተመለከተች የሐዋርያውንም ትምህርት ሰማች እንዲሁም ትምህርቱን እያዳመጠች ሳትበላና ሳትጠጣ ሦስት ቀኖች ቆየች ትምህርቱም በልቧ አደረ አባትና እናቷ ቤተሰቦቿ ሁሉ አዘኑ። ከምክርዋም እንድትመለስ ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዳትከተል ለመኑዋት ነገር ግን አልሰማቻቸውም።
ሁለተኛም አባቷ ወደ ንጉሡ ሒዶ ሐዋርያው ጳውሎስን ከሰሰው ንጉሡም ወደ እርሱ አስቀርቦ ስለ ሥራው ጠየቀው። ነገር ግን የሚቀጣበት ምክንያትን በላዩ አላገኘም ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዲአሥሩት አዘዘ።
ይህች ቅድስት ቴክላም ልብሶቿንና ጌጦቿን ከላይዋ አስወገደች። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሒዳ ከእግሩ በታች ሰገደች በእርሱም ዘንድ እየተማረች ተቀመጠች። ወላጆቿም በፈለጓት ጊዜ አላገኟትም በሐዋርያው ጳውሎስ ዘንድ እርሷ እንዳለች ሰዎች ነገሩዋቸው በመኰንኑም ዘንድ ከሰሱዋት እርሱም በእሳት እንዲአቃጥሉዋት አዘዘ። እናቷም ስለርሷ ሴቶች ሁሉ እንዲገሠጹና እንዲፈሩ አቃጥሏት እያለች ጮኸች ብዙዎች የከበሩ ሴቶች በሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርት አምነው ነበርና እርሷ ግን በሚአቃጥሏት ጊዜ ልቧን አጽንታ ቅዱስ ጳውሎስን ተመለከተችው።
ዳግመኛም ሲጸልይ ቅዱስ ጳውሎስን አወጡት በላይዋም በመስቀል ምልክት አማተበ። ራሷንም ወደ እሳቱ ምድጃ ወረወረች። ሴቶችም ያለቅሱላት ነበር። ያን ጊዜም እግዚአብሔር ብዙ ዝናብን በረድና መብረቅን ላከ የእሳቱም ምድጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ሆነ ቴክላም ሩጣ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ተሠውሮ ወደ አለበት ቦታ ደረሰች ራሷንም ላጭቶ ትከተለው ዘንድ ለመነችው እንዲሁም አደረገላት።
ወደ አንጾኪያ ከተማም በሔደች ጊዜ ከመኳንንቶች አንዱ ሊአገባት ፈለገ መልኳ እጅግ ውብ ነበረና እርሷም ዘለፈችው ረገመችውም እርሱም በዚያች አገር ገዥ በሆነ በሌላ መኰንን ዘንድ ከሰሳት እርሱም ለአንበሶች እንዲጥሏት አዘዘ። በአንበሶች መካከልም ሁለት መዓልት ሁለት ሌሊት ኖረች እነዚያም አንበሶች እግርዋን ይልሱ ነበር እንጂ ምንም አልከፉባትም።
ከዚህም በኋላ በሁለት በሬዎች መካከል አሥረው በከተማው ውስጥ ሁሉ አስጐተቷት። ነገር ግን ምንም ምን ክፉ ነገር በላይዋ አልደረሰም ከዚያም በኋላ ለቀቁዋት። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሔደች እርሱም አረጋጋት አጽናናትም። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትሰብክ አዘዛት።
ከዚህም በኋላ ቆሎንያ ወደሚባል አገር ሔዳ ሰበከች ከዚያም ወደ አገርዋ ሔዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረች አባትና እናቷንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መለሰቻቸው።
ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም አረፈች። የሐዋርያነት አክሊልንም ተቀበለች። ሥጋዋም በግብጽ ደቡብ ሰንጋር በሚባል አገር እስከ ዛሬ አለ። ከሥጋዋም ብዙ ድንቅና ተአምር ተገለጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_እንዲኒና
በዚህችም ቀን ባና ከሚባል አገር ቅዱስ እንዲኒና በሰማዕትነት አረፈ።ይህም ቅዱስ ጎልማሳ ነበር። ወላጆቹም ከሀገር ሽማግሌዎች የሆኑ ምዕመናን ነበሩ።
ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ። በመኮንኑም ፊት በመቆም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኮንኑም በፍላፃ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት ነገር ግን ከፍላፃዋች ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም።
ከዝህም በኋላ አሥሮ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ከእርሱም ጋር ቅዱስ ቢማኮስና ሌሎች ሁለት ሰማዕታት ነበሩ። የእስክንድርያውም ገዥ አሠራቸው።
ቅዱስ እንዲኒናን ግን በአፍንጫው ብዙ ዳም እስኪፈስ ድረስ ዘቅዝቆ ሰቀለው። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም ብዙ አሠቃየው። ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ፈርማ ወዳሚባል አገር ላከው።
በዚያም በወህኒ ቤት ቅዱስ ሚናስን አገኘውና ደስ አለው። እርስ በርሳቸውም ተፅናኑ። ከዚህም በኋላ መኮንኑ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃየው በእሳት ባጋሉትም መጋዝ ሥጋውን ሰነጥቀው። በብረት ምጣድ ውስጥም አበሰሉት ጌታችንም ያለጉዳት በጤና አስነሣው።
መኮንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንተአምራት የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ። ለበሽተኞችም ፈውስ ተደረገ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ይስሐቅ_ሰማዕት
😘5❤3😍2🥰1🕊1
#ሐምሌ_25
Jul 31, 2026#ሐምሌ_25
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ አምስት በዚች ቀን #የቅዱስ_መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤቱ እና ልደቱ ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ #አባ_ሕፃን_ሞዐ አረፈ፣ #ቅድስት_ቴክላ አረፈች፣ #ቅዱስ_እንዲኒና በሰማዕትነት አረፈ፣ #አባ_ይስሐቅ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅድስት_ኢላርያ ሰማዕት ሆነችች፣ #ቅዱሳት_ቴክላና ሙጊ ሰማዕታት ሆኑ፣ #ቅዱስ_አበከረዙን ሰማዕት ሆነ፣ #ቅዱስ_ዱማድዮስ አረፈ፣ ነቢዩ #ቅዱስ_ሄኖክ የዕርገቱ መታሰቢያ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ
ሐምሌ ሃያ አምስት በዚች ቀን ቁጥር የሌላቸው ተአምራትንና ድንቆችን ባሳየባት በምስር አገር የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ሆነ። ልደቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡
ታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡
ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡
መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች
🥰4😍4❤2😘2🕊1
እንቋዕ አብጽሐክሙ ለበዓለ ቅዱስ አባኖብ ወዮሐንስ ዘክብራን
Jul 30, 2026እንቋዕ አብጽሐክሙ ለበዓለ ቅዱስ አባኖብ ወዮሐንስ ዘክብራን
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘይደምጽ እመብረቅ
ወእምነጐድጓድ ረቂቅ ሰማዕተ አማኑኤል ኖብ ዘትርጓሜ ስምከ ወርቅ እስመ ይቤሉከ ባርከነ እለ እምዓረብ ወሠርቅ ወእለ በስምከ አምኑ ብዙኃን ደቂቅ።
/መልከአ አባኖብ ሰማዕት/
❤7🥰4😍2💯1😘1
✞ ቅድስት ደብረ ሊባኖስ
Jul 30, 2026✞ ቅድስት ደብረ ሊባኖስ
❖በ1523 ዓ/ም በዚሁ ቀን (ሐምሌ 24) ነበር
በሰይጣን መልእክተኛ (በግራኝ አሕመድ) የተቃጠለው፡፡
"" እግዚኦ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቤተ ክርስቲያን፡፡
(አቤቱ የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት አታሳየን፡፡) "
DnYordanos Abebe
😘6😍4❤3🥰3💯1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 30, 2026ከእስክንድርያ እንዲያሳድዷቸው አዘዘ።
Jul 30, 2026ከእስክንድርያ እንዲያሳድዷቸው አዘዘ።
ንጉሡም ይህን አባት እጅግ ወደደው አከበረውም እንደወደደም አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን ይሠራ ዘንድ ፈቀደለት። እርሱም በምስር ሰሜን አልዋህ በሚባል አገር አብያተ ክርስቲያን ሠራ በሹመቱም ዘመን ሌሎች ብዙዎችን ሠራ።
ካደረጋቸው ተአምራቶቹ ሌላው ይህ ነው ሚናስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ሙቶ ከተገነዘ በኋላ በዚህ አባት ጸሎት ተነሣ። የመነሣቱ ምክንያትም እንዲህ ነበር ይህ አባት ስምዖን በመላው አብያተ ክርስቲያናት ንብረት ንዋየ ቅድሳትና አልባሳት ላይ መጋቢ አድርጎ ይጠብቅ ዘንድ ቄሱን ሾመው። ሁልጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በቤትህ ውስጥ አታኑር እያለ ያዝዘው ነበር።
ከዚህም በኋላ ድንገተኛ ደዌ አገኘውና አንደበቱና ጒረሮው ተጣጋ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ስለ አቢያተ ክርስቲያናትም ንብረት ያንን ቄስ ከሞት ያድነው ዘንድ በዚያች ሌሊት እግዚአብሔርን እየለመነ መላዋን ሌሊት ለጸሎት ተጋ።
መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ያ ቄስ ለመሞት እንደተቃረበ ይህ አባት ሰምዖን ሰማ ስለ አቢያተ ክርስቲያናት ነብረት ይጠይቃት ዘንድ አዝዞ ወደ ቄሱ ሚስት ረዳቱን ላከ።
ወደ ቄሱ ቤትም በቀረበ ጊዜ ሰዎች እያለቀሱለት ጩኸታቸውን ሰማ በገባ ጊዜም ሙቶ ልብሰ ተክህኖ መጐናጸፊያ ሲያለብሱት በዐልጋ ላይም ሲያስተኙት ብዙዎችም በዙሪያው ሲያለቅሱ አገኛቸው ያም ረዳቱ የቄሱን በድን ሊሳለም ዘንበል አለ። ያን ጊዜም ያ የሞተው ቄስ ተነሥቶ አቀፈውና የክቡር አባ ስምዖን ፈጣሪ እግዚአብሔር ሕያው ነው አለው። ረዳቱም በርታ አትፍራ አለው። ቄሱም በጌታው በአባ ስምዖን ጸሎት አዎ በእውነት ጸናሁ እግዚአብሔር ሕይወትን ሰጥቶ ከሞት አስነሥቶኛልና አለ።
ያን ጊዜም ያ ረዳት ስለ መሞቱ ደንግጠው የነበሩትን ካህናት እነሆ ቄሱ ከሞት ተነሥቷል ብሎ ጠራቸው። ካህናቱና ሕዝቡም ወደርሱ በቀረቡ ጊዜ ቄሱ እንዲህ አላቸው እኔ ሙቼ እንደነበረ ዕወቁ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት አቆሙኝ ከአባት ሐዋርያ ማርቆስ እስከ አባ ይስሐቅ ያሉትን ሁሉንም የጳጳሳት አለቆች ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቁመው አየኋቸው እኔንም ከወንድማችን ከሊቀ ጳጳሳት ስምዖን የአብያተ ክርስቲያናትን ንብረት ለምን ሸሸግህ ብለው ገሠጹኝ። ያን ጊዜም ጌታ ክርስቶስ ይቺን ነፍስ በውጭ ወዳለ ጨለማ ውሰዱአት ብሎ አዘዘ።
ሊወስዱኝም በጐተቱኝ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ዙፋን ፊት የጳጳሳት አለቆች ሰገዱ እንዲህ እያሉም ማለዱ ይህን ሰው አንድ ጊዜ ማረው ንብረታቸውን ስለሚጠብቅላቸው አብያተ ክርስቲያናት ብሎ ወንድማችን ስምዖን ስለ እርሱ እነሆ ቁሞ ይጸልያልና። ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሴን ወደ ሥጋዬ መለሰ እንዲህም አለኝ እነሆ ስለ ምርጦቼና ስለ ወንድማቸው ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስምዖን ማርኩህ አንተም የአብያተ ክርስቲያናትንም ንብረት ግለጥለት። አለዚያ ግን ወደዚህ እመልስሃለሁ የእነዚህንም ልመናቸውን ስለአንተ ሁለተኛ አልቀበልም።
በዚያ የነበሩም ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ይህም ቄስ ይህን ተአምር ለሁሉ እየተናገረ ብዙ ዘመናት ኖረ።
ይህም አባት ስምዖን በበዐቱ ውስጥ በገድል የተጸመደ ሁኖ ኖረ መንጋዎቹንም ያስተምራቸው፣ ይገሥጻቸውና በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
† ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት
3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር)
4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ
5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ)
6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በርከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4🥰3😍3💯1😘1
አባ ዘዮሐንስም በደሴቷ ላይ በጾም በጸሎት ጸንተው ተቀመጡ፣ ትሎችም ሰውነታቸውን እንዲመገቡ ያድርጉ ነበር፡፡ ገብርኤልና መስቀል ክብራ የተባሉትም ደጋግ ባለትዳሮች የሚያስፈልጋቸውን ይወሰዱላቸው ነበርና ባገኙዋቸው ጊዜ ትሎቹን ከሰውነታቸው…
Jul 30, 2026አባ ዘዮሐንስም በደሴቷ ላይ በጾም በጸሎት ጸንተው ተቀመጡ፣ ትሎችም ሰውነታቸውን እንዲመገቡ ያድርጉ ነበር፡፡ ገብርኤልና መስቀል ክብራ የተባሉትም ደጋግ ባለትዳሮች የሚያስፈልጋቸውን ይወሰዱላቸው ነበርና ባገኙዋቸው ጊዜ ትሎቹን ከሰውነታቸው ላይ ሲያራግፉላቸው ‹‹ተዋቸው እኔን ሊመገቡ ተፈቅዶላቸዋል›› አሏቸው፡፡ አባታችን አንድ ቀን የሰው ድምፅ ሰምተው ወደ ውጭ ወጥተው ሲመለከቱ የአካባቢው ሰዎች አንድ ማድጋ ወተት፣ አንድ በግና አንድ ከብት ለዘንዶ ሲገብሩ አይተው ያንን ዘንዶ በሥላሴ ስም በመስቀል ምልክት አማትበው ከሰዎቹ ፊት ገደሉት፡፡ ይህን የሰማውና ሰዎቹን እንዲገብሩ የላካቸው ጃን ቹሐይ የተባለው ጣኦት አምላኪ የአገሩ ሹም ‹‹የማመልከውን ዘንዶ እንዴት ትገድላለህ?›› በማለት እንዲታሰሩ አደረጋቸው፡፡ ንጉሥ ዐምደ ፅዮንም ይህን ሲሰማ ሠራዊቱን ልኮ ያንን ጣኦት አምላኪ የአገሩን ሹም ገድለው አባ ዘዮሐንስ እንዲፈቷቸው አደረገ፡፡
አባ ዘዮሐንስም ወንጌልን እያስተማሩ፣ ሙትን እያስነሱና ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ በደሴቷ ላይ ተወስነው ተቀመጡ፡፡ በደመናም ተጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን አምጥተው በደሴቷ ላይ ክብራን ገብርኤል ገዳምን መሠረቱ፡፡ ደመናም ደሴቷ ላይ ስታደርሳቸው ኤልያስና ዮሐንስ በቀኝ በግራው እየተራዱአቸው እርሳቸው ሠራዒ ቄስ ሆነው ቀደሱ፡፡ ደሴቷንም መጀመሪያ እንደመጡ ባሳረፈቻቸው ገደኛ ሴት ስም ሰየሟት፡፡ ለሴቶች መነኮሳት ከዚያው አጠገብ የሚገኘውን እንጦንስ ገዳምን አድርገው ክብራን ገብርኤልን ለወንዶች ብቻ አደረጓት፡፡
አንድ ቀን አባ ዘዮሐንስ በደብረ ሊባኖስ መሥዋዕት ለማቅረብ እያጠነ ሳለ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌላ ሀገር የመጣ እንግዳ ሰው መስሎ ታየውና ‹ሰላም ለአንተ ይሁን› አለው፡፡ አባታችን ዘዮሐንስም ‹ወንድሜ ሆይ! የእግዚአብሔር ፍቅር አንድነት ከአንተ ጋር ይሁን› አለው፡፡ ‹አንተ እንግዳ ሰው ከየት ሀገር የመጣህ ነህ? ከዚህ በፊት አላውቅህም› አለው፡፡ ጌታችንም ከልቡናው ፍግግ አለና ‹ከእናትህ ማኅፀን ሳትወጣ እኔ አውቅሃለሁ› አለው፡፡ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ያደረገለትን ከመወለዱም አስቀድሞ የሆነውን ሁሉ፣ ከተወለደም በኋላ እስከዚያ ቀን ድረስ ያደረገለትን፣ አባቱንም በአመፀኛው በጎዶልያ እጅ ከመሞት እንዳዳነው፣ እናቱንም ዕቁባቱ ሊያደርጋት እንደነበረ ምሥጢሩንም ሁሉ ነገረው፡፡ ይህንንም ብሎ ዳግመኛ ተነጋገረው፡- ‹ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ዘዮሐንስ ይሁን፣ አንተ የዓለሙ ሁሉ ደስታ ነህና የሚያለቅሱም በአንተ ደስ ይላቸዋል› አለው፡፡›› ‹‹በደመናም ተጭነው ኢየሩሳሌም ደርሰው ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን አምጥተው ክብራን ገብርኤል አስገብተው በዚያም ሲኖሩ በጣም አርጅተው ነበርና ራሳቸውን ወደ ምድር አጎንብሰው ይሄዱ ነበር፡፡
ከዚህም በኋላ ሐምሌ 10 ቀን ለዓርብ አጥቢያ ሲጸልዩና በግንባራቸው ወደ ምድር ሲሰግዱ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ ሚካኤልንና ገብርኤልን አስከትሎ መጥቶ ‹ወዳጄ አባ ዘዮሐንስ ሆይ! ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከበሽታ ወደ ሕይወት፣ ከዚህ ዓለም ዐይን ወዳላየውና ጆሮ ወዳልሰማው ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት አሳርፍህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ› አለው፡፡ ይህንንም ብሎ ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ከእርሱ በረከት እንደማይጠፋ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ ‹ገድልህን የሚጽፍ ወይም የሚያነብ እኔን እንደመሰለ እንደ መልከጼዴቅ ካህን በእኔ ዘንድ የተመረጠና የተወደደ ይሆናል፣ በበዓልህ ማኅሌት የቆመ የመላእክት ባልንጀራ ይሆናል፣ እነዚህን ልጆችህንም የመላእክት አምሳያ አደርጋቸዋለሁ› አለው፡፡ ‹ይህችን ደሴት እንደ ኢየሩሳሌም ሀገሬ፣ እንደ ደብረ ዘይትና ለባሪያዬ ለሙሴ ሕግን እንደ ሰጠሁባት እንደ ደብረ ሲና አድርጌያታለሁ፣ በረከቴም ከእርሷ አይታጣም፣ እኔም ከእርሷ አልለይም ይልቁንም በተጠመቅሁባት ቀን ከዚህች ገዳምህ አልለይም፣ የዚህች ደሴትና የሀገሬ የኢየሩሳሌም መክፈቻ በአንድ ላይ አንድ ይሁን› አለው፡፡ ‹ከዚህች ሀገርም ያለንስሓ የሕፃናትና የጎልማሶች ሞት አይሁን፣ እስከ ዘለዓለምም ድረስ ጸሎት ከእርሷ አይቋረጥ› አለው፡፡
ጌታችንም ለአባ ዘዮሐንስ ይህን ከተናገረው በኋላ ቡራኬ ሰጥቶት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወደቀደመ ቦታው ዐረገ፡፡›› ጻድቁ በ105 ዓመታቸው ሐምሌ 24 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ስምዖን
በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከምሥራቅ አገር ሰዎች ወገን ነው። ወላጆቹም ከእስክንድርያ በስተምዕራብ ወዳለች በውስጧም የቅዱስ ሳዊሮስ ሥጋ ወደ አለባት ገዳም አመጠትና በዚያ መንኵሶ ጽሕፈትን ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ሁሉ አጠና ቅስናም ተሾመ።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። በተሾመ ጊዜም መንፈሳዊ መምህሩ የሊቀ ጵጵስናውን ሥራ አስተማረው በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ። እንጀራና ጨውም አይበላም ነበር ነገር ግን በእሳት ያላበሰሉትን ጎመን ከተልባ ጋራ ይበላ ነበር። እንዲህም አድርጎ ደማዊት ነፍሱን ለነባቢት ነፍሱ አስገዛ።
እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራትን በእጆቹ ላይ አደረገ ከእነዚህም ከእስክንድርያ ካህናት ክፉዎች ሰዎች ቀኑበት ወደመተተኞችም ሒደው ብዙ ገንዘብ ሰጧቸው የሚገድል መርዝንም አዘጋጁለት እሊህ ክፉዎችም ያን መርዝ ወስደው ከሚጠጣው መጠጥ ጋራ በብርሌው ውስጥ ደባለቁት ጠጥቶም ይባርካቸው ዘንድ እንዲጠጣ እየለመኑት ለሊቀ ጳጳሳቱ ሰጡት እርሱም ቅዱስ ቍርባንን ከተቀበለ በኋላ ያንን መርዝ ጠጣው ከክፉም ነገር ምንም ምን አልደረሰበትም ሁለተኛም ሦስተኛም ሰጥተውት ምንም ምን አልጎዳውም ከመዳኑም የተነሣ አደነቁ።
ከዚህም በኋላ ወደ ገበያ ሒደው ሁለት አዳዲስ በለስን ገዙ በውስጡም የሚገድል መርዝን አደረጉ ቅዱስ ቍርባንን ከመቀበሉ በፊት በጾም ሳለ ይሰጡት ዘንድ ተስማሙ መሠርያኖች ይህን በለስ ከቍርባን በፊት ቢበላ ሆዱ ይሠነጠቃል ብለዋቸው ነበርና።
ያን ጊዜም ወደርሱ በተንኮል ሒደው ከዚያ በለስ ይበላ ዘንድ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት አብዝተውም አስገደዱት ከቅዱስ ቍርባን በፊት ሳይፈቅድ በእጁ ውስጥ አደረጉለትና በላ ነገር ግን መሠርያኖች እንዳሉአቸው አልሆነም ሆዱም አልተሠነጠቀም ነገር ግን አርባ ቀን ታመመ።
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና የደዌውን ምክንያት አስረዳው ያንን መርዝ ያደረጉበትንም ስማቸውን ገለጠለት።
በዚያ ወራትም የግብጽ ንጉሥ አብዶ አልዓዚዝ ወደ እስክንድርያ ከተማ መጣ ይህ አባት ሊቀ ጳጳሳት ስምዖንም ሊቀበለው ወጣ ንጉሡም በሊቀ ጳጳሳቱ ፊት ላይ የደዌ ምልክት አይቶ መሳፍንቶቹን መልኩ እንዲህ እስኪለወጥ ድረስ ሊቀ ጳጳሳቱ ምን ደረሰበት ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም ክፉዎች ካህናት በእርሱ ላይ እንዳደረጉበት መርዝንም እንዳበሉት ነገሩት ንጉሡም ተቆጣ ካህናቱንና መሠርያኑንም በእሳት እንዲአቃጥሏቸው አዘዘ ያን ጊዜም ይህ አባት ከንጉሡ እግር በታች ወድቆ ይምራቸው ዘንድ እያለቀሰ ለመነው ንጉሡም አይደለም እንደሚገባቸው ያቃጥሏቸው እንጂ አለው። ይህም አባት ስለእኔ አንተ ከአቃጠልካቸው ለእኔ ክህነትና ሊቀ ጵጵስና አይገባኝም አለው። ንጉሡም ሰምቶ ከየዋህነቱና ከርኅራኄው የተነሣ አደነቀ እነዚያን ካህናትና መሠርዮች
😍5🥰4😘3❤2💯1
#ሐምሌ_24
Jul 30, 2026#ሐምሌ_24
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ አራት በዚች ቀን ከንሒሳ ከተማ #ቅዱስ_አባ_ኖብ ሰማዕት ሆኖ ሞተ፣ ጣና ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት #አቡነ_ዘዮሐንስ_ጻድቅ ዕረፍታቸው ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ስምዖን አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኖብ
ሐምሌ ሃያ አራት በዚች ቀን ከደቡባዊ ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ሆኖ ሞተ።
የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ቅዱሳን ንጹሐንና የሚራሩ ነበሩ። ይህንንም ቅዱስ ኖብን በወለዱት ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆነው ፈሪሀ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጉት። ቤተ ክርስቲያንን የመጻሕፍትን ቃል መስማትንና መማርን የሚወድ ሆነ።
ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የክርስቲያን ወገኖችን ዲዮቅልጥያኖስ በአሠቃያቸው ጊዜ ይህ ቅዱስ ደሙን ስለ ጌታችን ሊአፈስ አሰበ ያን ጊዜም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ ቄሱንም ምእመናንን እንዲህ እያለ ሲያስተምራቸውና ሲያበረታቸው ‘’ጣዖታትን ከምታመልኩ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስለ ክርስቶስ ነፍሳችሁን ለሞት አሳልፋችሁ ብትሰጡ ለእናንተ መልካም ነው’’ ሲላቸው ሰማው።
ይህም ቅዱስ እያዘነና እየተከዘ ወደ ቤቱ ተመለሰ አባቱም የተወለትን ወርቁንና ብሩን ልብሶችን ሁሉ ተመልክቶ እንዲህ አለ ሁሉ ነገር የዚህ ዓለም ፍላጎቱም ሁሉ እንደ ሚያልፍ እነሆ ተጽፏል። ከዚህም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ።
ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ገምኑዲ ሔደ በእግሩም ሲጓዝ በባሕሩ ዳርቻ ሉስዮስ የሚባለውን መኰንን አገኘው በፊቱም ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ። መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት በእርሱ ላይም የሚደርሰውን ሁሉ ነግሮት አጽናናው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ሰሜን አገር ሲጓዝ የከበረ ኖብን ከእርሱ ጋራ በመርከብ ወሰደው በመርከቡም ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው መኰንኑም ሊበላና ሊጠጣ ተቀመጠ በመኰንኑም እጅ የነበረው ጽዋ ወዲያውኑ እንደ ደንጊያ ሆነ የወታደሮቹም ዐይኖቻቸው ታወሩ የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ወርዶ አባ ኖብን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው በአፍንጫውና በአፉ የወረደውንም ደሙን አሻሸለት።
ከዚህ በኋላም መልካም ነፋስ ነፍሶ መርከቢቱ ተጓዘች። ወደ አትሪብ ከተማም ደረሱ ወታደሮችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ትጥቃቸውን ፈተው በመኰንኑ ፊት ጣሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ ሰማዕታትም ሆነው ራሳቸውን ቆረጡአቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
መኰንኑም በአትሪብ ከተማ ቅዱስ አባ ኖብን ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር ከእሳት አዳነው። ከዚህም በኋላ በመጋዝ መገዙት ሕዋሳቱንም ቆራረጡ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ አዳነው ያለ ጉዳትም በጤና አስነሣው።
ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ወሰዱት በዚያም ብዙ አሠቃዩት በላዩም እባቦችን ሰደዱ ግን አልቀረቡትም ከእባቦችም አንዱ ሒዶ በመኰንኑ አንገት ተጠመጠመ ያስጥሉትም ዘንድ ሟርተኞቹን አዘዛቸው ግን አልተቻላቸውም ከዚህም በኋላ ያድነው ዘንድ ቅዱስ አባ ኖብን ለመነው ቅዱሱም ከይሲውን ትቶት ከአንገቱ እንዲወርድ አዘዘው።
መኰንኑም ሁለተኛ በእሳት እንዲአቃጥሉት ሟርተኞችንና ሥራየኞችን አዘዛቸው እሳቱም ምንም አልነካውም። አቅፋሐስ ከሚባል አገርም ዮልዮስ መጣ ከእርሱም እንደ ተረዳ ገድሉን ጻፈ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾለት አጽናናው እንዲህ ብሎም ቃል ኪዳን ሰጠው ሥጋህ በሚኖርበት ቦታ ከእርሱ ታላቅ ፈውስ ይሆናል እንዲሁም በመከራው ጊዜ ስምህን በመጥራት ከእግዚአብሔር ርዳታ ለሚሻ ሁሉ ድኅነት ይደረግለታል። መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማም ለሚያጠጣ፣ ለቤተ ክርስቲያንም በስምህ መባ ለሚሰጠው፣ የገድልህንም መጽሐፍ ለሚጽፍ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ።
ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡ ተጋድሎውንም ፈጸመ ሥጋውንም ቅዱስ ዮልዮሰ አንሥቶ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋራ ንሒሳ ወደ ሚባል አገሩ ላከው። የመከራውም ወራት በተፈጸመ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩለት በውስጣቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ዘዮሐንስ_ጻድቅ_ዘክብራን_ገብርኤል (ኢትዮዽያዊ)
ዳግመኛም በዚህች ቀን ጣና ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት አቡነ ዘዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም አባቱ ዘካርያስና እናቱ ሶፍያ እግዚአብሔርን በማመን የተመሰገኑ ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የሀገር ሰዎችም መክረው ዘካርያስን በእነርሱ ላይ ጌታና ገዥ አደረጉት፡፡ እርሱም በጥሩ አገዛዝ በፍቅር ገዛቸው፡፡ እነርሱም እንደ አሽከሮች ሆኑት፣ እርሱም እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ ለሸዋ ሰዎች እንደ ቸር እረኛ ሆናቸው፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ ሶፍያም በጎ ሥራን ሁሉ አላቋጡም፡፡ ምጽዋትን መስጠትን፣ ከገንዘባቸውም ከፍለው ለእግዚአብሔር አሥራት መስጠትን አላቋረጡም፡፡ የተቸገሩትን፣ የተራቡትንና የተጠሙትን ሁሉ ያበላሉ፣ ያጠጣሉ፡፡ ይህንንም ሲሄዱም ሲመለሱም ሁልጊዜ ያደርጋሉ፡፡
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስንና የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የጻድቃንና የሰማዕታን መታሰቢያም ያድርጋሉ፡፡ ልጅም አልነበራቸውምና ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ይማፀኑ ነበር፡፡ ሶፍያም ጠዋት ማታ እንዲህ እያለች ትጸልይ ነበር፡- ‹መካን ለነበረች ለሐና ልጅ እንደሰጠኻት፣ ለአብርሃም ሚስት ለሣራም፣ ለጸጋ ዘአብ ሚስት እግዚእ ኀረያም እንደሰጠኻቸው አቤቱ እንደ እነርሱ አንተን ደስ የሚያሰኝህን ልጅ ስጠኝ› እያለች እመቤታችንንም እየተማፀነች ታለቅስ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም መጥምቁ ዮሐንስን የመሰለ ልጅ ‹አባ ዘዮሐንስ› የተባለ ቅዱስ ልጅ ሰጣቸው፡፡ እሱም በሸዋ፣ በመራቤቴ እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ የሚያበራ መብራት ሆነ፡፡››
በኋላም በጣና ሐይቅ ላይ የሚገኘውን ‹‹ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን›› የመሠረቱት እኚህ አባ ዘዮሐንስ የተባሉ ጻዲቅ ናቸው፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ታሪካቸውንና የተሰጣቸውን አስደናቂ ቃልኪዳን እንመለከት፡- ለአባ ዘዮሐንስ በጌታ ዘንድ ታዘው ነቢዩ ኤልያስና ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ ሰጥተዋቸዋል፡፡ እመቤታችንም ተገልጣላቸው ወደ ደብረሊ ሊባኖስ ሄደው እንዲመነኩሱ ነግራቸው ኤልያስና ዮሐንስ እየመሩ ከቦታው አድርሰዋቸዋል፡፡ ሰባት ዓመትም በዚያ ሲያገለግሉ ኖሩ፡፡ ስግታቸውም ሁልጊዜ ስምንት ሺህ ነበር፡፡ ጌታም በደብሊባኖስ ሲያጥኑ ተገልጦላቸው ስምህ ‹‹ዘዮሐንስ ይሁን›› ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ተጥቷቸዋል፡፡ ደመናም ተሸክማ ወስዳ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አድርሳቸው በዚያም ከቆዩ በኋላ ደመናዋ መልሳ ወደ ሸዋ አምጥታቸዋለች፡፡ በትግራይ ለራሳቸው መጠለያ ሲሠሩ የጌታ ፈቃድ አልነበረምና ከባድ የሆድ ሕመም መጣባቸው፡፡ ደመናዋም ደራ ሮቢት አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም እንደደረሱ ገብርኤልና መስቀል ክብራ በሚባሉ እግዚአብሔርን በሚወዱ ደጋግ ባለትዳሮች ቤት ዕረፍት አደረጉ፤ ለሰባት ቀናትም በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም መልአኩ ተገልጦ ወደ ደሴቷ እንዲሄዱና እርሷም ዕጣ ክፍላቸው እንደሆነች ነገራቸው፡፡
🥰5😍5❤3😘3💯1
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 30, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😘4❤3😍3🥰1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 30, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
🥰6❤3😘3😍1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 30, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
❤3🥰3😍3😘3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 30, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍5😘3❤2🥰1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 29, 2026#ሐምሌ_23
Jul 29, 2026#ሐምሌ_23
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ሦስት በዚች ቀን #ቅድስት_መሪና ሰማዕት ሆነች፣ #ቅዱስ_ለንጊኖስ ሰማዕት ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_መሪና
ሐምሌ ሃያ ሦስት በዚች ቀን ቅድስት መሪና ሰማዕት ሆነች። የዚችም ቅድስት የአባቷ ስም ዳኬዎስ ነበር እርሱም በአንጾኪያ ሀገር ለጣዖታት ካህናት አለቃ ነበር ያን ጊዜ ንጉሡም ከሀዲው ዳኬዎስ ነበር።
አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ እናቷ ሞተች አባቷም ከከተማ ውጭ ለምትኖር ሞግዚት ሰጣት እርሷም ክርስቲያናዊት ነበረች የክርስቶስ የሆነ የሃይማኖት ትምህርትን ሁሉ አስተማረቻት። ዐሥራ አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ አባቷ ሞተ።
ከዚህም በኋላ ሰዎች የሰማዕታትን ተጋድሏቸውንና መከራቸውን ሲናገሩ ሰምታ የጌታ ክርስቶስ ፍቅር በልቧ አደረ በሰማዕትነት መሞትንም ፈልጋ ሔደች።
በዚያን ጊዜም ከሀዲ መኰንን ወደዚያች አገር ደረሰ እርሷንም አይቶ ወደርሱ አስመጣትና ከወዴት ነሽ አላት ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ሰዎች ወገን ነኝ ስሜም መሪና ነው አለችው። ደም ግባቷንና ላሕይዋንም አይቶ መታገሥ ተሳነው እሺ ትለው ዘንድ በብዙ ነገር አባበላት። እርሷ ግን ረገመችው የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች።
ያን ጊዜም በብረት ዘንጎች ይደበድቧት ዘንድ ደሟ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሕዋሳቷን ይቆራርጡ ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ጸለየች የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳናት። ሁለተኛም ወደ ወህኒ ቤት ያስገቧት ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ወደ ሰማይ አውጥቶ የቅዱሳን ሰማዕታትንና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳይቶ ወደ ቦታዋ መለሳት። በማግሥቱም ሥጋዋን በመጋዝ እንዲሠነጥቁ ጐኖቿንም እንዲሰነጣጥቁና በእሥር ቤት እንዲጥሏት አዘዘ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አዳናት።
በወህኒ ቤቱ ውስጥም ቁማ ስትጸልይ እጅግ የሚያስፈራ ታላቅ ዘንዶ ወደ ርሷ መጣ በአየችውም ጊዜ ደነገጠች ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠ መናገርም ተሳናት። ያን ጊዜም እጆቿ በመስቀል ምልክት አምሳል እንደተዘረጉ በልቧም ስትጸልይ ወደርሷ ቀርቦ ዋጣት። ያን ጊዜም ሆዱ ተሠንጥቆ ያለ ጉዳት ወጣች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው።
ሁለተኛም በጥቁር ሰው አምሳል ሰይጣንን አየችው እጆቹም በጉልበቶቹ ላይ ተጨብጠው ነበር። ፊቷንም በመስቀል ምልክት አማትባ በራሱ ጠጉር ይዛ ደበደበችው። በእግሮቿም ረገጠችው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና የጌታ ክርስቶስ ዕፀ መስቀል ተገለጠላት በላዩም ነጭ ርግብ ተቀምጣ እንዲህ ብላ አነጋገረቻት መሪና ሆይ የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ አረቦን ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ።
በማግሥቱም መኰንኑ ልብሷን አራቁተው ዘቅዝቀው ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ደግሞም ውኃ ከአፈሉበት ጋን ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ። በውስጡም ሁና ስትጸልይ ከሰማይ ርግብ መጣ በአፉም ውስጥ የወርቅ አክሊል ነበር ማሠሪያዋንም ፈትቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሦስት ጊዜ አጠመቃት እግዚአብሔርንም እያመሰገነች ከውኃው ውስጥ ወጣች።
መኰንኑም እንደ ዳነች በአየ ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ወደ ሰማዕትነቱ ቦታም በደረሰች ጊዜ ነፍሷን በፍቅር ይቀበል ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየች። ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገለጠላት ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያዋንም ለሚያደርግ ገድሏንም ለሚጽፍ ወይም ለሚያነበውና ለሚሰማው ኃጢአቱን እንዲአስተሠርይለት ለርሷም ርሱን እንዲሰጣት ቃል ኪዳን ሰጣት።
ከዚህም በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጡ ከእርሷም ብዙ ተአምር ተገለጠ ዕውራን አይተዋልና፣ ሐንካሶች በትክክል ሔደዋልና፣ ደንቆሮዎችም ሰምተዋልና፣ ዲዳዎችም ተናግረዋልና ቁጥር የሌላቸው ብዙ ሰዎችም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ለንጊኖስ_ሰማዕት
በዚችም ቀን ከቀጰዶቅያ አገር ለንጊኖስ ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ ከጲላጦስ ጭፍሮች ውስጥ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ደኅንነት መከራ እንዲቀበል የፈቀደበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ የፈለጉትን ያደርጉ ዘንድ ለዐመፀኞች ፈቅዶላቸው ነበር። ይህም ለንጊኖስ ጌታን ይሰቅሉት ዘንድ ጲላጦስ ከአዘዛቸው ወታደሮች ውስጥ ነበር።
በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ ጌታችንን የቀኝ ጐኑን ወጋው ከጐኑም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ይህንንም አይቶ እጅግ አደነቀ ከዚህም በፊት ፀሐይ እንጨለመ፣ ጨረቃ ደም እንደሆነ፣ ዐለቱም እንደተሠነጠቀ፣ ሙታንም እንደተነሡ አይቶ ነበር።
ጌታችንም በተነሣ ጊዜ ስለ ትንሣኤው የሆነውን ሰምቶ ይህን ምሥጢር ይገልጽለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ሐዋርያው ጴጥሮስንም ላከለት እርሱም ነቢያት ስለ ጌታችን፣ ስለ መከራው፣ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ መሞቱ፣ ስለ መነሣቱ፣ ስለ ዕርገቱም ትንቢት እንደተናገሩ ነገረው። እርሱም ከቅድስት ድንግል በሥጋ ተወልዶ ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆነ አስረዳው።
ያን ጊዜም በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል አመነ የምድራዊ ንጉሥ አገልግሎትንም ትቶ ወደ ቀጰዶቅያ ሔደ በውስጧም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሐዋርያት ሰበከ።
አይሁድም በጠላትነት ተነሡበት በመሳፍንትም ዘንድ ከሰሱት በላዩም የሐሰት ምስክር አስነሡበት ስለዚህም ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
† ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቋ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት)
3.ቅዱስ አብጥልማዎስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘5😍4🥰3❤🔥1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 29, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
😍6😘5🥰2❤1
🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
Jul 29, 2026🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
😍5❤2🥰2😘1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 29, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤6😍3🥰2😘2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 29, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
✝ ንዒ ኀቤነ #ኦ_ድንግል ምስለ #ኤልያስ #ወኤልሳዕ #ነቢያተ_እስራኤል ወምስለ #ዕዝራ #ሱቱኤል ወምስለ #አባ_ጊዮርጊስ ድንግል ጽዋዐ ልቡና ዘአስተዮ #ዑራኤል
Jul 28, 2026✝ ንዒ ኀቤነ #ኦ_ድንግል ምስለ #ኤልያስ #ወኤልሳዕ #ነቢያተ_እስራኤል ወምስለ #ዕዝራ #ሱቱኤል ወምስለ #አባ_ጊዮርጊስ ድንግል ጽዋዐ ልቡና ዘአስተዮ #ዑራኤል
✝️እንኳን አደረሰን!
🥰5😘3❤2😍2🕊1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 28, 2026ምውት ተነሥቶ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የሁሉ ጌታ እንደሆነ ተናገረ።
Jul 28, 2026ምውት ተነሥቶ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የሁሉ ጌታ እንደሆነ ተናገረ።
ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ብዙ አሕዛብ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ መኰንኑም ተቆጥቶ ያመኑትን ራሳቸውን አስቆረጠ ሰማዕታትም ሆነው የሰማዕታትን አክሊል ተቀበሉ። በዚያም የእንዴናው ገዥ አርያኖስ ነበረ በተመለሰ ጊዜም ቅዱስ መቃርስን ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ ሀገረ ሰጥኑፍም በደረሰ ጊዜ መርከቢቱ ቆመች የማትንቀሳቀስም ሆነች እነሆ ጌታችንም ለእርሱ ተገልጦ ተጋድሎውን በዚያ እንደሚፈጽም ነገረው።ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ።
ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖታትን ቤቶች እንዲዘጉ አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲከፍቱ አዘዘ። ያን ጊዜም ስሙ አውሎጊዮስ የሚባል ምእመን መኰንን አብያተ ክርስቲያናትን ሊሠራ ጀመረ። ቅዱስ መቃርስም ተገለጠለትና ሥጋው ያለበትን ነገረው። መኰንኑም ወደ አመለከተው ቦታ ሔዶ የቅዱስ መቃርዮስን ሥጋ አገኘ ከዚያም ወሰደው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረ። ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ለውንትዮስ
በዚህችም ቀን ቅዱስ ለውንትዮስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ክርስቲያን ከሀድያን ከሆኑ ሠራዊት ጋር ይኖር ነበር ሀገሩም ጠራብሎስ ነው መልኩም ያማረ በገድሉም ፍጹም የሆነ ነበር። አምላክ ያስጻፋቸው መጻሕፍትንም ያነብ ነበር።ይልቁንም የዳዊትን መዝሙር ሁልጊዜ ያነብ ነበር። ባልንጀሮቹ ለሆኑ ወታደሮችም ያስተምራቸው ይመክራቸውም ነበር።እግዚአብሔርንም እንዲፈሩ ያስገነዝባቸው ነበር። የማይጠቅሙ የረከሱ የአማልክትንም ሸክም ከትከሻችሁ ጣሉ ይላቸው ነበር። ከስሕተትም ተመልሰው ክብር ይግባውና በጌታችን ያመኑ አሉ። ከእነርሱም ወደ መኰንኑ ሒደው ለውንትዮስ አማልክትን አቃለላቸው ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው ይላል ብለው የከሰሱት አሉ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀርቦ ጠየቀው እርሱ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስን እንደሚያመልከው በመኰንኑ ፊት ታመነ ጳውሎስ ከፈጣሪዬ ከክርስቶስ ማን ይለየኛል እንዳለ ከታናሽነቴ ጀምሮ በፍጹም ልቡናዬ አመልከዋሁ ለእርሱም እሰግዳለሁ አለው። መኰንኑም እጆቹንና እግሮቹን አሥረው በወህኒ ቤት ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። በማግሥቱም መኰንኑ አቅርቦ እንዲህ አለው በምን ኃይል የንጉሥን ትእዛዝ ደፍረህ ትተላለፋለህ ሰዎችንም አማልክትን ከማምለክ በምን ኃይል ትመልሳቸዋለህ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት። በእውነት ሰዎች ሁሉ ክብር ይግባውና ወደጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት እንዲገቡ እኔ እሻለሁ አንተም ስሕተትህን ትተህ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስን ብታመልከው የረከሱ አማልክትንም ማምለክ ብትተው የዘለዓለም መንግሥትን በወረስህ ነበር። ይህንንም በሰማ ጊዜ መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስም ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እርሱም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ያመሰግነው ጀመረ። ከወታደሮችም አንዱ አዘነለትና በጆሮው አሾከሾከ እኔ ስለአንተ አዝናለሁ ጉልምስናህንም ላድን እወዳለሁ አንተ ለአማልክትም እንደምትሠዋ ለመኰንኑ አንዲት ቃልን ብቻ ተናገር እኔም እዋስሃለሁ አለው። ቅዱሱም ሰይጣን ከኋላዬ ሒድ ብሎ ገሠጸው። መኰንኑም ጭካኔውን አይቶ ሥጋው እስከ ሚቆራረጥ ደሙም እንደ ውኃ በምድር ላይ እስኪፈስ ድረስ ሥቃዩን እጥፍ ድርብ አደረገበት። ከዚህም በኋላ በውኃ እንዲዘፍቁት በእግሩም እንዲጐትቱትና በወህኒ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በዚያም ነፍሱን አሳለፈ ገድሉንም ፈጸመ። የምታምን ሀብታም ሴት መጥታ ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥታ የቅዱሱን ሥጋ ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው የወርቅ ሣጥንም አሠርታ በውስጡ አኖረችው። ሥዕሉንም አሣለች በፊቱም ሁልጊዜ የሚያበራ ፋና አኖረች። ለዚችም ሴት ቅዱሱ ያደረገላት የድካም ዋጋዋ ሰኔ አንድ ቀን ተጽፎ አለ።
† ሐምሌ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው)
5.ቅዱስ መርካሎስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ ጳውሊ የዋህ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4😍3😘3🥰2🕊1
በዚያንም ጊዜ በዚያች ጉዳና ሊጓዙ የሚሹ የዓረብ ሰዋችን አያቸው ወደ እርሳቸውም ሒዶ አብረሮአቸው ይሔድ ዘንድ ለመናቸው እነርሱም በደስታ ተቀበሉት ወደ አንድ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ እስከሚደርስ የሦስት ቀን ጉዳና ተጓዘ በዚያም የጠ…
Jul 28, 2026በዚያንም ጊዜ በዚያች ጉዳና ሊጓዙ የሚሹ የዓረብ ሰዋችን አያቸው ወደ እርሳቸውም ሒዶ አብረሮአቸው ይሔድ ዘንድ ለመናቸው እነርሱም በደስታ ተቀበሉት ወደ አንድ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ እስከሚደርስ የሦስት ቀን ጉዳና ተጓዘ በዚያም የጠራና የቀዘቀዘ ውኃ አለ ዳግምም የሰሌን የተምር ዕንጨቶች መቃቃዎችም በብዛት አሉበት እንጦኒዮስም ያንን ቦታ ወደደው ዓረቦችም ምግቡን የሚያመጡለት ሆኑ ብዙዎች የከፋ አራዊትም ነበሩ በጸሎቱም እግዚአብሔር አስወገዳቸው ወደዚያም ቦታ ከቶ አልተመለሱም። አንዳንድ ጊዜም ወደ ባሕሩ ዳርቻ በመውጣት ደቀ መዛሙርቶቹን ጉብኝቶና አረጋግቶ በበረሀ ወስጥወደአለው ቦተው ይመለሳል ።
ከዚህም በኋላ በጸድቁ ንጉሥ ቁስጠንጢስዘንድ ዜናው በተሰማ ጊዜ በጸሎቱያስበው ዘንድ ንጉሡ አየለ መነዉ ደብዳበ ጻፈለት የከበረ እንጦንዮስ ግን ወደ ንጉሥ ደብዳቤ ዘወር አላለም ለወገኖቹ እንዲህ አላቸውእንጂ የንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ደብዳቤ እንሆበላያችን ይነበባል ወንድሞችም እንዲህ ብለው ለመኑት ይህ ንጉሥ የክርስቲያንን ወገኖች የሚወድ ጻድቅ ሰው ነው ደብዳቤ ጽፈህ ልታጽናናው ይገባል ከዚህም በኃላ እያፅናናውና እየባረከው ፃፈለት።
ዳግመኛም በአፍርንጊያ ንጉስ ዘንድ ዜናው በተሰማ ጊዜ ወደ ከበረ እንጦንዮስ እንዲህ ብሎ ፃፈ ወደ እኛ መጥተህ በእኛ ላይ በአገራችንና በሰራዊታችን ላይ በረከትን ታሳድር ዘንድ ስለ ጌታችን ክርስቶስ መከራዎች እኔ ወዳንተ ፈፅሜ እማልዳለሁ።
የከበረ እንጦንዮስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ቁሞም እንዲህ ብሎ ፀለየ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እለምንሀለሁ በአፍርጊያ ውስጥ ወዳለ ወደ በርኪኖን አገር እንድሄድ ፈቃድህ ከሆነ ምልክትን ግለጥልኝ ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይሁን ይህንንም ባለ ጊዜ ብርህት ደመና መጣች በዚያችም ሰአት ተሸክማ ወደ አፍርንጊያ አገር አደረሰችው ንጉሱም ደስ አለው ህዝቡና ሰራዊቱም ሁሉ በሽተኞችንም አቀረቡለትና ሁሉንም ፈወሳቸው የፅድቅና የህይወትንም መንገድ እያስተማራቸው ከእነርሱ ዘንድ ስድስት ወር ኖረ። በእሁድም እለት ያቺ ብርህት ደመና ተሸክማ ወደ ገዳሙ ታደርሰውና ከልጆቹ ጋር ተገናኝቶ ያረጋጋቸዋል በማግስቱም ዳግመኛ ተሸክማ ወደ አፍርንጊያ አገር ትመልሰዋለች። ከዚህም በኃላ በእግዚአብሄር ፈቃድ በደመና ተጭኖ ወደ ገዳሙ አንደኛውን ተመለሰ።
በአንዲት እለትም ስንፍና መጣበት እንዲህ የሚለውም ቃል መጣ ታይ ዘንድ ወደ ውጪ ውጣ በወጣ ጊዜም መልአኩን አየው በላዩም የምንኩስና ልብስ አለ መታጠቂያ ቅናት የመስቀል ምልክት ያለው ቀሚስ በወገቡም አስኬማ በራስ ቁር አምሳልም በራሱ ላይ ቆብ አለ እርሱም ተቀምጦ ሰሌን ይታታል ከዚያም ተነስቶ ይፀልያል ዳግመኛም ተቀምጦ ሰሌኑን ይታታል በየሰአቱም እንዲህ የሚል ቃል ወደርሱ መጣ እንጦንዮስ ሆይ እንደዚህ ስራ አንተም ከሰንፍና ከሰይጣናት ጦርነት ታርፋለህ ያንን ያየውንም ተቀብሎ እንዲሁ አስመስሎ የሚሰራ ሆነ ከዚያችም እለት ወዲህ ስንፍናና የሰይጣናት ወጊያ አልመጣበትም።
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ ተገልፆ አረጋግቶታል አፅንቶታልም። አሁንም እንዲህ አለው የመረጥሁህ እንጦንዮስ ሆይ በእውነት እነግርሀለሁ እኔን ስለመውደድህ በዚች በረሀ ውስጥ ብቻህን በመጋደልህና በማገልገልህ ስለ ድካምህ ስምህን ክፍ ከፍ አደርጋለሁ ስልጣንህንም በአለም ዳርቻ ሁሉ ከፍ አደርገዋለሁ።
ገዳማትንና አድባራትንም መነኩሳትን የተመሉ ሆነው ቅኖች የዋሀን ፃደቃን እንደሚኖሩባቸው አደርጋቸዋለሁ ይልቁንም ያንተ ገዳማት እነርሱ እስከ ፍፃሜ ይኖራሉ። መታሰቢያህንም የሚያደርገውን ሁሉ ለድሆች ምፅዋትን ለቤተክርስቲያን መባ በስምህ የሚሰጠውን ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ ከቶ ስቃይን አያያትም በውስጡ ስጋህ የሚቀበርበትንም ገዳም እጅግ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ በውስጡም እንደ መላእክት የሆኑ ደጋጎች መነኮሳት እንዲኖሩበት አደርጋለሁ ከእነርሱም እስከ አለም ፍፃሜ አለቃ የሚሆን አይታጣም የምድር ነገስታት መሳፍንትና ሹማምንት ለገዳምህና ፍለጋህን ለሚከተሉ ልጆችህም እጅ መንሻ ተሸክመው እንዲመጡ አደርጋለሁ ጌታችንም ይህንን ከተናገረው በኃላ ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በታላቅ ክብር አረገ አባ እንጦኒም ፈፅሞ ደስ አለው።
ከዚህም በኃላ ስለ ቤተክርስቲያን መፍረስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ መናፍቃን በላይዋ ይሰለጥናሉ ከዚህም በኃላ ወደ ቀድሞው ስርዓቷ ትመለሳለች ዳግመኛም ስለ መነኮሳት እነርሱ እጅግ እንደሚበዙ ገዳሞቻቸውንና አድባራቶችን በመተው ወርደው ከአለማውያን መካከል በከተማዎችና በቦታዎች ውስጥ እንደሚኖሩ ስለ አለም ፍፃሜም ትንቢት ተናገረ። ይህም አባ እንጦንዮስ አባ መቃርስን አስኬማንና የምንኩስና ልብስን ያለበሰው ያረጋጋውና ያፅናናው ከእርሱ የሚሆነውንም ያስረዳው ነው ደቀ መዝሙሩና ልጁ ስለሆነ።
ከዚህም በኃላ የገዳማውያን አለቃ ወደሆነ ወደ አባ ቡላ ሄደ እርሱም ለስጋው ያሰበና በሀዋርያዊ አትናቴዎስ ልብስ የገነዘው ነው። እረፍቱም እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ በትሩን ለልጁ ለአባ መቃርስ ምንጣፉን ለአባ አትናቴዎስ የፍየል ሌጦ ዐጽፉን ለልጁ ለኤጲስቆጶስ ለአባ ስራብዮን እንዲሰጡ ልጆቹን አዘዛቸው።
ከዚህም በኃላ ከምድር ላይ ጋደም አለ ነፍሱንም በእግዚአብሄር እጅ ሰጠ ወደርሱም ሁሉም የመላእክት ማኅበር መጥተው በክብር በምስጋና ፍፁም ተድላ ደስታ ወዳለበት ዘላለማዊ እረፍት ተቀብለው አሳረጉት።
ስጋውን ግን ልጆቹ እንዳዘዛቸው ሰወሩት እርሱ የቅዱሳን ሰማእታትን ስጋቸውን የሚገልጡትን ይገስፃቸው ነበርና ስለ እነርሱ ስጋ ብዙ ገንዘብ እስከመቀበል ደረሰው አለማዊ ጥሪት ያደርጉታልና። ይህም የከበረና የተመሰገነ አባት እንጢንዮስ እስከ መልካም ሽምግልና ደረሰ እጅግም አረጀ ግን ወደ ወደደውም ክርስቶስ እስከ ሄደ ድረስ መልኩ አልተለወጠም ብርታቱ ፅናቱም መላው እድሜው መቶ ሀያ አመት ነው ጥር ሃያ ሁለት ቀንም ዕረፍቱ በድምቀት ይከበራል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መቃርስ
ሐምሌ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን የጭፍሮች አለቃ የሆነ የፋሲለደስ ልጅ ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት ሆነ። ይህንንም ቅዱስ አማልክትን እርሱ እንደማያመልክ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ዘንድ ወነጀሉት ንጉሥም ወደ እስክንድርያ ወስደው በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።
እርሱም ወላጆቹን በተሰናበታቸው ጊዜ ለድኆችና ለችግረኞች እንዲአስቡ አደራ አላቸው። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሔደ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም ተገልጾለት አጽናናው የሚደርስበትንም ነገረው። ወደ እስክንድርያ ከተማም በደረሰ ጊዜ በመኰንን ኅርማኖስ ፊት ቆመ መኰንኑም የጭፍሮች አለቃ የፋሲለደስ ልጅ እንደሆነ አውቆ ብዙ አባበለው ለመነውም እርሱ ግን አልሰማውም ከመልካም ምክሩም አልተመለሰም።
ከዚህም በኋላ ሰውነቱ እስከምትቀልጥ ድረስ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በሥቃይም ውስጥ እያለ ጌታችን የቅዱሳንን ማደሪያዎችንና የአባቱንና የወንድሙን ማደሪያ አሳየው። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ኒቅዮስ ሀገር ሰደደው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ምላሱንና ክንዱን ቆረጡት በጎኖቹም ውስጥ በእሳት ያጋሉአቸውን የብረት ችንካሮች ጨመሩ ጌታችንም አዳነው ያለ ጉዳትም በጤና አስነሣው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በእጆቹ ላይ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከእነርሱም ብዙ ሰዎች የሞተ ሰው ተሸክመው ሊቀብሩ ሲሔዱ አየ። ሁሉም እያዩት ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ማለደ። ስለዚያም ምውት ተነሥቶ ያየውን ይነግራቸው ዘንድ ለመነ። ወዲያውኑም ያ
😍4❤3🥰3🕊1😘1
ቦታ ስለሆነ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም በዚህ በጨረሻው ሀሳብ ይስማማል፡፡
Jul 28, 2026ቦታ ስለሆነ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም በዚህ በጨረሻው ሀሳብ ይስማማል፡፡
ሰማያዊ ክብርን የሚያስገኝ አኩሪ ገድል በመፈጸም የቤተክርስቲያን ታላቅ አለኝታ አባትና መሪ የሆኑት የዘመናችንን ታላቅ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን ትውልዱ የግድ ሊያስባቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (united nations) አቡነ ዼጥሮስን "የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት" ወይም በፈረንጅኛው አፍ (MARTYR OF THE MILLENIUM) በሚል መጠሪያ ሰይሟቸዋል፡፡ ላልተነገረላቸውና ላልተዘመረላቸው ለእኚህ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያናችን ድንቅ አባት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም እኚህን ሰማዕት ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ›› ተብለው እንዲጠሩ ወስኗል፡፡ በስማቸውም መቅደስ እንዲታነጽ ፈቅዶ በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረት (ኢሳ 56፡4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራ መታሰቢያ አቁማላቸዋለች፡፡ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም በስማቸው የተሰየመው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና መታሰቢያ ሐውልታቸው ሲሠራ የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ጭምር ለግንባታ የሚሆን አሸዋ ከመርዳት አንስቶ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ድንኳን እስከመትከል ተሳትፈዋል፡፡ በገንዘብም በጉልበትም ተባብረዋል፡፡ ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የአባታችንን እጅግ አኩሪ ታሪክ ሲያዘክራቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም በአ.አ መሐል ከተማ ላይ ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_እንጦንስ_ርዕሰ_መነኮሳት
በዚህች ቀን የመነኰሳት ሁሉ አባት በገዳም ለሚኖር እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው አባት እንጦንዮስ የከበረች ቤተክርስቲያኑ የከበረችበት (ቅዳሴ ቤቱ) ነው። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ንፁሀን ክርስቲያን ናቸው እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ተንኮል ሽንገላ በልቡ ውስጥ የለውም ከወላጆቹም ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሂዶ በቆረበ ጊዜ ከህፃናት ጋር በመጫወት ከቶ አይሳሳቅም ነበር። ጥቂት በአደገም ጊዜ ራሱን ዝቅ አድርጎ ለወላጆቹ ይታዘዝ ነበር ሰባት አመትም በሆነው ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መፃህፍትን ተማረ ያን ጊዜም የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ቲዎናስ የተሾመበት ዘመን ነበር የእንጦንዮስንም ወሬውን ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ባረከውና ስለርሱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ይህ ህፃን በእግዚአብሄር ፊት ታላቅ ይሆናል ዜናውም በአለሙ ሁሉ ይወጣል እጁንም በላዩ ጭኖ ዲቁና ሾመው።
ከዚህም በኃላ ወላጆቹ በሞቱ ጊዜ ታናሽ ብላቴና እኅት ትተውለት ነበር።ከሰባት ወርም በኃላ እንደ ልማዱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በሄደ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር በልቡ አደረበትና በኀሳቡ በአለም የሚሰራውን ሁሉ አባቶቻችን ሀዋርያት ሁሉን የአለምን ስራ ትተው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ተከተሉት በሀዋርያት ስራ መፅሀፍም እንደተፃፈ ጥሪታቸውን እየሸጡ የሽያጩንም ዋጋ በሀዋርያት እግር ስር ያኖሩትን አሰበ እግዚአብሄር በሰማያት ያዘጋጀላቸው ዋጋቸው ምን ያህል ይሆን አለ ይህም ኀሳብ በልቡ ውስጥ የሚመጣ የሚወርድ ሆነ። ከዚህም በኃላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ የክብር ባለቤት ጌታችን በከበረ ወንጌል ለባለፀጋው የተናገረውን ሰማ እንዲህ ሲል ፍፁም ትሆን ዘንድ ከወደድክ ሂድ ጥሪትህን ሁሉ ሸጠህ ለድኆች ስጥ በሰማይም ላንተ ድልብ አድርገው መጥተህም ተከተለኝ።
ከእግዚአብሄርም ዘንድ ይህን ልዩ ኀሳብ አግኝቶ ይህ ቃል ስለርሱ እንደተነገረ አሰበ በዚያንም ጊዜ ከቤተ ክርስቲያን ወጣ ለአባቱም ያማረ ሰፊ ምድር ነበረው ለአገሩም ሰዎች ሰጣቸው ለርሱ የተውለትንም ጥሪታቸውን ሁሉ ሸጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው እኅቱንም ወስዶ ከደናግል ገዳም አስገባት።
በዚያንም ወራት የምንኩስና ስርአት አልተገለፀም ነበር እግዚአብሄርንም ለማገልገል የሚሻ ከመንደር ጥቂት ወጣ ብሎ ብቻውን በመቀመጥ በፆም በፀሎት ተወስኖ ይጋደላል የከበረ እንጦንዮስም እንዲሁ አደረገ ሰይጣናትም በስንፍናና በዝሙት ጦር የሚዋጉት ሆኑ በህልሙም የሴት ገፅ በማሳየት አብራውም እንደምትተኛ ያደርጓታል።
ከዚህም በኃላ በባህር ዳርቻ ወዳለች የመቃብር ቤት ሂዶ በዚያ የሚኖር ሆነ በላዩ በአደረ በእግዚአበሄርም ረድኤት በተጋድሎ በረታ ምግቡንም ከዘመዶቹ ወገን ያመጡላት ነበር ሰይጣናትም ሲጋደል አይተው ቀኑበት ታላቅ ዱብደባንም ደብድበው ጥለውት ሄዱ ዘመዶቹም ሲመጡ እንደ ሞተ ሆኖ ወድቆ አገኙት ተሸክመውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት ጌታችንም አዳነው በነቃም ጊዜ ወደ ቦታው ተመልሶ ይጋደል ዘንድ ተጋድኖውን ጀመረ። በዚያንም ጊዜ ሰይጣናትን ወደርሱ ሲመጡ አያቸው በአራዊት አምሳል በአንበሶችና በተኩላዎች የተመሰሉ አሉ በእባቦችና በጊንጦችም የተመሰሉ አሉ ያስፈሩትም ዘንድ አንዱም አንዱ በላዩ ተነሳሱ እንጦንዮስም በእኔ ላይ ለእናንተ ስልጣን ካላችሁ ከእናንተ አንድ ያሸንፈኝ ነበር ብሎ ዘበተባቸው ወዲያውኑ እንደ ጢስ ተበተኑ በሰይጣናት ላይ ድልን እግዚአብሄር ሰጥቶታልና ሰይጣናትም ከሚያመጡበት መከራና ስቃይ አረፈ።
ምግቡንም በአመቱ ሁለት ጊዜ ያበስላል በፀሀይም ያደርቀዋል ወደበአቱም ማንም እንዲገባ አያሰናብትም የሚሻውም ሁሉ በውጭ ይቆምና ድምፁን ይሰማል እንጂ ሀያ አመትም እንዲህ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በገደል ተጠምዶ ኖረ።
ከዚህም በኃላ ፍፁም የሆነ እግዚአብሄርን መፍራትንና አምልኮቱን ለሰዎች ወጥቶ ያስተምር ዘንድ እግዚአብሄር አዘዘው ስለዚህም ወደ ፍዩም አገር ወጥቶ ብዙዎች ደቀ መዛሙርትን ሰብሰቦ አስተማራቸው በእግዚአብሄርም ህግ አፀናቸው ደቀ መዛሙርቶቹ በውስጣቸው የሚኖሩባቸው ብዙዎች ገዳማት ተሰሩለት።
ስለ ሀይማኖትም ስደት በሆነበት ወራት በሰማእትነት መሞት ወዶ ወደ እስክንድርያ ሀገር ሄዶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ከቶ አልያዙትም በክርስቶስም ስም የታሰሩ እስረኞችን በመጎብኘት ቢአረጋጋቸውና ቢአፅናናቸውም አልያዙትም መኮንኑም እንደማይፈራ ባየው ጊዜ ከፍርድ አደባባይ ውስጥ እንዳይታይ አዘዘው እርሱ ግን ሁልጊዜ መታየቱን አለተወም እንዲአሰቃየውና በሰማእትነትም እንዲሞት የሚያስቆጣውን ነገር ይናገረው ነበር መኮንኑም በእርሱ ላይ ምንም ክፉ ነገር አላደረገም አምላካዊት ኃይል ከልክላዋለችና።
ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ ለሰማእታት ፍፃሜ ሆኖ የመከራው ወራት ከአለፈ በኃላ እንጦኒ ወደ ገዳሙ ተመለሰ ይህም በአምላክ ፍቃድ ሆነ የሚለብሰውም ማቅ ነበር በዘመኑ ሁሉ ገላውን በውኃ አልታጠበም ብዙዎች በሽተኞችም ወደርሱ ይመጣሉ በላያቸውም ሲፀልይ ይድናሉ። ብዙዎች ህዝቦችም ትምህርቱን ሊሰሙ ወደርሱ ሲመጡ በአያቸው ጊዜ ብቻውንም ይኖር ዘንድ እንዳልተውት አይቶ ከእርሱ ስለሚደረገው ነገር ልቡ እንዳይታበይ ፈራ እነርሱ ወደሚያውቁት ቦታ ወደላይኛው ግብፅ ይሄድ ዘንድ ወዶ ወደ ባህሩም ወደብ ደርሶ መርከብ እየጠበቀ ተቀመጠ ከሰማይም ወደርሱ ቃል መጣ እንዲህም አለው እንጦንዮስ ሆይ ወዴት ትሄዳለህ ከዚህስ ምን ትሻለህ አለው እርሱም ብዙዎች ወደእኔ ስለሚምጡ እንደምፈልገው ለብቻ መኖር አልተቻለኝም ስለዚህም ወደ ላይኛው ግብፅ እሄድ ዘንድ ወደድኩ አለ ያም ቃል መልሶ እንዲህ አለው ወደ ላይኛው ግብፅ ብትሄድ ድካምህ ደግሞ እጥፍ ይሆናል ብቻህን መኖር ከወደድክ ግን የሶስት ቀን ጎዳና ያህል ወደ ውስጠኛው በረሀ ተጓዝ።
❤3🥰3😘3🕊1😍1
ዳኞቸ ሦሰት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንቶች ናቸው፤ መካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል ‹ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል› የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም ‹ካህናቱም ሆኑ የቤ…
Jul 28, 2026ዳኞቸ ሦሰት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንቶች ናቸው፤ መካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል ‹ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል› የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም ‹ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፡- ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ፡፡ ‹‹ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ፡- ‹አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን› ብለው አወገዙ፡፡ ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍጥነት ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ እርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ፡፡ ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣሊያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ በዚህን ጊዜ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊው ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡ የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው፡፡
የሀገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒያ እውነተኛ ጳጳስ እንዲገደሉ ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይመታ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሄድ ከመካነ ፍትሑ ዐሥር ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ ‹ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‹ይህ ያንተ ሥራ ነው› ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡
ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ፡፡ ከዚያም በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተ ጀመርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ፣ ወዲያው አዛዡ ‹ተኩስ!› በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡ ብፁዕነታቸው የተገደሉበት ቦታ መሐል አዲስ አበባ ላይ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው›› በማለት የጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛው ፖጃሌ ስለ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?›› ሲል በወቅቱ አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ በቦታው ላይ በአካል በመገኘት ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩትን ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውውም የሚከተለውን ተናረዋል፡- ‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት፡፡ ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ፡፡ ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደልኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ፡፡ ‹እንዴት?› ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ?› አለኝ፡፡ ‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት፡፡ ‹እንዴት?› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡ ‹ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ› ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ሰዓታቸውንም ጭምር አሳየኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተበስቷል፡፡ መስቀሉም ልክ በመሐሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል፡፡ የኪስ ሰዓታቸውንም እንዳየሁት እንዲሁ ጥይት በስቶታል›› ብለው በወቅቱ የተመለከቱትን መስክረዋል፡፡
ብፁዕ አባታችን በአደባባይ በሕዝብ ፊት የሰማዕትነት ጽዋቸውን ሲቀበሉ ከሕዝቡ ጋር ሆና ትመለከት የነበረች አንዲት ከድጃ የምትባል እስላም ሴት ማንም ሰው ያላየውን ታላቅ ነገር እርሷ ተመልክታለች፤ ይኸውም አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ሲቀዳጁ ተመልክታ በዚያው እርሷም ‹‹የእኚህን አባት ሃይማኖት እከተላለሁ›› ብላ በመጠመቅ ክርስቲያን ሆናለች፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ሰማዕቱን አቡነ ጴጥሮስን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ ቀብራቸው በምሥጢር መፈጸሙን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምሥጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም ‹‹ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምሥጢር ቀበሯቸው›› ከሚል ከመላምት ያለፈ ነገር ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ‹‹ፉሪ ለቡ›› ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው ‹‹ሙኒሳ ጉብታ›› ላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ እየተነገረ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የአቡነ ጴጥሮስን ሥጋ በተመለከተ ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአ.አ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር እንዲቀበር መደረጉ በትንሣኤ መጽሔት ቁ.58 1978 ዓ.ም ላይ የተገለጠ ቢሆንም ነገር ግን አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ቅዱሳን መላእክት የጻድቃንን በድን እያመጡ ወደሚያስቀምጡበትና በውስጡ የሚቀመጥ አስክሬን ወደማይፈርስበት አቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ገዳም መላእክት ወስደው እንዳስቀመጡትና በዚያም እንደታየ ይናገራሉ፡፡ ሰሜን ሸዋ ሚዳ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው በአቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ውስጥ የቅዳሱኑ አጽም ሳይፈርስና ሳይበሰብስ የአንገት ክራቸው ራሱ ሳይበጠስ እንደዛው እንደነበሩ ስለሚገኝ ቦታውም እጅግ ትልቅ የቃልኪዳን
😍4🥰3❤2🕊1😘1
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Jul 28, 2026✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ዼጥሮስ_ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ)
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ፡፡ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ‹‹አለቃ ተጠምቀ›› የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው «ኀይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ›› ብለዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል፡፡ ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መመህር ኀይለ ማርያም ይባሉ ነበር፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔው አውድማ ጎጃም በመሄድ በሸዋራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል፡፡ የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሄደው ተምረዋል፡፡ በመቀጠልም ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር ይመግቡ ወደነበሩት ወደ ሊቁ አካለ ወልድ ዘንድ በመሄድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በሚገባ አሒዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በ1900 ዓ.ም ወሎ አምሐራ ሳይንት ሄደው በምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ፡፡ በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ፡፡ ከዚያም መምህርነት ተሹመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ሄደው ለ6 ዓመታት ካስተማሩ በኋላ በ1916 ዓ.ም እንደገና በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት ተሹመው ለ3 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በ1919 ዓ.ም ወደ አ.አ በመምጣት የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የንስሓ አባት ሆኑ፡፡ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በራሷ ተወላጅ ጳጳሳት ልጆቿ እንድትመራ ከ1600 ዓመታት በኋላ ስለተፈቀደላት ከዚህ በኋላ በሃይማኖታቸውና በስነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ደጋግ አባቶች ሲመረጡ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን ጳጳስ ስትሾም አቡነ ጴጥሮስ ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ፡፡ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባታችን ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቀ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ›› ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ፡፡
ብፁዕ አባታችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ቅድስት ሀገራችን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር፡፡ በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስም ይህንን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ማይጨው ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው በመርዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ አ.አ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ጫካዎች ውስጥ መሽጎ የነበረው የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር እና በሸንኮራ በኩል መሽጎ የነበረው የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር እንደሁም በምዕራብ ይመራ ከነበረው የእነ ደጃዝማች አባ ነፍሶ ጦር ሦስቱም በአንድ ጊዜ ወደ መሐል አ.አ በመግት አ.አ ላይ መሽጎ የነበረውን ፋሽስትን ለመውጋት ታቅዶ የነበረው ዕቅድ በመረጃ ክፍተት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ፡፡ በተለያየ ጊዜ መሐል አ.አ እየደረሱ ማለትም በመጀመሪያ የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር ለብቻው በኮተቤ አድጎ የካ ሚካኤል ላይ ሲድርስ ተመቶ ተመለሰ፤ ይሄኛው እንዳለቀ ቀጥሎ የእነ አባ ነፍሶ ጦር በባቡር ጣቢያ መጣሁ ቢልም በጠላት ጦር ድካሚ ተመቶ ተመለሰ፤ መጨረሻ ላይ የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር በእንጦጦ በኩል ቢመጣም እርሱም በጠላት ጦር ተመቶ ተመለሰ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሦስቱም የአርበኞች ጦር በመረጃ ክፍተት ምክንያት እየተመታ ወደመጣበት ሲመለስ አቡነ ጴጥሮስ አብረው ከአርበኛው ጦር ጋር መመለሱን አልፈለጉትም ይልቁንም ‹‹ብችል ጠላት በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት ሆኖ የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሣ አደርገዋለሁ ካልሆነም ደግሞ እዚሁ እሞታለሁ›› በማለት አባታችን ከአርበኞቹ ተነጥለው አ.አ ቀሩ፡፡ ይሁን እንጂ ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎች አባታችንን እንዳሰቡት ሊያነቀሳቅሷቸው አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም አባታችን ‹‹የሀገሬን ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሰማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል›› ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑና የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለሆነው ለራስ ኀይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡት፡፡ እርሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጧቸው፡፡ ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ በሰማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሒደት ኮርየሬ ዴላሴራ የተባለው ጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ፖጃሌ የተባለው ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ በነበረ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰጠውን ፍርድና የተፈጸመውን የግፍ ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር፡-
‹‹ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ቄርሎስ የተባሉት ግብፃዊ ጳጳስ ቀርበው ‹ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ እንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም››› ሲሉ ለግራዚያኒ ነገሩት፡፡ አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስን ሕይወት ለማትረፍ አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ግራዚያኒ የአቡነ ጴጥሮስ የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብጽ ከአ.አ ውጭ እንኳ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን እንዲፈጸም መመሪያ አስተላላፈ፡፡ ወደ ምሥራቅ አፍሪካው ዜና መዋዕል አዘጋጁ ወደ ፖጃሌ ዘገባ እንመለስና የአቡነ ጴጥሮስን መልካቸውንና ተክለ ቁመናቸውን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡- ‹‹ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድ የተሰየሙት
😍5😘4❤3🥰2🕊1
#ሐምሌ_22
Jul 28, 2026#ሐምሌ_22
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን #የሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፣ ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብጹዕ #አቡነ_ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ፣ የመነኰሳት ሁሉ አባት #የቅዱስ_እንጦንስ የከበረች ቤተክርስቲያኑ የከበረችበት (ቅዳሴ ቤቱ) ነው፣ የፋሲለደስ ልጅ #ቅዱስ_መቃርስ ሰማዕት ሆነ፣ #ቅዱስ_ለውንትዮስ በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ዑራኤል
ሐምሌ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡ ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡
በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ ‹‹አጋእዝት›› ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ ‹‹ኪሩቤል›› ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ሰብና ገጸ አንበስ ናቸው፡፡ በሦስተኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ሱራፌል ይባላሉ፡፡ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፡፡ በትንቢተ ኢሳያስ በምዕራፍ 6 ላይ የተገለጹትና ኢሳያስን ከለምጹ እንዲፈወስ ያደረጉት ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ላህምና ገጸ ንስር ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ ‹‹ከሩቤል›› ወይም ‹‹ሱራፌል›› የሚባሉ የግለሰብ መጠሪያ ስሞች ስህተት ናቸው፡፡ አንደኛ እነዚህ ስሞች የብዙ መላእክት መጠሪያን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ለአንዱ ሲሆን ‹‹ኪሩብ፣ ሱራፊ›› ይባላል፡፡ ‹ኪሩቤል› ወይም ‹ሱራፌል› ማለት ግን የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የቅዱሳን መላእክትን ስም እንዳለ በቁሙ ወስዶ ለግል መጠሪያ ስም ማዋል ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ወለተ ሚካኤ፣ ክብፈ ገብርኤል….›› እየተባሉ ይሰየማሉ እንጂ ቀጥታ ‹ሚካኤል›፣ ‹ገብርኤል› እያሉ ሰዎችን መሰየም ስህተት ነው፡፡ 4ኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ኃይላት ይባላሉ፡፡ የእሳት ሰይፍ ይዘው በሥሉስ ቅዱስ ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት የዛሉና የደከሙ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡)
ዳግመኛም እግዚአብሔር በራማ ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹አርባብ›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ እልፍኝ አስከልካዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፡፡
አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ሁለተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹መናብርት›› ይባላሉ፡፡ ለእግዚአብሔርን እጅግ ቅርብ የሆኑ ናቸው፡፡ የመብረቅ ጋሻቸውን የእሳት ጦራቸውን ይዘው የሥላሴ ጋሻ ጃግሬዎች ሆነው በተጠንቀቅ ይቆማሉ፡፡ የሰውን ችግር ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፡፡ መዝ 88፡6፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሦስተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹ሥልጣናት›› ይባላሉ፡፡ መላውን ፍጥረት ለመጠበቅ ሥልጣን የተሰጣቸውና የምጽአት ዕለት አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ ዳን 12፡1፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው፡፡
ዳግመኛም እግዚአብሔር በኤረር ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹መኳንንት›› ይባላሉ፡፡ የስላሴ የእሳት ባለ ቀስት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልዩ ጠባቂዎች ናቸው፤ በተለይ በአደጋ ጊዜ ሎጥን እንዳዳኑት ፈጥነው ይደርሳሉ፡፡ በዕለተ ምጽዓት የሰውን ሁሉ ዐፅም ሰብስበው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ያበቃሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ነው፡፡ ሁለተኛዎቹ ‹‹ሊቃናት›› ይላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ፈረሶች ናቸው፡፡ በእሳት ፈረስ ይመላለሳሉ፡፡ እነዚህም 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሲሆኑ አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል ነው፡፡ በኤረር ከተማ የሰፈሩት ሦስተኛዎቹ ‹‹መላእክት›› ይባላሉ፡፡ ፍጥረትን ሁሉ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ አለቃቸው ቅዱስ አናንኤል ነው፡፡ በእነዚህ የማይጠበቅ ፍጥረት የለም፡፡ ከአዝርእት ጀምሮ ሁሉን ይጠብቃሉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ 8፡2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› የሚለው ስም ‹ዑር› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችንን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፡፡ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
😍6🥰4❤3🕊1😘1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 28, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🥰4😘4❤2😍2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 28, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤5😍3🥰2😘1
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Jul 28, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
❤6🥰4
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 28, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
❤3🥰3😍3😘3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 28, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😘4🥰3😍2❤1
እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል: ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን:: በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር::አሜን
Jul 27, 2026እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል: ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን:: በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር::አሜን
😘7❤3🥰2😍2
✝ ኦ ድንግል፦
Jul 27, 2026✝ ኦ ድንግል፦
#እህቶሙ #ለመላእክት፤
#ትንቢቶሙ #ለነቢያት፤
#ጣዕመ ስብከቶሙ #ለሐዋርያት፤
#እሞሙ #ለሰማዕት፤
#ሞገሶሙ ለመስተጋድላን #ጻድቃን፤
#መጽደቂቶሙ #ለኃጥአን፤
#ናዛዚቶሙ #ለኅዙናን፤
#ፈዋሲቶሙ #ለሕሙማን . . .
☞በዝንቱ ዕለተ በዓልኪ ኢትምሕሪዮሙኑ ለሰብአ #ኢትዮጵያ አብዳን? (ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል)
(ድንግል ሆይ! . . . በዚህ ደገኛ በዓልሽ ስንፍና የሰለጠነብንን ኢትዮጵያውያንን አትምሪምንም?)
✝ ንዒ ኀቤነ #ኦ_ድንግል ምስለ #ኤልያስ #ወኤልሳዕ #ነቢያተ_እስራኤል ወምስለ #ዕዝራ #ሱቱኤል ወምስለ #አባ_ጊዮርጊስ ድንግል ጽዋዐ ልቡና ዘአስተዮ #ዑራኤል
❤3❤🔥1🕊1
#ሐምሌ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፣ ታላቁ አባት #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ዕረፍቱ ነው፣ ጃንደረባው #ቅዱስ_ሱስንዮስ አረፈ፣ …
Jul 27, 2026#ሐምሌ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፣ ታላቁ አባት #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ዕረፍቱ ነው፣ ጃንደረባው #ቅዱስ_ሱስንዮስ አረፈ፣ አስተዋይ የሆነ የተመሰገነ #ቅዱስ_አወ_ክርስቶስ አረፈ፣ ምፅዋት መስጠትንም የሚወድ #ቅዱስ_ላእከ_ማርያም አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባሕር…
🥰6😍3😘3❤2
ከስምሪቱም በገባ ጊዜ የእንግዶችን እግር ያጥብ ነበር። እርሷም ማዕድን በማዘጋጀት ታገለግል ነበር። ፍጹማን መነኰሳትም ሥራቸው እንዴት እንደሆነ ይገልጥላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጠየቁ ጊዜ ገድላችሁ በአወ ክርስቶስና በሚስቱ ተጋድሎ…
Jul 27, 2026ከስምሪቱም በገባ ጊዜ የእንግዶችን እግር ያጥብ ነበር። እርሷም ማዕድን በማዘጋጀት ታገለግል ነበር። ፍጹማን መነኰሳትም ሥራቸው እንዴት እንደሆነ ይገልጥላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጠየቁ ጊዜ ገድላችሁ በአወ ክርስቶስና በሚስቱ ተጋድሎ መጠን አልደረሰም የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ።
እነዚያ መነኰሳትም ሒደው ሥራቸውን መረመሩ በጭንቅ በግዳጅም ሥራቸውን ገለጡላቸው እያደነቁም ተመለሱ በእንዲህ ያለ ሥራም ኑረው በሰላም አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ላዕከ_ማርያም_ሔር
በዚህችም ቀን ደግ የሆነና በጎ ምግባር ያለው ምፅዋት መስጠትንም የሚወድ ላእከ ማርያም አረፈ። የዚህ ቅዱስም የእናቱ ስም ሮማነ ወርቅ ነው እርሷም መካነ ሥላሴን የሠራች የኢትዮጵያ ንጉሥ የናዖድ ልጁ ናት አባቱም የንጉሠ ገይኝ ልጅ ነው።ይህም ቅዱስ ከተወለደ በኋላ በክርስቲያን ወገኖችና በንጉሥ ልብነ ድንግል ላይ መከራና ስደት ሆነ። የዚህን ንጉሥ ዜና ግን በነገሥታት ታሪክ ተጽፎ ስለሚገኝ ትተንዋል።
ንጉሥ ልብነ ድንግልም ከአረፈ በኋላ ገላውዴዎስ ነገሠ። እስላሞችም በእርሱ ላይ ተነሡ ከቀኖችም በአንዱ ሲዋጋ ድል ለእርሱ ሆነ በኋላ ግን ድሉ ለእስላሞች ሆነ የዚች ዓለም ሥርዓቷ እንዲህ ተለዋዋጭ ነውና ያን ጊዜም ይህን ጻድቅ ላእከ ማርያምን ይዘው አሚም ወደሚባለው አለቃቸው አደረሱት እርሱም በክብር አኖረው።
በሃይማኖታቸውም እንዳልተባበራቸው አየው የተማረኩትንና የተገደሉትን በሚያያቸው ጊዜ ያለቅስ ነበርና። ስለዚህ እንዲሰልቡት አዘዘ። ይህንንም የጃንደራባነት ዕድል ሁሉ የሚያገኘው አይደለም ለተሰጠችው እንጂ። ክብር ይግባውና ጌታችን እንዳለ ከእናታቸው ሆድ ጀምሮ ሕፅዋን የሆኑ አሉ፣ በጦርነት ጊዜ ሰዎች ሕፅዋን ያደረጓቸውም አሉ፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን ሕፅዋን ያደረጉ አሉ ይህን ሊፈጽም የሚሻ ይፈጽም።
ከዚህ በኋላም ወደ ቱርክ ወሰዱት በመንገድም ብዙ መከራ አገኘው በግመል ላይ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉበት ጊዜ ነበረ፣ በውኃ ጥማትና በፀሐይ ቃጠሎ የሚያሠቃዩበት ጊዜ ነበረ በጌታችንም ፈቃድ ከየመን አገር ደረሰ። የእስላሞች ንጉሥም ወደርሱ እንዲአቀርቡት አዘዘ ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ በየገጹ ሊናገሩት በማይቻል በታላቅ ተአምር ወደ ኢትዮጵያ ሀገር ተመለሰ።
ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠራ በድኆችና በችግረኞች ላይ ቸርነትን አደረገ። ብዙ ትሩፋትንም አደረገ የጻድቃንና የሰማዕታትንም መታሰቢያቸውን ያደርጋል። ይልቁንም አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም የበዓሏን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ነበር። ዕረፍቱም በደረሰ ጊዜ ይኸውም የጥበብ ሁሉ ፍጻሜ ሞት ነው ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ነፃ አውጥቶ አባቶቹ ወደ ሔዱበት ዓለም ሔደ።
† ሐምሌ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
3.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
4.ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር (ኢትዮጵያዊ)
5.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ኢትዮጵያዊ) ልደታቸው
6.ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ (ጻድቃን)
7.ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ
8.ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን (የመቶ አለቃው)
† ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
4.አባ አሮን ሶርያዊ
5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘6🥰2🕊2😍2
አንዲት ድንግል መነኩሲት ከክብር ያሳነሳት ርጉም የሆነ አንድን መነኩሴ አገኙትና አባታችን መክረው ገሥረው ንስሓ ግባ አሉት፡፡ ነገር ግን እርሱ በወቅቱ እሺ ብሎ ንስሓ ሳይገባ ቀረ እንዲያውም በአባታችን ላይ ክፉ ያስበ ጀመር፡፡
Jul 27, 2026አንዲት ድንግል መነኩሲት ከክብር ያሳነሳት ርጉም የሆነ አንድን መነኩሴ አገኙትና አባታችን መክረው ገሥረው ንስሓ ግባ አሉት፡፡ ነገር ግን እርሱ በወቅቱ እሺ ብሎ ንስሓ ሳይገባ ቀረ እንዲያውም በአባታችን ላይ ክፉ ያስበ ጀመር፡፡
እንዲሁም ክህነት ሳይኖረው በውሸት ካህን ነኝ እያለ ሲቀድስ የነበረን አንዲን ዲያቆን አባታችን አግኝተው ‹‹የክርስቶስን ሥጋ ቅዱሳን መላእክትስ እንኳን መንካት የማይቻላቸውን አንተ በውሸት ለመንካት እንዴት ደፈርክ….›› ብለው በመምከር ንስሓ እንዲገባ አዘዙት፡፡ ነገር እነዚህ ሁለት ክፉ ሰዎች ንስሓ ከመግባት ይልቅ በአባታችን ላይ ክፋትን ያስቡ ጀመር፡፡ ወደ ንጉሡም ዘንድ ሄደው ‹‹በጸሎተ ሚካኤል የሚባለው መነኩሴ ‹ፈርዖንና ሠራዊቱን በባሕር ያሰጠመው እንደዚሁ ሁሉ ይህንንም ንጉሥ ያስጥመው› እያለ ይረግምሃል›› ብለው አወሩለት፡፡ ንጉሡም ተቆጥቶ አባታችንን ከነልጆቻቸው አስረው ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ አስረው አምጥተውም በንጉሡ ፊት ኦቆሟቸው፡፡ ንጉሠም አባታችንን ‹‹ለምን ትረግመኛለህ›› ሲላቸው እሳቸውም ‹‹ጠላትህን ውደድ ያለንን የአምላክ ሕግ እንከተላለን እንጂ አንተንስ የረገመህ የለም፤ ጳውሎስም በምንኩስና ሥርዓት ሰይጣንንም እንኳ አትርገሙ ብሏል፡፡ ሰይጣንን እንኳ መርገም የሚከለክል ከሆነ ንጉሥን እንዴት ይረግሙታል›› አሉት፡፡ ንጉሡም የከሰሱትን ሁለቱን ሰዎች አምጥቶ ለአባታችን አሳቸው፡፡ እሳቸውም የእያንዳንዳቸውን ክፉ ሥራ ለንጉሡ ነገሩት፡፡ ንጉሡም ይርታ ጠይቆ አባታችንን በሰላም አሰናበታቸው፡፡
ከዚህ በኋላ ጠላት ዲያብሎስ በቅዱሳን ላይ ክፉ ሥራ ይሠራ ዘንድ በንጉሡ ልብ ክፉ ሀሳብን አስነሣ፡፡ ንጉሡም ‹‹እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ያሉ ቅዱሳንን አምጧቸው›› ብሎ በሕዘቡ ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡ ቅዱሳንንም ሁሉ ሰብስበው አመጧቸው፡፡ አቡነ ዘአማኑኤል ከልጆቹና ከአባታችን ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሡም በቁርባንና በጸሎት ከእኔ ጋር ተባበሩ (አንድ ሁኑ) የምትፈልጉትን ሁሉ አሟላላችኋለሁ፣ ከእኔ ጋር መተባበርን እምቡ ካላችሁ ግን ወደ እርሱ እሰዳችሁ ዘንድ ሊቀ ጳጳሱ አዘዋልና ወደ ግብጽ በረኃብና በጥም ትሄዳላችሁ በመንገድም ሰውን የሚገድሉ ሽፍቶች አሉ›› አላቸው፡፡ የአቡነ ዘአማኑኤል ደቀ መዛሙርት ግን ‹‹እኛ ከአንተ ጋር እንተባበራለን፣ ያዘዝከንን ሁሉ እንፈጽማለን›› ብለውት የሚሹትን ሁሉ ሰጥቷቸው በሰላም አሰናበታቸው፡፡
መምህራቸው አቡነ ዘአማኑኤል ግን ይህን አልፈልግም ብሎ ብቻውን ተሰደደ፡፡ ንጉሡም ወደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል መኳንንቱን በመላክ ከእርሱ ጋር እንዲተባበሩ ወርቅና ብሩን ላሞችንና ጥሪቶችን ሁሉ እንደሚሰጣቸው ካልሆነ ግን ወደ ኢሩሳሌም መንገድ እንደሚልካቸውና በመንገድም በሽፍቶች እንደሚገደሉ ነገራቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ወርቅህና ብርህ ጥሪትህም ሁሉ ከአንተ ጋራ ለጥፋት ይሁንህ›› ብለው መለሱለት፡፡ ከልጆቹም ጋር አባታችንን በግዳጅ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሲወስዷቸው የንጉሡን ምግብ እንዳይቀምሱ ተማምለው አንደኛው መነኩሴ የገንዘባቸው የገዙትን ጎመን ተሸክሞ አብሯቸው ሄደ፡፡ ንጉሡም ባየው ጊዜ በጽኑ ጅራፍ እያስገረፈው እያለ ሕይወቱ በዚያው አለፈች፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ በግዞት ወደ አረማውያን መኖሪያ እየነዱ እንዲወስዷቸው አዘዘ፡፡
ወደ ግሎ ማክዳ ምድር እንዳደረሱት በዚያ ያሉ ቅዱሳን በደስታ ተቀበሉት፡፡ ስማቸውም ማርቆ፣ ክርስቶስ አምነ፣ አባ ሲኖዳና ማማስ ናቸው፡፡ ማማስም ለአባታችን ለጸሎት የሚሆነውን የድንጋይ ዋሻ አሳየው፡፡ አባታችንም ‹‹ይህች ዋሻ ለዘላለም ማረፊያዬ ናት›› ብሎ ውስጧን በድንጋይ ይወቅር ጀመር፡፡ በውስጧም አገልገሎቱን ፈጸመ፡፡ ወደ ቅዱሳኑ ወደ እነ አባ ማርቆስ፣ ክርስቶስ አምነ እና ሲኖዳ መጥተው የመቃብር ጉድጓድ እንዲቆፍሩ መልአክት ላከባቸው፡፡ በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ደቀ መዝሙሩ ዕንባቆም በአገኘውና ‹‹ነገ አባትህን ወደ መቃብር ትጥለዋለህ›› አለው፡፡
በማግሥቱም እሁድ ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ሲመክራቸው ዋለ፡፡ በመጨረሻም አንዱን ደቀ መዝሙሩን ብቻ አስከትሎ ወደ ዋሻዋ ግቶ በ4ቱም ማዕዘን ባረካት፡፡ ከዚህም በኋላ እጁንና እግሩን ዘርግቶ ነፍሱን በፈጣሪው እጅ አስረከበ፡፡ ነቢዩ ‹‹የጻዲቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው›› እንዳለ ያለ ምንም ጻዕር ዐረፈ፡፡ መዝ 115፡6፡፡
ደቀ መዛሙርቱም በመጡ ጊዜ ዐርፎ አገኙት፡፡ እነርሱም መሬት ላይ ወድቀው ‹‹አባት እንደሌላቸው እን ሙት ልጆች ለማን ትተወናለህ፣ በስውር የሠራነው ኃጢአትስ ማን ይነግረናል….›› እያሉ ጽኑ ልቅሶን አለቀሱ፡፡ አስቀደሞም እርሱ ደቀ መዛሙርቱ በስውር የሚሠሩትን ሥራ ሁሉ እርሱ በግልጽ እያየ ‹‹አንተ ይህን ሠርተሃልና ንስሓ ግባ›› እያለ ይመክራቸው ነበርና፡፡ ልቅሶአቸውንም ከፈጸሙ በኋላ ራሱ በጠረባት የድንጋይ ዋሻ ውስጥ ቀበሩት፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች ክፉዎች ናቸውና ከጊዜም በኋላ ደቀ መዛመርቱ የአባታችች ዐፅሙን አፍልሰው ወደ ሌላ ቦታ አስቀመጡት፡፡ እስከ ኢትዮጵያ ጳጳስ አባ ያዕቆብ መምጣት ድረስ ደብቀው አኖሩት፡፡ አባ ያዕቆብም የአባታችንን ዐፅም ያመጡለት ዘንድ አዘዘቸው፡፡ ከጊዜም በኋላ ዐፅሙን ወደ ጋስጫ አፍልሰውታል፡፡ ይኸውም ጋስጫ ከሊቁ አባታችን ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ሥር የሚገኝ ነው፡፡ ዋሻ ቤተ መቅደሱም በግሩም አሠራር የተሠራ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሱስንዮስ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ጸጋ ጥበብ ማስተዋልና ዕውቀት የተሰጠው ጃንደረባው ቅዱስ ሱስንዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከንጉሥ ቴዎዶስዮስ መኳንንቶች ውስጥ ነበር እርሱም ለሰው ሁሉ ርኅራኄ የሚያደርግ በሽተኞችንም የሚጐበኛቸውና የሚያረጋጋቸው ነበር። በችግርና በመከራ ስለሚኖሩትም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይጸልይ ነበር።
ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን የኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ የጉባኤው ርእሰ መንበር የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስም በመጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ሱስንዮስ ኤጲስቆጶሳቱንና ቅዱስ ቄርሎስን ያገለግላቸው ነበር። በዚያን ጊዜም በአስጨናቂ ደዌ ተይዞ ታመመ በደዌውም ውስጥ ሳለ ቃል ከሰማይ ወደ ታላቅ ሠርግ እንደሚጠራው ራእይን አየ።
ለቅዱስ ቄርሎስም ነገረው አባት ቄርሎስም ያድንህ ዘንድ ስለ አንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እለምነው ዘንድ ትፈቅዳለህን አለው እርሱም ገንዘቤን ለድኆች እስከምሰጥ አዎ አባቴ እሻለሁ ብሎ መለሰ። ቅዱስ ቄርሎስም ጸለየለትና ከደዌው ዳነ።ተነሥቶም ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ። ከዚህም በኋላ ተመልሶ ተኛና በሰላም አረፈ። ቅዱስ ቄርሎስም በላዩ ጸሎት አድርሶ ገንዞ ቀበረው በአረፈባት በዚች ዕለትም መታሰቢያውን እንዲአደርጉለት አዘዘ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ብጹዕ_አወ_ክርስቶስና_ሚስቱ
በዚህችም ቀን አስተዋይ የሆነ የተመሰገነ አወ ክርስቶስ አረፈ። ሚስት በአገባ ጊዜም በጾምና በጸሎት እያገለገሉ በድንግልና በአንድነት ኖሩ በሌሊትም ማቅ ለብሰው እየብቻቸው ይተኙ ነበር በቀንም እርሱ በጎችን እየጠበቀ በዱር ይውል ነበር እርሷም ለእንግዳ ምግብ እያዘጋጀች ትውል ነበር።
🥰7❤3😍2😘2🕊1
እግሩ ሥር ወድቀው ‹‹አንተ ብፁዕ ነህ የተሸከመችህም ማኅፀን ብፅዕት ናት… ›› ብለው ይቅር እንዲላቸው ለመኑት፡፡ አባታችንም ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ መነኮሳት ልጆቹ ሩቅ ቦታ እየሄዱ ውኃ በመቅዳት ቢቸገሩ ውኃን አፍልቆላቸዋል፡፡ ከዚህ…
Jul 27, 2026እግሩ ሥር ወድቀው ‹‹አንተ ብፁዕ ነህ የተሸከመችህም ማኅፀን ብፅዕት ናት… ›› ብለው ይቅር እንዲላቸው ለመኑት፡፡ አባታችንም ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ መነኮሳት ልጆቹ ሩቅ ቦታ እየሄዱ ውኃ በመቅዳት ቢቸገሩ ውኃን አፍልቆላቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ሰዎቹ አንድ ነገር ልንነግርህ እንወዳለን አሉት፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ንገሩኝ ባላቸው ጊዜ የአባቱን ሚስት ስላገባው ንጉሥ ነገሩትና ሄዶ እንዲያስተምረው እንዲገሠጸው ለመኑት፡፡ አባታችንም ‹‹በጽኑ ማሰሪያ ታስሬ በእስር ስለነበርሁ አልሰማሁም›› ካላቸው በኋላ ሄዶ ቢሰማው እንደሚመክረው ባይሰማውና ባይመለስ ግን እንደሚያወግዘው ነገራቸው፡፡ አባታችንም ልጆቹን አስከትሎ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄደ፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ‹‹ንጉሡ የአባቱን ሚስት በማግባቱ ሄደን ስንገሥጸው መከራ ቢያጸናብን ከሰማዕትነት ይቆጠርልናል›› ብሎ ሲነግራቸው ከሰማይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በሁሉም በላያቸው ላይ ሲወርድ አባታችን በግልጽ ተመለከተ፡፡ በረኃብ በጥም ሆነው ከተጓዙ በኋላ ትግራይ ሰወን ከምትባል ሀገር ደረሱ ንጉሡ ከዚያ ነበረና፡፡ ንጉሡም ቅዱሳኑ መክረው ሊመልሱት ካልሆነም ሊያወግዙት መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ ጭፍሮቹን ልኮ ቅዱሳኑን ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘ፡፡
ለማስፈራራትም ብዙ ጦረኛ ጭፍሮችንና የታሰሩ አስፈሪ አንበሶችን በፊቱ አቆመ፡፡ ቅዱሳኑንም ‹‹ስለምን ወደዚህ ከተማ መጥታችኋል?›› አላቸው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ‹‹እውነትን ስለማጽናት ከአንተ ጋር ለመነጋገር መጥተናል›› አሉት፡፡ ንጉሡም እሺ ንገሩን በላቸው ጊዜ አባታችን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለጠበቁ ደጋግ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ንጉሡን አስተማሩት፡፡
ትእዛዙንም ያልጠበቁትን አመፀኞችን እንደቀጣቸው ነገሩት፡፡ በመጨረሻም ‹‹የአባትህን ሚስት ሀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፣ የአባትህ ሀፍረተ ሥጋ ነውና›› የሚለውን ኦሪት ዘሌ 18፡6 በመጥቀስ አስተማሩት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ የአባቱን ሀፍረት ገልጧልና መሞትን ይሙት ሁለቱም በደለኞች ናቸውና›› የሚለውን የሙሴን ሕግና ሌላም ከሐዲስ ኪዳን እየጠቀሱ አስተማሩት፡፡ አባታችን ካስተማሩት በኋላም ‹‹የክርስቲያን ሚስቱ አንድ ብቻ ናት አንተ ግን ብዙ ሚስት አግብተህ የአባትህንም ሚስት አግብተሃልና ሕግ ተላልፈሃል›› አሉት፡፡ ንጉሡም ተምሮ ከመመለስ ይልቅ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱሳኑን ይደበድቧቸው አዘዘ፡፡ ሲደብድቧቸውም ታላቅ ጩኸት ተነሣ፡፡ ለየብቻ አስረው ካሳደሯቸው በኋላ ንጉሡ ለየብቻ ወደ እርሱ እያስመጣ አናገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም በ7 ገራፊዎች በታላቅ ጅራፍ አስገረፋቸው፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ምድር ላይ ፈሰሰ፡፡ ከደማቸውም እሳት ወጣና እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደላይ እየነደደ ቆየ፡፡ በዚህም ንጉሡ እጅግ ደንግጦ ብዙ ውኃ ከወንዝ እየቀዱ እሳቱን እንዲያጠፉ አዘዘ፡፡ የበዛ ውኃም ባፈሰሱበት ጊዜ የእሳቱ መጠን ይበልጥ ይጨምር ነበር፡፡ ዳግመኛም ብዙ ጨምረው ውኃ እየቀዱ ቢያፈሱበትም ማጥፋት እንዳልተቻላቸው ባየ ጊዜ ንጉሡ የወንዙን ውኃ በቦይ መልሰው እንዲያመጡ አዘዘ፡፡ ንግሥቲቱ ዛንመንገሣም ንጉሥ ዐምደ ጽዮንን ‹‹የእግዚአብሔርን ቁጣ አታስተውልምን›› ብላ ተናገረችው፡፡ ወዲያውም ነጭ የዝንብ መንጋ መጥቶ የንጉሡን ፈረሶችና በቅሎዎች ነከሳቸውና ሞቱ፡፡ ንጉሡም ፈርቶ በሌሊት ሸሽቶ ወጣ፡፡ ቅዱሳኑንም አንድ መውጫና መግቢያ ብቻ ባላት ደራ ወደምትባል ታላቅ ተራራ ቦታ አውጥተዋቸው እንዲያስሯቸው አደረገ፡፡
በዚያም የሚኖሩት አሕዛብ ስለሆኑ ክርስቶስንም አያውቁም፣ ነፍሰ ገዳዮችም ነበሩ፡፡ ንጉሡም አቡነ በጸሎተ ሚካኤልንና ልጆቹን ይገድሏቸው ዘንድ ወደ እነርሱ መልእክት ይልክ ነበር፡፡ ነገር ግን አባታችን ወንጌልን ሰበከላቸውና አሳምኖ የክርስቶስ ተከታዮች አደረጋቸው፡፡ እነርሱም ወደ ንጉሡ ሄደው ክርስቲያን እንደሆኑ ነገሩት፡፡
የአባታችን የተአምሩ ዜና በሀገሩ ሁሉ በተነገረ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሳንን አሳደው ስሙ ዝዋይ ወደሚባል ታላቅ ባሕር ውስጥ ያገቧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ አባታችንና ልጆቹንም አረማዊያን ወዳሉበት ደሴት አስገቧቸው፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ ከግዞት መልሰው በማውጣት በሴዋ አውራጃ እንዲያስተምሩ ፈቀደላቸው፡፡ ንጉሡም ናርእት የሚባሉ ሰዎችን በጦር ይወጋቸው ዘንድ ተነሣ፡፡ እነዚህም ሰዎች አስቀድመው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ስብከት በጌታችን ያመኑ ክርስቲያኖች ሆነዋል፡፡ ንጉሡም ድጋሚ አባታችንን አሠራቸውና ማስፈራራት ጀመረ፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ግን የንጉሡን ማስፈራራት በመናቅ ተናገሩት፡፡ እንዲህም አሉት፡- ‹‹በጦር ብታስወጋኝ ሕዝቅኤልን አስበዋለሁ፤ አንበሶች እንዲበሉኝ ብታዝ ዳንኤልን አስበዋለሁ፤ ወደ እሳት ውስጥ ብትጥለኝ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን አስባቸዋለሁ፤ በእንጨት መቁረጫ መጋዝ እንዲቆርጡኝ ብታዝ ኢሳይያስን አስበዋለሁ፤ በድንጋይ እንዲወግሩኝ ብታዝ ኤርሚያስን አስበዋለሁ፤ በሰይፍ አንገቴንም እንቆርጡኝ ብታዝ በወንደሙ ፊሊጶስ ሚስት ምክንያት የገደለው የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ መጥምቅን አስበዋለሁ፤ ልዩ ልዩ መከራዎችን ብታጸናብኝም መከራ የተቀበሉትን ሐዋርያትንና ሰማዕታትን አስባቸዋለሁ›› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ ንጉሡም ከዚህ በኋላ አባታችንን ‹‹ይቅር ይበሉኝ›› አላቸው፡፡ በአባታችን ምክር ብዙ የንጉሡ መኳንንቶችም ክፉ ሥራቸውን በመተው በንስሓ ተመለሱ፡፡ ንጉሡም አንዲት ሚስቱን ለጭፍራው አሳልፎ ሰጥቶት ነበርና እርሷም አባታችንን ስታገኛቸው ንስሓ ገባች፡፡ ንጉሡም ይህቺ የተዋት ሚስቱ ንስሓ እንደገባች ሲሰማ ‹‹ዛሬ ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኝቼ ንስሓዋን አስተዋታልሁና ይዛችሁ አምጡልኝ›› ብሎ ጭፍሮቹን ላከ፡፡ አባታችንም ሴቲቱን በንስሓዋ ወደዋት ነበርና አሁን ንጉሡ በእርሷ ላይ ሊያደር ያሰበውን ልጆቹ ነገሩት፡፡ አባታችንም ይህን ሲሰማ የቀረበውን ማዕድ ሳይቀምሱ አስነስቶ ሁሉም እንዲጸልዩ አዘዘና እርሱም ቆሞ መጸለይ ጀመረ፡፡ በዚያችም ሌሊት ወዲያው ንጉሡ ድንገት በጠና ታመመ፡፡ ያንጊዜም ንጉሡ ‹‹ይህ ድንገኛ ሕመም የመጣብኝ አቡነ በበጸሎተ ሚካኤል ጸሎት ነው›› ብሎ ያችን ሴት ካመጡበት ቦታ እንዲመልሷት አዘዘ፡፡ ወደ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ! ይቅር በለኝ፣ ይህ ሕመም ያገኘኝ በአንተ የተማጸነችውንና ንስሐ የገባችውን ሴት በኃጢአት ላረክሳት ስላሰብኩ ነው፤ አሁንም ልጅቷን ወደነበረችብ መልሻታሁና አባቴ ሆይ ከዚህ በሽታዬ ከዳንኩ በሕግህ እኖራለሁ›› ብሎ መልእክተኛ ላከ፡፡ አባታችንም የቤተ መንግሥቱን ካህናተ ደብራዎች ወቀሳቸው፡፡ ‹‹ከእናንተ በቀር ይህን ንጉሥ የሚያስተው የለም ያለ ሥራው እያሞገሳችሁ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲሠራ የምታድርጉ እናንተ ናችሁ›› ብለው በተናገሯቸው ጊዜ ደብተራዎቹም ‹‹እኛም በሕግህ እንኖራለን ይቅር በለን፣ ጉሡንም ይቅር ብለህ ከመጣበት ደዌው ፈውሰው›› ብለው ለመኗቸው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ‹‹ንጉሡ ከኃጢአቱ ተመልሶ ንስሓ እንደማይገባ እኔ ዐውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ሞቱ በእኔ ቃል ምክንያት እንዳይሆን እግዚአብሔር ከበሽታው ይፈውሰው›› አሏቸው፡፡ ካህናቱም ‹‹ከደዌው በሚድን ነገር እንወስድለት ዘንድ የእግርህን ትቢያ ስጠን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ‹‹የእግሬን ትቢያ አልሰጣችሁም ነገር ግን ሂዱ ከደዌው ሁሉ ተፈውሶ ታገኙታላችሁ›› አሏቸው፡፡ ካህናቱም ወደ ቤተ መንግሥት በሄዱ ጊዜ ንጉሡን ከደዌው ፍጹም ተፈውሶ አገኙት፡፡
😍5❤3😘2🥰1🕊1
ለወላጆቹ አብሯት እንዲተኛ መስማማቱን ነገረቻቸው፡፡ ነገር ግን በዚያች ሌሊት በጸሎተ ሚካኤል ማንም ሳያየው ተነሥቶ ከእናት አባቱ ቤት ወጥቶ ሄደ፡፡
Jul 27, 2026ለወላጆቹ አብሯት እንዲተኛ መስማማቱን ነገረቻቸው፡፡ ነገር ግን በዚያች ሌሊት በጸሎተ ሚካኤል ማንም ሳያየው ተነሥቶ ከእናት አባቱ ቤት ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ደብረ ጎል አደረሰው፣ ይኸውም ቀሲስ አኖርዮስ በብቸኝነት ሸሽቶ የሚጋደልባት ደብረ ጽሙና ናት፡፡ በጸሎተ ሚካኤልም በዚያ ከመነኮሰ በኋላ ጽኑውን የተጋድሎ ሕይወት መኖር ጀመረ፡፡ በጾም በጸሎት ሆኖ ቀን የጉልበት ሥራ ይሠራል ሌሊት ቆሞ ሲጸልይ ያድራል፡፡ 90 ሸክም የወይራ ፍልጥ እየፈለጠ ለቤተ ክርስቲያኑና ለአበ ምኔቱ ያመጣ ነበር፡፡ እንጨቱንም ሲቆርጥና ሲፈልጥ የብረት መቆፈሪያ ብቻ ይጠቀም ነበር እንጂ ስለታም የሆኑ ምሳርና መጥረቢያ አይጠቀምም ነበር፡፡ ምክንያቱም የወጣትነት ኃይሉና ሥጋው በእጅጉ ይደክም ዘንድ ነው፡፡ እንዲህም ሲሠራ ጾም፣ ጸሎት፣ ሥግደቱን አያስታጉልም ነበር፡፡ እስከ 4 ቀንም የሚጾምበት ጊዜ አለ፡፡ በጸሎተ ሚካኤል በእንደዚህ ያለ ጽኑ ተጋድግሎ 13 ዓመት በድቁና ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሥጋውን ማድከም ቢሳነው ከእኩለ ቀን ጀምሮ ፀሐይ ስታቃጥል አለቱ ሲግል ጠብቆ ሄዶ አለቱ ላይ ይተኛል፣ ከግለቱም የተነሣ የሥጋው ቆዳ እስኪበስል ድረስ በአለቱ ላይ ይተኛል፡፡
በጸሎተ ሚካኤልም ከዚህ በኋላ ቅስና ተሾመ፡፡ ወደ ዋሻም ገብቶ በዓቱን አጸና፡፡ ከምግባር ትሩፋቱ የተነሣ ሌሎች ቅዱሳን ሁሉ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እንደ መልአክ ያዩት ነበር፡፡ እርሱም ከሰው ጋር ላለመገናት ብሎ በቁመቱ ልክ ጉድጓድ ቆፍሮ መጻሕፍቱን ብቻ ይዞ ከዚያ ገባ፡፡ ቅዱሳንም መጥተው ‹‹አንተንም ሌሎችንም የምትጠቅመው ከዚህ ጉድጓድ ውስጥተህ ብታስተምር ነው…›› እያሉ በብዙ ልመና ከጉድጓዱ አወጡት፡፡ ከዚህም በኋላ የተሰወረውን ሁሉ በግልጥ የሚያይ ሆነ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን ያስተምራል፡፡ ወደ በዓቱም እየገባ በቀን 8ሺህ ስግደትን ይሰግዳል፡፡ ከስግደቱም ብዛት የተነሣ ምድሪቱ ጎድጉዳ እስከ ጉልበቱ ትውጠው ነበር፤ ከሰገደበትም ቦታ ወዙ መሬትን ጭቃ እስኪያደርጋት ድረስ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡
ከመነኮሰበት ጊዜ ጀምሮ ተቀምጦ በእጁ ላይ አረፍ ይላል እንጂ በጎኑ ተኝቶ አያውቅም፡፡ ጌታችንም ተገልጦለት ማደሪያው ከጴጥሮስና ከጳውሎስ ጋር መሆኑን ነግሮታል፡፡ አባታችን ወደተለያዩ ገዳማት በመሄድ የቅዱሳንን በረከት ተቀበለ፡፡ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ ከአቡነ አረጋዊ ጋር ተነጋገረ፣ ወደ አባ መጣዕ ቤት በመሄድ ከአባ ሊባኖስ ጋር ተነጋገረ፣ ወደ አባ ገብረ ናዝራዊ ገዳምበሄድም ከጻዲቁ ጋር ተነጋገረ፡፡ ከሰንበት በቀር እህል ባለመቅመስ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ሱባኤ በያዘ ጊዜ እግዚአብሔር የተለያዩ ምሥጢራትን ይገልጥለታል፡፡ በሄኖክ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያለው የሰማይ ምሥጢር ሁሉ ተገለጠለት፡፡ የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የብርሃናት አፈጣጠራቸው፣ የንፋስ መስኮቶቸን ሁሉ በግልጥ ባየ ጊዜ ነቢዩ ሄኖክን ‹‹ሄኖክ ሆይ የራእይህ ምሥጢር እንደዚህ ብሩህ ነውን? የምሥጢርህ መሰወር እንዲህ ግልጥ ነውን?›› ይለዋል፡፡ ዳግመኛም የነቢያት የትንቢታቸው ራእይ ይገለጥለት ዘንድ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ሱባኤ በያዘ ጊዜ የመጻሕፍቶቻቸው ምሥጢር ይገለጥለታል፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በመማለጃ (በጉቦ) ክህነት በሚሰጥ ጳጳስ ምክንያት በሐዋርያት ግዝት ዓለም ሁሉ በግዝት እንደሚኖር ተመለከተ፡፡ ወደ ጳጳሱ አባ ዮሐንስ ዘንድ ሄደና አገኘው፡፡ ጳጳሱም ‹‹ልጄ በጸሎተ ሚካኤል ደህና ነህን?›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹ደህና ነኝ›› ባለው ጊዜ ጳጳሱ ‹‹ስለምን መጣህ?›› አለው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ሰው ሁሉ ከአጠገባቸው እንዲርቅ ካደረገ በኋላ ጳጳሱን እንዲህ አለው፡- ‹‹ቅዱሳን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው መጽሐፍ ‹በመማለጃ ክህነትን የተቀበለና የሰጠ የተለየ የተወገዘ ነው› ያሉትን አልሰማህምን?›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እጄን በጫንኩበት መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ዘንድ ተናገሩ ብሎ በሐዋርያት እግር ሥር ወርቁን አምጥቶ ባፈሰሰው ጊዜ ሲሞን መሠርይን ጴጥሮስ እንዳወገዘው አልሰማህምን? ጴጥሮስም ‹ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ በወርቅ የምትገዛ ይመስልሃልን?› አለው፡፡ በመራራ መርዝ ተመርዘህ አይሃለሁና፡፡›› ሐዋ 8፡19፡፡ ‹‹አባቴ ሆይ የውኃ ምንጭ የፈሰሰ የደፈረሰ እንደሆነ የምፈሰውም ውኃ ሁሉ ይደፈርሳል፡፡ ምንጩ ንጹሕ ከሆነ ግን የውኃው ፈሳሽም ሁሉ የጠራ ይሆናል፡፡ አንተ በሐዋርያት ውግዘት ብትገባ ሁሉም የተወገዘ ይሆናል›› አለው፡፡ ጳጳሱም ተቆጥቶ ‹‹አንተ ከእኔ ተማር እንጂ ለእኔ መምህር ልትሆነኝ ትፈልጋለህ?›› በማለት ተናገረው፡፡ በወንጌል ላይ ‹‹እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምዘጉ ወዮላችሁ፣ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም ትከለክሏቸዋላችሁ›› ያለው የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ላይ ደረሰ፡፡ ማቴ 23፡14፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወደ ካህናተ ደብተራ በመሄድ ከንጉሡ ጋር ያገናኙት ዘንድ ጠየቃቸው፡፡ የቤተ መንግሥት ካህናትም ለንጉሡ ነግረውለት አስጉት፡፡ አባታችንም ንጉሡን ‹‹መንግሥትህ በግዝት ጨለመች፣ ሐዋርያት ጥምቀትም ቢሆን ወይም ክህነት በመማለጃ (በጉቦ) የሚሰጥንና የሚቀበልን አስቀድመው ሐዋርያት አውግዘዋል›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነሆ ይህ ጳጳስ የሐዋርያትን ትእዛዝ ተላልፎ በጉቦ ክህነት ይሰጣል፣ ጳጳሱም በሐዋርያት ግዝት ከገባ በእጁ የተጠመቁና የተሾሙት ሁሉ የተወገዙ ይሆናሉ፣ እንደዚሁ ዓለሙ ሁሉ በውግዘት ውስጥ ይኖራል›› አሉው፡፡ ንጉሡም ሦስቱ አንድ ላይ ሆነው እንዲመጋገሩ ቀጠሮ ሰጠውና በሌላ ቀን ሦስቱም ተገናኙ፡፡ ጳጳሱም ለንጉሡ ‹‹ይህ በጸሎተ ሚካኤል እኔን ከሹመቴ አንተን ከመንግሥትህ ሊሽረን ይፈልጋል ስለዚህ ልጄ የምነግርህን ስማኝ አስረህ ወደ ትግራይ ይወስዱት ዘንድ እዘዝ›› አለው፡፡ ንጉሡም የጳጳሱት ክፉ የሀሰት ምክር በመስማት ‹‹ይሁን አንተ እንዳልከው ይሁን›› በማለት አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን በጽኑ ማሠሪያ አስረው በግዞት ወደ ሳርድ ይወስዱት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም እንደታዘዙት አደረጉና አባታችን በዚያ በግዞት ሁለት ዓመት ታስሮ ቆየ፡፡ ከዚያም ወደ ጽራይ ምድር ወሰዱትና ቆራር በተባለ ቦታ ለተሾመው ሰው ‹‹እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ይህንን መነኩሴ እሰረው›› ብለው ሰጡት፡፡ የሀገሩ ሰዎችም አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እጅግ ወደዱትና ወደ ጽራር ሀገር ገዥ ሄደው እንዲፈታው ለምነው ከእስራቱ አስፈቱት፡፡ በሀገራቸውም ወንጌልን አስተምሮ ብዙ ተአምራት እያደረገላቸው ከቆየ በኋላ ወደ ልጁ ሳሙኤል ለመሄድ ተነሣ፡፡ ሲሄድም አቡነ ገብረ ናዝራዊ ጋር ደረሰና አብረው ሳሙኤል ጋር ደረሱ፡፡
አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በቅዳሴ ጊዜ ጌታችን በሕፃን ልጅ አምሳለ በመንበሩ ተቀምጦ ስለሚያየው ሁልጊዜ ሲቀድስ ያለቅሳል፡፡ አንድ ቀን አባታችንን ሲቀድስና ሕፃኑን በመንበሩ ላይ ሲሠዋው ወንድሞቹና ልጆቹ አይተውት በድንጋጤና በፍርሃት ሆነው አልቅሰዋል፡፡ የሕፃኑንም ሥጋ በፈተተው ጊዜ የአባታችን እጁ በለመለመ ሥጋ ይመላል፡፡ ቅዳሴውም ከተፈጸመ በኋላ ሁሉም መጥተው ሥጋወደሙን በፍርሃት ይቀበላሉ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አስቀድመው ስለ ሥጋወደሙ መለወጥ ጥርጣሬ የነበራቸው ሰዎች ስለነበሩ የእነርሱን ጥርጣሬ ዐውቆ አባታችን ቅዳሴውን ከፈጸመ በኋላ ‹‹ኅብስቱ የክርስቶስ ሥጋ ወይኑም ደሙ መሆን ይችላልን እያላችሁ በልባችሁ ስታስቡ አይቻለሁና ይኸው ዛሬ በግልጽ እንዳያችሁት አማናዊ ሆኖ ይለወጣልና ተጠራጣሪ አትሁኑ›› ባላቸው ጊዜ
😘5❤2🥰2😍2🕊1
#ሐምሌ_21
Jul 27, 2026#ሐምሌ_21
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ አንድ በዚህች ቀን #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፣ ታላቁ አባት #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ዕረፍቱ ነው፣ ጃንደረባው #ቅዱስ_ሱስንዮስ አረፈ፣ አስተዋይ የሆነ የተመሰገነ #ቅዱስ_አወ_ክርስቶስ አረፈ፣ ምፅዋት መስጠትንም የሚወድ #ቅዱስ_ላእከ_ማርያም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባሕር
ሐምሌ ሃያ አንድ በዚህች ቀን አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ከደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር የተሻገሩት ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፡፡
አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ሲሆኑ፤ አባታቸው ክርስቶስ ሞዐ ሲሆን እናታቸው ስነ ሕይወት ይባላሉ፡፡ ደጋግ የሆኑ ወላጆቻቸው በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ በአደጉም ጊዜ ከአባ ዘካርያስ እጅ መነኮሱ፡፡ ታላላቅ ቅዱሳን እስኪያደንቋቸው ድረስ በጽኑ ተጋደሎ ሲኖሩ ጌታችን ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር ተገልጦላቸው በንፍሐት መንፈስ ቅዱስን አሳደረባቸው፡፡ "ከእናትህ ማኅፀን የመረጥኩህ ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ ለብዙዎች ወንጌልን ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ፡፡ አንተን የሰማ እኔን ሰማ፣ አንተንም ያልሰማ እኔን ያልሰማ ነው" ካለቸው በኋላ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ፡፡
አባታችን ቅስናን ከተሸሾሙ በኋላ ወንጌልን መስበክ ጀመሩ፡፡ እነ አቡነ አብሳዲን ጨምሮ ብዙዎችንም አመንኩሰው ደቀ መዛሙርቶቻቸው አደረጓቸው፡፡ እጅግ አስገራሚ ተአምራትን በማድረግ ለብዙ ሕሙማን መድኃኒት ሆኗቸው፡፡
ልጆቻቸውን ሰብስበው ከመናፍቃን ጋር በፍጹም እንዳይቀላቀሉ በመምከር አቡነ አብሳዲን ሾመውላቸው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ቅዱሳት ቦታዎችን ተሳለሙ፡፡ በመንገዳቸውም የክርስቶስን ወንጌል እየሰበኩ ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሷቸው፡፡ ወደ አርማንያም ሄደው ወደ ኢያሪኮ ባሕር በደረሱ ጊዜ መርከበኞችን እንዲያሳፍሯቸው ቢለምኗቸው እምቢ አሏቸው፡፡ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ግን አጽፋቸውን በባሕሩ ላይ ዘርግተው በስመ ሥላሴ አማትበው አጽፋቸውን እንደመርከብ አድርገው ልጆቻቸውን ይዘው ባሕሩን ተሻገሩ፡፡ ልጆቻቸውን ‹‹ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ፣ ለእኔ ግን ከእናንተ አንዱ እንደሚጠፋ ይመስላኛል›› አሏቸው፡፡ ይህንንም እንዳሉ ከመካከላቸው አንዱ የቂም በቀል መከማቻ ነበርና ወዲያው ሰጠመ፡፡
አባታችን አርማንያ ደርሰው ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ቡራኬን ከተሰጣጡ በኋላ ማስተማር ጀመሩ፡፡ የአርማንያ ሰዎች ሁሉም በሃይማኖት አንድ እስኪሆኑ ድረስ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ አስተምረው አጠመቋቸው፡፡ አባታችን ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታችን ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ከሰጣቸው በኋላ መስከረም 18 ቀን ዐርፈው ሊቀ ጳጳሳቱና ካህናቱ በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ቀብረዋቸዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል
በዚህችም ቀን ታላቁ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ከካህናት ወገን የሆነው አባቱ ማርቆስ ሲሆን እናቱ እግዚእ ክብራ ትባላለች፡፡ እግዚእ ክብራም ወደ ወላጆቿ በሄደች ጊዜ ‹‹ከመኳንንቶቹ ለአንዱ እናጋባታለን›› ብለው ወደ ባሏ ተመልሳ እንዳትሄድ ከለከሏት፡፡ ማርቆስም ስለዚህ ነገር አዝኖ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ሚስቱን እንደከለከሉት ለአንድ መነኩሴ ነገረው፡፡ መነኩሴውም ሄዶ ቢጠይቃቸው ወላጆቿ ድጋሚ ለመነኩሴውም ከለከሉት፡፡ ማርቆስም እየተመላለሰ መነኩሴውን ቢያስቸግረው ይዞት ሄደ ነገር ግን ወላጆቿ ጥላቻቸውን አበዙባቸው፡፡ መነኩሴውም ‹‹ማርቆስንና ሚስቱን ለአንድ ቀን ብቻ ሁለቱን አንድ ላይ ላናግራቸው›› በማለት ይዟቸው አደረ፡፡ እርሱም በማደሪያው እንዲያድሩ ከነገራቸው በኋላ ‹‹በዚህች ሌሊት ሩካቤ ሥጋ ሳትፈጽሙ እንዳታድሩ›› አላቸው፡፡ ሁለቱም በመነኩሴው ቤት አድረው ሳለ ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለማርቆስ ተገለጠለትና ‹‹ሚስትህ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ በወለደችም ጊዜ ስሙን በጸሎተ ሚካኤል ትለዋለህ፣ ለቤተ ክርስቲያንም ዐምድ ይሆናል›› አለው፡፡ ማርቆስም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ከሚስቱ ጋር ተገናኘና አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ተፀነሱ፡፡
እግዚእ ክብራ ከፀነሰች በኋላ ፊቷ እንደፀሐይ የሚያበራ ሆነ፡፡ የታመሙ ሰዎችም ሆዷን በነኩት ጊዜ ይፈወሱ ነበር፡፡ በወለደችም ጊዜ በቤቷ ውስጥ ቀስተ ደመና ተተክሎ ታየ ሲሆን አስቀድሞ መልአኩ ስሙን እንዳወጣለት ‹‹በጸሎተ ሚካኤል›› አሉት፡፡ አባቱም ካህን ነውና ምግባር ሃይማኖትን ጠንቅቆ እያስተማረ አሳደገው፡፡ በጸሎተ ሚካኤል ገና ሕፃን ሳለ መዝሙረ ዳዊትን፣ የነቢያት ጸሎትን በማዘውተር በጾም በጸሎት ሲጋደል ወላጆቹ ‹‹ይህ ሕፃን ልጃችን በረሃብ ይሞትብናል›› በማለት በግድ እየገረፉ እንዲመገብ ያስገድዱት ነበር፡፡ በግድ አፉን ይዘው ምግብ ከጨመሩበር በኋላ ‹‹ይኸው ጾምህን ፈታህ›› ሲሉት እርሱ ግን በሕፃን አንደበቱ ‹‹እኔ በፈቃዴ በአፌ ውስጥ ብጨምረው ጾሜን በሻርኩት ነበር፣ እናንተ በአፌ ውስጥ በግድ ከጨመራችሁት ግን ጾሜ አይሻርም›› እያላቸው እስከ ማታ ይጾም ነበር፡፡
ከዚህም በኋላ አባቱ ወደ ጳጳስ ዘንድ ወስዶ ዲቁና እንዲሾም አደረገው፡፡ ባደገም ጊዜ አባቱ ማርቆስ ሚስት ያጋባው ዘንድ ባሰበ ጊዜ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ሸሽቶ ወደ ገዳም ገባ፡፡ አበ ምኔቱም ከእርሱ ጋር አስቀምጦ የምንኩስናን ቀንበር ያሸክመው ዘንድ ብዙ ፈተነው፡፡
ወላጆቹም መጥተው አስገድደው ከገዳሙ ሊያወጡት ሲሉ እምቢ ቢላቸው እናቱ ዘመዷ ወደሆነው ንጉሡ ውድም ረአድ በመሄድ ስለ ልጇ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ከወታደሮቹ ውስጥ በአለንጋ ይዞ የሚገርፍ ወታደር ላከላት፡፡ የተላከው ወታደርም በጸሎተ ሚካኤልን እየገረፈ በማስገደድ ከገዳም አውጥቶ ለወላጆቹ ሰጠው፡፡
በጸሎተ ሚካኤልም በወላጆቹ ቤት ሳለ ወላጆቹን ‹‹እመነኩስ ዘንድ እስካልተዋችሁኝ ድረስ የቤታችሁን ምግብ አልበላም›› ብሎ ማለ፡፡ አባቱም ‹‹ምግብ ካልበላህ›› በማለት ጽኑ ድብደባ እየደበደበው ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ፡፡ በጸሎተ ሚካኤልም ሦስቱንም ቀን እቤት ሳይገባ የቀን ፀሐይ ሐሩሩ የሌሊት ውርጭ ቅዝቃዜ እየተፈራረቀበት እቤትም ሳይገባ በደጅ ሆኖ በጾም በጸሎት ቆየ፡፡ በዚህም በአባቱ እጅ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ጌታንም ‹‹ለምድር ሰላምን ያመጣሁ አይምሰላችሁ ሰይፍን ነው እንጂ፡፡ የመጣሁትስ ሰውን ከአባቱ ልጅንም ከእናቷ ልለይ ነው›› ያለው ቃል በአባታችን ላይ ተፈጸመ፡፡ ማቴ 10፡34፡፡ አባቱ ማርቆስም ሥጋው እስኪያልቅ ድረስ በግርፋት ብዛት የልጁን ሀሳብ ለማስለወጥ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ሲያውቅ መልሶ ወደ ገዳሙ እንዲወስዱት አገልጋዮቹን ላካቸው፡፡ አበ ምኔቱም መምህር ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማር ሲነግረው ‹‹እኔ መነኩሴ መሆን እንጂ መምህር መሆን አልፈልግም›› በማለቱ ሳይስማሙ ቀሩና ወደ ሌላ ገዳም ወሰዱት፡፡ በዚያም እንዲሁ ሆነ፡፡ መልሰውም ወደ አባቱ ቤት ባመጡት ጊዜ ወላጆቹም ልጃቸው የምንኩስናን ሀሳቡን ይተወው ዘንድ ከአንድ ሴት ጋር ተማክረው በዝሙት እንድትጥለው ተነጋገሩ፡፡ ሴቷም ወደ በጸሎተ ሚካኤል ቀርባ በዝሙት ልትጥለው ብዙ ሞከረች፡፡ እርሱም ዐውቆ ‹‹ከእኔ ጋር አብረሽ መተኛት ደስ ካሰኘሽ እሺ ከእስራቴ ፍቺኝና እንተኛለን›› አላት፡፡ ይህንንም ያላት ከታሰረበት እንድትፈታውና እንዲያመልጥ ነው፣ እርሷ የእውነት መስሏት ደስ አላትና ሄዳ
😘4❤3😍3🥰2🕊2
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 27, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
🥰4😍3😘1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 27, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
✝በዚህች ሐምሌ 20 ዕለት የጻድቁ ዓቢየ እግዚእ ታናሽ እህት ትቀድሰነ ማርያም ልጅ፤ የደብረ ሃሌሉያው ኮከብ አቡነ ሳሙኤል (በ1347 ዓ/ም) ዐረፉ
Jul 26, 2026✝በዚህች ሐምሌ 20 ዕለት የጻድቁ ዓቢየ እግዚእ ታናሽ እህት ትቀድሰነ ማርያም ልጅ፤ የደብረ ሃሌሉያው ኮከብ አቡነ ሳሙኤል (በ1347 ዓ/ም) ዐረፉ
✝እናታቸው ትቀድሰነ ማርያም አባታቸው ይስሐለነ እግዚእ ይባላሉ።
✝የመጀመሪያ ስማቸው አቡነ አብየ እግዚእ ነአኩቶ ለአብ ብለዋቸዋል
✝አባ እንጦንስ ኢትዮጵያዊ አቡነ ሳሙኤል ብለዋቸዋል።
✝ደቀመዝሙራቸውአባገብረ መስቀል ይባላሉ።
✝️ "በረከታቸው በዝታ ትደርብን!"
❤9🥰3😘3😍2💯2
#ሐምሌ_20 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ በዚህች ቀን #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋራ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣ ታላቅና ክቡር የሆነው የ…
Jul 26, 2026#ሐምሌ_20 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ በዚህች ቀን #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋራ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣ ታላቅና ክቡር የሆነው የሠራዊት አለቃ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ሐምሌ ሃያ በዚህች ቀን እመቤታችን ድንግል ማርያም…
🥰10❤4🕊3😘3😍2
ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው።
Jul 26, 2026ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው።
ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል።
በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት።
በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣ ወይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ።
ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት አንተ ከሀዲ እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ።
ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው።
ከዚያ በኋላም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩለት ስብጥ በሚባል በአባቱ አገርም በተሠራች ገዳም ሥጋውን አኖሩ ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ተደረጉ ታላቅ ፈውስም ሆነ።
† ሐምሌ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም (በሰማንያ ዕለት)
2.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ
4.አራት መቶ አራት ሰማዕታት (የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር)
5.ቅድስት አውስያ (የማር ቴዎድሮስ እናት - በልጇ ምክንያት ያመነች እናት ናት)
† ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
😘8❤3💯3🥰2😍2
#ሐምሌ_20
Jul 26, 2026#ሐምሌ_20
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ በዚህች ቀን #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋራ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣ ታላቅና ክቡር የሆነው የሠራዊት አለቃ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም
ሐምሌ ሃያ በዚህች ቀን እመቤታችን ድንግል ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋራ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣
ለስም አጠራሯ ክብር ይሁንና እመ ብርሃን ድንግል ማርያም በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች:: በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት እንደ አንዱ አይቆጠርም:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሊቃውንት በዓታ ከበዓታ ጋር ይስማማል ብለው የታኅሣሥ ሦስትን በዓል ከሰላሳ ሦስቱ ደምረውታል::
እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ሁለት ጊዜ ሲሆን:-
1.ዛሬ የምናከብረውና በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የገባችበት ነው:: (ከግንቦት 1 ጀምረን እናስላው 80 ቀን ይመጣል::)
ኦሪት እንዳዘዘው ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ንጽሕት ሕፃን ድንግል ማርያምን ታቅፈው የርግብ ልጆች (ግልገሎች) ዋኖስም ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሒደዋል::
ካህናቱ ዘካርያስና ስምዖን ወጥተው በደስታ ተቀብለዋቸዋል:: እመቤታችን ለወላጆቿ ማኅጸን የከፈተች በኩር ናትና በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋታል::
2.ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደ ስዕለታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ወስደው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋት ተመልሰዋል::
እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን:: በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቴዎድሮስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነው የሠራዊት አለቃ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ ። የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።
ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ።
አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።
ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው።ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው።
የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።
ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ አለው።
ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ የበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና። ንጉሡም እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ አለው።
በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በእግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ አላቸው። እነርሱም ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን አሉት እርሱም ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ አላቸው።
ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ አሉት።
ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው ጌታዬ አምላኬ ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከአእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን።
ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በመስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።
አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።
በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው።
ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል እግዚአብሔርም ይበቀልላታል አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ።
ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።
🥰9😍4❤2💯2😘2
🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
Jul 25, 2026🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
😍4❤3🥰3😘1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 25, 2026በአንዲትም ዕለት ቅዱስ በጥላን በከተማው አደባባዮች ሲያልፍ እባብ የነደፈውን አንድ ሰው ሲጨነቅ አየው እባቡም በርሱ ዘንድ ቆሞ ነበር በልቡም የመምህሬን ቃል ልፈትን ክብር ይግባውና በክርስቶስ ከአመንክ በስሙ ታምራት ታደርጋለህ ብሎኛልና…
Jul 25, 2026በአንዲትም ዕለት ቅዱስ በጥላን በከተማው አደባባዮች ሲያልፍ እባብ የነደፈውን አንድ ሰው ሲጨነቅ አየው እባቡም በርሱ ዘንድ ቆሞ ነበር በልቡም የመምህሬን ቃል ልፈትን ክብር ይግባውና በክርስቶስ ከአመንክ በስሙ ታምራት ታደርጋለህ ብሎኛልና አለ። እባብ ወደ ነከሰውም ሰው ቀርቦ ኃይሉን ይገልጽለት ዘንድ እባቡንም ይገድለው ዘንድ ሰውዬውን ያድነው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ረጅም ጸሎትን ጸለየ ያን ጊዜም ሰውዬው ያለ ምንም ጉዳት ድኖ በጤና ተነሣ ከይሲውም ወደቀ ወዲያውም ሞተ። የበጥላንም ሃይማኖቱ ተጨመረለት።
ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ሁልጊዜም ወደ ቄሱ እየመጣ ይማር ነበር። በአንዲት ቀንም ያድነው ዘንድ አንድ ዕውር መጣ። የቅዱስ በጥላን አባትም ባየው ጊዜ ዕውሩን ከውጭ መልሶ ሰደደው በጥላንም አባቱን ማነው የፈለገኝ ብሎ ጠየቀው አባቱም ልታድነው የማትችል አንድ ዕውር ነው አለው።
እርሱም አባቱን የእግዚአብሔርን ክብር ታይ ዘንድ አለህ አለው ይህንንም ብሎ ዕውሩን ጠራውና ዐይኖችህ ቢገለጡ ያዳነህን ታመልከዋለህን አለው ዕውሩም አዎን አምናለሁ አለ ቅዱስ በጥላን በዕውሩ ላይ ረጅም ጸሎትን ጸለየ እጆቹንም በዕውሩ ዐይኖች ላይ አኑሮ እንድታይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመን አለው ወዲያውኑም ዐይኖቹ ተገለጡ።
አባቱም ይህን ድንቅ ሥራ በአየ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ከዕውሩ ጋር አመነ ቅዱስ በጥላንም ወደ ቄሱ ወሰዳቸውና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ከዚህም በኋላ ባሮቻቸውን ነፃ አወጡ ገንዘባቸውንም ለድኆችና ለችግረኞች አከፋፈሉ።
ቅዱስ በጥላንም ጥበብን ያደርግ ነበር። ያለ ዋጋም ሰዎችን ያድናቸው ነበር። ነገር ግን ክብር ይግባውና በክርስቶስ እንዲያምኑ ይሻ ነበር። ስለዚህም ጥበበኞች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሡ ወደ ንጉሥም ሒደው ከቄሱ ጋራና ከአዳነውም ዕውር ጋራ በጌታችንም ከአመኑ ከብዙዎች ጋራ ከሰሱት። ወደ ንጉሡም በቀረቡ ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ ለአማልክት ሠዉ አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ በጥላንን የጸና ሥቃይን አሠቃየው። ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ በእጁም ብዙ ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ። በሰማዕትነትም ሞቱ። ንጉሡም አይቶ በበጥላን ላይ ተቆጣ። ለአንበሳም አስጣለው አንበሳውም እግሩን ላሰው እንጂ ክፉ አላደረገበትም። ሁለተኛም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚህም ምስክርነቱን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት አክሊልን ተቀበለ።
† ሐምሌ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ
3.ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ሰማዕት እና ማኅበሩ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ
4.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😍10❤2🥰2🕊2😘2
#ሐምሌ_19
Jul 25, 2026#ሐምሌ_19
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ እና #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ፣ #ቅዱሳን_ሱርስ_ኀርማን_ያኑፋና_ስንጣንያ የሚባሉ የእስና ሀገር ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ፣ ብልህ የሆነ #ቅዱስ_በጥላን በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ
ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው።
ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።
ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ።
መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።
በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው።
ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው።
ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ሱርስ_ኀርማን_ያኑፋ_እና_ስንጣንያ
በዚህች ቀን ስማቸው ሱርስ፣ ኀርማን፣ ያኑፋ፣ ስንጣንያ የሚባሉ የእስና ሀገር ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ። የሰማዕትነታቸው ምክንያትም እንዲህ ነው መኰንኑ አርያኖስ ወደ እስና ከተማ ሦስት ጊዜ ደረሰ። በመጀመሪያ የተባረከች መስተጋድልት የሆነች ዳላዢን ገደላት። ስማቸውን አስቀድመን የጠራናቸው አራቱን ልጆቿንም ገደላቸው። የሰማዕትነታቸውም ፍጻሜ ግንቦት ሰባት ቀን ሆነ።
በሁለተኛም ጊዜ ስማቸው አውሳፍዮስ፣ ታማን፣ ኀርማን፣ ባኮስ የሚባል አራቱን መኳንንት ገደላቸው። የሰማዕትነታቸውም ፍጻሜ ሰኔ ሰባት ቀን ሆነ። በሦስተኛም ጊዜ በቤቷ ውስጥ በዐልጋዋ ላይ ተኝታ የነበረችውን አሮጊት የአርያኖስ ወታደሮች ስለ እነዚህ ቅዱሳን ከጠየቋት በኋላ ገደሏት።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከክርስቲያን ወገን ያገኙትን ሁሉ እንዲገድሉ የተክል ማጠጫ በተባለች በከተማዋ ምዕራብም መግደልን እንዳያቋርጡ አዘዘ ወደ ከበረ አባት ወደ ባሕታዊ ይስሐቅም እስኪደርሱ ድረስ በመንገድ ብዙ ሕዝብን አገኙ።
ያን ጊዜም ጠባቂያቸው እንዲህ እያለ ያጽናናቸውና ያረጋጋቸው ነበር። ወደ ሰማያዊት መንግሥት እንድትገቡ ጸንታችሁ ታገሡ። እንዲህም ሲወስዷቸው መኰንኑ ደረሰ በአዩትም ጊዜ ሁሉም በአንድ ቃል እኛ ክርስቲያን ነን እያሉ በግልጽ ጮኹ መኰንኑም ሁሉንም እንደበግ ያርዷቸው ዘንድ አዘዘ።
ጭፍሮች ግን በላያቸው በሰይፎች አጋና ተጫወቱ። በዚችም በሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ ቀን የእስናን ከተማ ሰዎች ከታናሾቻቸው እስከ ታላቆቻቸው ሴቶችንና ወንዶችን ጨረሷቸው። የመላእክት ሠራዊትም ነፍሶቻቸውን ይቀበሉ የብርሃን አክሊሎችንም ያቀዳጁአቸው ነበር።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከዚያ ወደ እስዋን ከተማ ሔደ ሁለተኛም ወደ እስና ከተማ ተመልሶ ሦስት ገበሬዎችን የእርሻ ዕቃቸውን ተሸክመው አገኘ። መኰንኑንም በአዩት ጊዜ እኛ ክርስቲያን ነን ብለው በግልጥ ጮኹ መኰንኑም ሰምቶ ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ በእርሻ መሣሪያቸውም ገደሏቸው የእነዚህም ስማቸው ሱሩፋስ፣ አንጣኪዮስ፣ ስሐድራ ይባላል የሰማዕትነታቸውም ፍጻሜ መስከረም ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
ይህንንም ቅዱስ አባት ኤጲስቆጶስ ይስሐቅን መኰንኑ አሥሮ ለጣዖት እንዲሠዋ አስገደደው። እምቢ ባለውም ጊዜ ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ የሰማዕትነቱም ፍጻሜ ታኅሣሥ ዐሥራ አራት ቀን ነው ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት። የስደቱ ወራትም ከአለፈ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በስሙ አከበሩዋት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_በጥላን_ጠቢብ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ትዕማዳን ከምትባል ከተማ ብልህ የሆነ ቅዱስ በጥላን በሰማዕትነት ሞተ። አባቱም አረማዊ ነበረ ስሙም አውሱጢኪዮስ ነበር እናቱ ግን አማኝ ነበረች ስሟም ኤልያና ነበር። በአደገ ጊዜም አባቱ ጥበብን ሁሉ አስተማረው እጅግም አዋቂ ሆነ።
በበጥላን ቤት አቅራቢያም አንድ ቄስ ይኖር ነበር። በጥላንም በፊቱ ሲያልፍ መልኩንና ዕውቀቱን ብልህነቱንና አሰተዋይነቱንም ይመለከት ነበር ከሀዲ ስለመሆኑም ስለርሱ ያዝን ነበር። ቄሱም በጥላንን መንገድ መርቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ያስገባው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው።
ስለ በጥላንም ልመናውን በአዘወተረ ጊዜ በጥላን በእርሱ እጅ ያምን ዘንድ እንዳለው ጌታችን በራእይ ገለጠለት ቄሱም ደስ አለው ሁልጊዜም በፊቱ ሲያልፍ በጥላንን ያነጋግረውና ሰላምታ የሚሰጠው ነበር። ስለዚህም በመካከላቸው ፍቅር ጸና።
ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ቤት ይገባና ስለ ሃይማኖት ይነጋገር ነበር። ቄሱም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ምን ያህል ክብር እንዳላት ለሚያምኑበትም ሁሉ ዕውቀትና ማስተዋል እንደሚሰጣቸው ድንቆችና ታላላቅ ተአምራቶች እንደሚደረግላቸው ታላቅ ፈውስም እንደሚያደርጉ ገለጠለት።
በጥላንም ክብር ይግባውና በክርስቶስ የሚያምኑ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት በዚያ ቄስ ትምህርት በጌታ አመነ ቄሱም ሁልጊዜ የሃይማኖትን ትምህርት ያስተምረው ጀመር።
❤9😍3🥰2🕊2😘2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 25, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
😍4😘3🥰1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 25, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤5😘4😍2🥰1
ሥርዓተ ማኅሌት ሐምሌ ፲፱
Jul 25, 2026ሥርዓተ ማኅሌት ሐምሌ ፲፱
❤6😍4🥰3💯2😘2
#ሐምሌ_18 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ስምንት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ያዕቆብ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱስ_አትናቴዎስ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተ፣ ሰማዕት የሆኑ #የ…
Jul 24, 2026#ሐምሌ_18 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ስምንት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ያዕቆብ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱስ_አትናቴዎስ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተ፣ ሰማዕት የሆኑ #የቅዱስ_ኤስድሮስ_ማኅበርተኞች መታሰቢያቸው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ያዕቆብ ሐምሌ ዐሥራ ስምንት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የጌታችን ወንድም የሚባለው…
😘12😍4❤3🥰2💯1
ተቀዳጁ፡፡
Jul 24, 2026ተቀዳጁ፡፡
ቅዱስ ኤስድሮስንም ቸንክረው ሰቀሉት፡፡ ሕጻኑም ተሰቅሎ ሳለ በእናቱና በእኅቱ የሆነውን ነገር ይመለከት ነበር፡፡ ሆዱን ሰንጥቀው በመቅደድ አንጀቱን አውጥተው ወስደው በተራራ ላይ ጣሉት፡፡ ጌታችንም ከሞት አሥተነስቶት እንደ ቀድሞው ሕያውና ፍጹም ጤነኛ አደረገው፡፡ ቅዱስ ኤስድሮስም ተመልሶ ሄዶ ከከሃዲው ንጉሥ ፊት ቆመ፡፡ አሁንም በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከሥር እሳት አነደዱበት፡፡ ሁለተኛም በብረት ላይ አስተኝተው ፈጩት፡፡ ነገር ግን ጌታችን አሁንም ከሞት አስነሣው፡፡ በዚህም ብዙዎች ‹‹በኤስድሮስ አምላክ አምነናል›› እያሉ በምስክርነት ዐረፉ፡፡ ዳግመኛም በእርሱ አምላክ ካመኑት ከሰምንት መቶ ነፍሳት ጋር ሰቀሉት፡፡ አሁን ጌታችን አድኖ አሥነሳው፡፡ በሥቃይም ብዛት አልሞት ቢላቸው አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት ነገር ግን አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አሥነሣው፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኤስድሮስን ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አስረው ወደ ባሕር ጣሉት፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ከባሕሩ ውስጥ አውጥቶ በንጉሡ ፊት አቆመው፡፡ ዳግመኛም ወደ ከተማ ወስዶ ሰቅሎ ገደለው፣ ጌታችንም ለ4ኛ ጊዜ ከሞት አሥነሣው፡፡ ለተራቡ አንበሶች ሲሰጡት እነርሱም ምንም ሳይነኩት ቀሩ ይልቁንም አክብረው ሲሰግዱለት ቢመለከቱ በንዴት ሰውነቱን ቆራርጠው ወደ ባሕር ጣሉት፡፡ ጌታችንም ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ተገልጦለት ለ5ኛ ጊዜ ከሞት አሥነሣው፡፡ ንጉሡም እጅግ አፈረና የሚያደርገው ቢያጣ በግዞት ወደ ሰሎንቅያ ሀገር ላከው፡፡ በዚያም ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ወደ ንጉሡ መለሱት፡፡ ንጉሡም በእሥር ቤት አሥሮ በርሃብ እንዲሠቃይ አደረገው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ኤስድሮስ ግንቦት 19 ቀን የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነና ተሰቅሎ ዐረፈ፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀ፡፡ ቅዱስ ኤስድሮስ የኖረበት ዘመን 12 ዓመት ነው፡፡ በቅዱስ ኤስድሮስ ምክንያት በጌታችን አምነው ከኤስድሮስ ጋር አብረው በሰማዕትነት የሞቱት ሰዎች ብዛት 8 መቶ 5 ሺህ ሰባት ሰዎች ናቸው፡፡ ጌታችንም ለሕፃኑ ሰማዕት ለቅዱስ ኤስድሮስ አስደናቂ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡
† ሐምሌ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት-የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሰማዕት
4.ዘጠኝ ሺህ ሰማዕታት (የቅዱስ ኤስድሮስ ማኅበር)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘9😍6❤4🥰2💯1
#ሐምሌ_18
Jul 24, 2026#ሐምሌ_18
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ ስምንት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ያዕቆብ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱስ_አትናቴዎስ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተ፣ ሰማዕት የሆኑ #የቅዱስ_ኤስድሮስ_ማኅበርተኞች መታሰቢያቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ
ሐምሌ ዐሥራ ስምንት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የጌታችን ወንድም የሚባለው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት ሞተ።
ይህም ቅዱስ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው። እርሱም ከልጆቹ ሁሉ የሚያንስ ነበር። እርሱም ንጹሕ ድንግል ነበር ከጌታችንም ጋራ አደገ ስለዚህም ክብር ይግባውና የጌታችን ወንድም ተባለ። ከጌታችን ዕርገትም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ላይ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተምሮ ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው።
እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ። በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ አንድ ሽማግሌ አገኘ። ቅዱስ ያዕቆብም ሽማግሌ ሆይ በቤትህ ታሳድረኛለህን አለው። አረጋዊውም እሺ እንዳልክ ይሁን አለ በአንድነትም ሲጓዙ ጋኔን ያደረበት ሰው አገኘው በአየውም ጊዜ የክርስቶስ ሐዋርያ ሆይ እኔ ካንተ ጋር ምን አለኝ ልታጠፋኝ መጣህን ብሎ ጮኸ ሐዋርያውም በናዝሬቱ ኢየሱስ ስም ተጠጋ ከሰውዬውም ውጣ አለው። ወዲያውም ያ ጋኔን ከሰውዬው ላይ ወጣ።
ያ ሽማግሌም ይህን ድንቅ ተአምር አይቶ ደነገጠ ከሐዋርያው እግር በታችም ወድቆ እንዲህ አለው። ወደ ቤቴ ልትገባ አይገባኝም ነገር ግን እድን ዘንድ ቤተሰቦቼም ሁሉ ይድኑ ዘንድ ምን ላድርግ አለ ያን ጊዜም ሐዋርያው አቤቱ ጌታዬ ሆይ መንገዴን አሳምረህልኛልና አመሰግንሃለሁ ብሎ ጌታችንን አመሰገነው። ወደ ሽማግሌውም ተመልሶ የድኅነትን ነገር ነገረው ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ሰው መሆን ስለ መከራው ስለ ሞቱና ስለ መነሣቱ አስተማረው።
ከዚህም በኋላ ያ ሽማግሌ ሐዋርያውን ወደ ቤቱ አስገባው ቤተሰቦቹም ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ ቅዱስ ያዕቆብም አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው።
የከተማው ሰዎችም በሰሙ ጊዜ በሽተኞችን ሁሉ ወደርሱ አመጡ ሁሉንም አዳናቸው ለእነርሱም ሃይማኖትን አስተምሮ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው። ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመላቸው ያንን ሽማግሌም ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው ክብር ይግባውና የጌታችንንም ወንጌል ሰጣቸው ከዚህም በኋላ ያስተምር ዘንድ ወደ ሌሎች አገሮች ወጥቶ ሔደ።
አንዲት መካን ሴት ነበረች እግዚአብሔር ልጅን ይሰጣት ዘንድ ስለርሷ እንዲጸልይላት ቅዱስ ያዕቆብን ለመነችው። እርሱም ጸለየላትና ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው ልጅዋንም ተሸክማ ወደ ሐዋርያው መጥታ ሰላምታ አቀረበችለት ከልጅዋም ጋር ከእርሱ ተባረከች ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ብዙዎች አይሁድ ወደርሱ ተሰበሰቡ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስም የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ጠየቁት እነርሱ እርሱ ጌታን የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ እርሱም ወንድሙ እንደሆነ እንደሚነግራቸው አስበው ነበርና።
ቅዱስ ያዕቆብም በሦስተኛ ደርብ ላይ ወጥቶ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ከአብ ጋራም ትክክል እንደሆነ ይገልጽላቸው ጀመረ።
ይህንንም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቄጡ ከደርቡ ላይ አውርደው የጸና ግርፋትን ገረፉት ከእነርሱም ውስጥ የልብስ ማጠቢያ የዕንጨት ገበታ የያዘ አንድ ሰው መጣ በዚያ ዕንጨትም ቅዱስ ያዕቆብን ራሱ ላይ መታው ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
ስለ እርሱም ወይን እንዳልጠጣ፣ ደም ካለው ወገን እንዳልበላ፣ በራሱም ላይ ምላጭ እንዳልወጣ፣ በውሽባ ቤት እንዳልታጠበ፣ ሁለት ልብስንም እንዳልለበሰ፣ ሁልጊዜም እንደሚቆምና እንደሚሰግድ ተጽፎአል። ከመቆም ብዛት የተነሣም እግሮቹ አብጠው ነበር ከዚህም በኋላ አረፈና በቤተ መቅደሱ ጐን ቀበሩት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አትናቴዎስ
በዚህችም ቀን ከቍልዝም ከተማ ቅዱስ አትናቴዎስ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ከነገሥታት ወገን ነበረ በሃይማኖቱም የጸና ነበረ። እኒህ ከሐዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ የጣዖታትን አምልኮ በዓወጁ ጊዜ ይህን አትናቴዎስን ለግብጽ አገር ገዥ አድርገው ሾሙት አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲአፈርስ አዘዙት።
እርሱ ግን ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ሒዶ በረከትን ተቀበለ እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ነገረው በእርሱም ደስ አለው። ንጉሡም በሰማ ጊዜ ይዞ ይመረምረው ዘንድ ሌላ መኰንን ላከ።
መኰንኑም በደረሰ ጊዜ ተገናኘውና የአማልክትን ፍቅር ለምን ተውክ አለው። አትናቴዎስም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ ከታናሽነቴ ጀምሬ ክብር ይግባውና የክርስቶስ ነኝ የቀናች ሃይማኖቴንም አልተውም።
መኰንኑም የንጉሥን ትዕዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ቅጣት እንዲአገኘውና በጽኑ ሥቃይ እንዲሠቃይ አታውቅምን አለው። ቅዱስ አትናቴዎስም እንዲህ አለው አንተ ሰነፍ በአንተ ላይና በንጉሥህ ላይ ቸር ሕይወት ሰጭ እግዚአብሔርን በሚጠላ በአባትህ ሠይጣን ላይ የሚመጣው የዘላለም ሥቃይን እስከምታይ ጥቂት ታገሥ አለው።
መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ቅዱስ አትናቴዎስም ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋራ እንዲያሳርፍ ከቤተ ክርስቲያንም መከራን እንዲያርቅ የሮምንና የአኲስምን የክርስቲያን መንግሥት እንዲአጸና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጸሎቱም በፈጸመ ጊዜ በርከክ ብሎ ሰገደ ጭፍሮችም ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ቀበሩት። ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የቅዱስ_ኤስድሮስ_ማኅበር
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የቅዱስ ኤስድሮስ ማኅበርተኞች የሆኑ ዘጠኝ ሺህ ሰማዕታት በዓመታዊ በዓላቸው ታስበው ይውላሉ፡፡ ይኸውም ሰማዕት ኤስድሮስ ጌታችን 5 ጊዜ ከሞት እያስነሣውና ስለ ስሙ ምስክር የሆነለት የ12 ዓመት ሕጻን ነው፡፡ ከእርሱም ጋር ማኅበርተኞቹ የሆኑ 8 መቶ 5 ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ በዚህች ዕለትም ማኅበርተኞች የሆኑ ዘጠኝ ሺህ ሰማዕታት በዓመታዊ በዓላቸው ታስበው ይውላሉ፡፡
(የዕረፍታቸውን ዕለት ግንቦት 19ን ይመለከቷል፡፡)
ሕጻኑ ሰማዕት ቅዱስ ኤስድሮስ ሀገሩ እስክንድርያ ሲሆን አባቱ በድላዖን እናቱ ሶፍያ ከቤተ መንግሥት ወገኖች ናቸው፡፡ አባቱ የዲዮቅልጥያኖስ መኰንን ነበር፡፡ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በክርስቲያኖች ላይ እጅግ አሠቃቂ መከራ ባደረሰ ጊዜ አባቱ በድላዖን ምስፍናውን ትቶ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ገዳም ገባ፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍሮቹን ልኮ አስመጣውና እምነቱን እንዲክድ ጠየቀው፡፡ በድላዖንም ‹‹ክርስቶስን በተውከው ሰዓት እኔም አንተን ተውኩህ›› አለው፡፡ ወዲያም አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ኤስድሮስም ገና የ12 ዓመት ሕፃን ልጅ ነበርና ይመለስ ይሆናል በሚል በእሥር ቤት እንዲቆይ ተደረገ፡፡ በማግሥቱም ‹‹ክርስትናህን ትተህ የንጉሡን ሃይማኖት ተቀበል›› ብለው ሲያባብሉት እምቢ አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ በንጉሡ ፊት አቅርበው ደሙ እንደ ውኃ እስኪወርድ ድረስ አሠቃቂ ግርፋትን ገረፉት፡፡ እናቱ ሶፍያም የሕፃኑን ልጇን ደም በዲዮቅልጥያኖስ ፊት ላይ እረጭታ እረገመችው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም በንዴት ከሴት ልጇ ጋር ከወገባቸው ላይ ከሁለት አስቆረጣቸውና ሰማዕትነታቸውን ፈጽመው የክብር አክሊል
🥰9😘4❤3😍2💯1
ቤማ የበገና ማሰልጠኛ ተቋም
Jul 24, 2026 ቤማ የበገና ማሰልጠኛ ተቋም
ለጀማሪዎችና ለተሻለ ደረጃ ላይ ላሉ✅
✅ በአካል በቤት 🏠
✅ በኦንላይን 💻
© በግል 1 ለ 1 በብቁ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና ነው። ትምህርቱ ከሰኔ ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል ! ምዝገባ እንደቀጠለ ነው ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ምዝገባ እንደቀጠለ ነው ፈጥነው ይመዝገቡ !!!
📍 አድራሻችን፦ ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ብሎክ 24
🔔 ለምዝገባ፦ +251902564674 | @Bem38 ✉️
🔵 ቴሌግራም ቻናል፦ T.me/Bema_begena
🥰5😍3😘3❤2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 23, 2026ወንድሞች ሆይ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ፊት ለፍጡር ማምለጥ ይቻለዋልን። ይህስ ዮናስ የእስራኤልን ልጆች ከሚያስተምሩ ነቢያት ውስጥ ሲሆን ይህን አያውቅምን ነገር ግን አግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ ይህን አደረገ እንጂ የዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆ…
Jul 23, 2026ወንድሞች ሆይ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ፊት ለፍጡር ማምለጥ ይቻለዋልን። ይህስ ዮናስ የእስራኤልን ልጆች ከሚያስተምሩ ነቢያት ውስጥ ሲሆን ይህን አያውቅምን ነገር ግን አግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ ይህን አደረገ እንጂ የዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ መውጣት መድኃኒታችን በመቃብር ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ ከዚህ በኋላ ከሙታን ተለይቶ ለመነሣቱ ምልክት ይሆን ዘንድ ነው።
ዮናስም ከዓሣ አንበሪ ሆድ ያለ ምንም ጥፋት እንደመጣ እንዲሁ መደኃኒታችን ያለመለወጥ ተነሥቷልና።
እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ፊት ዮናስ ሸሽቶ ወደ ተርሴስ አገር ሊሔድ ተነሣ ወደ ኢዮጴ አገርም ወርዶ ወደ ተርሴስ አገር የሚሔድ መርከብን አግኝቶ በገንዘቡ መርከቡን ተከራየ።
ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሏልና ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሔድ ዘንድ ወደ መርከቡ ወጣ እግዚአብሔርም ታላቁን ነፋስ ወደ ባሕር አመጣ የባሕሩም ማዕበል ከፍ ከፍ አለ መርከባቸውም ሊሰበር ቀረበ። ቀዛፊዎችም ፈርተው ወደ ጣዖቶቻቸው ጮኹ መርከባቸውም ይቀልላቸው ዘንድ ገንዘባቸውን፣ ዕቃቸውን አውጥተው ወደ ባሕር ጣሉ። ዮናስ ግን በዚያን ጊዜ ወደ ከርሠ ሐመሩ ወርዶ ተኝቶ ያንኰራፋ ነበር።
መርከቡንም የሚቀዝፍ ቀዛፊ ወደ ርሱ ወርዶ ምን ያስተኛሃል እንዳንሞት እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ የፈጣሪህን ስም ጥራ አለው። ይህች መከራ ያገኘችን ስለማናችን ኃጢአት እንደ ሆነ እናውቅ ዘንድ እርስ በርሳቸው ኑ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ በተጣጣሉም ጊዜ ዕጣ በዮናስ ወጣበት። እነርሱም ይህች መከራ ያገኘችን በማናችን ኃጢአት እንደሆነ ንገረን አንተስ የምታመልከው ምንድንነው ከወዴትስ መጣህ አገርህስ የት ነው ወዴትስ ትሔዳለህ ወገንህስ ማንነው አሉት።
ዮናስም እኔስ የእግዚአብሔር ባርያው ዕብራዊ ነኝ ፈጣሪዬም ምድርንና ሰማይን ባሕሩንና የብሱን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው አላቸው። እነዚያም ሰዎች ታላቅ ፍርሀትን ፈርተው ምን አድርገሀል አሉት እሱ ነግሮአቸዋልና ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሎ እንደሔደ እነርሱም አወቁት።
ባሕሩ ይታወክ ነበርና ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና ባሕሩ ይተወን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ አሉት። ዮናስም አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ይተዋችኋል ይህ ታላቅ የማዕበል ሞገድ የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ አላችው።
ባሕሪቱ ትታወካለችና ማዕበሊቱም በእነሣቸው ትነሣለችና እነዚያ ሰዎች ወደ ምድር ሊመለሱ ወደዱ ነገር ግን ተሳናቸው። ሁሉም አንድ ሁነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ አቤቱ ስለዚህ ሰው በእውነት ልታጠፋን አይገባህም አቤቱ እንደ ወደድክ አድርገሃልና የጻድቅ ሰው ደም አታድርግብን አሉ። ከዚህም በኋላ ዮናስን አንሥተው ወደ ባሕር ጣሉት ባሕርም ድርጎዋን ተቀብላ ጸጥ አለች። እነዚያም ሰዎች እግዚአብሔርን ፈሩት ለእርሱም መሥዋዕትን ሠዉ ስእለትንም ተሳሉ።
እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንባሪን ዮናስን ይውጠው ዘንድ አዘዘው ዮናስም በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ኖረ። ዮናስም በአንበሪ ሆድ ውስጥ ሳለ ጸሎትን ጸለየ ከዚህም በኋላ በነነዌ አገር በኩል ያ ዓሣ አንበሪ ዮናስን ወደ የብስ ምድር ተፋው።
የእግዚአብሔርም ቃሉ ዳግመኛ ወደ ዮናስ መጣ ቀድሞ አስተምር ብዬ እንደ ነገርኩህ ወደ ታላቂቱ የነነዌ አገር ተነሥተህ ሒደህ አስተምራቸው አለው።
ዮናስም እግዚአብሔር አስተምር ብሎ እንደ ነገረው ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሔደ። ነነዌ ግን ለእግዚአብሔር ታላቅ አገር ናት በዙሪያዋ ያለ ቅጽርዋም ከበር እስከ በር ድረስ በእግር የሦስት ቀን ጐዳና ነው። ወደ ከተማም ሊገባ ደርሶ ያንድ ቀን መንገድ ሲቀረው ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች ብሎ አስተማረ።
የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል አመኑ ጾምን እንጹም ብለው አዋጅ ነገሩ የክት ልብሳቸውንም ትተው ማቅ ምንጣፍ ትልቁም ትንሹም ለበሱ። የነነዌ ንጉሥም ይህን ሰምቶ ከዙፋኑ ተነሣ ልብሰ መንግሥቱንም ትቶ ማቅ ለበሰ በአመድ በትቢያ ላይም ተቀመጠ።
ሰዎችም ቢሆኑ ከብቶችም ምንም ምን አይብሉ ትልልቆችም ትንንሾችም አይጠጡ እንስሶችም ወደ ሣር አይሠማሩ ውኃም አይጠጡ ብሎ አዋጅ ነገረ። እግዚአብሔርም ከክፉ ሥራቸው እንደ ተመለሱ አይቶ በእነርሱ ላይ ያደርገው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ በእነርሱ ላይም ክፉ ጥፋትን አላደረገም።
ዮናስም ጽኑ ኀዘንን አዘነ ወደ ፈጣሪው እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ለመነ ጥንቱን በአገሬ ሳለሁ እንዲህ ብዬ የተናገርሁ አይደለሁምን አንተ ይቅር ባይ ርኅሩኅም ከመዓት የራቅህ ቸርነትህ የበዛ እውነተኛ የሆንክ ክፉ ነገርን ከማምጣት እንደምትመለስ አውቃለሁ ስለዚህ ከአንተ ኮብልዬ ወደ ተርሴስ ሔድሁ።
ነቢየ ሐሰት እየተባልኩ ከመኖር ሞት ይሻለኛልና አቤቱ አሁን ነፍሴን ከሥጋዬ ለያት አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን በዚህ ነገር አንተ እጅግ ታዝናለህን አለው እርሱም አዎን አዝናለሁ አለ። ከዚህም በኋላ ዮናስ ከከተማ ወጥቶ ከከተማው ውጭ ተቀመጠ ጎጆም ለራሱ ሠራ በአገር ላይ የሚደረገውን ነገር እስኪያይ ድረስ ከጥላዋ ሥር ተቀመጠ።
ይበቅል ዘንድ በዮናስ ራስ ላይ ይሸፍነው ዘንድ እግዚአብሔር ቅልን አዘዘ ቅሉም በዚያን ጊዜ በቅሎ የዮናስን ራስ የፀሐይ ትኩሳት እንዳያሳምመው በዮናስ ራስ ላይ ሸፈነው ዮናስም በቅሊቱ መብቀል ታላቅ ደስታ አደረገ።
እግዚአብሔርም በማግሥቱ ትሉን ይምጣ ቅሉንም ይምታ ብሎ አዘዘ ቅሊቱንም ቆረጣት እርሷም ደረቀች እግዚአብሔርም ፀሐይ በወጣ ጊዜ የሚያቃጥል ሐሩር ያለበት ነፋስ ይምጣ ብሎ ዳግመኛ አዘዘ። ነፋሱም መጥቶ የዮናስን ራስ አሳመመው እርሱም አእምሮውን እስከማጣት ደርሶ በልቡናውም ተበሳጭቶ ከመኖር ሞት ይሻለኛል አለ።
እግዚአብሔርም ዮናስን በቅሊቱ መድረቅ እጅግ አዘንክን አለው እርሱም አዎን ልሙት እስከ ማለት ደርሼ አዘንኩ አለ። እግዚአብሔርም አንተስ በአንድ ሌሊት በቅላ በአንድ ሌሊት ለደረቀች ውኃ ላላጠጣሃት ላልደከምክባት ቅል ታዝናለህ። ቀኝና ግራቸውን ላልለዩ ከዐሥራ ሁለት እልፍ የሚበዙ ሰዎች እንዲሁም ብዙ እንስሶች ላሉባት ታላቅ አገር ለሆነች ነነዌ እኔ አላዝንላትምን ከበደሉ ተመልሶ ንስሐ ለሚገባ እኔ መሐሪና ይቅር ባይ ነኝና አለው።
ከዚህም በኋላ ዮናስ ተነሥቶ ወደ አገሩ ተመልሶ በሰላም አረፈ መላው ዕድሜውም መቶ ሰባ ነው። የነቢዩ የዕረፍት በዓል መስከረም 25 እንደሚከበር ስንክሳሩ ያስረዳናል።
=> ሐምሌ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ (ከአሣ አንበሪ ሆድ የወጣበት)
2.ቅድስት አውፎምያ (ጻድቅትና ሰማዕት)
3.ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት (ታላቁ)
4.ቅዱስ ዘካርያስ
=> ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌና_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)
😍5😘4❤3🥰2🕊1
#ሐምሌ_17
Jul 23, 2026#ሐምሌ_17
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን #ቅድስት_አውፎምያ በሰማዕትነት ሞተች። #የቅዱስ_ዮስጦስ የከበረች ዐፅሙ በክብር ተገኘች፣ #ታላቁ_ነቢይ_ዮናስ ከዓሣ አንበሪ ሆድ ለወጣበት መታሰቢያው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_አውፎምያ
ሐምሌ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ቅድስት አውፎምያ በሰማዕትነት ሞተች። ይቺንም ቅድስት በርሴፎስ የሚባል ከዲዮቅልጥያኖስ መኳንንቶች አንዱ አሠቃያት። የታሠሩ ሰማዕታት በሚያልፉ ጊዜ በአንገታቸው የሚከብዱ ሰንሰለቶች ነበሩ። እንደ ውሾችም ይጐትቷቸው ነበር። ግፋቸውንም ባየች ጊዜ ይቺ ቅድስት አለቀሰች ልቡናዋም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ፍቅር ተቃጠለ ዲዮቅልጥያኖስንና የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች። ያንንም መኰንን እንዲህ ብላ ዘለፈችው ርኅራኄ የሌለህ ልብህ እንደ ደንጊያ የሆነ ለእኒህ ቅዱሳን ሰዎች አትራራምን ፈጣሪያቸውስ እንዳያጠፋህ አትፈራምን።
መኰንኑም ሰምቶ ወደርሱ ያቀርቡአት ዘንድ አዘዘ። ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት እርሷም ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ አመነች። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ በግርፋትና በስቅላት ታላቅ ሥቃይን አሠቃያት።
ከዚህ በኋላ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩዋት ነገር ግን ከሥቃዩ የተነሣ ምንም ጉዳት አልደረሰባትም። በዚያን ጊዜም በእሳቱ መካከል ቆማ ጸለየች ፊቷንና መላ ሥጋዋንም በመስቀል ምልክት አማትባ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮስጦስ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የቅዱስ ዮስጦስ የከበረች ዐፅሙ በክብር ተገኘች፡፡ በሰማዕትነት ያረፈው የአንጾኪያው ንጉሥ የኑማርያኖስ ልጅ ነው፡፡ ታላቁ የአንጾኪያ ንጉሥ ኑማርያኖስ በጦርነት ውስጥ በሞተ ጊዜ ልጁ ቅዱስ ዮስጦስም በሌላ ቦታ በጦርነት ውስጥ ስለነበር መንግሥትም ያለ ንጉሥ ቀረች፡፡
የቴዎድሮስ በናድልዮስ አባት ሲድራኮስና ቅዱስ ፋሲለደስ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ሃይማኖቱን እስከካደ ድረስ የመንግሥቱን አስተዳደር ይመሩ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ታላቁ የአንጾኪያ ንጉሥ ኑማርያኖስ የፋርስና የቁዝ ሰዎች በጦር በርትተው በመጡበት ጊዜ ቅዱስ ፋሲለደስንና ህርማኖስን ጠርቶ ‹‹እነሆ እኔና የተረፉት ሠራዊት ሄደን የቁዝን ሰዎች እንዋጋለን እናንተ ቤተ መንግሥቱን ጠብቁ፣ ልጆቼን ለእናንተ አደራ ሰጥቻለሁ›› አላቸው፡፡ ንጉሡም የመንግሥቱን ልብስ አውልቆ ዘውዱን ጥሎ ተራ ልብስ ለብሶ ሲዋጋ በጦር ተወግቶ ሞተ ነገር ግን የቁዝ ሰዎች አላወቁትም ነበር፡፡
ጦርነቱም ባለቀ ጊዜ የሮም መንግሥት ያለንጉሥ ብቻዋን ቀርታ አንድ ዓመት ሙሉ ቅዱስ ፋሲለደስና ህርማኖስ የመንግሥት ሕጓንና ሥርዓቷን እየጠበቁ ቆዩ፡፡ የቁዝ ሰዎችም የሮም መንግሥት ያለ ንጉሥ መሆኗን ሲያውቁ ዳግመኛ ሊያጠፏቸው በጦር በርትተው መጡ፡፡ የሮም ሰዎችም ተሰብስበው ቅዱስ ፋሲለደስን ‹‹በስራችን ወዳሉ ግዛቶች ወደ ግብጽም ተዋጊ አርበኞችን ይልኩልን ዘንድ እንጠይቃቸው›› አሉት፡፡ መኳንንቱም ወደ ግብጽ ወርደው በጦር ኃይለኛ የሆኑ ሰዎችን ይዘው ተመለሱ፡፡ ከግብጽ ካመጧቸው ኃይለኛ ሰዎች ውስጥ ከላይዕላይ ግብጽ ስሙ ከርቢጣ የሚባል ፍየል የሚጠብቅ አንድ ኃይለኛ ሰውን ወደ አንጾኪያ አመጡ፡፡
ቅዱስ ፋሲለደስና ህርማኖስም ይህ ሰው የሚያስፈራ በሥራውም ኃይለኛ ጉልበቱ የጸና ጨካኝ መሆኑን አይተው በንጉሡ ፈረስ ላይ ባልደራስ ወይም ሹም አድርገው ሾሙት፡፡ ከጥቂት ወራትም በኋላ ታላቂቱ የንጉሡ ልጅ ከቤተ መንግሥት ሆና በመስኮት በኩል ሆና ሲወጣ ባቱን ሲገባ ደረቱን አይታ በሀፀ ዝሙት ተነድፋ እጅግ ወደደችው፡፡ እርሱንም ሰይጣን ከልጅነቱ ጀምሮ ይከተለው ነበር፡፡ የንጉሡም ሴት ልጅ ወስዳ አገባችውና ስሙን ዲዮቅልጥያኖስ ብላ አነገሠችው፡፡ ይኽም ዲዮቅልጥያኖስ ከካደ በኃላ ሰይጣን ማደሪያው አድርጎት ከ470,000 (አራት መቶ ሰባ ሺህ) በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖችን በግፍ በሰማዕትነት የገደለ ነው፡፡
የንጉሡ ልጅ ቅዱስ ዮስጦስ ጦርነቱን አሸንፎ በድል ወደ ቤተ መንግሥት በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስ ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ሲያመልክ ቢያገኘው እጅግ አዝኖ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ተመኘ፡፡ የሀገሩም ሰዎች ወደ ዮስጦስ ዘንድ ቀርበው ‹‹እኛ ዲዮቅልጥያኖስን እንገድለዋለን አንተ በአባትህ ዙፋን ተቀመጥ›› አሉት፡፡ እርሱ ግን ከምድራዊው መንግሥት ይልቅ ሰማያዊውን መንግሥት መርጧልና እሺ አላላቸውም፡፡ በጌታችንም ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ መረጠ፡፡ በንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስም ዘንድ ቀርቦ ስለ ጌታችን ክብር መሰከረ፡፡
ንጉሡም ገና ሲያየው እጅግ ፈርቶና ደንግጦ ‹‹ጌታዬ ዮስጦስ ሆይ! ይህን ታደርግ ዘንድ ያስገደደህ ማነው?›› አለው፡፡ ቅዱስ ዮስጦስም ከሃዲውን ንጉሥ ‹‹በምስክርነቴ ደሜን እንዳፈስ ካልጻፍክ ሕዝቡን በአንተ ላይ አስነስቼ ከመንግሥትህ እንደማስወጣህ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እምልልሃለሁ›› አለው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም እየፈራ የዮስጦስን ፈቃድ ይፈጽምለት ዘንድ ከሚስቱ ከታውክልያና ከልጁ ከአቦሊ ጋር ወደ ግብፅ እንዲወስዷቸው አዘዘ፡፡ እንዲያባብለውም ለእስክንድርያው መኮንን ጻፈለት፡፡
የእስክንድርያውም ገዥ እጅግ ፈርቶ ዮስጦስን ‹‹ጌታዬ ዮስጦስ ሆይ! እንዲህ አታድርግ ለአንተ ክብርህ ይሻልሃል…›› እያለ ሊያግባባው ሲሞክር ቅዱስ ዮስጦስ ግን ‹‹የመንግሥትህን ክብር እንዳታጣ ሰማዕትነቴን ፈጸምልኝ›› አለው፡፡ እርሱም ፈርቶ ወደ ላይኛው ግብፅ ወደ እንዴናው ገዥ ላከው፡፡ ከአገልጋዮች ጋራ ሚስቱን ቅድስት ታውክልያን ፃ ወደምትባል አገር ሲልካት ልጁን አቦሊን ደግም ወደ ሀገረ ብስጣ ላከው፡፡ ከአገልጋዮቹም ውስጥ እንዲያገለግሏቸው በማለት አንድ አንድ ሰጣቸው፡፡ ሚስቱ ቅድስት ታውክልያም ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ የክብርን አክሊል ተቀዳጀች፡፡
ቅዱስ ዮስጦስንም የእንዴና ከተማ ጣዖት አምላኪዎች ብዙ ካሠቃዩት በኋላ የካቲት 10 ቀን በሰይፍ ራሱን ቆርጡትና የተመኘውን ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ለሕሙማንም ታላቅ ፈውስ ሆነ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ነቢዩ_ዮናስ
በዚህች ቀን ታላቁ ነቢይ ዮናስ ከዓሣ አንበሪ ሆድ ለወጣበት መታሰቢያው ነው። ይህም እውነተኛ ነቢይ ዮናስ የሲዶና ክፍል በምትሆን ስራጵታ በምትባል አገር ለምትኖር መበለት ልጅዋ የሆነ ነቢይ ኤልያስም ከሙታን ለይቶ ያሥነሣው ኤልያስንም ያገለገለውና የትንቢት ጸጋ የተሰጠው ነው።
ከዚህም በኋላ ስሙ ከፍ ከፍ ያለና የተመሰገነ እግዚአብሔር ወደ ነነዌ አገር ሒደህ ሀገራቸሁ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ትጠፋለች ብለህ አስተምር ብሎ አዘዘው።
እግዚአብሔርም ይህን በአለው ጊዜ ዮናስ በልቡ እንዲህ ብሎ አሰበ እግዚአብሔር ሊአጠፋቸው ቢወድ ኖሮ ሒደህ አስተምር ብሎ ባላዘዘኝ ነበር እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ሲምራቸው እኔ በእነርሱ ዘንድ ሐሰተኛ ነቢይ እንዳልባል እፈራለሁ ከቶ ትምህርቴን አይቀበሉኝም ወይም ይገድሉኛል ወደዚያች አገርም ሒጄ እንዳላስተምር ከእግዚአብሔር ፊት ብኰበልልና ብታጣ ይሻለኛል።
🥰7❤3🕊2😍2
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Jul 23, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
😍7🥰3❤1😘1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 23, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
🥰7😍4❤1😘1
📖 ስለ ምልጃ በሃያ ክፍል የተጠየቁ ጥያቄዎች እና በጽሑፍ የተመለሱ (የተላለፉ) ትምህርቶች በእነዚህ ሊንኮች ይገኛል👇
Jul 23, 2026📖 ስለ ምልጃ በሃያ ክፍል የተጠየቁ ጥያቄዎች እና በጽሑፍ የተመለሱ (የተላለፉ) ትምህርቶች በእነዚህ ሊንኮች ይገኛል👇
📖 አማላጅ ማለት ምን ማለት ነው❓
📖 ማማለድ ምንድን ነው❓
📖 አማላጅ የምንለው ማንን ነው❓
📖 የቅዱሳን አማላጅነት ለምን አስፈለገ❓
📖 የቅዱሳን አማላጅነት በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን❓
📖 የቅዱሳን መላእክት አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው❓
📖 የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት እንዴት ይገለጻል❓
📖 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እና ተራዳኢነት ስንል ምን ማለታችን ነው❓
📖 ክርስቶስ አማላጅ ነው? አምላክ ነውና ወደ ማን ይማልዳል❓
ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇
🤗https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
🥰5😍4😘3❤2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 23, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😘6❤4🥰3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 23, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😘7🥰2
✝ሐምሌ ፲፮/16✝
Jul 22, 2026✝ሐምሌ ፲፮/16✝
☞ፍልሠተ ሥጋሁ ለኃያል ወመስተጋድል #ማር #ጊዮርጊስ ልዳዊ፤ መክብበ ሰማዕታት። (እምልዳ ኀበ እስክንድርያ)
✝️ በረከቱ ትብጽሐነ! አሜን፡፡
😘5❤3😍3🥰2💯2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 22, 2026#ሐምሌ_16
Jul 22, 2026#ሐምሌ_16
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌሉ_ዘወርቅ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን ቅዱስ አባት ወንጌሉ ዘወርቅ የተባለ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ነበር አባቱም አጥራብዮስ የሚባል ባለጠጋ ነው። የእናቱም ስም ብዱራ ይባላል። እንዲማርም ለመምህር ሰጡት ቅዱሳት መጻሕፍትንም ተማረ።
ከዚህም በኋላ ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራለት ዘንድ አባቱን ለመነው አባቱም እንደፈለገው አሠራለት ሁል ጊዜም ያነበው ነበር። በሚያነብ ጊዜም አባቱና እናቱ ደስ ይላቸው ነበር።
በዚያም ወራት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ መነኵሴ ወደ እነርሱ መጣ በእነርሱም ዘንድ አደረ ከቅዱስ ዮሐንስም ጋራ ተነጋግሮ የምኵስናን ሥራ አመሰገነለት ይህን ዓለም እስከ ናቀና እንደ እርሱ መነኰስ ይሆን ዘንድ እስከ ወደደ ድረስ ልቡን ማረከው።
ያን ጊዜም ያ መነኰስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ሁለተኛም ተመልሶ እንደ ልማዱ በእነርሱ ዘንድ አደረ። ቅዱስ ዮሐንስም መነኵሴው ወደ ገዳሙ ይወስደው ዘንድ ፈለገ መነኲሴውም አባትህን እፈራዋለሁ ልወስድህ አይቻለኝም አለው። ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሱ ጋራ እንዲወስደውና ነፍሱን እንዲያድን አማለው።
ከዚህም በኋላ በስውር ወሰደው በመርከብም ተጭነው ያ መነኰስ ወደሚኖርበት ገዳም ደረሱ የገዳሙም አበ ምኔት የወጣቱን ዮሐንስን መልኩን አይቶ አደነቀ። ቅዱስ ዮሐንስም የምንኵስናን ልብስ ያለብሰው ዘንድ አበ ምኔቱን ለመነው አበ ምኔቱም ልጄ ሆይ የምንኵስና ሕግ እጅግ ጭንቅ ናት እኮ አለው። አብዝቶም በለመነውና ግድ ባለው ጊዜ ራሱን ላጭቶ አመነኰሰው።
ከዚህም በኋላ ከጾም ከትጋትና ከኀዘን የተነሣ ሥጋው ደርቆ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ በብዙ ተጋድሎ ተጸመደ። አበ ምኔቱም ልጄ ሆይ ለሰውነትህ እዘን ድካምህንም ቀንስ መነኰሳቱም ሁሉ እንደሚሠሩት ሥራ እያለ ያጽናናውና ይመክረው ነበር።
በዚህ ተጋድሎም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከእነርሱ በረከትን ትቀበል ዘንድ ከመሞትህ በፊት ወደ አባትህና እናትህ ሒድ የሚል ራእይ አየ። ይህንንም ራእይ በሦስት ሌሊቶች ውስጥ አየ ለአበ ምኔቱም እንዴት እንዳየ ነገረው አበ ምኔቱም ይህ ራእይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ ልትሔድ ይገባሃል አለው። ከገዳሙም በወጣ ጊዜ አንድ ምስኪን ሰው ጨርቅ ለብሶ አገኘ። የእርሱንም ልብስ ሰጥቶት ጨርቁን ወሰደ።
ወደ አባቱ ቤትም በደረሰ ጊዜ በትንሽ ጎጆ ውስጥ በአባቱ ደጅ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደለ ባሮች ከአባቱ ማዕድ የሚጥሉለትን ፍርፋሪ እየተመገበ ሰባት ዓመት ኖረ። እናቱም በአንጻሩ ስታልፍ የሚከረፋ ሽታው ያስጨንቃት ነበር። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰባት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ትወጣለህ ብሎ ነገረው።
ያን ጊዜም ወደ እናቱ ልኮ ልመናውን ልትሰማ ወደ እርሱ መጣች ልጅዋም እንደሆነ ፈጥኖ አልነገራትም ነገር ግን በዚያች በታናሽ ማደሪያ ውስጥ በላዩ ባለ ጨርቅ እንድትቀብረው የለበሰውንም ጨርቅ እንዳትለውጥ አማላት። ከዚህም በኋላ ያንን የወርቅ ወንጌል ሰጣት። እንዲህም አላት ይህን መጽሐፍ አንብቡ እኔንም አስቡኝ።
አባቱም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል አሳየችው እርሱም ለልጁ ያሠራለት ወንጌል እንደሆነ አወቀ። አባቱና እናቱም ወደ እርሱ ሔደው ስለ ልጃቸው ጠየቁት እርሱም ከዚህ ጨርቅና ከዚህ ትንሽ ማደሪያዬ ውስጥ በቀር በሌላ እንዳትቀብሩኝ ማሉልኝ አላቸው።
በአማላቸውም ጊዜ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ ነገራቸው ያን ጊዜም ጮኹ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ የሮሜ ከተማ ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበሰቡ ሰባቱ ቀንም ሲፈጸም ቅዱስ ዮሐንስ አረፈ። እናቱም መሐላዋን ረስታ አስቀድማ ለሠርጉ ያዘጋጀቻቸውን ያማሩ ልብሶች አውጥታ ገነዘችው። በዚያችም ጊዜ ታመመች አባቱ ግን መሐላውን አስታውሶ እነዚያን ያማሩ ልብሶች አስወገደ በጨርቆቹም ገነዙት በዚያ በትንሹ ማድሪያም ውስጥ ቀበሩት ከሥጋውም በሽተኞች የሚፈወሱበት ታላቅ ድኅነት ተገኘ።
ከዚህም በኋላ በስሙ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ። ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
† ሐምሌ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
❤5😍3🥰2💯2😘2
🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
Jul 22, 2026🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
😍7❤4😘2🥰1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 22, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤4😍3😘2🥰1
⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
Jul 22, 2026⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
የሁሉንም አባቶች ትምህርት ይፈልጋሉ❓️
--------------------------------------------------
❤4🥰3😘3😍2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 22, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤4😍3😘3🥰2
✝እግዝእትየ፦
Jul 21, 2026✝እግዝእትየ፦
መዝገበ #በረከት፤
መዝገበ #ቅድሳት፤
መዝገበ #ንጽሕ፤
መዝገበ #ርህራሄ፤
መዝገበ #የዋሃት፤
✞ባርክኒ በእዴኪ፤ በከመ ባረኪዮ #ለኤፍሬም ፍቁርኪ፤ በበረከተ ወልድኪ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ፡፡
✝ እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
🥰5😍4❤2🕊2😘2
✝የበረከት፥ የቅድስና፥ የንጽሕና፥ የርኅራኄ፥ የየውሃት መዝገብ እመቤቴ ሆይ፦
Jul 21, 2026✝የበረከት፥ የቅድስና፥ የንጽሕና፥ የርኅራኄ፥ የየውሃት መዝገብ እመቤቴ ሆይ፦
አፈ መዓር የተባለ ቅዱስ ኤፍሬምን እንደባረክሺው፤
እኔ ኃጥኡንም በመሐሪው ልጅሽ፥ በቸር አባቱና ሕይወት በሆነ መንፈስ ቅዱስ በረከት ባርኪኝ!
☞ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፥ ዘደረሰ ላቲ በመንፈስ ቅዱስ አባ ኤፍሬም ለብሐዊ ዘሀገረ ሶርያ፥ ዘይትነበብ በዕለተ .......... !
✝ሰአ(ዓ)ሊ ለነ ቅድስት!
😘8😍3❤2🥰2🕊2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 21, 2026ቅዱሳን (Saints)
Jul 21, 2026በዚህች ዕለት፦
Jul 21, 2026በዚህች ዕለት፦
ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ፤
ጻድቁ አፄ ዮሐንስን ከኢትዮጵያ፤
ለዘለዓለም መንግሥቱ የጠራ ቸሩ መድኀኔ ዓለም፤
ዳግመኛ ስለ ቅዱስ ኤፍሬም ፈንታ ፥ እነ አፈ ወርቅ ቅዱስ ዮሐንስን፤
ስለ አፄ ዮሐንስ ፈንታ ፥ ሰማዕቱን ንጉሥ አፄ ኢያሱ አድያም ሰገድን የተካ ቸሩ፤
ለሃገራችን ደግ ንጉሥ፥ ጻድቅ ጳጳስን ያድላት!
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (ከ298 - ሐምሌ 15, 365)
ጻድቁ አፄ ዮሐንስ (ከ1659 - ሐምሌ 15, 1674)
ያስታወስከኝ ደገኛው የታሪክ ባለሙያ ወንድሜ ሐዋ ሲሳይ (Sisay Sahilie Mahiyewi) ፥ አመሰግናለሁ።
😘5❤4😍3🥰2🕊1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 21, 2026ሐዋርያትም የምድራዊ ንጉሥ ጭፍራ መሆንን እንዲተዉ ፈረሶቹንና የጦር መሣሪያውንም እንዲመልሱለት ክብር ይግባውና በክርስቶስ በግልጥ እንዲአምኑ አዘዟቸው። እነዚያ ጭፍሮቹም ወደ ንጉሣቸው ጰራግሞስ ሔደው በፊቱ ቆሙ ታመጧቸው ዘንድ የላክኋችሁ…
Jul 21, 2026ሐዋርያትም የምድራዊ ንጉሥ ጭፍራ መሆንን እንዲተዉ ፈረሶቹንና የጦር መሣሪያውንም እንዲመልሱለት ክብር ይግባውና በክርስቶስ በግልጥ እንዲአምኑ አዘዟቸው። እነዚያ ጭፍሮቹም ወደ ንጉሣቸው ጰራግሞስ ሔደው በፊቱ ቆሙ ታመጧቸው ዘንድ የላክኋችሁ እነዚያ ሁለት ባለ ሥራዮት ወዴት አሉ አላቸው። የልጅህን ዐይኗን በማዳን በጎ በሠሩልህ ፈንታ ለምን በክፋት ትፈልጋቸዋለህ አሉት። ከዚህም ጥሩራቸውንና ትጥቃቸውን ፈትተው ገንዘብህን ውሰድ እኛ ግን ከአንተ የተሻለ ንጉሥ አግኝተናል ይኸውም የጴጥሮስና የጳውሎስ አምላክ ነው ብለው ከፊቱ ጣሉለት። በሰማ ጊዜም ደነገጠ ተቆጥቶም እስከሚገድላቸው ድረስ በወህኒ ቤት ይጨምሯቸው ዘንደ አዘዘ።
ከዚህ በኋላም ራሱ ይይዛቸው ዘንድ ተዘጋጀ የጦር መሣሪያውንም አዘጋጀ ወደ ፊልጶስ አገር ሔደው እስከ መሠረቷ ያጠፏት ዘንድ ሃያ ሺህ አራት መቶ እግረኞች ጭፍሮችን አዘዛቸው። ቅድስ ጴጥሮስም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ አለው። ወንድሜ ሆይ አገርን እንዳያጠፋ ሳይወጣ ወደ ጰራግሞስ ተነሥ እንሒድ አለው ከዚህም በኋላ ጸሎትን ጸለዩ ወጥተውም በደመና ተጫኑ በቤተ መንግሥት መካከልም አወረዳቸውና በጰራግሞስ ፊት ቆሙ እንዲህም አሉት እነሆ እኛ በፊትህ ነን ስለ እኛ አገርን አታጥፋ። ያን ጊዜም ጭፍሮች እንዲመለሱ አዘዘ።
ሐዋርያትንም እንዲህ አላቸው አገሩን ሁሉ በሥራይ የምታጠፉ ሥራየኞች አናንተ ናችሁን እነርሱም ይህ ሥራ ለእኛ አይገባም አሉት። ሁለተኛም ኃጢአታችሁ ነው ወደዚህ ያመጣችሁ አላቸው።
ችንካር ያላቸው ሁለት የራስ ቁሮችን ከብረት እንዲሠሩ አቃቂርንም እንዲመሉአቸው በእሳትም አግለው በሐዋርያት ራስ ላይ እንዲደፉአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ያን ጊዜም ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ የጌትነትህን ኃይል በጰራግሞስ ላይ ግለጽ። ያን ጊዜም ጰራግሞስ ከወገኖቹ ሁሉ ጋር በነፋስ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ። በዚያን ጊዜም ጌቶቼ ሆይ ይቅር በሉኝ ከዚህ ፆዕርም አድኑኝ እያለ ጮኸ የእንዶር ንጉሥ አስቶኛልና የተረገመ ይሁን በእናንተም ላይ ክፉ የሚናገር ሁሉ የተረገመ ይሁን አለ። ቅዱስ ጴጥሮስም የታሠሩትን ጭፍሮች ይፈቷቸው ዘንድ እስከምታዝ ከዚህ ስቅላት አትወርድም አለው እርሱም ወደ ልጁ ወደ ሎይ ተጣርቶ ትፈታቸው ዘንድ አዘዛት እርሷም አንዳዘዛት ፈታቻችው።
ቅዱስ ጴጥሮስም ዳግምኛ አለው አሁንም ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም በምድር ላይም እንደእኔ ያለ ርኩስ የለም ብለህ ካልጻፍህ አትወርድም ይህችንም በከተማው መካከል ያነቧት ዘንድ ታዝዛለህ። ንጉሡም ወረቀትንና ቀለምን ታቀብለው ዘንድ ወደ ልጁ ተጣራ እርሷ ብቻዋን ከስቅላት ቀርታ ነበርና ባመጣችለትም ጊዜ ቊልቊል ተሰቅሎ እያለ ጻፈ በከተማውም መካከል ያነቧት ዘንድ ላካት።
ያን ገዜም ጰራግሞስንና ወገኖቹን አወረዷቸው ወደ ሐዋርያትም መጥተው ከእግራቸው በታች ሰገዱላቸው ንጉሡም ጌቶቼ ይቅር በሉኝ እኔ በአምላካችሁ አምናለሁ አለ ሕዝቡም ሁሉ ሕያው በሆነ አምላካችሁ እናምናለን እያሉ ከሐዋርያት እግር በታች ወድቀዉ ሰገዱ።
እነርሱም ሃይማኖትን አስተምረው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው ጭፍሮችንም አጠመቋቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን አንድ ሆኑ። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ከአዋቂዎቻቸውም ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾሙላቸው። ነገረ ምሥጢርንም እያስገነዘቡአቸው በእነርሱ ዘንድ ኖሩ። ሃይማኖታቸውንም ይጸና ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰጧቸው። እንዲህም አሏቸው በሃይማኖታችሁ ጽኑ እኛ ካስተማርናችሁ ትምህርት አትናወጹ ወደ እናንተም እንመለሳለን። ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥተዋቸው ወደ ፊልጶስ ሀገር ሔዱ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት_ዘዋልድባ
ዳግመኛም በዚህች እለት የዋልድባው አቡነ ተስፋ ሐዋርያት የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡ አባታቸው ተክለ ሐዋርያት ሲባሉ እናታቸው ወለተ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ ቦታ ሰሜን ጎንደር ሲሆን የእናታቸው ደግሞ ሽሬ ነው፡፡
በዋልድባ ከሳሙኤል ዘዋልድባ ቀጥለው በገዳሙ የተሾሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ይኸውም የሆነው በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትእዛዝ መሠረት ነው፡፡
አቡነ ተስፋ ሐዋርያት በአቡነ ሳሙኤል መቃብር ላይ የፈለቀውን ፀበል ለአትክልት አንድ ጊዜ ብቻ በማጠጣት ለብዙ ጊዜ ዳግመኛ አያጠጡትም ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ በዋልድባ አካባቢ ያለው የለምነት ምሥጢር ይኸው ነው፡፡
አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ልዩ ስሙ አባ ነፅዓ በተባለው ቦታ ገዳማቸውን ከመሠረቱ በኋላ በዋልድባ ያለውን የአንድነት ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረውታል፡፡ በጣም ብዙ መነኮሳትንም አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ በታላቅ ተጋድሎአቸው በእጅጉ ይታወቃሉ፡፡
በመጨረሻም ሞትን ሳይቀምሱ በዚህች ዕለት ተሰውረዋል፡፡
† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ
3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅድስት እንባ መሪና
4.ቅድስት ክርስጢና
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤4😍4🥰3🕊1😘1
#ሐምሌ_15
Jul 21, 2026#ሐምሌ_15
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የሶርያ ሰው #ቅዱስ_አባት_ኤፍሬም አረፈ፣ #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ጴጥሮስና_ጳውሎስ በንጉሥ ጰራግሞስ ላይ ተአምራትን አደረጉ፣ የዋልድባው #አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ (አፈ በረከት)
ሐምሌ ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የሶርያ ሰው ቅዱስ አባት ኤፍሬም አረፈ። ይህም ቅዱስ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው አባቱም ክብር ይግባውና የክርስቶስን አምልኮት የሚጠላ የጣዖት ካህን ነበር።
በዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሰችውና አነሳሥታ የንጽቢን ጳጳስ ወደሆነው ወደ አባ ያዕቆብ ወሰደችው እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው በእርሱም ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።
የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት አሕዛብን ተከራክሮ ይረታቸው ነበር። ኒቅያ በሚባል ከተማ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከአባ ያዕቆብ ጋራ ወደ ቅዱሳን ጉባኤው ሔደ።
ከሀዲው አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ ከዚህ ራእይም የተነሣ አደነቀ ይገልጽለትም ዘንድ ወደ ጌታ ጸለየ ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ።
ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወድዶ ወደ ቂሣርያ ሀገር ተጓዘ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በማእዘኑ በኩል ቆመ ቅዱስ ባስልዮስንም ወንጌልን ሊያነብ በወጣ ጊዜ ዋጋው ብዙ የሆነ ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ አየው። ሦስት ምልክቶችንም እሰኪያይ ድረስ ተጠራጠረ ምልክቶችም እኒህ ናቸው ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች ሁለተኛም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተዋሐስያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር። ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል ወጥቶ በምእመናን ላይ ያድር ነበር።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠራውና እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተለዋወጡ። በአስተርጓሚ ይነጋገሩ ጀመሩ። የየራሳቸውንም ቋንቋ ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመነው። በጸለየ ጊዜም ተገልጾላቸው ያለ አስተርጓሚ ተነጋገሩ።
ከዚህ በኋላም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው ከጥቂት ወራትም በኋላ ቅስና ሾመው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ተገለጡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ተጋደለ። አንዲት በወገን የከበረች ባለ ጸጋ ሴት ነበረች ራስዋንም ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ ጽፋ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አመጣች። አባቴ ሆይ በዚህ ክርታስ ውስጥ ያሉት ኃጢአቶቼ ይደመሰሱ ዘንድ ተናገር ብላ ለመነችው እርሱም እንዳልሺው ይሁንልሽ አላት።
እርሷም ክርታሱን በገለጠች ጊዜ ከአንዲት ኃጢአትዋ በቀር ኃጢአቷ ሁሉ ተደምስሶ አገኘች ያችም ኃጢአት አስጨናቂና ታላቅ ኃጢአት ነበረች።
ባገኘቻትም ጊዜ ያቺን የቀረች ኃጢአቷን ያጠፋላት ዘንድ አልቅሳ ለመነችው እርሱም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒጂ እርሱ ይህችን የቀረች ኃጢአትሽን ያስተሠርይልሻል አላት። ወዲያውም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሔዳ ከርሷ የሆነውን ሁሉ ነገረችው። እርሱም እንዲህ አላት ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሒጂ ግን ሙቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኝዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይህችን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመሰስልሻል።
ያቺም ሴት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ተመለሰች ሙቶ ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱትም አገኘችው። ያንንም ክርታስ በአስክሬኑ ላይ ጣለችው ወዲያውኑም ተደመሰሰላት። ይህም ቅዱስ ኤፍሬም ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል በዘመኑም ዲዳን የሚባል አንድ ከሀዲ ተነሣ ይህም አባት ኤፍሬም ተከራክሮ ረታው።
እጅግም ብዙ የሆኑ ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ከእርሳቸውም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴዋ ነው። አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሶአል። መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው ወደ እግዚአብሔር ሔደ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ሐዋርያት_ጴጥሮስና_ጳውሎስ
በዚህችም ቀን ለአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በንጉሥ ጰራግሞስ ላይ ተአምራትን አደረጉ። አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት በኋላ ደመና ነጥቆ ወሰዳቸውና በቤተ መንግሥት መካከል አወረዳቸው ንጉሥ ጰራግሞስም በአያቸው ጊዜ ደንግጦ እናንተ ምንድን ናችሁ አላቸው። እነርሱም መንግሥታትን ሁሉ የሚያጠፋ የሚሰሙትንም ማዳን የሚችል የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ ባሮች ነን አሉት።
ንጉሡም ነገራችሁ ትክክለኛ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ አላቸው። ከዚህ በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ያደረጋቸውን ድንቆችንና ተአምራቶቹን ነገሩት።
የቀኝ ዐይኗን ወፍ ያወጣው አንዲት ልጅ አለችኝ እርሷን ካዳናችኋት በአምላካችሁ አምናለሁ አላቸው ልጅህን ወደ እኛ አምጣ አሉትና ልጁን ወደ እነርሱ አመጣት። ሐዋርያትም ወደ እግዚአብሔር ጸልየው እጆቻቸውን በዐይኗ ላይ አኖሩ። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዳነች። ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ አይተው ከሐዋርያት እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችንም አመኑ።
ከዚህም በኋላ ሐዋርያት ክብር ይግባውና ጌታችን እንዳዘዛቸው ወደ ሀገረ ፊልጶስ ሔዱ። ሰይጣንም በእንዶር ንጉሥ ተመስሎ አጋንንትን በጭፍራ አምሳል አስከትሎ ወደ ንጉሥ ጰራግሞስ መጣ በሥራያቸው አገርን ሳያጠፉ እኒህን ሁለቱን ሥራየኞች ፈጥነህ የማታጠፋቸው ለምንድነው አለው።
የንጉሥ ጰራግሞስም ልብ ወደ ክህደት ተመለሰ። ሐዋርያትንም ያመጧቸው ዘንድ ዐሥር ሺህ ጭፋሮችንና ሁለት መቶ ፈረሰኞችን ላከ ጭፍሮችም ሔደው ከተማዋን ከበቧት የከተማዋ ሰዎችም ደንግጠው ለሐዋርያት ነገሩዋቸው። ሐዋርያትም ከከተማው ወጥተው በጭፍሮቹ ፊት ቁመው ርዳታን ይልክላቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለዩ።
ያንጊዜም የጭፍሮቹ ፈረሶች ወደ ሐዋርያት ተመለሱ እግሮቻቸውንም አስተካክለው ተንበርክከው ሰገዱ እንደሚያለቅስም በቃጪን ድምጽ ጮኩ። ከፈረሶችም አንዱ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ እንደ ሰው ተናገረ እናንት ሰነፎች የጰራግሞስ ጭፍሮች ክብር ይግባውና የክርስቶስን ጭፍሮች ጴጥሮስንና ጳውሎስን ለምን ትፈልጓቸዋላቸሁ ሥራየኞችስ ለምን ትሏቸዋላችሁ እነርሱ ግን ሥራይንና የሰይጣንን ሥራ ሁሉ ሊያጠፉ መጥተዋል። ክብር ይግባውና ከንጉሣቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው አታዩአቸውምን ለክብር ንጉሥ ለክርስቶስ ጭፍሮቹ ትሆኑ ዘንድ ስሞቻችሁም በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍ ዘንድ ስለ እናንተ ይለምናሉ። እኛ እንኳ እንስሳ ስንሆን ለአምላካችው እንሰግዳለን ፈረሱም ይህንን ተናግሮ ዝም አለ።
ከዚህም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ተሰማ ሐዋርያቶቼ ሆይ ሐዲሶች አትክልቶችን ቸለል አትበሏቸው። ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ዐይኖቻቸውን ቀና አድርገው በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ሲዐርግ ጌታችንን አዩት እነዚያም ዐሥር ሺህ ሁለት መቶ ጭፍሮች ክብር ይግባውና በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ አመኑ ለሐዋርያትም ተገዙላቸው።
🥰6❤3😍2🕊1😘1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 21, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🥰4😍4❤3😘1
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Jul 21, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😍4😘4❤3🥰3
⛪️ ስለ ንስሐ
Jul 21, 2026⛪️ ስለ ንስሐ
----------------------👇
1ኛ/ ንስሐ ማለት ምን ማለት ነዉ❓
2ኛ/ ንስሐ መቼ እና እንዴት እንግባ❓
3ኛ/ ለመጋባት ያሰቡ እጮኞች ንስሐ መግባት አለባቸዉ?ወይስ❓
4ኛ/ ንስሐ ገብቶ የቆረበ ሰዉ በኃጢአት ቢወድቅ መልሶ መቁረብ ይችላል❓
🥰4😍4😘4❤2
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 21, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
😘5😍3🥰2❤1
🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
Jul 21, 2026🎧 ለቅዱስ ገብርኤል የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙራት ስብስብ 𝐉𝐨𝐢𝐧 👇👇
😍3🥰2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 20, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
🥰6😘4❤2😍2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 20, 2026ተስፋ መቁረጥን በልባቸው አሳደሩባቸው፡፡ በአጋንንት ምክንያት ይህም እንደሚመጣባቸው አባ እንጦንስ አስቀድመው ነግረዋቸው ነበር፡፡ ወደ አባ እንጦንም በመሄድ በአጋንንቱ የደረሰባቸውን ፈተናና ጾር ነገሯቸው። አባ እንጦንስም አመንኩሰው እን…
Jul 20, 2026ተስፋ መቁረጥን በልባቸው አሳደሩባቸው፡፡ በአጋንንት ምክንያት ይህም እንደሚመጣባቸው አባ እንጦንስ አስቀድመው ነግረዋቸው ነበር፡፡ ወደ አባ እንጦንም በመሄድ በአጋንንቱ የደረሰባቸውን ፈተናና ጾር ነገሯቸው። አባ እንጦንስም አመንኩሰው እንዲጸኑ በመምከር ወደ በዓታቸው ሸኟቸው፡፡ አንድ እርኩስ መንፈስ ያደረበት ባሕታዊ አግኝቶ ትንሣኤ ሙታንን አላምንም ቢላቸው ሙት አስነሥትው አሳይተው አሳምነውታል፡፡ ሙቱንም አጥምቀው አምነኩሰውት 7 ዓመት በተጋድሎ ኖሮ በሰላም ዐረፈ፡፡
አባ መቃርስ በበረሃ ውስጥ ራቁታቸውን ጌታችን ከብርዱም ሆነ ከሙቀቱ እየጠበቃቸው 40 ዘመን የኖሩ ጻድቃንን አገኟቸውና ‹‹እንደ እናንተ እንድሆን ምን ላድርግ?›› ቢሏቸው ‹‹ወደ በዓትህ ተመልሰህ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ አንተም እንደ እኛ ትሆናልህ›› አሏቸው፡፡ አባ መቃርስም የጻድቃኑን በረከታቸውን ተቀብለው ወደ በዓታቸው ተመልሰው ማልቀስ ጀመሩ፡፡ ጻዲቁ በመጨረሻ ነፍሳቸውን መላእክት ሲያሳርጓት ይፈትኗቸው የነበሩ አጋንንት ‹‹መቃርስ ሆይ አመለጥከን አሸነፍከን…›› እያሉ ሲጮኩ አባ መቃርስም ‹‹እስከ ዛሬ ገና ነኝ፣ በጌታዬ በቀኙ ልቁም በግራው አላወኩምና›› ብለው በትሕትና መለሱላቸው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አሞንዮስ
ዳግመኛም በዚሀች ዕለት የሰማዕቱ የአሞንዮስ መታሰቢያቸው ሆነ፡፡ ጨካኙ አርያኖስ የክርስቲያን ደም እንደውኃ እያፈሰሰ ወደ እስና አገር በደረሰ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው በአባ አሞንዮስ ሥር ተቀምጠው ሃይማኖትን ሲማሩ አገኛቸውና ሁሉንም ይዞ ገደላቸው፡፡ አባ አሞንዮስን ግን አሥሮ ወስዶ ለጣዖታቱ እንዲሰግዱና እንዲሠው አዘዛቸው፡፡ አባ አሞንዮስ ግን ‹‹ከንቱ የሆነ የእንቆቅልሽ ጨዋታህን ብላሽ የሆነ ነገርህንም መስማት አልወድም፣ የረከሱ ጣዖቶችህንም ማየት አልፈልግም›› ብለው ለመኮንኑ ለአርያኖስ መለሱለት፡፡ አርያኖስም በዚህ ጊዜ እጅግ በቁጣ ተመልቶ አባታችንን በሕይወት ሳሉ እሳት ውስጥ እንዲጣሉ አዘዘ፡፡
አባታችንም ወደ እሳቱ ውስጥ ከመጣላቸው በፊት እጅና እግራቸውን እንደታሰሩ ስለ አርያኖስ ጸለዩለት፡፡ ጸሎታቸውንም ከፈጸሙ በኋላ አርያኖስም ተመልሶ እርሱም ራሱ ሰማዕት እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አባ አሞንዮስ ወደ እሳቱ ተወርውረው ያማረ ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጸሙ፡፡ የድል አክሊልንም ተቀዳጁ፡፡
ሥጋቸውንም እሳቱ ከነደደበት ቦታ ባወጡ ጊዜ የእሳቱ ነበልባል ምንም አልነካቸውም ነበር፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡
በአባ አሞንዮስም ትንቢት መሠረት ጨካኙ መኮንን አርያኖስም በመጨረሻ ዘመኑ በጌታችን አምኖ ሰማዕት ሆኖ በክብር አርፎ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀብሏል፡፡
† ሐምሌ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ክርስቶፎሮስና ቴዎዳስያ (ወላጆቹ)
3.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት አለቃ)
4.ቅዱስ አሞንዮስ
† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘11😍4❤3🥰2
#ሐምሌ_14
Jul 20, 2026#ሐምሌ_14
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ #ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የታላቁ #አባ_መቃርስ እና #የሰማዕቱ_አሞንዮስ መታሰቢያቸው ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ
ሐምሌ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የጌታ ክርስቶስ ጭፍራ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከኢየሩሳሌም ነው የአባቱ ስም ክርስቶፎሮስ ነው ትርጓሜውም ክርስቶሰን የለበሰ ማለት ነው። ክርስቲያንም ነበረ የእናቱም ስም ቴዎዶስያ ነው እርሷ ግን ጣዖታትን ታመልክ ነበረች።
አባቱም በአረፈ ጊዜ እናቱ ወሰደችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ገንዘብ ይዛ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደች ልጅዋንም በእስክንድርያ ከተማ ገዥ አድርጎ ይሾመው ዘንድ ለዲዮቅልጥያኖስ እጅ መንሻ ሰጠችው እርሱም ሾመው የሹመት ደብዳቤውንም ጽፎ ክርስቲያኖችን እንዲአሠቃይ አዘዘው።
ከአንጾኪያም ከተማ ወጥቶ ጥቂት እንደተጓዘ ወደእርሱ የሚያስፈራ ቃል ከሰማይ መጣ በስሙም ጠርቶ እንዲህ አለው ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ እንዳዘዘህ ብታደርግ አንተ በክፉ አሟሟት ትሞታለህ።
እርሱም ራስህን ትገልጥልኝ ዘንድ ጌታዬ ሆይ እለምንሃለሁ አለው ወዲያውኑም የብርሃን መስቀል ታየው ዳግመኛም በኢየሩሳሌም የተሰቀልኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ የሚለውን ቃል ሰማ።
ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ተመልሶም ከአንጥረኛ ዘንድ የወርቅ መስቀል አሠራ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ተጓዘ በጉዞውም ውስጥ ሊገድሉት ዐመፀኞች አረማውያን ተነሡበት እርሱም በእነርሱ ላይ በርትቶ ክብር ይግባውና በጌታ ክርስቶስ መስቀል ድል አደረጋቸው።
እናቱም በጦርነት ላይ ለረዱህና ላዳኑህ አማልክት መሥዋዕትን ሠዋ አለችው እርሱም እንዲህ አላት እኔስ አዳኝ በሆነ በመስቀሉ ኃይል ላዳነኝ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ።
ይህንንም በሰማች ጊዜ ልጅዋ አብሮኮሮንዮስ ክርስቲያን እንደሆነ ወደ ዐመፀኛው ዲዮቅልጥያኖስ ልካ ነገረችው። ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍራ ልኮ ወደ ቂሣርያ ከተማ አስወሰደው የቂሣርያውንም ገዥ ስለ ርሱ እንዲመረምርና እንዲአሠቃየው አዘዘው።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ በአቀረቡት ጊዜ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ለመሞት እስቲደርስም ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው ከዚህም በኋላ አሠረው። በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ብርሃን ውስጥ ታየው ከእርሱም ጋራ ብርሃናውያን መላእክት ነበሩ ከማሠሪያውም ፈታውና በመለኮታዊ እጁ ዳሰሰው ከቍስሎቹም ሁሉ አዳነው።
በማግሥቱም መኰንኑ ስለ ቅዱሱ ዜና ሙቶ እንደሆነ ወይም አልሞተ እንደሆነ ጠየቀ ለእርሱ የሞተ መስሎት ነበረና። ቅዱሱም በመጣ ጊዜ ጤነኛ ሁኖ አየውና መኰንኑ አደነቀ በዚያ የነበሩ ሕዝቡም አይተው እጅግ አደነቁ እንዲህም እያሉ ጮኹ እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አብሮኮሮንዮስ አምላክ እናምናለን። ከእነርሱም ጋራ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች እናቱ ቴዎዶስያም ነበሩ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ። እነርሱም ቆረጡአቸው። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ሐምሌ ስድስት ቀን ተቀበሉ።
ቅዱስ አብሮኮሮንዩስን ግን ምን እንደሚያደርግበት እስቲአስብ ድረስ ሦስት ቀን አሠረው ከዚህም በኋላ አውጥቶ እንዲህ አለው ልብህ እንዲመለስ ነፍስህንም እንድታድን ለአማልክትም እንድትሠዋ እነሆ በአንተ ላይ ሦስት ቀናት ታገሥኩ። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት መኰንን ሆይ የለም ልቤ ወደ ስሕተት አይመለስም ክብር ይግባውና ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አውቄ ተረድቼአለሁ ጣዖታቱም ሁሉ ከዕንጨትና ከደንጊያ በሰው እጅ የተሠሩ ፍጡራን ናቸው እንጂ አማልክት አይደሉም አይጐዱም አይጠቅሙም።
መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ጐኖቹንም በሰይፍ እንዲሰነጣጥቁ አዘዘ አርኬላዎስ የሚባል ባለ ሰይፍም የቅዱሱን ጐኖቹን ሊሠነጥቅ እጁን ዘረጋ ያን ጊዜም እጁ ደረቀች ወድቆም ሞተ። መኰንኑም ተቆጥቶ በምድር ጥለው ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እንደ አዘዘም ገረፉት በሰይፍም ጐኖቹን ሠንጥቀው በቍስሉ ውስጥ መጻጻ ጨመሩ እስከ ወህኒ ቤትም ድረስ በእግሩ ጐተቱት በዚያም ሁለት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ አውጥቶ እሳትን በተመላች ጕድጓድ ውስጥ ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችንም አዳነው ምንም ምን አልነካውም።
ብዙ ከማሠቃየቱም የተነሣ መኰንኑ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ
ዳግመኛም በዚሀች ዕለት የታላቁ አባ መቃርስ መታሰቢው ሆነ፡፡ መቃርስ (መቃርዮስ) ማለት "ቅዱሱ ለእግዚአብሔር" ማለት ነው፡፡ ከደቡባዊ ግብፅ ከተወደዱ ደጋግ ክርስቲኖች የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ሣራ ይባላሉ፡፡ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳሉት እንደ አብርሃምና ሣራ እጅግ ደጎች ነበሩ፡፡ ልጅ ግን አልነበራቸውምና በስለት መቃርስን ወለዱ፡፡ ሲያድጉም በግድ ያለፈቃዳቸው ሚስት አጋቧቸው፡፡ አባ መቃርስ ግን ወደ ሙሽራይቱ በገቡ ጊዜ ዐውቀው እንደታመሙ ሆነው ተኙ፡፡ ‹‹ከበሽታዬ ለጥቂት ጊዜ ጤና ባገኝ ወደ ገዳም ልሂድ›› ብለው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሄዱ፡፡ መልአክም ተገልጦ ‹‹ይህች አስቄጥስ የአንተና የልጆችህ ርስት ናት›› አላቸው፡፡ ወደ ቤተሰባቸውም በተመለሱ ጊዜ ሙሽራ እጮኛቸው በድንግልና እንዳለች ሞታ ደረሱ፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ እናትና አባታቸውም ዐረፉ፡፡ እርሳቸውም ንብረታቸውን ሁሉ ለድሆች መጽውተው ገዳም ገቡ፡፡ ሕዝቡም ደግነታቸውንና እውነተኛነታቸውን አይተው ትንሽ ማረፊያ ሠርተው ሌሎች እንዲያገለግሏቸው አደረጉ፡፡
ከዕለታትም በአንድ ቀን አንዲት ሴት ልጅ ከጎረምሳ አርግዛ ሳለ ጎረምሳው ‹‹አባትሽ ሲጠይቅሽ ከአባ መቃርስ አረገዝኩ በይ›› ብሎ መከራትና ለአባቷ እንደተባለችው ተናገረች፡፡ ‹‹አባ መቃርስ በግድ ደፍረውኝ አረገዝኩ›› አለች፡፡ የከተማው ሰውም አባ መቃርስን ከበዓታቸው አውጥተው ለሞት እስኪደርሱ ድረስ ደበደቧቸው፡፡ መላእክትም በሰው አምሳል ተገልጠው ዋስ ሆነው ለልጅቷም ምግቧን ሊሰጡ ተስማምተው ወደ በዓታቸው መለሷቸው፡፡ አባ መቃርስም ለራሳቸው ‹‹መቃርስ ሆይ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባለ ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃል›› እያሉ ቅርጫቶችን እየሠፉ ለሚያገለግላቸው ልጅ እየሰጡት እርሱ ሸጦ እያመጣ ብዙውን ለዚያች በዝሙት ጸንሳ በሳቸው ላሳበበች ሴት ይሰጡ ጀመር፡፡ መውለጃዋም በደረሰ ጊዜ እስከ 4 ቀን ድረስ በጽኑ ሥቃይ ቆየች፡፡ እውነቱንም ተናግራ ንስሓ በገባች ጊዜ ወደ አባ መቃርስ ዘንድ አደረሷት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ‹‹አባታችን ይቅር በሉን›› ብለው ከእግራቸው ላይ ሲወድቁ ይቅር ብለዋቸው ቀድሰው አቆረቧቸው፡፡
ከዚህ በኋላ መልአኩ ወስዶ አስቄጥስ ገዳም አደረሳቸው፡፡ የቅዱሳኑ የመክሲሞስና የዱማቴዎስ በዓት ወደ ሆነች ቦታም አስገብቶ በዚያ በልጆቻቸው ቦታ ላይ በዓታቸውን እንዲያጸኑ ነገራቸው፡፡ አባ መቃርስ ወደ አባ እንጦንስ ዘንድም በመሄድ በረከታቸውንና ምክራቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ ሰይጣናትም በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱትን ክፉ ነገር ሲመካከሩ ይሰሟቸው ነበር፡፡ በእሳት እያቃጠሉ ፈተኗቸው፣ የዝሙት መንፈስ እያመጡም ፈተኗቸው፣ በዚህም ትዕግስትን ቢያደርጉ በሌላም ዓለማዊ ክብርን መውድን፣ ትዕቢትን፣ መመካትን፣ ታካችነትን፣ ስድብን፣ ሃይማኖት ማጣትን፣
❤11😘4🥰3😍1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 20, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
🥰7❤4😍3😘1
💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
Jul 20, 2026💬 የነገረ ማርያም ትምህርቶች (ጥያቄና መልስ) ከስር ያለዉን በመጫን ይከታተሉ❕
❤6😍3😘2
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 20, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤5🥰4😍2😘2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 19, 2026#ሐምሌ_13
Jul 19, 2026#ሐምሌ_13
ሐምሌ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የሀገረ ቅፍጥ ኤጲስቆጶስ #አባ_ብስንድዮስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አሞን ምስክር ሁኖ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ብስንድዮስ_ሊቅ_ወጻድቅ
ሐምሌ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የሀገረ ቅፍጥ ኤጲስቆጶስ አባ ብስንድዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ሰው መንኩሶ በታላቅ ገድል ተጠመደ ቅዱሳት መጻሕፍትንም አጠና ከቅዱሳት መጻሕፍትም ውስጥ የዳዊትን መዝሙርና የነቢያትን መጻሕፍት አጥንቶ ነበር። ከነቢያት ትንቢትም አንዳንዱን መጽሐፍ ያነብ ነበረ። ትንቢቱ የሚነበብለት ነቢያም ወደርሱ መጥቶ ንባቡን እስቲፈጽም ይቆይ ነበር።
ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ እጆቹን አንሥቶ በሚጸልይ ጊዜ ጣቶቹ እንደ ፋና ይበሩ ነበር እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ።
እርሱም በዕድሜው ዘመን ሁሉ የሴት ፊት አላየም።ራሱን ወደ ምድር ያዘነብል ነበር እንጂ። በሆድዋ ውስጥ ታላቅ ደዌ የነበረባትም አንዲት ሴት ነበረች ከበዓቱ ደጅ ጠበቀችውና በድንገት አገኘችው። እርሱም ሮጠ እርስዋም ተከትላው ሮጠች። ወደርሱ መድረስም በተሳናት ጊዜ እግሩ የረገጠቻትን አንዲት እፍኝ አፈር ዘግና በእምነት በላች ከደዌዋም ፈጥና ተፈወሰች።
በአንዲት ዕለትም የሚያበሩ ሦስት ሰዎችን አየ እነርሱም አንተ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትመግባት ዘንድ አለህ እያሉ መክፈቻ ቁልፍን ሰጡት። ከዚህ በኃላ ቅፍጥ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ። የቁርባን ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜም ጌታችንን እጆቹ በመሠዊያው ላይ ሁነው ይመለከተው ነበር መላእክቶቹንም በዙሪያው ቁመው ያያቸው ነበር።
በአንዲት ዕለትም አንድ ቄስ ሊቀድስ ገባ በቅዳሴ እኩሌታ ላይም በመሠዊያው ፊት እያለ ምራቁን ተፋ። ቅዳሴውም በተፈጸመ ጊዜ ይህ አባት ገሠጸው እንዲህም አለው በሚያስፈራ መሠዊያው ፊት በምትቆም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጌትነት የተነሣ አትፈራምን የተፋኸውስ ምራቅ በመሠዊያው ዙሪያ በቆመ ኪሩብ ክንፎች ላይ እንደደረሰ አታውቅምን ።ያን ጊዜም ያንን ቄስ መንቀጥቀጥ ያዘው ተሸክመውም ወደ ቤቱ ወሰዱትና ታሞ ሞተ።
ይህም ቅዱስ አባት አንደበቱ ጣዕም ያለው ነበር በሚያነብ ጊዜ በሚያስተምርም በሚመክርም ጊዜ አይጠገብም ነበር። የዕረፍቱም ቀን በቀረበ ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና አስተማራቸው መከራቸውም በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህም በኃላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ።ከሥጋውም ብዙ ተአምር ተገለጠ ደቀ መዝሙሩ ከመግነዙ ጥቂት ቁራጭ ወስዶ በእምነት በሽተኞችን ሁሉ ይፈውስ ነበር።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አሞን_ሰማዕት
ዳግመኛም በዚች ቀን ከግብጽ ደቡብ ከቡና አውራጃ ጡሕ ከሚባል አገር ቅዱስ አሞን ምስክር ሁኖ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጸለት ከእርሱ የሚሆነውንም ሁሉ ነገረው።
ከዚህ በኃላ ወደ እንዴናው ከተማ ሒዶ አውግስጦስ በሚባል መኮንን ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኮንኑም በመንኩራኩር ውስጥ በእሳት ላይ በመጣል በእሳት በአጋሉት በብረት ዐልጋ ላይ በማጋደም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃዩት።
የራሱንም ቆዳ ገፈው በራሱ ላይ የእሳት ፍም አኖሩ እግዚአብሔርም ያጸናው ነበር ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ ያስነሣው ነበር። ከዚህም በኃላ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ክርስቶስ በጎልማሳ አምሳል በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ተገለጠለትና አጽናናው እንዲህም አለው ወዳጄ አሞን እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁ ስምህን የሚጠራውን መታሰቢያህን የሚደርግውን ሁሉ ወይም ገድልህን የሚጽፈውን ሁሉ እኔ በመንግሥቴ ውስጥ አስበዋለሁ እጠብቃለሁ ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ።
ይህም ቅዱስ በሥጋው ሳለ ታላላቅ ተአምራቶችንና ድንቆችን አደረገ ወዲያውኑም በሰይፍ ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። ቅዱስ ዮልዮስም በዚያ ነበረ ሥጋውን ወስዶ በመልካም ልብስ ገነዘው ከሁለት አገልጋዮቹም ጋራ ወደ አገሩ ላከው በላይኛው ግብጽም ታላላቅ የሆኑ ድንቆችንና ተአምራቶችን እያሳየ እስከ ዛሬ አለ።
† ሐምሌ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብስንድዮስ ሊቅ ወጻድቅ
2.ቅዱስ አሞን ሰማዕት (ዘሃገረ ጡህ)
† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘8❤2🥰2😍2💯2
#ሐምሌ_12 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ሖር በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞…
Jul 18, 2026#ሐምሌ_12 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ሖር በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን የፋርስ ንጉሥ ወደ…
🥰10❤4😘4😍3
#ሐምሌ_12
Jul 18, 2026#ሐምሌ_12
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ሖር በሰማዕትነት ሞተ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል
ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን የፋርስ ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት እግዚአብሔር ላከው ከሰናክሬም ሠራዊትም መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ወንዶችን ገ*ደለ።
ይህም እንዲህ ነው ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ ሕዝቅያስንና ፈጣሪው እግዚአብሔርን እየዘለፈ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ እንዲህም አለ እግዚአብሔር ያድናችኋል እያለ ሕዝቅያስ አያስታችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው።
የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም እጅግ አዘነ ወገኖቹንና ሀገሩ ኢየሩሳሌምንም ያድን ዘንድ ማቅ ለብሶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀብሎ ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ላከለት። ድንቅ ሥራንም ሠርቶ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አዳናቸው።
ስለዚህም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን በዓል መታሰቢያ በዚች ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሖር
በዚህችም ቀን ስርያቆስ ከሚባል አገር አባ ሖር በሰማዕትነት ሞተ፡፡ አባቱም አንጠረኛ ነበር አንዲት እኅትም ነበረችው። ጐልማሳም በሆነ ጊዜ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደ ሀገረ ፈርማ ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ከሥቃዩም ድኖ ተነሣ።
መኰንኑም በእጁ ላይ ጌታችን ያደረገውን ይህን ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ አመነ። በሌላ መኰንን እጅም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ በሰማዕትነት ሞተ።
ቅዱስ አባ ሖርን ግን ወደ እንዴናው ላከው በዚያም በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃዩት በመንኰራኵሮችም አበራዩት ዘቅዝቀውም ሰቅለው በእሳት በአጋሉት የብረት በትር ደበደቡት።
መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
=>ሐምሌ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ንጉሥ
2.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
3.ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት
4."147" ሰማዕታት (የአባ ሖር ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
🥰6😍4😘4❤2🕊2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 17, 2026በዚያም ወራት ሉቀ ጳጳሳቱ አባ ቄርሎስ አረፈ። የወንጌላዊው የማርቆስ መንበርም ያለሊቀ ጳጳሳት ነበር። ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ይሾሙት ዘንድ በአንድ ምክር ተስማሙ ሰይጣን ግን ክፉዎች ሰዎችን አ…
Jul 17, 2026በዚያም ወራት ሉቀ ጳጳሳቱ አባ ቄርሎስ አረፈ። የወንጌላዊው የማርቆስ መንበርም ያለሊቀ ጳጳሳት ነበር። ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ይሾሙት ዘንድ በአንድ ምክር ተስማሙ ሰይጣን ግን ክፉዎች ሰዎችን አነሣሥቶ ተቃወሙት። ሹመቱንም አልፈቀዱም። ነገር ግን መንፈሳዊ አባት የነበረውን የከሊል ልጅ አባ አትናቴዎስን ሾሙት። እርሱም መንጋውን በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ።
እርሱም በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆሳትና የሕዝብ አለቆች ዳግመኛ ተሰበሰቡና በእጃቸው ጽፈው አባ ገብርኤል እንዲሾም ፈቀዱ ሁለተኛም በሕዝቡ መካከል ሁከት ተነሣ ከሌሎችም ጋራ ዕጣ ያጣጥሉት ዘንድ ተስማሙ ስሞቻቸውንም ጽፈው በመንበሩ ላይ አኖሩ በላዩም እየጸለዩና እየቀደሱ ሦስት ቀኖች ሰነበቱ። ከዚህም በኋላ ታናሽ ብላቴና አምጥተው በውስጡ የአባ ዮሐንስ ስም ያለበትን ክርታስ አወጣላቸው። ያም አባ ዮሐንስ ተሾመ። ይህን አባ ገብረኤልን ግን ለማዕልቃ ቤተ ክርስቲያን ተከራካሪ አድርገው ሾሙት።
በዚያ ወራትም በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሁኖ ነበር። ይህ አባ ገብርኤልም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሒዶ በጾምና በጸሎት በስግደትም በቀንና በሌሊት ሲጋደል ኖረ። ከቅዱሳን መነኰሳትም ብዙዎች መልካም ራእይን አዩለት ከእርሳቸው በእስክንድርያ ከተማ የሊቀ ጳጳሳት ልብስን እንደሚአለብሱት ብዙዎች ከአሕዛብ የተመለሱ ክርስቲያኖችም እንደሚያጅቡት ያየ አለ። ደግሞም ይሾምባት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ሲሔድ ያየለት አለ። ቁጥር የሌላቸውንም መክፈቻዎችን ሲቀበል ያዩ አሉ።
ከገዳሙም ሊወርድ ብዙ ጊዜ ይሻ ነበር ነገር ግን አልተቻለውም። ከዚህ በኋላ አባ እንጦንስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ገዳም ትወርድ ዘንድ እኔ አልፈቅድም ጊዜው ሳይደርስ አትውረድ አለው።
ከሦስት ዓመት በኋላም አንዱ አረጋዊ የከበረ መልአክ እንግዲህስ አባ ገብርኤልን ወስደው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙታል እያለ እንደሚያነጋግረው ራእይ አየ። በዚያችም ቀን የሀገረ እንጣፊ መኰንን መጣ ከእርሱም ጋር ብዙዎች መሳፍንቶች ነበሩ። አባ ገብርኤልን አምጥተው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ የሚያዝዝ የንጉሥ ደብዳቤም ከእርሱ ጋር ነበረ።
ከዚህም በኋላ ያለ ፈቃዱ ወስደው በወንጌላዊው በማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስናን ሾሙት። በዚያችም ቀን እርሱ ለኢየሩሳሌም አንድ ጳጳስና ሌሎችንም ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመ። ከዚህም በኋላ ሦስት ጊዜ ሜሮን አከበረ ባረከ እንደዚህም አድርጎ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኖረ።
በዚያን ጊዜም አባ እንጦንስ ተገልጦ እንዲህ አለው እነሆ ዕረፍትህ ቀርቦአል ከዐሥራ ስምንት ወሮች በኋላ ወደ እግዚአብሔር ትሔዳለህ የዘላለም ሕይወትንም ትወርሳለህ።
ከዚህም በኋላ በክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራ ሆነ። ይህም አባት ወገኖቹን ያድን ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ሕዝቡን ይቅር አለ።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ከመንበረ ሢመቱ ወጥቶ በምስር አገር ዓመት ሙሉ ተሠወረ። ከአንድ ምእመን በቀር ማንም አላወቀበትም በቀንና በሌሊት በገድል ከመቀጥቀጡ የተነሣም መልኩ ተለወጠ ሥጋውም ደረቀ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እርሱን ለሚፈራው ለአንድ ምእመን ሥራውን ገለጠ። እርሱም ከዚያ ቦታ አውጥቶ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አስቀመጠው በጸሎትና በቅዳሴ እያገለገለ ኖረ። ድኆችንም ይጐበኛቸው ነበር። የሚሹትንም ይሰጣቸው ነበር። ወደ ርሱ የሚመጡትንም ሕዝቦች ያስተምራቸውና ያጽናናቸው ነበር።
በአንዲት ዕለትም ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስ በግልጽ ታየው እንዲህም አለው ስለዚህ ፈጽሞ አትዘን ከዚህ ብዙ ድካምና መከራ እግዚአብሔር ያሳርፍሃልና አነሆ ምድራዊ ኑሮህን የሚፈጽም ደዌ በአንተ ላይ ይመጣል ነገር ግን ደስ ይበልህ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለሃልና። የዘላለም ሕይወትንና የማያልቅ ተድላ ደስታንም ትወርሳለህና አለው።
በዚያን ጊዜም በሚያስጨንቅ ደዌ ታሞ እየተጨነቀ ኖረ። ስለ ነፍሱም መውጣትና በእግዚአብሔር ፊት ስለ መቆሙ ይፈራና ይደነግጥ ነበር የእመቤታችን ማርያም ሥዕልም በዚያ ነበረ። ወደርሷም አዘውትሮ ይማልድ ነበረ በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ራሱ እግዚአብሔር በብሩህ ገጽ ተገለጠለት መንግሥተ ሰማያትን አግኝተሃልና ደስ ይበልህ እንጂ አትፍራ እስከ ሦስት ቀንም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ትወጣለህ በማለት አረጋጋው። ይህንንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ በሦስተኛውም ቀን በሰላም አረፈ። በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ክብር ተቀበረ።
† ሐምሌ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ)
3.አባ ኢሳይያስ ዘገዳመ አስቄጥስ
4.አባ ገብርኤል ሊቀ ጳጳሳት
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘10🥰3❤2🕊2😍2
#ሐምሌ_11
Jul 17, 2026#ሐምሌ_11
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን #ቅዱሳን_ዮሐንስና_ስምዖን በሰማዕትነት ሞቱ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ገብርኤል አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ
ሐምሌ ዐሥራ አንድ በዚህች ቀን መርባስ የሚባል አገር ሰዎች የሆኑ ቅዱሳን ዮሐንስና የአባቱ ወንድም ልጅ ስምዖን በሰማዕትነት ሞቱ። የዚህ ቅዱስ ዮሐንስ እናቱ መካን ነበረች አባቱም ልጅን ይሰጠው ዘንድ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይለምነው ነበር ከዚህም በኋላ ልጁን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ሊአደርገው ተሳለ።
መጥምቁ ዮሐንስም እግዚአብሔር ልጅን እንደሚሰጠው በራእይ ተገልጦ ነገረው። ይህን ቅዱስም በወለደው ጊዜ ዮሐንስ ብሎ ጠራው በመጥምቁ ዮሐንስም ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራ። ከዚህ በኋላ አድጎ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎች እረኛ አደረገው ምሳውንም ለእረኞችና ለመንገደኞች ሁል ጊዜ ይሰጥ ነበር እርሱ ግን እስከ ምሽት ይጾም ነበር።
አባቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ስለዚህ ሊአረጋግጥ ወደ ርሱ ሔደ አባቱንም በአየው ጊዜ ዮሐንስ ፈርቶ ሊሸሽ ወደደ። አባቱም የዛሬ ምሳህን አሳየኝ አለው ብላቴናውም ታይ ዘንድ ግባ አለው ወደ መጠለያውም በገባ ጊዜ አገልግሉን ትኩስ እንጀራን ተመልቶ አገኘው እጅግም አደነቀ ከልጃቸው የሆነውንም ለሚስቱ ነገራት።
ከዚያችም ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ አደረችበት አወቁ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማር አደረጉት እንጂ በጎችን የሚጠብቅ እረኛ እንዲሆን አልተዉትም።
ከዚህም በኋላ አባቱ ሊአጋባው ወደደ። እርሱ ግን ይህን አልወደደም። ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነውም ጊዜ ቅስና ተሾመ የአባቱ የወንድም ልጅ የሆነ ስምዖንም በጎቹን ትቶ መጥቶ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆነ። እርሱም ስለ ተአምራቱ የተናገረ ነው። እግዚአብሔር በእጆቹ ላይ ድንቆችንና ተአምራቶችን ገልጧልና። ደዌ ያለባቸውንም ሁሉ ያመጡአቸው ነበር እርሱም በዘይቱ ላይ ይጸልይና ይቀባቸው ነበር ወዲያውኑም ከደዌያቸው ይድኑ ነበር። እርሱም ወደርሱ የሚመጡትን ከኃጢአት ይርቁ ዘንድ ያስተምራቸው ነበር። ይመክራቸውና ይገሥጻቸውም ነበር። ተአምራቱም የማይቈጠር ብዙ ነው። ከተአምራቱም አንዱ ይህ ነው። በአንዲት ዕለት አንድ የንጉሥ ጭፍራ አንዲት መበለት የተሸከመችውን ገብስ ቀምቶ ለፈረሱ አበላት ያችም መበለት በዚህ ቅዱስ ዘንድ ከሰሰችው ቅዱስ ዮሐንስም ረገመው ያን ጊዜም ፈረሱ ሞተች።
ዳግመኛም የንጉሥ የጭፍራ አለቃ ግብር ሊሰበስብ መጣ አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ አገልጋይም ነበረው። ከእርሱም ተባርኮ ወዲያውኑም የታወረች ዐይኑ ተገለጠች በእርስዋም ደኅና አድርጎ አየ። ይህም ቅዱስ የሰዎችን ሥራቸውን በግልጽ ያይ ነበር ስለ ኃጢአታቸውም ንስሓ ይገቡ ዘንድ ይገሥጻቸው ነበር።
ዜናውም በንጉሥ ማርያኖስ ዘንድ ተሰማ ለእርሱም አንዲት ሴት ልጅ ብቻ ነበረችው ወደ ሆድዋም ከይሲ ገብቶ ለሞት ተቃረበች ከዚህም በኋላ ያድኗት ዘንድ ገንዘቡን ለባለ መድኃኒቶች ሰጠ ነገር ግን አልተቻላቸውም። ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃው የባሪያውን ዐይን እንደ አዳነ የቅዱስ ዮሐንስን ዜና ነገረው ንጉሡም ጭፍራ ልኮ ወደርሱ ሊአስመጣው ወደደ ቅዱስ ዮሐንስም በመንፈስ ዐወቀ እርሱ ግን የመንገዱን ድካምና ባሕሩን ይፈራ ነበር ያን ጊዜም ደመና መጥታ ነጠቀችው ሰርመላስ ከሚባል አገርም ወደ አንጾኪያ ከተማ አደረሰችው። በንጉሡም ዐልጋ ላይ አቆመችው ንጉሡም ደነገጠ ቅዱስ ዮሐንስም ወደዚህ ወዳንተ ልታስመጣኝ የተመኘኸው ምስኪን ሰው እኔ ነኝ ብሎ ነገረው። አሁንም ልጅህን አምጣት አለው ልጁንም አመጣ። በላይዋም በጸለየ ጊዜ ከይሲው ሳያሳምማት ከሆድዋ ወጣ። ንጉሡም ከቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሁሉ ጋር ከእርሱ ተባረከ። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ጸጋ የሚሰጥ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
እጅ መንሻውንም ብዙ ገንዘብ አቀረበለት እርሱ ግን ምንም አልወሰደም። ንጉሡም በእርሱ ዘንድ ሊአኖረው ወደደ ቅዱሱ ግን አልወደደም ንጉሡም እንዳይሔድበት ቀሚሱን ያዘ ያንጊዜም ንጉሡ ቀሚሱን እንደያዘ ደመና ነጥቆ ወሰደው ቀሚሱም ተቆርጦ በንጉሥ እጅ ላይ ቀረ ቅዱስ ዮሐንስም በዚያች ሰዓት ወደ ሀገሩ ደረሰ።
ንጉሡም ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ የቀሚሱን ቁራጭ በውስጧ አኖረ ቤተ ክርስቲያኒቱም እስከ ዛሬ ድረስ የፊቃር ቤተ ክርስቲያን ተባለች። የቊርባን ቅዳሴ በሚቀደስ ጊዜም ሥጋውንና ደሙን መቀበል የሚገባቸውንና የማይገባቸውን ጻድቃንና ኃጥአንን ያያቸዋል።
ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ የጣዖትን አምልኮ በአቆመ ጊዜ ለአባቱ ወንድም ልጅ ለስምዖንም ይህን አስረድቶት ወደ እስክንድርያ ከተማ ሔዱ በመኰንኑ ፊትም ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይም አሠቃያቸው። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቈረጣቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ከሥጋቸውም ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ ለበሽተኞችም ታላቅ ፈውስ ተገኘ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ገብርኤል_ሊቀ_ዻዻሳት
ዳግመኛም በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ገብርኤል አረፈ። የዚህ ቅዱስ ወላጆች በእግዚአብሔር ሕግ የጸኑ ደጋጎች ፈቃዱንና ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ነበሩ።
ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት። በአንዲት ዕለትም ቅዱሳን መነኰሳት ወደርሱ መጡ ከውስጣቸውም መልካም ገድል ያለው አንድ አረጋዊ ነበረ። እርሱም ብዙዎች ኤጲስቆጶሳት ሕፃኑን ከበው እጃቸውን እንደሚጭኑበት እንደሚባርኩትና ይሁን ይሁን ይገባዋል እንደሚሉ ራእይን አየ።
ሽማግሌውም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ሕፃኑ ታላቅ እንደሚሆን አሰበ ለአባቱም ይህን ሕፃን አስተምረው ለብዙዎች ሕዝቦች አለቃ ይሆን ዘንድ አለውና አለው። አባቱም ሰምቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው ከዚህ ሕፃን ምን ይደረግ ይሆን አለ።
ሕፃኑ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ አባቱ አረፈ ብህና በሚባል አገርም ገድሉ የተደነቀ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ብሉያትንና ሐዲሳትንም የሚያውቅ የእናቱ ወንድም ስሙ ጴጥሮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ነበረ ሕፃኑንም ወስዶ አስተማረው ከተሰጠውም ጸጋና ከዕውቀቱ የተነሣ ያዩት ሁሉ ያደንቁ ነበር ዲቁናም ተሾመ።
ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሆነው ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ይህንም ኃላፊውን ዓለም ናቀ ኤጲስቆጶሱ አባ ጴጥሮስም በገድል ተጸምዶ ለሚኖር ለቀሲስ አባ ጴጥሮስ ሰጠው እርሱም በጥቂት ቀኖች የምንኵስናን ገድል አስተማረው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ታዩ።
ከዚህም በኋላ መምህሩ ቀሲስ አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ከዚያ ተነሥቶ ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሔደ በዚያም በጾምና በጸሎት በስግደት በመትጋት እየተጋደለ ያለ ማቋረጥ ብዙ ዘመናት ኖረ።
ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አባ መቃርስ ደብር ሔደ። በደብረ ማርስ ባለች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን አበምኔት አደረጉት ሕንፃዋንም አደሰ።
ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከቅዱሳት መካናት ተባረከ በዚያም በቅድስት ትንሣኤ በተሰየመች ቤተ ክርስቲያን በጳጳሱ በአባ ሚካኤል እጅ ቅስና ተሾመ። ከዚያም ወደ ምስር አገር ተመልሶ በማዕልቃ ባለች በእመቤታችን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጻፈ ተቀመጠ።
🥰10😘4❤2💯2
ቅዱሳን (Saints)
Jul 16, 2026#ሐምሌ_10 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥር በዚህች ቀን #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ልደታቸው ነው፣ ናትናኤል የተባለው #ቅዱስ_ስምዖን_ቀለዮጳ በሰማዕትነት አረፈ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱ…
Jul 16, 2026#ሐምሌ_10 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥር በዚህች ቀን #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ልደታቸው ነው፣ ናትናኤል የተባለው #ቅዱስ_ስምዖን_ቀለዮጳ በሰማዕትነት አረፈ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ከላድያኖስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_ብስንዳ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ሐምሌ ዐሥር በዚህች ቀን አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ…
ይህም ቅዱስ በወንጌላዊው በማርቆስ መንበር ዐሥራ አራት ዓመት መንጋውን እየጠበቀ ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_አባ_ብስንዳ_ጻድቅ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባት ብስንዳ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጥልቅ በሆነ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቆሞ ሲጋደል ኖረ መላእክትም ይጐበኙትና ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ነበር። ከዚህም በኃላ በሰላም አረፈ።
† ሐምሌ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ታላቁ አባ ብስንዳ ጻድቅ
3.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት
† ወርኀዊ በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😍12😘4❤2🥰2🕊2
#ሐምሌ_10
Jul 16, 2026#ሐምሌ_10
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዐሥር በዚህች ቀን #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ልደታቸው ነው፣ ናትናኤል የተባለው #ቅዱስ_ስምዖን_ቀለዮጳ በሰማዕትነት አረፈ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ከላድያኖስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_ብስንዳ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ
ሐምሌ ዐሥር በዚህች ቀን አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ልደታቸው ነው። ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው ‹‹እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡
አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን ‹‹ሳሙኤል›› አሉት፡፡ ትርጓሜውም ‹‹እግዚአብሔር ጸለቴን ሰማኝ›› ማለት ነው፡፡ ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኩሰውታል፡፡ ‹‹ደብረ ወገግ›› የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ አስቦ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ አስቦን የብርሃን ውጋጋን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም ‹‹ቦታውን ደብረ ወገግ›› (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት›› ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት እንዳረገ ድርሳነ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡
በቦታው ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡
ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን ሚስት እንጀራ እናቱን በማግባቱ ምክንያት አቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው ያወገዙትን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ወገኖች በየአውራጃው በተናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስንም ደሙ በምድር ላይ እስከሚንጣለል ድረስ ገርፈው ወደነበረበት ቤቱ ወሰዱት፤ ፊሊጶስም በሚሄድበት ቦታ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ሞተ፡፡
እንድርያስ፣ አኖሬዎስና ተክለ ጽዮን ሁላቸው ከተከታዮቻቸው ጋር በሰማዕትነት አርፈው እነስድስተይ በምትባል ምድር ተቀበሩ፡፡ ጳጳሱን አቡነ ያዕቆብንም ደሙ በምድር ላይ እንደውኃ እስኪወርድ ድረስ ገርፈው ወደ ሀገሩ እንዲሰደደ አደረጉት፡፡ ከዚያም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ በእነስድስታይ አገር ላሉ ሰዎችም ሁሉ አባት ሆናቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጁንም ታዲዮስን መምህርና አባት አድርጎ ሾመላቸውና ጽላልሽ ሄዶ እናቱን ይዞ ጽጋጋ ምድረ ወገግ ወስዶ አመነኮሳት፡፡
አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡
ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል›› ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በሰላም ዐርፈዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ናትናኤል_ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
በዚህች ቀን ናትናኤል የተባለው ቅዱስ ሐዋርያ ስምዖን ቀለዮጳ በሰማዕትነት አረፈ፡፡
ይህንንም ሐዋርያ አይሁድ የጌታችንን ወንድም ያዕቆብን ከገደሉት በኋላ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሐዋርያት ሾሙት። እርሱም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ከአይሁድ ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው ተአምራትንም አድርጎአልና በሽተኞችንም አድኗልና።
ንጉሡ እንድርያስም ሴቶችን ከባሎቻቸው እንደሚለይ ንጽሕናቸውንም እንዲጠብቁ እንደሚአዝዛቸው ስለ እርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ከእርሱም ጋር ቴዎና የምትባል አንዲት ድንግል ተገደለች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ከላድያኖስ_ሊቀ_ዻዻሳት
በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዘጠነኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ከላድያኖስ አረፈ።
🥰10❤4😍3🕊2😘2
🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
Jul 16, 2026🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🥰4😘4❤3😍3
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 16, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤4🥰4😘3😍1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 16, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
🥰4😘4❤3😍1
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 16, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍5🥰4❤3😘3
🔔 ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት (የስጋ ሩካቤ) ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ህግ እና ስርዓት አንጻር ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ከርስቲያን ለመንፈሳዊ ህይወቱ እና ለመልካም ስነምግባር ጉዞው ማወቅ ያለብት ትምህርት፦
Jul 15, 2026🔔 ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት (የስጋ ሩካቤ) ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ህግ እና ስርዓት አንጻር ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ከርስቲያን ለመንፈሳዊ ህይወቱ እና ለመልካም ስነምግባር ጉዞው ማወቅ ያለብት ትምህርት፦
🔗https://t.me/+4spyK-uT0MkyZmZk
🥰3😘3❤2😍2
#ሐምሌ_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅ…
Jul 15, 2026#ሐምሌ_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ታውድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መስተጋድል #አባ_ኅልያን አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት ለአቡነ…
😘8❤5🥰2😍2💯2
ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንን…
Jul 15, 2026ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።
ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።
ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ኅልያን_ገዳማዊ
በዚህችም ቀን መስተጋድል አባ ኅልያን አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።
በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ አላት።
ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።
ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።
ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር።
የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።
ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።
ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት።
=>ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ኅልያን ገዳማዊ
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)
3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት
4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ)
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘8😍4🥰3❤2💯2
#ሐምሌ_9
Jul 15, 2026#ሐምሌ_9
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ታውድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መስተጋድል #አባ_ኅልያን አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡
መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡
አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን "ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው" ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል።
አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን በዚህች ዕለት ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ "ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ" በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ" ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ "አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ" ስትላቸው "እግዚአብሔር ይፍታሽ" ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡
ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ (ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡) ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)
ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር።
ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።
ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም። መኰንኑም በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ ይምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው አለው።
መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ታውድሮስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ከቆጵሮስ አገር ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ አረፉ።
ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።
🥰6😘4❤2😍2💯2
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Jul 15, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
😘6🥰4😍3❤1
⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
Jul 15, 2026⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
የሁሉንም አባቶች ትምህርት ይፈልጋሉ❓️
--------------------------------------------------
🥰4❤3😍1😘1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 14, 2026ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ከእሳት እንዲጨምሩአቸውና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ደማቸው እስኪፈስ ድረስ እንዲገርፉአቸው አዘዘ።
Jul 14, 2026ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ከእሳት እንዲጨምሩአቸውና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ደማቸው እስኪፈስ ድረስ እንዲገርፉአቸው አዘዘ።
ዳግመኛም ስለታምና ረጃጅም በሆኑ ችንካሮች ሥጋቸውን ቸንክረው ከታች እሳትን አነደዱባቸው ጌታችንም መልአኩን ልኮ ከእሳቱ አዳናቸው። እንደገናም በታላቅ ዛፍ ላይ ዘቅዝቀው ይሰቅሏቸው ዘንድ አዘዘ። ከአፍንጫቸውና ከአፋቸው ብዙ ደም ወረደ ጌታችን ፈጣሪያችንም ከመላእክቱ ጋራ ወርዶ አዳናቸው መኰንኑም በፊቱ በቆሙ ጊዜ ከጽናታቸው የተነሣ እጅግ አደነቀ።
ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ፈርማ ላካቸው መኰንኑም ለአማልክት ዕጣን አጢሱ አላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ከኮምጣጤና ከሙጫ ጋራ ጨው ደባልቆ አፍልቶ በአፋቸውና በአፍንጫቸው ጨመረ እነርሱም ይህን ሁሉ ሥቃይ ታገሡ። ከዚህም በኋላ በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከታች እሳትን አነደዱባቸው የእጆቻቸውንና የእግሮቻቸውንም ጥፍሮች አወለቁ በብረት በትሮችም አጽንተው መቷቸው።
በዚያን ጊዜም የመኰንኑ ሚስት ሞተች እርሱም ደንግጦ ይቅር እንዲሉት ሚስቱንም እንዲአስነሡለት ቅዱሳኑን ለመናቸው። እነርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመኑት ያን ጊዜም ተነሣች መኰንኑም ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ በጌታችን አመነ ቅዱሳኑንም ወደ ሀገራቸው ይሔዱ ዘንድ ለቀቃቸው።
ወደ ሀገራቸው ወደ ገምኑዲም በደረሱ ጊዜ የቀረ ገንዘባቸውን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጡ የቅዱስ አንያኖስንም ሥጋ ስሙ ሰረባሞን ለሚባል አንድ ጻድቅ ሰው አደራ አስጠበቁት እንደቀድሞውም በፊቱ መብራትን እንዲአበራ አዘዙት።
ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ሔደው በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። መኰንኑም እንዲገርፉአቸውና እንዲጐትቱአቸው አዘዘ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ ደንቆሮና ዲዳ የሆነች ሴትም መጥታ ከቅዱሳኑ ደም ወስዳ አፏንና ጆሮዎቿን ልቧንም ቀባች ወዲያውኑም ድና ተናገረች ሰማችም።
መኰንኑ ግን አሠራቸው ከዚህም በኋላ እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በዚያም ከገምኑዲ አገር ሰረባሞንና ሌሎች ሰዎችም ነበሩ በበፍታና በከበሩ ልብሶች ገነዙአቸው መዓዛው ጣፋጭ በሆነ ሽቱም ቀቡአቸው ወደ አገራቸው ወደ ገምኑዲም ወሰዱአቸው።
ከገምኑዲም ከተማ ውጭ በደረሱ ጊዜ ሥጋቸው የተጫነበትን ሠረገላ የሚስቡ እንስሶች ቆሙ። ሥጋችን በውስጡ ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር የመረጠው ቦታ ይህ ነው የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ በዚያም አኖሩአቸው። ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው ሥጋቸውንም ከቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ጋር በውስጥዋ አኖሩ በገምኑዲ አገርም ድንቆችንና ተአምራቶችን እያሳዩ እስከ ዛሬ ድረስ አሉ።
ለእኒህ ቅዱሳንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውንም እንደችሎታው ለሚያደርግ ኃጢአቱ ይሠረይለታል ሥቃይንም ከቶ አያይም ብሎ መከራ በሚቀበሉበት ጊዜ ቃል ኪዳን ሰጣቸው።
#ቅዱስ_አባ_በላኒ
በዚህችም ቀን ከግብጽ ደቡብ አካ በሚባል አውራጃ ባራ በምትባል መንደር ይኖር የነበረ ቅዱስ ሰማዕት አባ በላኒ አረፈ። ይህም ቅዱስ ቄስ ነበር። የምእመናንን መከራቸውን የሰማዕታትንም መገደላቸውን በሰማ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጥቶ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመኰንኑ ፊት ታመነ መኰንኑም ጽኑ የሆነ ሥቃይን ብዙ ቀን አሠቃየው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀ።
#አባ_ቢማ_ሰማዕት
በዚህችም ዕለት ከላይኛው ግብጽ ከብህንሳ ከተማ አባ ቢማ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ሰው ባለጸጋና በጎ የሚሠራ ድኆችንም የሚወድ በሀገርም ላይ የተሾመ ነበር። በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በራእይ ፊቱ ከፀሐይ ብርሃን እጅግ እየበራ አየው እንዲህም አለው ሰላም ለአንተ ይሁን ወደ መኰንኑም ሒደህ በስሜ ታመን። እኔ የክብር አክሊልን አዘጋጅቼልሃለሁና።
ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ። ከዚህም በኋላ ጸሎት አድርጎ ከቤቱ ወጣ ሉቅያኖስ ወደሚባል መኰንንም ሒዶ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ።
መኰንኑም በአየው ጊዜ ሹም እንደሆነ አውቆ ከእርሱ ንዋየ ቅድሳትን ፈለገ ዳግመኛም ለአማልክት እንዲሠዋ ፈለገ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ስለ ንዋየ ቅድሳት ከእኔ ልትሻ አይገባህም የረከሱ አማልክትንም ስለማምለክ ትእዛዝህን አልሰማም እኔ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁና።
መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጥቶ ምላሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም እንደ ቀድሞው ምላሱን መለሰለት። ከዚህ በኋላ በማበራያ ውስጥ አበራዩት በብረት ዐልጋ ላይም ቸንክረው በበታቹ እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጉዳትም አስነሣው።
ከዚህ በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገልጾለት አጽናናው ከዚህም በኋላ በወህኒ ቤት ጨመሩት በዚያም ተአምራትን አደረገ። ጋኔን ያደረባት የአቅፋሃስ ሀገር ሰው የዮልያኖስ እኅት ነበረች ቅዱስ ቢማም ያንን ጋኔን ከእርሷ ላይ አወጣውና አሳደደው ዜናውም በሀገሩ ውስጥ በተሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ።
መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃየው በመንኰራኵርም የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች አወለቁ በእሳት በአጋሉት በብረት ሰንሰለትም አሥረው ጐተቱት። በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥም ጣሉት ከዚህም ጌታችን አዳነው። ከዚህም በኋላ በአንገቱ ታላቅ ደንጊያ አንጠልጥለው በባሕር ውስጥ ጣሉት አሁንም ጌታችን አዳነው። ሁለተኛም ከእሳት ጨመሩት። ከዚህም ጌታችን አዳነው በእሳቱም መካከል እየጸለየ ቆመ።
መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያም ያሠቃዩት ጀመሩ ዘቅዝቀውም ሰቀሉት ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ ጨምረዉ በላዩ እሳትን አነደዱበት ጌታችንም ተገለጠለትና ከእሳቱ አዳነው።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉን ለሚጽፍ በስሙም ምጽዋት ለሚያደርግ ሁሉ የዘለላም ሕይወትን ያድለው ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው።
መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንደ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ። የአቅፋሃስ ከተማ ሹም የሆነ የዮልዮስ ባሮችም ሥጋውን አንሥተው ወደ ሀገሩ ወሰዱት እስከ ስደቱ ዘመን ፍጻሜ ድረስም በመልካም ቦታ አኖሩት። ከዚህም በኋላ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያንንና ገዳምን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ በሽተኞችም ሁሉ ይፈወሱ ነበርና።
† ሐምሌ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ኪሮስ ጻድቅ (አረጋዊና ገዳማዊ)
2.አባ ብሶይ ጻድቅ (ኮከበ ገዳም)
3.አባ ሚሳኤል ነዳይ (ጻድቅ)
4.አባ ቢማ ሰማዕት
5.አባ በላኒ ሰማዕት
6.ቅዱሳን አቤሮንና አቶም (ሰማዕታት)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
4.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘8😍3❤2🥰2❤🔥1
በዚህችም ቀን አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረው አባ ሚሳኤል አረፈ። ዜናውም እንዲህ ነው። አባ ኪሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም ሔደ። ከዚያም ደርሶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተሳለማት በዚያም አምላክን የወለደች የእመቤ…
Jul 14, 2026በዚህችም ቀን አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረው አባ ሚሳኤል አረፈ። ዜናውም እንዲህ ነው። አባ ኪሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም ሔደ። ከዚያም ደርሶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተሳለማት በዚያም አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ሥዕል አየ። ከዐይኖቹም ዕንባ እያፈሰሰ እመቤቴ ሆይ አስቢኝ አላት ሥዕሊቱም ኪሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ከዚህም አትለፍ የአባትህን ዐፅም ትጠብቅ ዘንድ ወደ ማደሪያህ ተመለስ እንጂ አለችው። አባ ኪሮስም ይህን ሰምቶ ከሥዕሏ ፊት ሰባት መቶ ሰግደትን ሰገደ። በዕብራይስጥም ቋንቋ እንግዳ ነህና በቃህ በምሕረት መዝገብም ተመዝግቦልሃል የሚለውን ቃል ሰማ።
ከዚያም በአለፈ ጊዜ መነኰሳቱ መልኩ የተዋበ ሁለመናውም ያማረ እንደሆነ ተመለከቱ። እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ ይህ መነኵሴ ከመንግሥት ከተማ ከግብጽ አገር የመጣ ነው ሰውነቱ በጾምና በጸሎት አልጠወለገምና። እጅግም ነቀፉት አልተቀበሉትም።ነገር ግን ወደ ሌላ ወደሚንቁት ቦታ ሰደዱት።
በዚያም መስፈርስ በሚባል ሕማም ለብዙ ጊዜ የታመመና በምድር ላይ የተጣለ ድኃ ሰውን አገኘ። በራስጌውም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በግርጌው ቅዱስ ገብርኤልን በቀኙም ሩፋኤልን በግራውም ሰዳካኤልን አየ። እነርሱም በክንፋቸው ጋርደውት ነበር ከሰውም ያለርሱ ያያቸው አልነበረም። በገዳዩች ፊት ሞትን የማይፈራ ጐበዝ እንዴት ነህ ብለው ሰላምታ ሰጡት።
አባ ኪሮስም አደነቀ በልዕልና ነዋሪዎች ሆይ ከዚህ ለምን ተቀመጣችሁ አላቸው የህን ድኃ እንድንጠብቀው ከእግዚአብሔር ታዘናል አሉት አባ ኪሮስም እስከ መቼ ነው አላቸው። ከዚህ ድካም እስከሚአሳርፈው ድረስ ነው አሉት።
ከዚህም በኋላ ወደ ታመመው ደኃ ተመልሶ በዚህ ቦታ ከኖርህ ምን ያህል ዘመን ነው አለው በሽተኛውም ሰላሳ አምስት ዓመት ነው አለው ሁለተኛም ከታመምክ ስንት ዓመት ነው አለው ሃያ ዓመት ነው ብሎ መለሰ። አበ ምኔቱና የገዳሙ መነኰሳት ይጐበኙሃልን ብሎ ጠየቀው በሽተኛውም አባቴ ሆይ የለም አይጐበኙኝም ፊታቸውን ከአየሁ ዓሥራ አምስት ዓመት ይሆናል ብሎ መለሰ።
አባ ኪሮስም ና ንገረኝ አባትህ ማነው እናትህስ ማናት አለው በሽተኛውም እንዲህ ብሎ መለሰ አባቴ የኬልቄዶን ንጉሥ እናቴም የራሕራሕ ንጉሥ ልጅ ናት። አባቴ ኪሮስ ሆይ እውነት እልሃለሁ በአባቴ ቤት ያሉ ሰዎች ወርቁንና ብሩን ቀጭኑንም ልብስ በእግሮቻቸው ይረግጡአቸዋል።
አባ ኪሮስም ወደዚች ገዳም ማን አደረሰህ አለው ድውዩም እንዳንተ ያሉ ሁለት ሰዎች ወደ አባቴ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ። እኩለ ሌሊትም ሲሆን ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰውም ወደኔ መጣ ሚሳኤል ብሎ ጠርቶ ሲነጋ ተነሥተህ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋራ ሒድ አለኝ በእንዲህ ያለ ሥራ ወጥቼ ወደዚህ ቦታ ደረስሁ ምንም በጎ ሥራ ሳልሠራም እንደ እነርሱ ሆንሁ።
አባ ኪሮስም እኔ አጽናናሃለሁና ወንድሜ ሆይ ስማ ስሙ በብኑዳ የሚባል አንድ እጅግ ድኃ የሆነ በበረሃ የሚኖር መነኵሴ ነበረ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ወደርሱ መጥቶ አሳተው እግዚአብሔርም ሥጋውን ለአንበሳና ለሰማይ ወፎች ሰጠ እርሱም በወገን የከበረ ከሮም ንገሥ በታች የሚገዛ የኬፋዝ ንጉሥ ልጅ ነበረ።
ሁለተኛም እነግርሃለሁ የሮሜ ንጉሥ ልጅ የሆነ አንድ ድኃ ነበረ። እርሱም ከበትር ብቻ በቀር ከአባቱ ቤት ምንም ሳይዝ በቀስታ ወጣ ያንንም ሰው እኔ እጅግ አውቀዋለሁ። ከገዳም ወደ ገዳም ከተራራም ወደ ተራራ ይዞር ነበር ሞቱንም አላስተዋልኩም ሕይወቱንም አላወቅሁም።
ዳግመኛም አንድ የንጉሥ ልጅ ድኃ ነበረ። እርሱም በሰንበታት እነጂ በሌላ ቀን ምንም ሳይቀምስ ማቅ ለብሶ በቀንና በሌሊት ለጸሎት ይተጋ ነበር። በእንዲህ ያለ ሥራም ኑሮ አረፈ የብርሃን መላእክትም ነፍሱን ወስደው በመንግሥተ ሰማያት አኖሯት።
አሁንም ወንድሜ የምነግርህን ስማ። የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አታድንቅ የወደደውን ይገሥጻልና ያም በሽተኛ ድኃ መነኰስ እውነት ነው ለእኔ ይገባኛል ሰለ ኃጢአቴም ይህን ተቀበልሁ ብሎ መለሰ። ይህንንም ብሎ ዝም አለ።
በዚያች ሰዓትም ያን በሽተኛ በሞት ያሰናብተው ዘንድ አባ ኪሮስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በድንገት መጣ። እልፍ አእላፋት መላእክትም በዙሪያው ሆነው ከእርሱ ጋር ነበሩ ለጻድቃን ሞገሳቸውና ንጉሣቸው የሆነ አምላካችንን እናመስግነው ለችግረኞችም ተስፋ የሆነ አምላካችንን እናመስግነው እያሉ ይዘምሩ ነበር። በዚህ ዓለም በገድል የደከሙ በእርሱ ደስ ይላቸዋል።
አባ ኪሮስም በአየ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ወደዚህ ምን አመጣህ አለ ጌታችንም ስለ ጠራኸኝ መጣሁ አለው። አባ ኪሮስም ይህ ሰው ፃዕር በዝቶበታልና ያርፍ ዘንድ አሰናብተው አለው። ጌታችንም ምን ያህል እንደምወድህ የመላእክት ሠራዊት ያዩና ያውቁ ዘንድ ይቺን የገነት ተክል አበባ ከእጄ ወስደህ በዚህ በሽተኛ በፊቱ ላይ ጣል አለው። አባ ኪሮስም ያንን የገነት ተክል አበባ ከጌታችን እጅ ተቀብሎ በበሽተኛው ፊት ላይ አኖረ ያን ጊዜም ነፍሱ ያለ ፃዕር በፍጥነት ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ከእርሱም ጋር በብርሃን ሠረገላ ውስጥ አስቀመጣት አውጥቶም በሰማያዊ ክብር አኖራት።
አባ ኪሮስም እያደነቀ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ወደ አበምኔቱ ሔዶ እነሆ ያ ድኃ ስለ አረፈ መቃብር ቆፍረው ይቀበሩት ዘንድ ከመነኰሳቱ እዘዝ አለው አበ ምኔቱም ምን ግዴታ አለብኝ አለው አባ ኪሮስም ትኩር ብሎ ተመለከተውና ይህ የሰይጣን ሥራ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም አለው። ሰለ አስጨነቀውም ሰባት መነኰሳትን አዘዘለት እነርሱም ማዕጠንታቸውን ይዘው ተነሡ አባ ኪሮስም የሚአጥኑት አሉና የረከሱ ማዕጠንቶቻችሁን አስወግዱ። በቦታቸውም ተዉአቸው ነገር ግን ቅበሩት ብሎ አማላቸው።
ያን ጊዜም አራቱ የመላእክት አለቆች ሥጋውን በከርቤና በሚዓ አጠኑ መዓዛውም ያንን በዓት መላው እነዚህ መነኰሳትም የሚያሸተን ምንድነው ይህ መነኰስ ሥራይን ያውቅ ይሆን ተባባሉ። ከዚህም በኋላ ሥጋውን ወስደው በዚያው ገዳም በእንግዳ መቃብር ቀበሩት ከመቃብሩም ጥሩ ውኃ ፈልቆ ለበሽተኞች ፈውስ ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አቤሮንና_አቶም
በዚህችም ቀን ዳግመኛ ከእስክንድርያ ከተማና ከገምኑዲ የሆኑ ቅዱሳን አቤሮንና አቶም በሰማዕትነት ሞቱ። የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ነበሩ። ብዙ ምጽዋትንም ይሰጡ ነበር። የአባታቸውም ስም ዮሐንስ የእናታቸው ማርያም ነበር።
አባታቸው በአረፈ ጊዜ የአቤሮን ዕድሜ ሠላሳ የአቶምም ዕድሜ ሃያ ሰባት ዓመት ነበረ። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም የተፀመዱ ነበሩ የሚራሩም ነበሩ መጻተኞችንም በፍቅር ይቀበሏቸው ነበር በትሩፋት ሁሉና በበጎ ሥራ ፍጹማን ነበሩ።
ፈርማ በሚባል አገር ብዙ ሰዎች በሰማዕትነት በሞቱ ጊዜ እሊህ ቅዱሳን ገንዘባቸውን ይዘው ለንግድ ወደ ፈርማ ሔዱ። የንጉሥ ጭፍሮችንም አገኟቸው ከእርሳቸውም ጋራ የሰማዕቱ የቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ነበረ ለጭፍሮችም ብዙ ገንዘብ ሰጥተው ከጭፍሮች እጅ ወደ ቤታቸው ወሰዱት ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥም አኖሩት በፊቱም ሁል ጊዜ የሚበራ መብራትን አኖሩ። ከሥጋውም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
በዚያን ጊዜም እሊህ ቅዱሳን ስለዚህ ስለ ኃላፊው ዓለም ፍጻሜና በመንግሥተ ሰማያት ስላለው ዘለዓለማዊ የተድላ ደስታ ኑሮ አሰቡ።ከዚህም በኋላ ተስማምተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ሔዱ በመኰንኑም ፊት ቁመው ክብር
🥰9❤4😘3❤🔥2😍2
በዚህችም ዕለት በምዕራባዊ በረሀ የሚኖር ታላቅና ክቡር አባት የሆነው የአባ ኪሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። …
Jul 14, 2026በዚህችም ዕለት በምዕራባዊ በረሀ የሚኖር ታላቅና ክቡር አባት የሆነው የአባ ኪሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። ጌታቸንም መርቶ ወደዚች ምዕራባዊት በረሀ አደረሰው በውስጧም ብዙ ዘመናት ብቻውን ኖረ ከሰው ማንም አላየውም በዚህ ሁሉ ዘመን የዱር አራዊትም ቢሆኑ።
በአስቄጥስም ገዳም ስሙ አባ ባውማ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው። እርሱም እንዲህ አለ በቤተ ክርስቲያን ወስጥ እያለሁ አባ ባውማ ሆይ ተነሥ ወደ በረሀው ውስጥ ገብተህ ወደ ፀሐይ መግቢያ ሒድ ከቅዱሳን ሁሉ አብዝቶ ፈቃዴን የፈጸመውን የአንድ ገዳማዊ ሥጋ ትገንዝ ዘንድ የሚለኝን ቃል ከሰማይ ሰማሁ።
ያን ጊዜም ደስ ብሎኝ ተነሣሁ በበረሀውም ውስጥ ሦስት ቀን ተጉዤ ከአንድ ገዳማዊ በዓት ደርሼ ደጁን አንኳኳሁ አንድ ሽማግሌ ገዳማዊም ከፈተልኝና እርስ በርሳችን ሰላምታ ተለዋወጥን በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን ብዬ ጠየቅሁት አዎን አለኝ። ሁለተኛም ስምህ ማነው አባቴ ሆይ በዚችስ በረሀ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ኖርክ አልሁት ስሜ ስምዖን ነው በዚች በረሀ የኖርኩትም ሰባ ዓመታት ነው አለኝ።
ከእርሱ ዘንድም ወጥቼ ሦስት ቀን ተጓዝኩ ሁለተኛም ስሙ ባሞን የሚባል ገዳማዊ አገኘሁ ሰላምታም ሰጠሁትና በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን አልሁት አዎን አለ አለኝ። አራት ቀንም ተጓዝኩ ወደ አባ ኪሮስ በዓት ደረስኩ ቅዱስ አባት ሆይ ባርከኝ እያልኩ ደጁን አንኳኳሁ አባ ባውማ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ብሎ ከውስጥ ተናገረኝ። እግዚአብሔር ያከበረህ ሰው በሰላም በፍቅር ወደእኔ ግባ አለኝ ያን ጊዜ ገብቼ ከእርሱ ተባረክሁ በፊቱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ክብር አየሁ የራሱ ጠጉርና ጽሕሙ እንደ በረድ የነጣ ነበር።
ከዚህም በኋላ ተቀመጥሁ በብብቻውም አቀፈኝ እንዲህም አለኝ እነሆ ይችን ሰዓት እየጠበቅኋት በዚች በዓት ሃምሳ ሰባት ዓመት ኖርኩ ይህንንም ሲል ጥቂት ታመመና ተኛ እየደነገጠ ያቺን ሌሊት አደረ ሲነጋም በበዓቱ ውስጥ ታላቅ ብርሃን በራ ብርሃናዊ ሰውም ገባ በእጁም የብርሃን መስቀል አለ በአባ ኪሮስ አጠገብም ተቀምጦ ሳመዉ ባረከውም አጽናናው ሰላምን ፍቅርን አንድነትን አደረገለት ከእርሱም ተሠወረ እኔም ፈራሁ እንዲህ የሚበራ ይህን ክብር የተጐናጸፈ ይህ ማነው አልሁት።
እርሱም ልጄ ሆይ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ልማዱ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ይመጣል ያጽናናኛልም አለኝ። በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላቅ ጩኸትን ሰማሁ ከጩኸታቸውም ኃይል የተነሣ ምድር ተናወጸች። እኔም ይህ የምሰማው ጩኸት ምንድነው ብዬ ጠየቅሁት እርሱም ልጄ ሆይ ይህ በሲኦል የሚኖሩ የኃጥአን ጩኸት ነው ስለ ቅድስት ትንሣኤው የእሑድ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ እግዚአብሔር ያሳርፋቸዋልና ስለዚህም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል አለኝ።
በዚችም ዕለት ሐምሌ ሰባት ቀን ቅዱስ አባ ኪሮስ ጩኾ አለቀሰ ዛሬ በግብጽ አገር ታላቅ ምሰሶ ወደቀ ይኸውም የገዳማውያን አለቃ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ነው አለ።
ከዚህም በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ እሑድ ሌሊት እጅግ ደነገጠ በበዓቱም ውስጥ እነሆ ታላቅ ብርሃን በራ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ገብቶ በአባ ኪሮስ ራስ አጠገብ ተቀመጠ። አባ ኪሮስም መድኃኒታችንን ጌታዬ ሆይ ይህን ሰው ባርከው አለው መድኃኒታችንም የመረጥሁህ አባ ባውማ ሆይ ጽና አትፍራም ሰላሜ በረከቴም ከአንተ ጋራ ይኑር። አሁንም ታማኝ አገልጋዬ የሆነ የዚህን የቅዱስ ኪሮስን ያየኸውንና የሰማኸውን ወደፊትም ዳግመኛ የምታየውንና የምትሰማውን ገድሉን ጻፍ አለኝ።
ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አባ ኪሮስን እንዲህ አለው እነሆ አንተ ትሞታለህና አትዘን ሞትህ ሞት አይደለም የዘላለም ሕይወት ነው እንጂ። የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን የሚሰማውንም ሁሉ በምድርም መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሽህ ዓመት በዓል ምሳ ከእኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ አደርገዋለሁ ከቅዱሳኖቼም ጋራ እቆጥረዋለሁ። የኃጢአቱንም መጽሐፍ ቀድጄ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ። ለመሥዋዕት የሚገባውንም ዕጣኑንና ወይኑን መብራቱንም መባ አድርጎ ለሚሰጥም በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ። በበኵር ቤተ ክርስቲያንም ሥጋዬንና ደሜን አቀብላቸዋለሁ በዚህም ዓለም ቤታቸውን እባርካለሁ። ልጆቻቸውን አሳድጋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም ምን አያጡም።
አሁንም ከዚህ ዓለም ድካም ወደ ዕረፍት የዘላለም ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደ ብርሃን ቦታ እወስድህ ዘንድ ጊዜው ደረሰ መድኃኒታችንም ይህን ሲናገር እነሆ ነቢዩና ዘማሪው ዳዊት መጣ መሰንቆውም ከእርሱ ጋራ ነበረች። ይቺ ዕለት በእርሷ ፈጽሞ ሐሤት እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር የሠራት ናት እያለ አመሰገነባት።
መድኃኒታችንም አባ ኪሮስን እነሆ ዘማሪው ዳዊት መጥቷልና ይዘምርልህ ዘንድ የምትሻውን ንገር አለው። ዳዊትም ቅዱስ አባ ኪሮስን በየትኛው አውታር እንድዘምርልህ ትሻለህ ደግሞስ በየትኛው ዜማ በየትኛው ስልት በመጀመሪያው ነውን ወይስ በሁለተኛው ወይስ በሦስተኛው አለው። ቅዱስ አባ ኪሮስም በዐሥሩም አውታር በየስልታቸውና በየዜማቸው ልሰማ እሻለሁ አለ። ያን ጊዜ ዳዊት መሰንቆውን አዘጋጅቶ የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው አለ ዳግመኛም ጐለመስሁ አረጀሁም የሚወድቅ ጻድቅን አላየሁም አለ። ዳዊትም ድምፁን አሣምሮ ዘመረ መሰንቆውንም በስልት መታት። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ ኪሮስ ነፍሱ ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ለመላእክት አለቃ ለሚካኤልም ሰጣት።
እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ሥጋውን ቀበርኩ ከበዓቱም በወጣሁ ጊዜ በረሀው በሰማይ ሠራዊት ተመልቶ አየሁ መድኃኒታችንም የቅዱስ አባ ኪሮስ ሥጋው ባለበት በዓት ላይ መስቀሉን አኑሮ ዘጋት። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለኔ ሰላምታ ሰጥቶኝ መላእክትና የመላእክት አለቆች በፊቱ እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ዐረገ። የቅዱስ አባ ኪሮስን ነፍስ ከመድኃኒታችን ጋራ እንደዚህ አሳረጓት። እርሷም በተሰጣት ክብር ደስ እያላት ዐረገች።
እኔም አባ ባውማ በዚያ ቦታ ብቻዬን ቀረሁ ተመልሼም ወደ አባ አሞን በዓት ደረስሁ። ከዚያም የሦስት ቀን መንገድ ተጉዤ ወደ አባ ስምዖን በዓት ደረስሁ። ከዚያም ሦስት ቀን ተጉዤ ወደ ቦታዬ ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረስሁ። ለመነኰሳቱም ሁሉ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ስለ አባ ሲኖዳም ዕረፍት ትንቢት እንደ ተናገረ ነገርኋቸው።
መነኰሳቱም ሰምተው እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሚሳኤል_ነዳይ
😍8🥰3❤2❤🔥2😘2
#ሐምሌ_8
Jul 14, 2026#ሐምሌ_8
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ስምንት በዚች ቀን በጎ ስም አጠራር ያለው የዓለም ሁሉ ኮከብ የሆነው #ቅዱስ_አባት_አባ_ብሶይ አረፈ፣ታላቅና ክቡር አባት የሆነው #የአባ_ኪሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረው #አባ_ሚሳኤል አረፈ፣ #ቅዱሳን_አቤሮንና_አቶም በሰማዕትነት ሞቱ፣ ቅዱስ ሰማዕት #አባ_በላኒ አረፈ፣ #አባ_ቢማ በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ብሶይ
ሐምሌ ስምንት በዚች ቀን በጎ ስም አጠራር ያለው የአባ መቃርስ ገዳምና የዓለም ሁሉ ኮከብ የሆነው ቅዱስ አባት አባ ብሶይ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከግብጽ አገር ስሟ ሰነስ ከምትባል አገር ነበር ሰባት ወንድሞችም ነበሩት እናቱም የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር ያገለግለኝ ዘንድ ከሰባቱ ልጆችሽ አንዱን ስጪኝ ብሎሻል እያለ እንደሚያነጋግራት ራዕይን አየች።
እርሷም ጌታዬ ሆይ የወደድከውን ውሰድ ሁሉም ገንዘቦቹ ናቸውና አለችው። መልአኩም እጁን ዘርግቶ የብሶይን ራስ ይዞ ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይህ ልጅ ነው አለ። ይህ ብሶይ የከሳና ሥጋው የኮሰሰ ነበርና እናቱ ለዚያ መልአክ ጌታዬ ሆይ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ከእነዚህ አንዱን ጠንካራውን ውሰድ አለችው። መልአኩም እግዚአብሔር የመረጠው ይህ ነው አላት። ከዚህም በኋላ ከእርሷ ተሠወረ።
በአደገም ጊዜ የምንኵስና ልብስ ሊለብስ ወደደ። ወደ አስቄጥስም ገዳም ሔደ በአባ ባይሞይ ዘንድም መነኰሰ እርሱም አባ ዮሐንስ ሐፂርን ያመነኰሰ ነው። ከዚህም በኋላ እጅግ ጽኑ የሆነ ተጋድሎን መጋደል ጀመረ ምንም ምን ሳይቀምስ አርባ ቀን እስከ መጨረሻው ሦስት ጊዜ ጾመ።
በቀንና በሌሊት በጾምና በጸሎት እየተጋ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን ያረካት ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል እጅግ ይወድ ነበርና ከማር ከስኳርም እጅግ ይጥመው ነበርና በውኃ ዳርም እንዳለች ተክል ሆነ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያየው ዘንድ የተገባው ሆኖ ነበር ጌታችንም ብዙ ጊዜ ይገለጽለት ነበር። ከእርሱም ጋራ ይነጋገር ነበር። እርሱም እግሩን አጥቦ እጣቢውን ይጠጣው ነበር።
በአንዲት ቀንም የመድኃኒታችንን እግሮቹን አጥቦ ግማሹን ጠጥቶ ግማሹን ለደቀ መዝሙሩ እንዲጠጣ ተወለት። ረድኡም በመጣ ጊዜ ልጄ ሆይ ተነሥና በኵስኵስቱ ውስጥ ካለው ውኃ ጠጣ አለው ረድኡም በልቡ በመቅጃው ውስጥ ካለው ከጥሩው ውኃ ለምን አይሰጠኝም አለ። ይህንም ብሎ ቸለል አለ። መምህሩ እንዳዘዘውም አልጠጣም ሁለተኛም ልጄ ሆይ ተነሥና ከኵስኵስቱ ያለውን ያንን ውኃ ጠጣ አለው። ግድ ጠጣ ባለውም ጊዜ ተነስቶ ወደኵስኵስቱ ሔደ። ነገር ግን ውኃ አላገኘም አባ ብሶይም የጌታችንን እግር እንዳጠበና ግማሹን ጠጥቶ ግማሹን እንዲጠጣ ለእርሱ እንደተወለት አስረዳው። በነገረውም ጊዜ እጅግ አዘነ ፍጹም ድንጋፄም ደነገጠ።
አባ ብሶይም ረድኡን ራሱን እብድ አስመስሎ ወደሚኖር ወደ አንድ ጻድቅ ሰው ዘንድ ላከው እርሱም አረጋግቶ ወደ አባቱ ወደ አባ ብሶይ መለሰው። ድንጋጤውም ባልተወው ጊዜ ወደዚያ ጻድቅ ሰው ዳግመኛ ላከው በሔደም ጊዜ ሙቶ አገኘው አባ ብሶይም ለረድኡ ይህን በትሬን በላዩ አኑርና ተነሥተህ እንድታነጋግረኝ አባቴ አዞሃል በለው አለው ሔዶም የአባ ብሶይን በትር በዚያ ጻድቅ በድን ላይ አኖረ ወዲያውኑም ተነሥቶ ስማ ለአባትህም ታዘዝ ታዛዥ ብትሆን ይህ ድንጋጤ ባላገኘህም ነበር አለው ይህንንም ብሎ ተመልሶ ተኛ።
በአንዲት ቀንም ከቅዱስ አባ ብሶይ ደቀ መዛሙርት አንዱ መጣ ወደ እርሱም ከመግባቱ በፊት ከሰው ጋራ ሲነጋገር ሰማው በገባ ጊዜም ከሰው ማንንም አላገኘም አባቴ ሆይ ከአንተ ጋራ ሲነጋገር የነበረ ማን ነው ብሎ ጠየቀው አባ ብሶይም እንዲህ ብሎ መለሰለት ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወደኔ መጥቶ ይህ ታላቅ ክብር ለመነኰሳት እንዳላቸው አውቄ ቢሆን ኖሮ መንግሥቴን ትቼ መነኰስ በሆንኩ ነበር አለኝ እኔም ምን ጐደለብህ የጣዖትን አምልኮ አስወግደህ የቀናች ሃይማኖትን ሥልጣን አጽንተሃልና አልሁት።
እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ እግዚአብሔር ይመስገን ክብርንስ እጅግ አብዝቶ ሰጥቶኛል ነገር ግን የመነኰሳትን ክብር ያህል አይሆንም እነርሱ በእሳት ክንፎች እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሲገቡ አይቻቸዋለሁና አለኝ።
እኔም እንዲህ አልሁት የእግዚአብሔር ፍርድ በእውነት ትክክል ነው ለእናንተ ቤቶች፣ ሚስቶችና ልጆች፣ ሀብትና ለዓለም የተዘጋጀው ሁሉ አሉአችሁ በእነርሱም ትጽናናላችሁ። መነኰሳት ግን ከዚህ ከተድላ ዓለም የተለዩና በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ችግረኞች ናቸው ስለዚህም ይህን ታላቅ ክብር እግዚአብሔር ሰጣቸው አልሁት።
በአንዲት ዕለትም እግዚአብሔር አባ ብሶይን እንዲህ ብሎ ተናገረው ይህን ገዳም እንደርግቦች ማደሪያ አደርገዋለሁ። በውስጡም መነኰሳትን እመላለሁ። ቅዱስ አባ ብሶይም ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ የበዙ ከሆነ ምግባቸውን ከወዴት ያገኛሉ አለው። ክብር ይግባውና ጌታችንም እኔ አስብላቸዋለሁ ምንም ምን እንዲአጡ አልተዋቸውም አለው።
በሀገረ እንዴናው ስለሚኖር ስለ አንድ ገዳማዊ ሽማግሌ ተነገረ በትምህርቱ አምነው ወደ ርሱ ብዙ ሕዝቦች ተሰበሰቡ እርሱ መንፈስ ቅዱስ የለም ብሎ ተሳስቶ ነበርና። ብዙዎችም ተከትለውት ነበርና ቅዱስ አባ ብሶይም ይህን ነገር ሰምቶ ስለዚያ ገዳማዊ እጅግ አዘነ መስሚያውንም ሦስት ጆሮዎች አድርጎ ወደ ገዳመ እንዴናው ሔደ ከዚያ ገዳማዊ ሽማግሌ ጋራ ተገናኘ ብዙ ሕዝቦችንም በእርሱ ዘንድ አገኛቸው ሁሉም ለቅዱስ አባ ብሶይ ሰላምታ ሰጡት።
መስሚያ ስለአደረጋቸው ስለ ሦስቱ ጆሮዎችም ጠየቁት እንዲህም አላቸው። ለእኔ ልዩ ሦስት አካላት አሉኝ ሥራዬ ሁሉ በእነርሱ አምሳል ነው በውኑ መንፈስ ቅዱስ አለን አሉት። ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍትም ይተረጒምላቸው ጀመረ። ከሦስቱ አካላት አንዱ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ በመለኮትም አንድ እንደ ሆነ አብራራላቸው። ሁሉም ከስሕተት ተመልሰው ንስሓ ገቡ። ወደ ቀናች ሃይማኖትም ተመለሱ።
ለአባ ብሶይም የዋህ ረድእ ነበረው የእጅ ሥራውንም ሊሸጥ በሔደ ጊዜ ከአሕዛብ ወገን አንድ ሰው አገኘ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የፅርፈት ቃልን እስከሚናገር ድረስ ከዕውነት መንገድ አሳሳተው።
በተመለሰ ጊዜም በክርስትና ጥምቀት ያገኘው የልጅነት ክብር ከእርሱ እንደተለየው አባ ብሶይ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በአንተ ላይ የደረሰው ምንድነው አለው። እርሱም ያ ሽማግሌ እንዳሳተው ነገረው አባ ብሶይም ስለርሱ ሰባት ቀን ሲጸልይ ሰነበተ በፍጻሜውም በክርስትና ጥምቀት የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ልጅነት በርግብ አምሳል በላዩ ወርዶ በውስጡ ሲያድር አየ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም አመሰገነው። ረድኡንም እንዲጠነቀቅና የቀናች ሃይማኖቱን እንዲያጸና ልዩ ከሆነ ሰውም ጋር ስለ ሃይማኖት እንዳይነጋገር አዘዘው።
የበርበር ሰዎችም ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ ወደ እንዴናው ገዳም ሔዶ በዚያ ተቀመጠ ከዚህም በኋላ አረፈ። የመከራውም ወራት ጸጥ ባለ ጊዜ የቅዱስ አባ ብሶይን ሥጋ ከቅዱስ አባ ቡላ ሥጋ ጋር በአንድነት ወደ አስቄጥስ ገዳም አመጡ። ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ዘመኑ አምሳ ሰባት ነበር። በአስቄጥስም ገዳም እየተጋደለ ሀያ ሰባት ዓመት ኖረ። በእንዴናው ገዳም ዐሥር ዓመት ኖረ ከመመንኰሱም በፊት በዓለም ውስጥ ሃያ ዓመት ተቀመጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ኪሮስ_ጻድቅ
❤7🥰4😘4❤🔥2😍1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 14, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤6😍2😘2🥰1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 14, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤5🥰3😍3😘3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 14, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😍5🥰3❤1😘1
✝️ እንኳን አደረሰን !
Jul 13, 2026✝️ እንኳን አደረሰን !
"እንበለ ጽርዓት ወትረ፥ ጊዜ ትሴብሕ ሥላሴ፤
ሱራፌልሃ ትመስል፥ ወአኮ ብእሴ፤
#ጊዮርጊስ ነቅዓ ቅዳሴ!
ሰላም ለከ።" (ሰላምታ ዘቅዱስ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
መሐሪ ሥላሴ፦ ከአባ ጊዮርጊስ፥ ከአባ ሲኖዳ፥ ከአባ አግናጥዮስ፥ ከአባ እንድርያስ (ዘደብረ ሊባኖስ)፥ ከአበዊነ አብርሃም ወይስሐቅ፥ ከቅዱሳት ሣራ ወእኅተ ጴጥሮስ፥ ከሊቃውንት (ስብሐት ለአብ፥ ድንቁ፥ ክፍለ ዮሐንስ፥ ሲኖዳ . . .) ፥ ከንጉሡ አድያም ሰገድ ሐፄ ኢያሱ . . . በረከትን ያሳትፈን!
🥰4❤3😍2
✝መንክር ትእግስትከ፤
Jul 13, 2026✝መንክር ትእግስትከ፤
ወዐቢይ ትኅትናከ፤
ግሩም ግብርከ፤
ወንጹሕ ኅሊናከ፤
ጽድቅ ትምህርትከ፤
ወጥዑም ውዳሴከ፤
. . .
ሠግላዊ ጻድቅ፥ ወሐዋርያዊ መምህር፤
የዋህ ብእሴ እግዚአብሔር፤
ቡሩክ ብእሲሁ፤
አፈ መዓር ወሶከር፤
አፈ በረከት ወሊቀ ሊቃውንት፤
ጠቢብ ወማእምር፤
ቄርሎስ ዳግማዊ ዘብሔረ ኢትዮጵያ . . .
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ዘኮነ ልደቱ ወዕረፍቱ በዛቲ ዕለት)
በረከቱ ቅድስት፤
ወሀብተ ረድኤቱ ንጽሕት፤
ወጸሎቱ ውክፍት፤
ትብጽሐነ ወትረ፤
አሜን!
😘4😍3🥰2
#ሐምሌ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን #ሥሉስ_ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ #ቅዱስ_የአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፣ ቅዱስ አባት የባሕታውያን…
Jul 13, 2026#ሐምሌ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን #ሥሉስ_ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ #ቅዱስ_የአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፣ ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል #አባ_ሲኖዳ አረፈ፣ የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ሥላሴ ሐምሌ…
🥰5😍5❤3😘3❤🔥2
በዚችም ቀን የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያ…
Jul 13, 2026በዚችም ቀን የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያስተምር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን እንደሚያስገባቸው በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ አለው ቅዱሱም እኔ ለረከሱ ጣዖታት አልሠዋም ብሎ መለሰለት።
ንጉሡም ብዙ ቃል ኪዳኖችን በመግባት አባበለው በአልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሳ ሰጠው ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከዚህ በኋላ ያ አንበሳ ወደ ሥጋው አልቀረበም ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በመልካም ቦታም አኖሩት።
=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
😘6🥰4😍3❤2❤🔥1
በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዶ ነበር፡፡
Jul 13, 2026በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዶ ነበር፡፡
ዐፄ ይስሐቅ ለአባ ጊዮርጊስ ‹‹ምድረ ሰዎን›› የተባለውን የጳጳሳት መቀመጫ የነበረውን ሀገር በርስትነት ሰጥቶት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ በምድረ ሰዎን ንጉሥ ይስሐቅ ክረምቱን ያሳልፍበት በነበረው ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ በዚያም በማስተማርና በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ በጋሥጫ እያለ ዐፄ ይስሐቅ አስጠራው፡፡ በዚያ ጊዜ ንጉሡ የመናገሻ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ ስለነበር እንዲባርክለት ፈልጎ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በዚያ ጊዜ ታሞ የተኛም ቢሆን ወደ ንጉሡ ተጓዘ፡፡ እዚያ ሲደርስ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ሥርዓቱን ለመፈጸምም አቅም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ይስሐቅ በአልጋ ተሸክመውት እንዲዞሩና ቤተ ክርስቲያኗን እንዲባርካት አድርጓል፡፡ ቡራኬውን ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሮቹን ሰብስቦ ‹‹ከሞትኩ አባቴ በጸሎተ ሚካኤል መከራ ወደ ተቀበለባትና እኔም ቤተ ክርስቲያን ወዳነፅኩባት ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩኝ›› ሲል አዘዛቸው፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የመጨረሻ የስንብት ትምህርቱን አስተማራቸው፡፡ እነርሱም በአልጋ ተሸክመውት ወደ ጋሥጫ እያመሩ ሳለ በመንገድ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም በ60 ዓመቱ ዐረፈ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሲኖዳ
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል አባ ሲኖዳ አረፈ፡፡ ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት። ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ።
እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ አሉት። ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ አላቸው።
አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት። ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት አለ።
በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር።
አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና አለው። አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው።
ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እግዚአብሔር አዝዞሃል። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው።
ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ። ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት።
ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን ብሎ ሰላምታ አቀረበ። በመርከብ ያሉት ሁሉም ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ይህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ።
ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን።
ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ።
በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት ማኅበር ወደርሱ መጡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግመኛ አየው ልጆቹንም ክብር ይግባውና ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሰግድ ዘንድ አንሱኝ አላቸው አንሥተውትም ሰገደለት። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አላቸው ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠብቅኋችሁ ነፍሴም ከዚህ ከደካማው ሥጋዬ የምትለይበት ጊዜ ደርሷል እኔም ለአባታችሁ ለዊዳ እንድትታዘዙ አዝዛችኋለሁ ከእኔ በኋላ ጠባቂያችሁ እርሱ ነውና አላቸው።
ለልጆቹም ይህን በተናገረ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመረጥሁህ ሲኖዳ ሆይ ብፁዕ ነህ ቸርነቴም ይደረግልሃል በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አንተ የምወደውን ሥራ ሠርተሃልና እንግዲህ ወደ ዘለዓለም ተድላ ታርፍ ዘንድ ወደእኔ ና አለው። ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አግናጥዮስ
😘9🥰2😍2❤🔥1
ተደሰቱ፡፡
Jul 13, 2026ተደሰቱ፡፡
አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ ‹‹በምጽዓት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም›› የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው ነበረ፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚሸነፍ ስላወቀ ‹‹ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ›› የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡
ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በወኅኒ ቤት እያለ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ እየመጡ ያጽናኑት ነበር፡፡ ‹‹ውዳሴ ሐዋርያት›› የተሰኘውንና ከሐምሌ 5 ጀምሮ በ12ቱም ወራት የሚመሰገኑበት የሐዋርያትን ምስጋና የያዘውን መጽሐፍ ያዘጋጀው በወኅኒ ቤት ሆኖ ጴጥሮስና ጳውሎስ ከጎበኙት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ በእስር ላይ ሳሉ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት መሞታቸው ተሰማ፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ያሳሰረህ ንጉሥ ሞቷል›› በማለት ነገሩት፡፡ ይህንንም ተቻኩለው የነገሩት ያሰረው ንጉሥ መሞቱን ሲሰማ ይደሰታል ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሰጣቸው መልስ ‹‹አይ ንጉሡ ባይሞት እኔም እንደታሰርኩ ብቀር ይሻል ነበር፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትኮ እኔን ባይወደኝ የአምላክን እናት እመቤታችንን ይወዳት ነበር›› አላቸው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶት በጥንቱ ቦታ አስቀመጠው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን የቤተ መንግሥትን ነገር ለመሸሽ ስለ ፈለገ በጋሥጫ ከመቀመጥ ይልቅ ርቆ ጥንት ወደ ነበረበት ወደ ዳሞት በመሄድ ማስተማር ጀመረ፡፡ ወደ ዳሞት ሲሄድ እግረ መንገዱን ወደ ደብረ ሊባኖስ ገብቶ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሟል፡፡ በዚያ ጊዜ የደብረ ሊባኖሱ አበ ምኔት እጨጌ ዮሐንስ ከማ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ነበሩ፡፡ አባ ጊዮርጊስን በዕውቀቱ የሚቀኑበት፣ በችሎታው የሚመቀኙት ሰዎች ነገር ሠርተው ከንጉሥ ቴዎድሮስ ጋር ስላጣሉት እልም ካለ በረሃ እንዲጋዝ ተደረገ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከግዞት የወጣው ዐፄ ቴዎድሮስ ሲሞት ነበር፡፡
የአባ ጊዮርጊስ ሌላው ተማሪ የነበረው ዐፄ ይስሐቅ በ1399 ዓ.ም መንግሥቱን ሲይዝ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት አውጥቶ ወደ ጋሥጫ መለሰው፡፡ በዚያ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ እድሜው 42 ዓመት ሲሆን በስደትና በጤንነት መታወክ የተነሣ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜውን በጾም፣ በጸሎትና በድርሰት ያውለው ነበር፡፡ አንድ ቀን ቴዎድሮስ የተባለ መስፍን፣ ዳግመኛም የጦሩ አዛዥ የሚሆን፣ አባ ጊዮርጊስን ስለ ርትዕት ሃይማኖት በጠየቀው ጊዜ አባ ጊዮርጊስም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ሰጠው፡፡ ንጉሡና የምሥጢር ሊቃውንት የሆኑ ካህናት ይህንን በተመለከቱና ባነበቡ ጊዜ ‹‹በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ቍስጥንጥንያን መስላለች፣ ከእስክንድርያም በላይ ከፍ ከፍ ብላለች›› ብለው አደነቁ፡፡ ይህም ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘው ድንቅ ድርሰቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውንና የምታወግዘውን በግልጽና በዝርዝር የጻፈበት መጽሐፍ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በፍካሬ ሃይማኖት ድርሰቱ ላይ የዘረዘራቸው የመናፍቃን ስሞችንና ክህደታቸውን ስንምለከት በዘመኑ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያላቸውን ዕውቀት በግልጽ ያሳየናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ መከራ ያልተለየው አባት በመሆኑ አሁንም በቤተ መንግሥት የነበሩ ሰዎች የእርሱን መከበርና መወደድ አይፈልጉትም ነበር፡፡ በተለይም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተሰኘውን መጽሐፍ በመጻፉ በዚህም ዝናው የበለጠ ስለተነገረ እነርሱ በሁሉም ዘንድ መከበሩን አልወደዱትም ነበር፡፡ ስለዚህም ነገር ሠርተው ከዐፄ ይስሐቅ ጋር አሁንም አጣሉት፡፡
ዐፄ ይስሐቅ አባ ጊዮርጊስን አሳስሮ ውኃ ወደማይገኝበት ዓለታማ ቦታ አጋዘው፡፡ በዚያም በመከራ ለብዙ ጊዜ ኖረ፡፡ በዚያ እያለ ዘወትር በጸሎት አብዝቶ ይተጋ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ዐፄ ይስሐቅ ወደ ልቡናው እንዲመለስ አደረገ፡፡ ንጉሡ በአባ ጊዮርጊስ ላይ የፈጸመው ነገር ሁሉ ስለፀፀተው አገልጋዮቹን ጠርቶ አባ ጊዮርጊስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ነገር ግን እነዚያ ተንኮል ሠሪዎች የአባ ጊዮርጊስ መምጣት ተንኮላቸውን ስለሚያጋልጠው ‹‹አባ ጊዮርጊስ ሞቷል›› ብለው አስወሩ፡፡ ይህንን ሲሰማ ዐፄ ይስሐቅ ፈጽሞ አዘነ፡፡ አባ ጊዮርጊስም ሞቷል እየተባለ መወራቱን ከደቀ መዝሙሩ ስለ ሰማ በሕይወት የመኖሩን ዜና ጽፎ ለዐፄ ይስሐቅ እንዲያደርስለት መልእክቱን በአውሎ ንፋስ አሳስሮ ላከለት፡፡ አውሎ ንፋሱ ለአባ ጊዮርጊስ በመታዘዝ ደብዳቤውን ተሸክሞ በመሄድ ዐፄ ይስሐቅ በድንኳን ተቀምጦ በነበረ ጊዜ ጉልበቱ ላይ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡ ምትሐት የተሠራበት ስለመሰለው ደነገጠና መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስቦ ጉዳዩን ገለጠ፡፡ ወዲያውም ነፋሱ ያመጣለትን መልእክት እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ቢጥለው ሊቃጠል አልቻለም፡፡ ወደ ውኃም ቢጨምረው አልጠፋም፡፡ በዚህ ተደንቆ ወረቀቱን ከፍቶ አነበበው፡፡ ደብዳቤው ከአባ ጊዮርጊስ የተላከ መሆኑን ሲያውቅ ዐፄ ይስሐቅ ደነገጠ፡፡ እነዚያን መልእክተኞች ይዞ ወደ ወኅኒ ከጨመራቸው በኋላ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት ያወጡት ዘንድ ላከ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲመጣ ንጉሡ በደስታ ተቀብሎ ማረኝ ብሎ ለመነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይቅር አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብዳቤውን በማን እጅ እንደ ላከው ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ደብዳቤውን በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ በነፋስ እንደ ላከው አስረዳው፡፡
ከግዞት ከተመለሰ በኋላ እመቤታችን ተገልጣለት መከራው ሁሉ እንደ ሐዋርያት መሆኑን ገለጠችለት፡፡ አእምሮውን ብሩህ፣ ልቡናውን ትጉኅ የሚያደርግ እጅግ ብዙ ምሥጢርም ነገረችው፡፡ ተሰናብታው ከሄደች በኋላ ‹‹እጅግ ብዙ መብራት አቅርቡ አምስት ፈጣን ጸሐፊዎችንም አምጡ›› ብሎ አዘዘ፡፡ ከዚህም በኋላ እርሱ እየነገራቸው እነርሱ እየጻፉ እረፍት ሳያደርጉ ሦስት ቀን ሙሉ አጽፎ ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› የተሰኘውን መጽሐፍ ፈጸመ፡፡ አምስቱ ጸሐፍትም የየድርሻቸውን አጠናቅቀው በአንድ አደረጉት፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህን ተመልክቶ በእጅጉ አደነቀ፡፡ ‹‹እኔ የዚህን መጽሐፍ ቃል አልተናገርኩም፤ መንፈስ ቅዱስ በእኔ አፍ ተናገረ እንጂ›› ሲል በወቅቱ መስክሯል፡፡ የመጽሐፉንም ስም ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› ብሎ የሰየመው ራሱ ነው፡፡ የጻፈው
🥰5😍3❤2😘2❤🔥1
ባየ ጊዜ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ እንደ በድንም ሆነ፡፡ እመቤታችንም አነሣችውና ‹‹ሳትጠይቀኝ መጽሐፌን ትጽፍ ዘንድ ለምን ደፈርህ?›› አለችው፡፡ ‹‹እኔ ወድጄህ ከእናትህስ ማኅፀን መርጬህ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለዮሐንስ አደራ ሰጥቼህ የለም…
Jul 13, 2026ባየ ጊዜ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ እንደ በድንም ሆነ፡፡ እመቤታችንም አነሣችውና ‹‹ሳትጠይቀኝ መጽሐፌን ትጽፍ ዘንድ ለምን ደፈርህ?›› አለችው፡፡ ‹‹እኔ ወድጄህ ከእናትህስ ማኅፀን መርጬህ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለዮሐንስ አደራ ሰጥቼህ የለምን?›› አለችው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ‹‹እመቤቴ ሆይ ይቅር በይኝ፣ ደስ የሚያሰኝሽ መስሎኝ ይህን ባለማወቅ ሠርቼዋለሁና›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ ይቅር ብየሃለሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ልትጽፈው የወደድኸው መጽሐፍም እነሆ በእጄ አለ፣ ከአሁን በኋላ የተወደደ ልጄ በአንደበትህ ሊገልጸው ወዷል፡፡ ነገር ግን ከአርያም ከሰማይ ኀይልን እስክትለብስ ድረስ አትቸኩል፡፡›› ይህንም ብላው ከእርሱ ተሰወረች፡፡ ያን ጊዜም ልቡ እንደ ፀሐይ በራ፣ የመለኮትም ባሕር በኅሊናው አበራ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም መስተዋትነት የተሰወረውን ሁሉ አየ፡፡
የመጀመርያው ድርሰቱ አርጋኖን የተሰኘውና በቅኔ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያመሰግነው መጽሐፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚወድ በንጉሥ ዳዊት ዘመንም አርጋኖን መጽሐፍን ይደርስና ይጽፍ ጀመረ፡፡ በሦስትም ስሞች ጠራው እነዚህም አርጋኖና ውዳሴ፣ መሰንቆ መዝሙር፣ ዕንዚራ ስብሐት ናቸው፡፡ ስለ መጽሐፉም ጣፋጭነት ንጉሡ ዐፄ ዳዊት ድርሰቱን በጣም ከመውደዱ የተነሣ በወርቅ ቀለም አጻፈው፡፡ ወርቁን የሚያንጸባርቅበት ድንጋይ (ዕንቊ) ባጣ ጊዜ እመቤታችን ማርያም በሌሊት ራእይ ዘማት በሚባል አገር እንዳለ ለጊዮርጊስ ነገረችው ኅብሩንም አሳየችው፡፡ አባታችን ጊዮርጊስም ከደረስኳቸውና ከተናገርኋቸው ድርሳናት ሁሉ አርጋኖን ውዳሴ ይጣፍጣል ይበልጣል አለ፡፡
‹‹እንደዚሁም በፈጣሪው ቸርነት በእመቤታችን ረድኤት ብዙ ድርሳናትንና የጸሎት መጻሕፍትን ደረሰ፡፡ የእሊህም ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እሊህም ውዳሴ መስቀል፣ መጽሐፈ ብርሃን፣ መጽሐፈ ሰዓታት የመዓልትና የሌሊት፣ መጻሕፍተ ቅዳሴያት ናቸው፡፡ ጸሎተ ፈትቶ (የፍታቴ ጸሎት) የሐዋርያት ማኅሌት፣ መልክአ ቊርባን፣ እንዚራ ስብሐት፣ አርጋኖን ውዳሴ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣ ኖኅተ ብርሃን ይኸውም ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ የታተመው ነው፡፡ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ ምስጢር፣ ሕይወታ ለማርያም፣ ተአምኆ ቅዱሳን፣ ጸሎት ዘቤት ውስተቤት፣ ውዳሴ ስብሐት፣ ሰላምታ፣ ጸሎተ ማዕድ፣ ቅዳሴ እግዚእ ካልእ፣ መዝሙረ ድንግልና የመሳሰለው ነው፡፡›› ቅዱስ ገድሉ እንደሚናገረው የአባ ጊዮርጊስ ‹‹ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው›› ብሎ ከጀመረ በኋላ በቁጥር የተወሰኑትን ድርሰቶቹን ብቻ ጠቅሶ መጨረሻ ላይ ‹‹… እና የመሳሰለው ነው›› ብሎ ይደመድመዋል፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ደግሞ የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ከ12 ሺህ በላይ ቢሆኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየሰጡ ያሉት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ መሆናቸውን በቅዱሳን ታሪክ መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰውታል፡፡ ሌሎች ሊቃውንት አባቶቻችንም የአባ ጊዮርጊስን ድርሰቶች ከግምት ባለፈ ሁኔታ በቁጥር ወስኖ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጣሉ፡፡ ይኸውም ወደፊት ራሱን የቻለ በቂና ብዙ ጥናት ማድረግ ሳያስፈልገን እንደማይቀር አመላካች ነው፡፡
የመጀመርያውን ድርሰቱን አርጋኖንን እመቤታችን አብዝታ ስለወደደችለት ዚማት በሚባለው ሀገር በነበረ ጊዜ ‹‹ከድርሰቶችህ ሁሉ እንደ አርጋኖን የምወደው የለም›› ብላዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ የደረሰው ድርሰት ውዳሴ መስቀል ይባላል፡፡ ቀጥሎም መጽሐፈ ስብሐት ዘመዓልት ወዘሌሊት የተባለውን ወይም እርሱ ራሱ መጽሐፈ ብርሃን ብሎ የሰየመውን መጽሐፍ አዘጋጅቷል፡፡ መጽሐፉም የእግዚአብሔርን የምስጋናውን መንገድ ያበራል፣ አብርቶ ያመለክታልና፣ ልዑላነ ብርሃን የሆኑትን የማኅበረ ቅዱሳንንና የትጉኃንን የምስጋናቸውን መንገድ ያመለክታልና፣ የእመቤታችንንም የምስጋናዋን ጣዕም ይገልጣልና መጽሐፉ «መጽሐፈ ብርሃን» ተባለ፡፡ በዘመኑ በነበረው ልማድ ካህናቱ ቍርባን በሚያቀብሉ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ካህናቱ መጥተው ሲቀበሉ ንግሥቲቱ ግን ካለችበት ድረስ ካህናቱ ሄደው ነበር የሚያቆርቧት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን ‹‹ይህ ቁርባን ንጉሠ ነገሥት ነውና ንግሥቲቱ ወደዚህ መጥታ ልትቀበል ይገባታል እንጂ እኛ መሄድ የለብንም›› ሲል ተቃወመ፡፡ ይህ ነገር ንግሥቲቱንና አባ ጊዮርጊስን ስላጋጫቸው ዐፄ ዳዊት ችግሩን ለመፍታት አባ ጊዮርጊስን ወደ ሀገረ ዳሞት ንቡረ እድነት ሾሞ ላከው፡፡
ከዚህ በኋላ አባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ በማድረግ ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ጠይቆ ሲፈቀድለት የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡ ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ ‹‹ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ›› ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- ‹‹እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ ‹አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?› ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?›› ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡ ሊቃውንቱም በዚህ ጊዜ ታሞ አልጋ ላይ የነበረውን አባ ጊዮርጊስን እንዲመጣላቸው ፈልገው ‹‹እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ›› ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደርጎ በአልጋ ላይ ሆኖ በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ በነገሩት ጊዜ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ እንዲህ የሚል ነው፡- ‹‹እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?›› እያሉ የጥያቄ ዓይነት ባሽጎደጎዱለት ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ መልስ በማጣቱም አፈረ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ
🥰4😍4❤2❤🔥2😘2
ጌትነቱ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ጸጋ ያለመከራ አይሰጥምና ያለመፈተንም ማብዛት አይቻልም፡፡ ጌታችንን ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ሕፃን ደቀ መዛሙርቱ በጠየቁት ጊዜ ‹‹ይህ ሕፃን ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራ…
Jul 13, 2026ጌትነቱ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ጸጋ ያለመከራ አይሰጥምና ያለመፈተንም ማብዛት አይቻልም፡፡ ጌታችንን ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ሕፃን ደቀ መዛሙርቱ በጠየቁት ጊዜ ‹‹ይህ ሕፃን ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ነውን ወይስ በወላጆቹ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹እርሱም አልበደለም፣ ወላጆቹም አልበደሉም፣ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ›› አላቸው፡፡ ዮሐ 9፡1፡፡ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ እስኪወርድላቸው ድረስ በትንሽ ዕውቀት ነበሩ፡፡ ‹‹በመጻሕፍት ያለውን ገና ዐላወቁምና›› ተብሎ እንደተጻፈ እንዲሁ አባ ጊዮርጊስም ዕውቀት ስለ ተሰወረውና ጓደኞቹ በትምህርት ሲቀድሙት ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ጀመረ፡፡ ሁልጊዜም በሥዕለ ማርያም ሥር እየተንበረከከ ጥበብን እንዲሰጠው ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ በመለመን እንባንም በማፍሰስ ይጸልይ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ተገለጠችለትና አረጋጋችው፡፡ ዳግመኛም እንደምትመጣ ቀን ቀጥራው ከእርሱ ተሰወረች፡፡
በሰጠችውም ቀጠሮ መሠረት በነሐሴ 21ኛው ቀን እመቤታችን ሚካኤልና ገብርኤል በቀኝና በግራ ሆነው ኪሩቤልንና ሱራፌልን አስከትላ ተገለጠችለትና «አይዞህ ዕውቀት የተሰወረብህ ትምህርት ስለማይገባህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እንዲገለጥ ነው» አለችው፡፡ ‹‹የመረጥሁህ የልጄ ወዳጅ ጊዮርጊስ ብላ በስሙ ጠራችው፡፡ ከዕውቀት ወንዝ የመጣና ከጥበብ ምንጭ የተገኘ ከመለኮት ባሕር የተቀዳ ይህን ንጹሕ ጽዋ ንሣ ጠጣ›› በማለት ጽዋዓ ልቡናን አጠጣችው፡፡
ይኸውም ጽዋዕ ልቦና በዮሴፍ ቤት በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት የጠጡት መንፈሳዊና ሰማያዊ መጠጥ ነው፤ በበዓለ ሃምሳ ከጠጡት ያልተለየ ነው፡፡ ይኸውም የሚናገር እሳት፣ የሚያድን እሳት፣ መለኮታዊ እሳት ነው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ያስጌጠበት የመጻሕፍትን ምስጢራት፣ የማኅሌትንና የድርሳናትን ቃል፣ ምስጋናዎችንም ሁሉ እመቤታችን ገለጠችለት፡፡
እመቤታችን ማርያም ለብፁዕ ጊዮርጊስ ጽዋውን ካጠጣችው በኋላ ያን ጊዜ አምስት የምሥጢር ቃላትን አስተማረችው፡፡ የኅሊናን ዓይኖች ያበራሉና የልቡናንም ጆሮዎች ይከፍታሉና፡፡ ከዚህ በኋላ ከእርሱ ተሰወረች፤ ከማይተኙ ከትጉሃን መላእክትም ጋር ወደ ሰማይ ዐረገች፡፡ የአምስቱ የምሥጢር ቃላት ትርጉምም ዕውቀትን የተመሉ መንፈሳውያን አባቶቻችን እንደ ነገሩን ከእመቤታችን ማርያም እጅ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ትምህርት ሳይማር በአንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር ማጥናት ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊትን ግን ዕብራውያን በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ቁጥር ለአምስት ከፍለውታል፡፡ እነዚህም መስማት፣ ማየት፣ ማሽተት መቅመስና፣ መዳሰስ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል መጨረሻው 40ኛው መዝሙር ነው፤ የሁለተኛው ክፍል መጨረሻው 71ኛው መዝሙር ነው፡፡ ሦስተኛው ክፍል መጨረሻው 88ኛው መዝሙር ነው፤ አራተኛው ክፍል መጨረሻው 105ኛው መዝሙር ነው፡፡ አምስተኛው ክፍል መጨረሻው 150ኛው ነው፡፡ የእነዚህም ክፍላት መጨረሻ ለይኩን ለይኩን ባለ ጊዜ ይታወቃል፡፡ አባ ጊዮርጊስም የእነዚህን ምስጢር በልቡ ጠበቃቸው፡፡ አምስቱንም ቃላት በልቡ መዝገብነት ሰወራቸው፤ ሊገልጣቸው እግዚአብሔር አልፈቀደላትምና በተረዳ ነገር ግን መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ የገነትን ፍሬዎች ሁሉ የሰበሰበ መዝሙረ ዳዊት የገነት አምሳል ነውና አጋንንትን ያሳድዳል መላእክትንም ያቀርባል፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ ተለይታ ካረገች በኋላ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ የልቡ ዓይን ተከፈተለት፡፡ ኅሊናውም በመንፈስ ቅዱስ ክንፎች ተመሰጠ፡፡ ወደ አብም ደረሰ፤ በዚያም ኢየሱስን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ጰራቅሊጦስንም በአንድ አኗኗር አገኘው፡፡
ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ የዜማ የቅኔና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ተማረ፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡ የማስተማር ሥራውን የጀመረው በዚያው በሐይቅ እስጢፋኖስ ነበር፡፡
ከሐይቅ በኋላ በዚያ ዘመን ሸግላ በመባል ትጠራ ወደ ነበረችው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጋሥጫ ተጓዘ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ሸግላ ሲመጣ አባቱ በጣም አርጅቶና መንኩሶ ነበር፡፡ ስለዚህም በአባቱ እግር ተተክቶ በቤተ መንግሥቱ ያለችውን ሥዕል ቤት እንዲያገለግል ወደዚያው አስገቡት፡፡ በቤተ መንግሥቱም የንጉሡን ልጆች ከማስተማሩም በላይ በቤተ መንግሥቱ ዙርያ ከነበሩት ሊቃውንት መካከል አባ ጊዮርጊስ አንዱ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜ ነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበው ጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ በቤተ መንግሥቱ በነበረ ጊዜ የንጉሡን ልጆች ይስሐቅን፣ ቴዎድሮስን፣ እንድርያስን፣ ሀብተ ኢየሱስን፣ ሕዝቅያስን፣ ኢዮስያስን፣ ዘርዐ ያዕቆብንና ሴት ልጁን እሌኒን በምግባርና በሃይማኖት ቀርጿቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል፡፡ ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ ሊዛመደው ወዶ ስለነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደሚፈልግ ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ሄዶ ቅስናን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው መነኮሰ፡፡
ከመነኮሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ታላላቆች፣ ለንቡራነ እድና ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡
አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ ነበር፡፡ ታምሞ በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት የከበሩ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት ‹‹ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ መጣን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ›› ሲል ለመናቸው፡፡ እነርሱም ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሄዱ፡፡ ለዚህም ነው ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወድያው የድርሰት ሥራውን የጀመረው፡፡ የመጀመርያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት ነበር፡፡ በማግሥቱ በዚያው ላይ ሊጨምር በወደደ ጊዜ የተጻፈበት ጥራዝ ቀለሙ ጠፍቶ ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህም የተሰረቀ መስሎት ልቡ አዘነ፡፡ የተስተካከሉ ጥራዞችንም በቈጠረ ጊዜ ደኅና ሁነው አገኛቸው ሁለተኛም በድጋሚ ጻፈ፡፡ በማግሥቱም እንደ መጀመሪያው ነጭ ሁኖ አገኘው እስከ ሦስትና ዐራት ቀንም እየተደጋገመ እንዲሁ ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ አባታችን ወደ እመቤታችን ይጸልይ ጀመረ፡፡ ‹‹ይህ የሆነ በኃጢአቴ ነውን? ወይስ አይደለም? ግለጭልኝ›› አላት፡፡ አንድ ቀንም በሌሊት እኩሌታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ሲሄድ እመቤታችን በድንገት በማይነገር ክብር ለጊዮርጊስ ተገለጠችለት፡፡ ከእርሷም ጋር የቅዱሳን ማኅበር ሁሉ ነበሩ፡፡ በእጇም ከፀሐይና ጨረቃ የበለጠ የሚያበራ መጽሐፍን ይዛ ነበር፡፡ ጊዮርጊስም
❤4😍3🥰2😘2❤🔥1
#ሐምሌ_7
Jul 13, 2026#ሐምሌ_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን #ሥሉስ_ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ #ቅዱስ_የአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፣ ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል #አባ_ሲኖዳ አረፈ፣ የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሥላሴ
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡
አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡
እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ዘትግራይ እናቱ አምኃ ጽዮን ዘወለቃ ይባላሉ፡፡ ስለሆነም ሀገሩ ትግራይና ወሎ ቦረና ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በመባል የሚታወቀው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በድርሰቱ ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ስሙ የሚነሣ ታላቅ መመኪያችን የሆነ ጻድቅ አባታችን ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከመናኝ ጻድቅነቱ በተጨማሪ በመላእክትም ዘንድ የተመሰከረለት ታላቅ ፈላስፋና ደራሲም ነው፡፡ በድርሰቱ ላይ ስለ ሰማይ፣ ስለ መብረቅ፣ ስለ ደመና፣ ስለ ዝናብ አፈጣጠር፣ ስለ አራቱ ዓለማትና ስለ ሰባቱ ሰማያት… በእነዚህና በመሳሰሉት በመንፈሳዊው በሚገባና እጅግ በሚያስደንቅ መንገድ ተፈላስፎባቸዋል፡፡
ጻድቁ ድርሰቶቹን እርሱ ካለበት ወደ ሌላ ቦታ ለመላክ ንፋስ ይታዘዝለት ነበር፡፡ ስለ ጾምና ስለ በዓላት የደረሰውን ድርሰቱን ለሸዋው ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ በነፋስ ጭኖ ልኮለታል፡፡ አስደናቂ ገደሙ ወሎ ቦረና ውስጥ ይገኛል፡፡ ጋስጫ በድሮ ስሟ ደብረ ባሕርይ ትባላለች፡፡ በአጠገቡም ራሱ አባ ጊዮርጊስ የፈለፈላቸው ብዙ ዋሻዎች አሉ፡፡ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ለመገናኘት እንዲያመቻቸው ብለው የሠሩት ድልድይ ‹‹የእግዜር ድልድይ›› ይባላል፡፡ በእግር 5 ሰዓት የሚያስኬድ መንገድ ነው፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ጋሥጫ ገዳም የአውሬ ሰጋጅና ባሕታዊ ያለበት አስደናቂ ገዳም ነው፡፡ በየዓመቱ የስቅለት ዕለት ቁመቱ 60 ክንድ የሆነ ዘንዶ ከመቅደሱ ወጥቶ ግብረ ሕመማት ከሚነበብበት ከአትሮንሱ ሥር ሆኖ ተጠምጥሞ እራሱን ቀና አድርጎ ሲሰግድ ውሎ ካህኑ ሲያሰናብት ማታ ተመልሶ ወደ መቅደሱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የተሰኘውን የዚህን ድንቅ አባታችንን ዜና ሕየወቱን በደንብ መመልከቱ ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡
የተወለደው በ1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው፡፡ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ ወላጆቹ አስቀድሞ ልጅ አልነበራቸውምና በስለት ነው ያገኙት፡፡ አባ ጊዮርጊስ በመጀመርያ እናቱ ፈሪሐ እግዚአብሔርን እያስተማረች በጥበብና በዕውቀት አሳደገችው፡፡ ቀጥሎም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተማረው ከአባቱ ነበር፡፡ ሊቅ የነበረው አባቱ ካስተማረው በኋላ በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ጳጳስ የነበሩት ከአቡነ ሰላማ መተርጕም ዘንድ ወስዶ ዲቁና አሹሞታል፡፡
ዲቁና ከተቀበለ በኋላ ለትምህርት ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ወሰደው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት አልገባው ብሎ ለሰባት ዓመታት ተቀምጦ ነበር፡፡ አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች ‹‹ይህ ትምህርት የማይገባው ስለ ምንድን ነው? በእርሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ?›› ይሉት ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የሐይቁ መምህር የነበረው ዐቃቤ ሰዓት ሠረቀ ብርሃን ለአባቱ ‹‹ልጅህ ትምህርት አይገባውምና የቤተ መንግሥት ነገር አስተምረው›› ብሎ መለሰው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ግን ‹‹አንድ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ እዚያው ገዳሙን ያገልግል›› ብሎ እንደ ገና ወደ ሐይቅ ላከው፡፡ አባ ጊየርጊስ ከቀለም ትምህርቱ ይልቅ በሥራ እየደከመ የገዳሙን አባቶች ይረዳ ጀመር፡፡ በገዳሙ እንጨት ይሰብር ውኃ ይቀዳ ይልቁንም ደግሞ አብዝቶ እህል በመፍጨት ያገለግል ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ እህል ይፈጭበት የነበረውን የድንጋይ ወፍጮና ንፍሮ ይቀቅልበት የነበረው የድንጋይ ትልቅ ማሰሮ አሁንም ድረስ በሐይቅ ገዳም በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ ጊዮርጊስ ግን ትምህርቱን ለመረዳት የዘገየ ሆነ፣የእግዚአብሔር ቃልም አልገባውም ነበር፡፡ ይህም ስለ ኃጢአቱ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ሥራና
🥰5😍4😘3❤🔥2❤2
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Jul 13, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😍5😘4❤3🥰2
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 13, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
❤5😍3😘2🥰1
1. ማማተብ ማለት ምን ማለት ነው ❓
Jul 13, 20261. ማማተብ ማለት ምን ማለት ነው ❓
2. ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ማማተብ እንዴት አይነት ነው ❓
3. ወደ ላይ፣ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝና ወደ ግራ የምናማትብበት ሚስጢሩ ምንድን ነው❓
4. በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምናማትበው መቼ መቼ ነው ❓
5. በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓተ ቤተክርስቲያን መሰረት ካማተብን በኋላ የራሳችንን እጅ መሳም ተገቢ ነውን ❓
የሚሉትን ጥያቄዎች ??? ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ መልስ ለማግኘት ቻናላችንን JOIN በማድረግ ይቀላቀሉ 👇👇👇
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 13, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
(ሐምሌ 6) እንኳን ለሁሉም በዛሬው እለት ታስበው ለሚውሉ ቅዱሳን መላእክት እና ሰማዕታት ጻድቃን ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
Jul 12, 2026(ሐምሌ 6) እንኳን ለሁሉም በዛሬው እለት ታስበው ለሚውሉ ቅዱሳን መላእክት እና ሰማዕታት ጻድቃን ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
❤5🥰4😘4😍3
#ሐምሌ_6 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን #የነቢዩ_ዕዝራ ዕርገት ሆነ፣ #ቅድስት_ንስተሮኒን አረፈች፣ ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_…
Jul 12, 2026#ሐምሌ_6 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን #የነቢዩ_ዕዝራ ዕርገት ሆነ፣ #ቅድስት_ንስተሮኒን አረፈች፣ ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት #ገድለኛዋ_ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፣ የገርአልታው #አቡነ_አብርሃም መታቢያቸው ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ…
🥰4😍4😘4❤3💯1
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የገርአልታው አቡነ አብርሃም መታቢያቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውል ሀገራቸው ትግራይ ነው፡፡ በሥርዓተ ገዳማትና በሥርዓተ ቀኖና ዐዋቂነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አባት ናቸው፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ…
Jul 12, 2026ዳግመኛም በዚህች ዕለት የገርአልታው አቡነ አብርሃም መታቢያቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውል ሀገራቸው ትግራይ ነው፡፡ በሥርዓተ ገዳማትና በሥርዓተ ቀኖና ዐዋቂነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አባት ናቸው፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በስማቸው የተሠራው ገዳም በትግራይ ገርዓልታ የሚገኝ ሲሆን አጽቢ መንበርታ ደብረ ጽዮን አቡነ አብርሃም ገዳም ይባላል፡፡ ስለ አቡነ አብርሃም ከዚኽ ያለፈ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በገዳማቸው ያሉ አባቶችም የጻድቁን የዕረፍታቸውን ቀን ከመጠቆም ያለፈ ነገር ለመናገር ገድሉ የላቸዉም፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሐዋርያው_በርተሎሜዎስ
በዚህች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ መታሰቢያ ነው፡፡ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ዕጣ የደረሰው አልዋሕ በሚባል አገር ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊያደርሰው አብረው ወደ አልዋሕ ሄዱ፡፡ ወደ ከተማው ለመግባት ምክንያት ፈለጉና ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ በርተሎሜዎስን ‹‹አትክልተኛ ባለሙያ ነው›› ብሎ የወይኑን ቦታ እንዲጠብቅለት ለአንድ ባለጸጋ መኰንን ባሪያ አድርጎ ሸጠው፡፡ ባለጸጋውም በርተሎሜዎስን በ30 እስቴታር ገዝቶት ሄደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ገንዘቡን ደብቆ ለቅዱስ በርተሎሜዎስ በድብቅ ሰጥቶት እንዲመጸውተው ነግሮት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ አልዋሕ ከገባ በኋላ ቅዱስ በርተሎሜዎስ የወይን ቦታው አለቃ ሆኖ 40 ቀን ተቀመጠ፡፡ ወንጌሉን ባለመስበኩ በሀዘን እያለቀሰ ጌታችንን በጸሎት ጠየቀው፡፡ በገንዘቡ ገዝቶት ባሪያው ያደረገው ባለጸጋውም የወይኑን ቦታ ያይ ዘንድ እንደመጣ መርዘኛ እባብ ነድፎት ሞተ፡ ሕዝቡም ተሰብስቦ ሲያለቅስ በርተሎሜዎስ ግን ወደ ጌታችን ከጸለየ በኋላ ሄዶ ባለጸጋውን ሰው ከሞት አስነሣው፡፡ በዚህም ሕዝቡ ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡
በርተሎሜዎስም ወደ ሌሎች አገሮች ሄዶ አስተማረ፡፡ ጌታችን ወደ በርበሮች ዘንድ ሄዶ ወንጌልን እንዲሰብክ አዘዘው፡፡ ረዳት እንዲሆነውም እንድርያስን ከደቀ መዝሙሩ ጋር ላከለት፡፡ የሀገሪቱ ሰዎች ግን እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ በሐዋርያቱም ፊት በአስማት አስደናቂ ተአምራት እያሳዩ ትምህርታቸውን የማይቀበሏቸው ሁኑ፡፡ ይህን ጊዜ ጌታችን ሰውን ከሚበሉ አገር አንዱን ገጸ ከልብ ይታዘዝላቸው ዘንድ በሚያዙትም ነገር ሁሉ ከትእዛዛቸው እንዳይወጣ አዘዘው፡፡ ሐዋርያትም ወደ በርበሮች አገር ዳግመኛ በገቡ ሰዓት ይበሏቸው ዘንድ ኃይለኛ አራዊትን አውጥተው ለቀቁባቸው፡፡ ያ ገጸ ከልብም በአራዊቱ ላይ ተነሥቶ እየነጠቀ በላቸው፡፡ ይህንንም የተመለከቱት በርበሮች እጅግ ፈርተው በድንጋጤ ብቻ የሞቱ አሉ፡፡ በሐዋርያቱም እግር ሥር ወደቁ፡፡ ሐዋርያቱም አስተምረው ካሳመኗቸው በኋላ አጥምቀዋቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ በርተሎሜዎስ እግዚአብሔርን ወደማያውቁ አገሮች ሄዶ ብዙ ተአምራትን እያደረገ አስተምሮ አጠመቃቸው፡፡ የከሃዲው ንጉሡ የአግሪጳን ሚስትም ትምህርቱን ሰምታ በጌታችን አመነች፡፡ ንጉሡ አግሪጳም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ቅዱስ በርተሎሜዎስን ብዙ ካሠቃየው በኋላ አሸዋ በተሞላ ትልቅ ከረጢት ውስጥ ከቶ ከነሕይወቱ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አደረገ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን አውጥተው በክብር ቀብረውታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ይኽች ዕለት መታሰቢያ በዓሉ እንድትኾን አባቶቻችን አዘዋል፡፡
† ሐምሌ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት
5.ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌና_ዘመስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)
😍7❤3🥰3💯1😘1
#ሐምሌ_6
Jul 12, 2026#ሐምሌ_6
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን #የነቢዩ_ዕዝራ ዕርገት ሆነ፣ #ቅድስት_ንስተሮኒን አረፈች፣ ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት #ገድለኛዋ_ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፣ የገርአልታው #አቡነ_አብርሃም መታቢያቸው ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ መታሰቢያ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዕዝራ_ነቢይ
ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ እርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን የዕዝራ ዕርገት ሆነ። ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጽፍ ነበረ እርሱም ከሌዊ ወገን ነበረ። ከእግዚአብሔርም ጋራ ግሩም የሆነ ነገርን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ ምድርን በፈጠርካት ጊዜ አዳምን ታስገኝ ዘንድ አዘዝካት አስገኘችውም።
ሁለተኛው የጥፋት ውኃ በጊዜው እንደ መጣና ሁሉን እንዳጠፋ ተናገረ ኖኅ አብርሃምና ዳዊት እንዴት እንደ ተመረጡ ደግሞ ተናገረ። ዳግመኛም ነፍስ ከሥጋዋ እንደምትወጣና ሰባት ቀኖች እንደምትዞር ከዚያም በኋላ እንደ ሥራዋ ወደተዘጋጀላት ቦታዋ እንደምትገባ ተናገረ።
ከዚያም ስለ ፍርድ ቀን ተናገረ። ከእግዚአብሔር ከጌትነቱ ብርሃን በቀር ፀሐይና ጨረቃ መብራትና ብርሃንም እንደሌሉ ተናገረ። ዳግመኛም በልቧ እጅግ በምትጨነቅ በምታዝንና በምትተክዝ ሴት አምሳል ጽዮንን አያት ልብሶቿም የተቀደዱ ነበሩ ልጇም ወደ ጫጕላው ቤት በገባበት ቀን እንደሞተ ነገረችው። ከዚህም በኋላ እርሷን ከማየቱ የተነሣ ፈርቶ በድንጋፄ እስከ ወደቀ ድረስ ፊቷ በድንገት እንደ መብረቅ በራ።
ደግሞም ዐሥራ ሁለት ክንፎችና ሦስት ራሶች ያሉት ንስር ከባሕር ሲወጣ ከክንፎቹም ውስጥ ራሶች ሲወጡ አየ እኒህም በየዘመናቸው ገዝተው የጠፉ ነገሥታት ናቸው። ደግሞም ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መወለድ ተናገረ እንዲህም አለ። አንበሳ እያገሣ ከበረሀ ወጣ በሰው አንደበትም ሲናገር ንስሩንም ሲገሥጸው ሰማሁት አለ።
ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። በሌሊት ታላቅ ነፋስ ከባሕር ሲወጣ አየሁ ከማዕበሉ የተነሣ ባሕሩ ይታወክ ነበር ነፋሱም እንደ ሰው አምሳል ሁኖ ከባሕር ሲወጣ አየሁ። ደግሞም ከብዙ ኃይልና ክብር ጋር በሰማይ ደመና ማረጉን በአብ ቀኝ መቀመጡንም አይቶ ተናገረ።
ዳግመኛም በፈሳሹ ማዶ ያኖራቸው ዘጠኙ ነገድ እንደሚሰበሰቡ ተናገረ። ከዚህም በኋላ የነቢያት መጻሕፍትና የአባቶችን ትውልድ የያዙ መጻሕፍት ተደምስሰው መጥፋታቸውን በአሰበ ጊዜ ወደ በረሀ ገብቶ በጾምና በጸሎት ምሕላ ያዘ። ከእርሱም ጋር አምስት ጠቢባን ጸሐፊዎችን ወሰደ።
ከዕንጨቱም አንጻር ቃል ጠርቶት ዕዝራ አፍህን ክፈት ብሎ ኅብሩ እሳት የሚመስል ውኃን የተመላ ጽዋን ሰጠው። ያንንም ጽዋ ጠጣ ያን ጊዜም ልቡናው ጥበብን አገሣ። ተገልጾለትም መጻሕፍትን ሁሉ ሰበሰበ ለእነዚያም ሰዎች ልዑል አምላክ ዕውቀትን ሰጣቸው። መጻሕፍትንም ሁሉ በየተራቸው ጻፉ። በዚያም አርባ ቀን ኖሩ እነዚያ ግን ቀን ቀን ይጽፋሉ ማታ ማታም ይመገባሉ እርሱ ግን ቀን ይጽፋል ማታም ዝም አይልም በእነዚያ አርባ ቀኖችም ሁሉ መጻሕፍት ተጻፉ።
ከዚህም በኋላ ልዑል እንዲህ ሲል ተናገረው የዕውቀት ምሥጢር የጥበብም ምሥጢር እንደ ፈሳሽ ውኃም ያለ ዕውቀት ላላቸው ታስተምራቸው ዘንድ ይህን ተመልከት እንዳለውም አደረገ። በአራተኛውም ዘመን ከሚቈጠሩ ከብዙ ሱባዔ በአምስተኛው ሱባዔ ይህ ዓለም ከተፈጠረ ከአምስት ሺ ዘመን በኋላ ጨረቃ ሠርቅ አድርጋ ጨለማዋን ባጣች በአሥረኛው ቀን በሦስተኛው ወር በዘጠና አንድ እንደእርሱ ያሉ ደጋግ ሰዎች ወዳሉበት ዕዝራን ወሰዱት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ንስተሮኒን_ዘኢየሩሳሌም
በዚህችም ዕለት ቅድስት ንስተሮኒን አረፈች። እርሷም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ውስጥ ነበረች። እርሷም አስቀድማ ኃጢአተኛ ነበረች ከዚያም በኋላ ንስሓ ገብታ ወደ እግዚአብሔር በተቃጠለ ልብ ተመለሰች የሥጋን ፍላጐቶች ሁሉ ናቀች እመምኔት እስከ ሆነች ድረስ በበጎ ሥራ ሁሉ ትሩፋትንና ተጋድሎን አበዛች።
እኅቶችም ከገድል ብዛትና ምግብን ከመተው የተነሣ ሥጋዋ እንዳለቀ አይተው ሥጋሽን እንድትረጂ ጥቂት እህል በወጥ ብዪ አሏት። አብዝተውም ግድ ባሏት ጊዜ ልጆቼ ሆይ ወደ ቀድሞ ልማዴ እንዳልመለስ ጥቂት ወጥ ስለመብላት አትድከሙ ስለዚህ ወጥ አልበላም አለቻቸው። ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መርቄሎስ_ሐዋርያ
በዚህችም ዕለት ጳውሎስ የተባለ ቅዱስ መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ ነው። እርሱም ሐዋርያትን አገልግሎአቸዋል። ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር ሔደ። የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን መልእክቶች አደረሰ በመከራውም ጊዜ አገለገለው። ከእርሱም ጋር መከራ ተቀበለ ከእርሱም አልተለየም።
ወደ ሮሜ አገርም ከርሱ ጋር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን አስተማረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ከአረማውያን ብዙዎቹን መለሳቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው።
የሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ አቅርቦ ጠየቀው እርሱም ለሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ አመነ ደግሞም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ።
ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት። ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዴት ሁነህ መሞት ትሻለህ በምን አይነት ሞት ልግደልህ ንገረኝ አለው። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰ እኔ ሕይወት በሆነ በክርስቶስ ስም መሞት እሻለሁ አንተ ግን በፈለግኸው ዓይነት ግደለኝ ፈጥነህም ወደ ፈለግኸው አድርሰኝ።
ያን ጊዜም ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ቴዎዳስያ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት ገድለኛዋ ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፡፡ ከእርሷ ጋርም ሁለት መኳንንቶችና አሥራ ሁለት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።
ይህም እንዲህ ነው ይቺ ቅድስት ልጇ አብሮኮሮንዮስን ክርስቲያን ነው ብለው እንደወነጀሉትና ለሞት እስቲደርስ ጽኑዕ ሥቃይን እንዳሠቃዩት ሰማች። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያች ሌሊት ተገለጠለት ከሥቃዩም አዳነው ያለ ምንም ጉዳት ጤናማ ሆነ።
እኒህ ሁለቱ መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች ከእናቱ ጋር በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ እንዲህ ብለውም ጮኹ እኛ በአብሮኮሮንዮስ አምላክ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀበሉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_አብርሃም_ዘገርአልታ
😘5❤2🥰1😍1💯1
✝ቅዱስ ሳቁኤል መልአክ
Jul 11, 2026✝ቅዱስ ሳቁኤል መልአክ
✨ከ፯ቱ እና ከ፲፪ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ።
✨መልአከ ሞትን የሚያዘው መልአክ
ቅዱስ ሳቁኤል ጠባቂያችን
ሐምሌ፭ በዓሉ ነው።
✨አማላጅነቱ ጥበቃው አይለየን ከማይጠቅም ሞት ይጠብቀን።
😍5😘4
ቅዱሳን (Saints)
Jul 11, 2026ከዚህም በኋላ ወደ እሳቱ ምድጃ ተመልሶ ጳውሎስንና ስክንጥስን ከእሳቱስ ውስጥ ወጡ አላቸው ያንጊዜም የራሳቸው ጠጉር እንኳ ሳይቀነብር ወጡ በላያቸውም ላይ የቃጠሎ ሽታ የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በጌታችን በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶ…
Jul 11, 2026ከዚህም በኋላ ወደ እሳቱ ምድጃ ተመልሶ ጳውሎስንና ስክንጥስን ከእሳቱስ ውስጥ ወጡ አላቸው ያንጊዜም የራሳቸው ጠጉር እንኳ ሳይቀነብር ወጡ በላያቸውም ላይ የቃጠሎ ሽታ የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በጌታችን በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን እያሉ ጮኹ ከዚህም በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ስክንስንም ቅስና ሾመላቸው። ከዚሁ በኋላም ከሐዋርያ ፊልጶስ ጋራ ወደ ሁለት አገሮች በአንድነት ሔዱ በዚህም በጌታችን ስም ሰበኩ የአገሩ አለቆችም ያዙአቸው እጆቻቸውንና እግሮቻቸውንም አሠሩአቸው በአንገቶቻቸውም የብረት ሰንሰለቶችን አስገቡ ራሳቸውንም የሚሸፍን የሚሸፍን የብረት ቆብን ሠሩላቸው በእጅና በመሐል አጆቻቸውና በክንዶቻቸው እያንዳንዱን የብረት አጅ ጨመሩ ከብረቶችም ጋር ቸነከሩአቸው።
ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሠሩ በፉትና በኋላም ቸነከሩአቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሠሌዳ ሠሩ ከወገቦቻቸውም ጋራ ቸነከሩት ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከ አቈሳሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሠርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፉል ሠሩ ቀማሚዋችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባትን አመጡ ሰቡንና አድሮ ማሩን የእሳቱንም ኋይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉ ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ የወይን አረግንና ቅባት ያላቸውን ዕንጨቶች ሁሉ አመጡ።
በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትንም ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም አምጥተው ከስጋቸው ጋር እስከሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋሪያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት በእግራቸው እስከ ራሳቸውም ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩ ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆሟቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጠሉ አንዳንዱ የእሳቱ ነበልባል ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያት ግን ወደ እግዚአብሔር ይፀልዩ ነበር።
ከመኳንንቱም በአንድ ልብ ርኅራኄን አሳደረና እንዲፈቷቸው አዘዘ ፈቷቸው በፈቷቸውና ሠሌዳውን ከስጋቸው ላይ በአስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሰሌዳዋች ጋር ወጣ ብዙ ደምም ከስጋቸው ፈሰሰ። ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ለብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሱአቸው ያን ጊዜ ጌታችን ወርዶ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው ዝናምን የተመላች ብርህት ደመናም መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከበበቻቸው ከዚያችም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጸ በመንደፍ ብዙ ተሠቃዩ ከዚህም በሗላ ሙታንን በአነሡ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸውም ቤተ ክርስቲያንንም ሰሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናት ሐይማኖትም እስቲጸኑ አስተማሩአቸው ከዚያም ወጥተው ጌታችን ወደ አበዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ።
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጳውሎስ ተገለጸለትና የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን። መታሰቢያህ የሚያደርገውን በውስጧ የሚጸልየውን ስለትንና መባንም የሚሰጠውን በመታሰቢያህም ቀን ለድኇች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋራ በመንግሥተ ሰማያት አኖራቸዋለሁ አለው።
በስምህ የታነፁትንም አብያተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብር ዐረገ። ከዚህም በሗላ እልዋሪቆስ ወደምትባል ታላቅ ሀገር እስከ ሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲአጠምቃቸውና እንዲአስተምራቸው አዘዘችው።
ከዚህም በሗላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ ከበስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው በመጻሕፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልእክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት። መልካም ሩጫውንም ከፈጸመ በሗላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ድኑ ሥቃይን አሠቃየው እራሱንም በሰይፍ እድቆርጢት ለሰያፊ ሰጠው ከሰያፊውም ጋራ አልፎ ሲሔድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች የሆነች አንዲት ብላቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለርሱም አለቀሰች።
እርሱ ግን መጎናጸፊያሽን ስጨኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ አላት እርሷም መጎናጸፊያዋን ሰጠችውና ራስ ወደ ሚቆርጡበት ቦታ ሔደ ለሰያፊውም ራሱን በአዘነበለ ጊዜ በመጎናጸፊያዋ ፊቱን ሸፈነ ሰያፊውም የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፊያ እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው ያ ጳውሎስ ወዴት አለ አለችው ራስ የሚቆረጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፊያሽ ተሸፍኗል አላት።
እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት ዋሽተሃል እነሆ ጴጥኖስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልብሶችን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በዕንቁ የተጌጡ ዐይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል መጎናጸፊያዬንም ሰጡኝ እርሷም እነሗት ተመልከታት ብላ ለዚያ ሰያፊ አሳየችው ከርሱ ጋራ ለነበሩትም አሳየቻቸው አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
የዚህም ሐዋርያ ጳውሎስ ተአምራቶቹ ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው።
=>ሐምሌ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ)
4.ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)
6.ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
7.ቅዱሳት አንስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና
አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
4.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳት ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸው የቅዱሳት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
😘5❤4🥰3😍1💯1
እኔምሰ ስለ ስሜ መከራ ይበቀል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ። ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል አለ…
Jul 11, 2026እኔምሰ ስለ ስሜ መከራ ይበቀል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ። ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል አለው። ያን ጊዜም የሸረሪት ድር የመሰለ ከዐይኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ ዐይኖቹም ተገለጡ።
ወዲያውም አየ ተነሥቶም ተጠመቀ እህልም በልቶ በረታ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር በደማስቆ ጥቂት ቀን ሰነበተ። በዚያው ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰበከ አስተማረም። የሰሙትም ሁሉ አደነቁ እንዲህም አሉ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ያሳድድ የነበረው ይህ አልነበረምን ወደዚህስ የመጣው እያሠረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን።
አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም አደረበት ዕውነተኛውንም ሃይማኖት ግልጽ አድርጎ አስተማረ። ለኦሪት ሕግ የሚቀና እንደ ነበረ እንዲሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠራት ሕገ ወንጌል ዕጽፍ ድርብ ቅንዓትን የሚቀና ሆነ ከዚህም በኃላ በአገሮች ሁሉ ዞሮ ሰበከ በጌታችንም ስም ሰበከ። ድንቆችንና ተአምራትንም አደረገ። ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም አሳመናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመገረፍ በመደብደብና በመታሠር ብዙ መከራ ደረሰበት መከራውንም ሁሉ ታግሦ በሁሉ ቦታ ዙሮ አስተማረ።
በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙና ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ እኔ እነርሱን ለመረጥሁለት ሥራ ሳውልንና በርናባስን ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኃላ ጾመውና ጸልየው እጃቸውንም በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሙአቸው ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ። በደሴቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፉ ወደ ምትባል አገር ደረሱ።
በዚያም ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ ስሙ በርያሱስ የሚባል አንድ ሥራየኛ አይሁዳዊ ሰው አገኙ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባል ብልህ ሰው ከሆነ አገር ገዥ ዘንድ የነበረ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወደ በርናባስንና ሳውልን ጠራቸው። የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበርና ኤልማስ የሚሉት ያ ሥራየኛ ሰው ይከራከራቸው ነበረ ገዥውንም ማመንን ሊከለክለው ወዶ ነበር። ጳውሎስ በተባለው ሳውል ላይም መንፈስ ቅዱስ መላበት።
አተኲሮም ተመለከተው ኃጢአትንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሰይጣን ልጅ የፅድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ እያጣመምኽ ተው ብትባል እምቢ አልኽ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ በአንተ ላይ ተቃጥታለች ትታወራለህም እስከ እድሜ ልክህም ፀሐይን አታይም አለው። ወዲያውኑም ታወረ ጨለማም ዋጠው የሚመራውንም ፈለገ አገረ ገዢውም የሆነውን አይቶ ደነገጠ በጌታችንም አመነ።
ከዚህ በኃላ ሒደው ወደ ሊቃኦንያ ከዚያም ወደ ልስጥራንና ደርቤን ከተማ ወደ አውራጃውም ሁሉ ገብተው አስተማሩ። በልስጥራን ከተማም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እግሩ ልምሾ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ተቀምጦ ይኖር ነበረ እንጂ ለምሾ ከሆነ ጀምሮ ቆሞ አልሄደም። ጳውሎስንም ሲያስተምር አደመጠው ጳውሎስም ተመልክቶ ሃይማኖት እንዳለው እንደሚድንም ተረዳ።
ድምፁንም ከፍ አድርጎ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ቀጥ በልኽ ቁም እልሀልሁ አለው ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ። አሕዛብም ጳውሎስ ያደረገውን አይተው በጌታችን አመኑ። እርሱም በዚያ ሳለ አይሁድ ከአንጾኪያና ከኢቆንያ መጥተው ልባቸውን እንዲአስጨክኑባቸው አሕዛብን አባበሏቸው።
ጳውሎስንም በድንጊያ ደበደቡት ጎትተው ወደ ውጭ አወጡት። በማግስቱም ከበርናባስ ጋራ ወደ ደርቤን ከተማ ሄዱ። በዚያችም ከተማ አስተማሩ ብዙ አህዛብንም ወደ ሃይማኖት አስገቡ ለቤተ ክርስቲያንም ቀሳውስትን ሾሙላቸው ከዚያም ወደ መቄዶንያ አልፈው ሔዱ ጋኔን ሟርት የሚያሠራትን አንዲት ልጅ አገኙ ከምታገኘው ዋጋ ለጌቶቿ ብዙ ትርፍን ታስገባ ነበር።
እንዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው የሕይወትንም መንገድ ያስተምሯችኋል ብላ እየጮኸች ከጳውሎስ ኋላ ተከተለች ብዙ ቀንም እንዲሁ ታደርግ ነበር። ጳውሎስንም አሳዘነችው መለስ ብሎም መንፈስ ርኩስን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትወጣ አዝዤሃለሁ አለው ወዲያውኑም ተዋት።
ከዚህ በኃላም ሐለብ ከሚባል አገር ደረሰ የጢሞቴዎስንም እናት ስሟ በድሮናን ከሞት አስነሣት። በዚያም ያዙት ለዚያች አገር ጣዖትም ሊሠዉት ወድደው በሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት። ስለእነርሱም እየማለደ እጆቹን በመስቀል ምልክት አምሳል ዘረጋ። አሕዛብም በአዩት ጊዜ ስለዚህ ድንቅ ሥራ አደነቁ።
ከእሳት መካከልም እንደወጣ ማለዱት ምንም ምን ሳይነካው ወጣ ሰገዱለትም ክብር ይግባውና በጌታችንም አመኑ የአገሩ ሹም አርስጦስም አመነ። ሰባቱ የጣዖት ካህናቶች ግን ሸሽተው ተሠወሩ። ቅዱስ ጳውሎስም በጭላት አምሳል የተቀረጸውን ምስል ጠራው ምስሉም በአንበሳ ምሳሌ መጥቶ በምኩራቡ መካከል በጳውሎስ ፊት ቆመ።
ቅዱስ ጳውሎስም የሚያመልኩህ ካህናቶችህ ወዴት አሉ አለው አንበሳውም ያሉበትን እስክነግርህ ድረስ ጌታዬ ጥቂት ታገሠኝ አለው። ካህናቱም ወሰተሸሸጉበት ሔዶ አንዱን አንገቱን በአፉ ይዞ እየጎተተ አምጥቶ እንደ በድን በአደባባዩ መካከል ጣለው። ሰባቱንም እንዲሁ እየአንዳንዱን እየጎተተ አመጣቸው።
ሕዝቡም ሊገድሏቸው ወደዱ። ጳውሎስም ዛሬ በዚች ከተማ ማዳን እንጂ መግደል አይገባም አለ ከዚህም በኃላ ሁሉንም አጠመቃቸው ሃይማኖትንም አስተማራቸው። ያንንም አንበሳ የሆነ የጭላት ምስል አንበሳ ሆይ አትፍራ ስለ አገለገከኝ እስከ ምሻህ ድረስ ኑሮህ በበረሀ ይሁን አለው። ያን ጊዜም ወደ በረሀ ሔደ።
ጳውሎስም ከዚያ ተነሥቶ አካ ወደ ሚባል ከተማ ሔደ ስክንጥስ ከሚባል ደቀ መዝሙርም ጋራ ተገናኘ አይሁድም ዜናውን ሰምተው ከአሕዛብ ጋራ ተሰበሰቡ ይዘውም ጭንቅ የሆነ ሥቃይን አሠቃዩት ዳግመኛም ሁለት በሮችን አመጡ ከስክንጥስ ጋራም አሥረው በከተማው ጥጋጥግ በስለታም ድንጋይ ላይ አስጐተቷቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ ዐጥንታቸውም እስከሚታይ ድረስ ሥጋቸው ተቆራረጠ።
ወደ ጌታም ጸለዩ ያን ጊዜም በሮቹ ከሚነዳቸው ጋራ ደንጊያ ሆኑ። ሕዝቡም በአዩ ጊዜ ለመኮንኑ ነገሩት እርሱም ተቆጣ ወደርሱም እንዲአቀርቧቸውና በደንጊያ እንዲወግሩአቸው አዘዘ በቅዱስ ጳውሎስም ላይ እጅግ ተቆጥቶ አንተ የሥራይ ሰው እነሆ አሠቃይሃለሁ አለው በበሬ ቅርጽ የተሠሩ ሁለት የናስ ቀፎዎችንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ።
ዝፍት ሙጫና ድኝ አምጥተው በውጭ ቀላቅለው ሁለቱን የናስ ቀፎዎች በውስጥም በውጭም ቀቧቸው። ሐዋርያትንም በውስጥ ጨምረው በእሳት ምድጃ ውስጥ አስገቧቸው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም እሳት አነደዱባቸው።
መዳኒታችንም ክርስቶስም ከመላእክቶቹ ጋር መጣ እሳቱንም ከዚያ ፈልሶ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቶ የከተማውም ሰዋችሁሉ እንዲከባቸው አደረገው በተጨነቁም ጊዜ ጮኹ አለቀሱም መዳን ከፈለጋቹ ፈጥናቹ በአደባባዩ በአንድነት ተሰብሰቡ የሚል ቃል ከሰማይ ጠራቸው ጳውሎስም ወደ በረሀ አሰናብቶት የነበረውን አንበሳ መጣ ጳውሎስ በስሙ በሚያስተምርበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ እያለ ጮኸ።
😍7🥰5💯1😘1
ቅዱስ ጴጥሮስ ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘንም አለው። ከዚህ በኃላ ወደ ከተማ መካከል ገብተው ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማ ሰዎችና የጣዖታቱ አ…
Jul 11, 2026ቅዱስ ጴጥሮስ ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘንም አለው። ከዚህ በኃላ ወደ ከተማ መካከል ገብተው ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማ ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮች በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸ አጐሳቆሏቸውም ግማሽ የራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አስረውም በግንብ ወስጥ ጣሏቸው።
ከዚህ በኋላ ይረዳቸው ዘንድወደ እግዚአብሔር ጸለዮ ወዲያውኑም ክብር ይግባውና ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፌል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንደህ አላቸው የመረጥኳቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም ለመዘባበቻም በራሳቹ መካከል ስለላጩአቹ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብር የክህነት ስርዓትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዚህ ምልክት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አይችልም ።
ይህ ምልክት እያለው የሚሞት ካህንም ኃጢአቱ ይሠረይለታል። ይህን ካላቸው በኃላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ። ከዚህም በኃላ ጳውሎስ መጥቶ ዮሐንስን ተገናኘው የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድነው አለው እርሱም ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትንም አለቃ በእኔ ላይ በአደረጉት አማሳል አድርገውበታልና አለው። ጳውሎስም አጽናናቸው እንዲህም አላቸው እኔ በጌታችን ፈቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባችኃለሁ።
ከዚህም በኃላ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖተቸውንም እንደሚአመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲአቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲጠይቃቸው የከተማውን መኳንንት አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ጳውሎስ እንዲአቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ጳውሎስ ስለ ሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም ድንቆችንና ተአምራቶችን ለሚአደርግ ለክርስቶስ ደቀ መዝሙሮቹ እንደሆኑ ነገሩት።
ዳግመኛም እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁን አላቸው እነርሱም አዎ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን አሉት። ከዚህም በኃላ ከእናቱ ማሕፀን ዕውር ሆኖ የተወለደውን ዐይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውም ከተበላሸ በኃላ ከመቃብር አስነሡት። ንጉሡና የከተማ ሰዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውኃን አፈለቀ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱሰወ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው። ከዚህም በኃላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ብዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዊቻቸውና ከከብቶቻቸው ጋራ እንዳሠጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ።
ዮሐንስም ወደ እነርሱ ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒድ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመለሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሠርክ ነህ ብሎሃል በለው። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንዳዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ።
ከዚህም በኃላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር ላይ አውርዶ ጥሎ አጠፋው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዥ የአክርጶስ ቁባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ብዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው ርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ።
ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስን ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገድሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሔድ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማው ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና አቤቱ ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ አለው።
ጌታም ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እሔዳለሁ ብሎ መለሰለት ቅዱስ ጴጥሮስም አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን አለው። ያን ጊዜም ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅግ አዘኑ።
ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉትም በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደላይ ሆኖ ስለተሰቀለ እኔ ቁልቁል ልሰቀል ይገባኛል። ወዲያውኑም እንደነገራቸው ሰቀሉት። ተሰቅሎ ሳለም ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኃላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጳውሎስ
በዚህችም ቀን ዳግመኛ ልሳነ ዕረፍት የክርስቶስ አንደበት የዕውቀት አዘቅት የቤተ ክርስቲያን መብራት የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው። እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው። ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበረ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሪሳዊ ልጅ ነው።ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ነው።
ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበረ። እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አስዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኮራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ።
ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማይ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ። ሳውልም አቤቱ አንተ ማነህ አለው አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው: የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም። ሳውልም ከምድር ተነሣ ዐይኖቹም ተገልጠው ሳሉ አያይም ነበር እየመሩም ወደ ደማስቆ አስገቡት በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ሰነበተ።
በዚያም በደማስቆ ከደቀ መዛሙርት ወገን ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ጌታም በራእይ ተገለጠለትና ሐናንያ ብሎ ጠራው እርሱም አቤቱ ጌታዬ እነሆኝ አለ። ጌታም ተነሥና ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሒድ በይሁዳ ቤትም ጠርሴስ ከሚባል አገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ እርሱ አሁን ይጸልያልና አለው። ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ አቤቱ ስለዚያ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ ወደዚህም ከካህናቱ አለቃ አስፈቅዶ የመጣ ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ሊአሥር ነው። ጌታችንም ተነሥና ሔድ በአህዛብና በነገሥታት በእስራኤልም ልጆች ፊት ሰሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና ።
❤3🥰3😘3😍2💯1
#ሐምሌ_5
Jul 11, 2026#ሐምሌ_5
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጴጥሮስ
ሐምሌ አምስት በዚህች ቀን የሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስ የሰማዕትነት መታሰቢያ ነው። ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ ነበር ዓሣ አጥማጅም ነበር ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግሥት አግኝት መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው።
መድኃኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲአገለግለው ኖረ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ጌታችንም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎቹ ኤርሚያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል አሉት።ጴጥሮስ ግን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ አለ።
ጌታችንም የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ ብሎ ብፅዕና ሰጠው የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ አለው። አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተቀበለ በኃላ ተናጋሪዎች በሆኑ በዚህ ዓለም ተኩላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው።
ጌታችንም የማይቁጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸዉ ሦስት መልእክቶችም ጽፎ ለምእመናን ላካቸው ለማርቆስ ወንጌሉን ተርጎሞ አጽፎታል። ከዚያም በሗላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደ ሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገሩ በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የድንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ አሜን አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ ከንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ።
ከከተማ መኳንንቶችም ቀዉስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ ለምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኖችም ሰለመራራትና የመሳለለውን ቃል ጴጥርስ እንዴት እንዳስ ተማረ ነገራት እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቅታ ይህ ነገር መልካምና ድንቅ ነው አለች ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በሗላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድሖች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም። ከጥቂት ቀኖችም በሗላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ስራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልእክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህን በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም ምክንያቱም አመካኝቶ ይሠወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ እሷም ግን ምክንያት አታድርግ ነገር ግን ወደ ንጉሡ ሒድ የጴጥሮስ አምላክ ጎዳናህን ያቅናልህ አለችው።
እርሱም ነገርዋን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም በእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሱም ደረሰ ንጉሡም በደስታ እና በክብር ተቀበለው። ከሦስት አመት በሗላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለት ልጆቹ የተመረዘ ውኃ ጠጥተው እነሆ ሙተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለቸለት በሗላ ነገረችው በሰማ ጊዜም እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናልን የጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀውስጦስና አክሮስያ ሆይ የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለ ሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣችሗለሁ የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሡ ቀውጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
እኝህም ከሞት የተነሡ ልጆች ለቅዱስ ጴጥረስ ደቀ መዝሙሮች ሆኑ የአንዱ ስም ቀሌምንጦሶ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥኖስ ያየውንና ጌታችን በሥጋ ወደ ሰማይ በሚዐርግ ጊዜ የገለጠለትን ምሥጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምንጦስን ሊቀ ጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸውከዚህም በሗላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብርዋን በምሳሌ አየ።
በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላይዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳኑም ውስጥ አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸውስጥ የነበልባል ጦሮችንና ሰይፎችን የያዙ መላእክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበሩ እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር ከእርሷ የድኅነታችን ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ።
መሕፀንሽ የእግዚአብሔርን በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ ሁለተኛውም እንዲህ ይላት ነበር የብርሃን እናቱ ሆይ የምህረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረቱ ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ። መላእክትም ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናወጸች ሊነገር የማይቻል ሚስጥራትንም ገለጠላት ።
ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን በሀገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ዘንድ ጴጥሮስን አዘዘው ጴጥሮስም ወጥቶ ሔደ ኢዮጲ ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጲ ሳለ ብርህት ደመና ዞረችው እንሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድተ በዳ አውሬዋችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ የሚል ቃል ም ከሰማይ ጠራው ጴጥሮስም አቤቱ አይገባኝም እርኩስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም አለ።
ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹ ያደረገውን እርኵስ ነው አትበል አለው ያም ቃል ሥስት ጊዜ እንዲህ መላልሶ ነገረው በየንግግሩም ወደ እሪያዎች ወደ አራዊትና አዕዋፍ ስእሎች ጣት ያመለክተው ነበር ከዚህ በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ጴጥሮስም ስላየው እራእይ አደነቀ ይህም እራእይ ወደ ፈጣሪያቸወረ እግዚአብሔር የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃልን እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው ።
ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋራ ጌታችን እንዳዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገራቸውን ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ጴጥሮስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም ክፉ ነገርን ተናገሩት ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስም አለው አባቴ ሆይ የእሊህ ጐስቋሎች ክፋታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገስታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በገፀታችን ሰም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆን ይሆን እንዴትስ ሃይማኖት እናስተምራለን።
❤8🥰2😍2💯1😘1
🌸🌸
Jul 10, 2026🌸🌸
እንኳን
አደረሳችሁ
ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
ረድኤት በረከቱ ይደርብን
🌹❤️🌹................. ሐምሌ ❹
🥰8❤4😘4🙏1😍1
✝ደቂቀ ነቢያት ቅዱሳን አሠርቱ ወክልኤቱ፤
Jul 10, 2026✝ደቂቀ ነቢያት ቅዱሳን አሠርቱ ወክልኤቱ፤
እለ አውኃዙ ትንቢተ ለክርስቶስ በአፍቅሮቱ፤
ሶፎንያስ ዘገብረ ለእግዚአብሔር ዘከመ ሥምረቱ፤
አቡቂር ወዮሐንስ ጽዑራነ ዘሞቱ!
✝ እንኳን አደረሰን !
❤4🥰3😍3😘3
ቅዱሳን (Saints)
Jul 10, 2026#ሐምሌ_4
Jul 10, 2026#ሐምሌ_4
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ አራት በዚህች ቀን #የቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ፣ #የነቢዩ_ሶፎንያስ እረፍት ነው፣ የዐሥራ ሁለቱ #ደቂቀ_ነቢያት መታሰቢያቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ
ሐምሌ አራት በዚች ቀን የቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ። ይህም እንዲህ ነው እሊህ ቅዱሳን የካቲት ስድስት ቀን ሰማዕታት ሆነው በሞቱ ጊዜ ምእመናን ሥጋቸውን ተሸክመው ወስደው በእስክንድርያ ከተማ በስተሰሜን ባለች በቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥውር አኖሩዋቸው እስከ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ዘመንም በዚያ ኖሩ።
የእግዚአብሔር መልአክም ለቅዱስ ቄርሎስ ተገለጸለት ወደ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ሔዶ የቅዱሳን የአቡቂርንና የዮሐንስን ሥጋቸውን አውጥቶ እንዲሸከም አዘዘው። እርሱም ተነሥቶ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ሕዝቦች ነበሩ በደረሱም ጊዜ ጸለዩ ምድሩንም ሲቆፍሩ ሥጋቸው በውስጡ ያለበት ቦታ ተገለጠላቸው በባሕር ዳርቻ ወደ አለች ወደ ሌላዪቱም የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ተሸክመው አድርሰው በዚያ አኖሩ።
በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው በዚችም ቀን ታላቅ በዓል አደረጉ ከሥጋዎቻቸውም ድንቆች ተአምራት ተገለጡ አረማውያንም ተሰበሰቡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ትተው ክርስቲያኖች ሆኑ። በዚያቺም የጣዖቶች ቤት አሸዋ በላይዋ ተከመረባት ታላቅ ኮረብታም ሆነ። የቅዱሳንም ሥጋቸው ታምራትንና ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስን ያደርጋል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ነቢዩ_ሶፎንያስ
በዚህችም ቀን ደግሞ የአማርያ ልጅ፣ የሴዴቅያስ ልጅ፣ የጎዶልያ ልጅ፣ የኩሲ ልጅ የሶፎንያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እርሱም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ተናገረ። እንዲህም አለ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ፈጽመው ይጠፋሉ አለ ከብቶችና ሰዎች ያልቃሉ። የባሕር ዓሣዎችና በሰማይ የሚበሩ አዕዋፍም ያልቃሉ።
ዳግመኛም ስለሞአብ እንዲህ አለ ስለዚህ ሞአብ እንደ ሰዶም ትሆናለች የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ልጆች ይሆናሉ ደማስቆም እንደ እህል ታልቃለች። እርሱ እንደ ተነበየው እነዚያ አገሮች በናቡከደነጾር ምርኮ ይጠፋሉና።
ዳግመኛም ስለ ፋርስና ስለ ነነዌ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ የፋርስን ሰዎች አጠፋቸዋለሁ ነነዌንም ፍርስራሽና ውኃ እንደሌለባት ምድረ በዳ አድርጋታለሁ መንጋዎችም በመካከሏ ይሠማሩባታል። ይህቺም ከተማ በመቄዶናዊው እስክንድር እጅ ጠፍታለች።
ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ መምጣት እንዲህ ተናገረ። ያን ጊዜም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራ ዘንድ በአንድ ሕግም ይገዙልኝ ዘንድ የአሕዛብን ሁሉ አንደበት ወደ ሕግ እመልሳለሁ። ደግሞም እንዲህ አለ ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ መሥዋዕቴን ያመጡልኛል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ደቂቀ_ነቢያት
ዳግመኛም በዚች ቀን ስለ ክርስቶስ ትንቢታቸውን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያጐረፉ የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት መታሰቢያቸው ነው።
ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው፡፡ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት የሚባሉት፡- ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ኢዩኤል፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ እንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው፡፡
ሌሎቹ ዋና (ዓበይት) ነቢያት የሚባሉት አራት ሲሆኑ እነርሱም ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤልና ዳንኤል ናቸው፡፡ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ድረስ ያሉት ነቢያት ‹‹ደቂቀ ነቢያት›› የተባሉት ምክንያት አንድም የነቢያት ልጆች በመሆናቸው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የጻፏቸው ትንቢቶቻቸው ዓበይት ነቢያቱ ከጻፏቸው ጋር በንፅፅር ሲታይ አነሥተኛ ስለሆነ ነው፡፡
'ነቢይ' ማለት እግዚአብሔር የመረጠውና የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ የሚያስተላልፍ ብሎም የተሠወረውንና የሚመጣውን ሁሉ በግልጽ የሚመለከት ማለት ነው፡፡ ነቢያት ሲባሉ በአጠቃላይ ምግባር ሃይማኖታቸው ያማረ፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው የሰመረ ነውና አካሄዳቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ነው፡፡
=>ሐምሌ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."12ቱ" ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት
2.ቅዱስ ሶፎንያስ ነቢይ (ዕረፍቱ)
3.ቅዱሳን ሰማዕታት አቡቂርና ዮሐንስ (ቅዳሴ ቤታቸው)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ /ወንጌላዊው/
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ /ሰማዕት/
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤8🥰4😍2😘2
✝ቀዳማይ ምኒልክ✝
Jul 09, 2026✝ቀዳማይ ምኒልክ✝
✝ የቅዱስ ሰሎሞን እና የንግሥት ሳባ ልጅ።
✝ የቅዱስ ዳዊት የልጅ ልጅ።
✝ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት ታቦተ ጽዮንን ወደ ኢትዮጵያ ያመጣ።
✝አምልኮተ እግዚአብሔርን ያስፋፋ።
✝ሥርዓተ ኦሪትን ያመጣልን ደግ ሰው።
ሐምሌ 3 ዕረፍቱ ይከበራል።
ከበረከቱ ይክፈለን።
😘10❤4🥰3❤🔥2👌2😍2
✝ቄርሎስ ዐቢይ ዘሰመይዎ ዓምደ ሃይማኖት፤
Jul 09, 2026✝ቄርሎስ ዐቢይ ዘሰመይዎ ዓምደ ሃይማኖት፤
ታኦዶኮስ ይቤላ ለማርያም ቅድስት፤
ወክልስቲያኖስ ክቡር ዘሮሜ ሊቀ ጳጳሳት፤
ሉቅያስ ወምኒልክ ቀዳማይ እምነገሥት!
✝እንኳን አደረሰን !
🥰11😘4❤3😍2
#ሐምሌ_3 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቄርሎስ አረፈ፣ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ክልስቲያኖስ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ…
Jul 09, 2026#ሐምሌ_3 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቄርሎስ አረፈ፣ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ክልስቲያኖስ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቄርሎስ ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቄርሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው…
❤11😘4🥰3😍3🕊2
#ሐምሌ_3
Jul 09, 2026#ሐምሌ_3
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቄርሎስ አረፈ፣ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ክልስቲያኖስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቄርሎስ
ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቄርሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላ*ካውያት የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው።
ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርቱን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። ከዚህም በኋላ ሁልጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር በሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው።
ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። አባ ቴዎፍሎስም ከአረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስ*ጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ።
ይህን አባት ቄርሎስንም መርጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት። ንስጥ*ሮስንም ተከራከረው ስሕተ*ቱንም ገለጠለት። ከስሕ*ተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግ*ዘው ከመንበረ ሢመቱ አሳደ*ዱት። ይህም አባት ቄርሎስ ዐሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ ከእነርሱ በኋላ ግን ብዙዎች ድርሳናትን ተግሣጻትንና መልእክቶችን ደረሰ።
እሊህም በሁሉ ቦታ በምእመናን እጆች ይገኛሉ። ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትስብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራው ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ አስረዳ። ይህም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስን ወደ ሁለት የሚከፍሉትን መናፍ*ቃንን ሁሉንም አው*ግዞ ለያቸው።
በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነ ሥራውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ክልስቲያኖስ
በዚህችም ቀን ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ የነበረ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ክልስቲያኖስ አረፈ። ይህ አባ ዮናክንዲኖስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዱሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ ብሎ አዘዘው። ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲኖስ ባረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፋንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
በዚያን ወራት ደግ ንጉሥ አኖሬዎስ ነበረ። ከርሱም በኋላ ዐመ*ፀኛ ሉልያኖስ ነገሠ ። እርሱም ክልስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መና*ፍቁ ንስ*ጥርስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክልስቲያኖስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድ*ለውም ይሻ ነበር።
እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሔደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ሩፋኤልም ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው በዚያም ኑር አለው።
ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድ*ልህ ዘንድ በልቡ አስቧልና። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱ ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ። ወደ እንጾኪያም ከተማ ደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስን አገኘው ከዐመፀኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው።
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲኖስ በሌሊት ራእይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋር የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበረ። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ።
ንጉሥም ጌታዬ ምን ላድርግ አለው እነዚያም ሁለቱ አባቶች በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን ብለው መለሱለት እኔ አምናለሁ አላቸው ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስን ወደ መንበሩ መልሰው አሉት። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ ድምትርያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሢመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን ለመልእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሃለሁ።
መልክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት። በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደኅና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። የንስጥሮስም ክህ*ደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምክንያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ። ይህ አባት ክልስቲያኖስም በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደጉባኤው መምጣት አልተቻለውም ነገር ግን ንስ*ጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋራ ሁለት ቀሳውስትን ላከ።
ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲኖስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርቶሃልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው ተኵላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ።
ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ እንነሣና እንሒድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው። በዚችም ሰዓት ከዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን ሀገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው። ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ።
† ሐምሌ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)
2.ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ (ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
3.አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
🥰8😍4❤3😘3🕊2
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 09, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
❤3😍3🥰2😘1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 09, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 09, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
❤3😍2🥰1
✝ታዴዎስ ሐዋርያ ብእሲ ሔር፤
Jul 08, 2026✝ታዴዎስ ሐዋርያ ብእሲ ሔር፤
ወበዓለ ዐቢይ መንክር፤
በእንተ ዘረድኦ በፍኖት ሚካኤል ክቡር፤
ምስለ ዜና ድንግል ጻድቅት ተዝካሮ ንገብር!
✝እንኳን አደረሰን !
💯1😘1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 08, 2026#ሐምሌ_2 #ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሁለት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ…
Jul 08, 2026#ሐምሌ_2 #ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሁለት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላያቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው…
እንደ ለመነውም አደረገለት የሃይማኖትንም ሕግ አስተምሮ የክርስትናን ጥምቀትም አጠመቀው ሥጋውንና ደሙንም አቀበለው ሁሉንም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከዚህ በኋላ ከዚያ ወጣ በሰላምም ሸኙት በብዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ ከአይሁድና ከአረማውያንም መከራ ደረሰበት። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
=>ሐምሌ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
💯1
#ሐምሌ_2
Jul 08, 2026#ሐምሌ_2
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሁለት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላያቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚአምር ጐልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን አሉት።
እርሱም ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ አላቸው እነርሱም እንዳልክ አሉት። ያ ሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኅፍረት ነው ያ ሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና አለ። ይህንንም ብሎ ተነሥቶ እርፉን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበረና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችንም አረሰ።
የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን አላቸው እነርሱም እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን። ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት።
እኛም ወደዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውስጧ ለመኖር እንሻለን አሉት። ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት።
ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው አሉት እርሱም ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻችሁ ታይዋቸዋላችሁ አላቸው።
ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ አሉ። እኩሌቶቹም ልንገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማው መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም አሉ።
እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ታዴዎስም በአያት ጊዜ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ላክልን አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ስዎችም አዮዋት ያቺ ሴትም ከከተማዋ መኳንንቶች አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና ።
ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ስደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለችውን ሴት አወረዳት።
ከዚህ በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ ዕውሮች አዩ ሐንካሶችም በትክክል ሔዱ ዲዳዎች ተናገሩ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ አጋንንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን እስኪያምኑ ሙታን ተነሡ።
ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልብ አድሮም በሐዋርያው ታዴዎስ ላይ አነሣሣው ወደርሱም መጥቶ ሰገደለትና እንዲህ አለው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው አትግደል አትስረቅ አታመንዝር በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ ደግሞም ገንዘብህን ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ አለው።
ይህንንም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተመልቶ ሐዋርያው ታዴዎስን ይገድለው ዘንድ አነቀው። የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሣ ዐይኖቹ ተመዝዘው በወጡ ነበር። አባት ጴጥሮስም የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ አለው ያን ጊዜም ተወው ሐዋርያው ታዴዎስም ጌታችን እንዳንተ ላለው ሀብታም ባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ገመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብሎ በእውነት ተናገረ አለው።
ጐልማሳው ባለጸጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል አለ። በዚያን ጊዜም በዚያ ጐዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ። መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያውን ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያውም እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣልን አለው።
.ከዚህ በኋላ ባለ መርፌው ቀዳዳው ጠባብ የሆነውን መርፌ ባቀረበለት ጊዜ ኃይልህን ግለጥ ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ እጁንም ዘርግቶ ባለ ገመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋራ በመርፌ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ አለው ገብቶም አለፈ ሕዝቡ የፈጣሪያችን የክርስቶስን ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ አለው ባለ ገመሉም በመርፌው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከገመሉ ጋራ አልፎ ሔደ።
ሕዝቡም አይተው ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ያም ጐልማሳ ባለጸጋ መጥቶ ከሐዋርያው እግር በታች ወድቆ ሰገደና ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ ገንዘቤንም ሁሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፋፍል አለው።
😍1💯1
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
Jul 08, 2026⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
😍6❤2🥰2😘1
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Jul 08, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
😍6😘4❤1🥰1🤗1
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
Jul 08, 2026🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
🥰2😍2❤1😘1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 08, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Jul 08, 2026✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
💒 የኦርቶዶክስ ቻናል
✝አበው መስተጋድላን ብዮክ ወብንያሚን፤
Jul 07, 2026✝አበው መስተጋድላን ብዮክ ወብንያሚን፤
ቶማስ ሐዋርያ ወጻድቅ ገብረ መድኅን፤
ክልዮስ ወበርተሎሜዎስ ውሉደ አሐቲ ማኅጸን፤
አግናጥዮስ ወቅፍሮንያ ሰማዕተ እግዚእ መድኅን!
✝እንኳን አደረሰን !
❤🔥1🕊1😘1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 07, 2026አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ታአምር ተገለጠ።
Jul 07, 2026አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ታአምር ተገለጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ብዮክና_ብንያሚን
በዚህችም ቀን ቅዱሳን መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን አረፉ። እሊህም ቅዱሳን በግብጽ ደቡብ በቴዎዳ አውራጃ ቱና በሚባል አገር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ነበሩ። እነርሱም ወንድማማች ነበሩ። አባታቸውም የቤተ ክርስቲያን ሹም የሆነ ደግና የዋህ ሰው ነበረ እሊህም ሁለቱ ልጆቹ በእግዚአብሔር ጸጋና በቅድስና ፍጹማን ነበሩ።
እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ተአምራትን ያደርግ ነበር በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር እነርሱም ከቤተ ክርስቲያኑ የጉድጓድ ውኃ ቀድተው በሽተኞችን ያጥቧቸዋል ወዲያውኑም ከበሽታቸው ይድኑ ነበር።
የአባታቸው የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ በዚያን ሰዓት ቀሲስ ብንያሚን ቍርባን ያሳርግ ዘንድ የቅዳሴ ልብስ ለብሶ በቤተ መቅደስ ነበረ መልዕክተኞችም መጥተው አባቱ ለመሞት እንደ ተቃረበ እርሱንም እንደሚፈልገው ነገሩት።
ብንያሚንም የቍርባኑን ሥርዓት ሳልፈጽም ልብሰ ተክህኖውን አላወልቅም ከመሞቱ በፊት እንዳየው እግዚአብሔር ከፈቀደ ይቆየኛል ካልሆነም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አለ። አባቱም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ላከ አባ ብንያሚን ግን የቍርባኑን ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ አባቱ ሔደ ሙቶም አገኘው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅድሳትም እጅግ አዘነ እነርሱ በእርሱ ዘንድ እየኖሩ ዕቃዎችን ያኖረበትን ቦታ አላመለከታቸውም ነበርና።
ወንድሙ ብዮክም አባታቸው ስለ አስቀመጠው ንዋየ ቅድሳት ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ ቅዱሳን አረጋውያን ሒዶ እንዲጠይቅ መከረው። አባ ብንያሚንም በሔደ ጊዜ የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት አባ ዳንኤልን አገኘው አባ ዳንኤልም ስለርሱ የመጣበትን ሥራ ሁሉ ነገረው ነገር ግን ወደ አንድ ጻድቅ ሰው እንዲሔድ አዘዘው እርሱም ንዋየ ቅድሳቱ ያለበትን እንደሚያስረዳው ነገረው።
በሔደም ጊዜ እንደ አመለከተው ያንን ጻድቅ ሰው አገኘው። እርሱም ገልጾ አስረዳው በተመለሰም ጊዜ እንዳስረዳው አገኘው። ከዚህም በኋላ በመልካም ገድል ሁሉ ከወንድሙ ጋራ ተጠምዶ ኖረ። ለሕሙማን ነፍሳችው ሳትወጣ ያቀብሏቸው ዘንድ ከቅዱስ ቍርባን ከፍለው በሣጥን የማኖር ሥርዓት ነበራቸው ሰይጣንም ከይሲን አነሣሣውና ሣጥኑን ቀድዶ ከዚያ ከቅዱስ ቍርባኑ በላ።
ብዮክና ብንያሚንም ይህን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዘኑ ከይሲውንም ገደሉት ከዚህም በኋላ የተቀደሰውን ቍርባን ስለ በላ ከይሲውን ይበሉት ዘንድ ተማከሩ ፈቃዱም ከሆነ እንዲያስረዳቸው እግዚአብሔርን ለመኑት የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጸላቸውና ያን ከይሲ ይበሉት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም በሉት። ከበሉትም በኋላ አረፉ።
እግዚአብሔርም ሥራቸውንና ገድላቸውን ለአንዲት ድንግል ሴት ገለጸ እርሷም የእሊህን ቅዱሳን ገድል ለሕዝብ ተናገረች እነርሱም የአማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን አደረገ። ሥራ የሚሠራ አንድ ጎልማሳ ነበር ከሐዋርያው ቶማስም እጅ የተባረከ እንጀራ ከሕዝብ ጋራ ተቀበለ። ወደ አፉም ሊጨምረው በወደደ ጊዜ እጆቹ ደረቁ። ያዩት ሰዎች ግን በዚህ ሰው ላይ የሆነውን ለሐዋርያው ነገሩት።
ሐዋርያው ቶማስም ጠራው ልጄ ሆይ አትፈር ንገረኝ የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ ዘልፎሃልና አለው። ያም ሰው ከሐዋርያው እግር በታች ሰገደ መልካም ሥራ የሠራሁ መስሎኝ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁ አንዲት የጠጅ አበዛ ሴት ነበረች አስቀድሞ ወደርሷ እኔ እገባ ነበር። አንተም በንጽሕና እንድንኖር አስተማርከን ያችም ሴት ከእርሷ ጋራ እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ ስለዚህም ሰይፍ አንሥቼ አረድኳት ሐዋርያውም እንዴት እንዲህ ያለ ቁጣና የአውሬ ሥራን ሠራህ አለው።
ከዚህ በኋላም ውኃ ያመጡ ዘንድ ሐዋርያው አዘዘና በውኃው ላይ ጸለየ ጐልማሳውንም በእግዚአብሔር ታምነህ እጆችህን ታጠብ አለው ሲታጠብም ዳነ። ከዚህም በኋላ የዚያች ሴት በድን ወደ አለበት ና ምራኝ አለው ያም ጐልማሳ መርቶ ወደ ቦታዋ አደረሰው በደረሰም ጊዜ አይቷት እጅግ አዘነ።
ወደ ውጭም አውጥተው በዐልጋ ላይ ያኖሯት ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ እጁንም በላይዋ ጭኖ ጸለየ። ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጐልማሳውን ሒድ እጇን ይዘህ እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ በላት አለው። እርሱም እንዳዘዘው አደረገ እጇንም ይዞ ሳባት ፈጥናም ተነሣች ሐዋርያውንም አየችው ዐልጋዋንም ትታ ከሐዋርያ ቶማስ እግር በታች ሰገደች የልብሱንም ጫፍ ይዛ በአንተ ዘንድ አደራ ያስጠበቀኝ ባልንጀራህ ወዴት አለ አለችው።
ሐዋርያም ወደየት ደርሰሽ ነበር ንገሪኝ አላት እርሷም አንተ ከእኔ ጋራ እያለህ እንዴት ንገሪኝ ትለኛለህ አለችው ያየሽውን ንገሪ አላት። ከሥጋዬ በተለየሁ ጊዜ አንድ ልብሱ የቆሸሸ ሽታውም የሚከረፋ ጠቋራ ተቀበለኝ የእሳት ጉድጓድና የእሳት መንኰራኵር ወደአለበት ቦታ ወሰደኝ ደግሞም እድፍንና ትልን የተመላ ጉድጓድን አየሁ ነፍሳትም በውስጡ ይንከባለላሉ። በዚያም በምላሳቸው የተንጠለጠሉ አሉ በጠጉራቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በእጆቻቸውም በእግሮቻቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በላያቸውም ድኝ ይጤስባቸዋል ያስጨንቋቸዋልም።
ያ የሚመራኝም እኒህ ነገረ ሰሪዎች፣ ሐሰተኞች፣ አመንዝራዎችና ቀማኞች፣ ሌቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ድኆችንና በሽተኞችን የማይጐበኙ፣ የእግዚአብሔርንም ሕግ የማያስታውሱ ናቸው ስለዚህ እንደ ሥራቸው ይቀጣሉ አለኝ አለች።
ሐዋርያው ቶማስም ከዚያ የነበሩትን ይቺ ሴት የምትለውን ሰማችሁን ያለው ሥቃይ ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ከዚህ የሚከፋ አለ እናንተም የኃጢአትን ሥራና ክፉ አሳብን ትታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። ትሕትናን፣ የዋህነትንና ፍቅርን፣ ንጽሕናንም ጠብቁ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ጸጋን ትቀበላላችሁ አላቸው።
ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሕዝብ አመኑ ለድኆችም ምጽዋትን ሊሰጡ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው አመጡ ለድኆች ምጽዋት መስጠት ለሐዋርያው ልማዱ ነበርና።
ወሬውም በየሀገሩ ሁሉ ደርሶ በሽተኞችን ሁሉ አጋንንት የያዟቸውንም አምጥተው በጎዳና ዳር አኖራአቸው ሁሉንም በእግዚአብሔር ኃይል አዳናቸው።
† ሐምሌ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሰማዕት
2.አበው ቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን
3.ቅድስት ቅፍሮንያ (ሰማዕት ወጻድቅት)
4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
5.አቡነ ገብረ መድኅን ጻድቅ
6.አባ ክልዮስ ዘሮሜ
† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ_እና_ታኅሣሥ)
🕊1💯1🏆1
#ሐምሌ_1
Jul 07, 2026#ሐምሌ_1
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ አንድ በዚህችም ቀን #ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው፣ ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች #ቅድስት_ቅፍሮንያ ሰማዕት ሆነች፣ #ቅዱሳን_ብዮክና_ብንያሚን አረፉ፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን አደረገ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ
ሐምሌ አንድ በዚችም ቀን የሊቀ ጳጳሳቱ የአግናጥዮስ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙሩ ነው በስብከተ ወንጌልም በማገልገል ከእርሱ ጋር ብዙ አገሮችን ዙሮ አስተምሮአል ከዚህም በኋላ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው በውስጥዋመሰ ሕይወተሰ የሆነ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱም ልቡናቸውን አበራላቸው።
ከዚህም በኋላ ጣዖትን ለሚያመልኩ ስሕተቻተውን በገለጠላቸው ጊዜ ተቆጡ። ወደ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጠራብዮስ ሔደው ከሰሱት እንዲህም አሉት "አግናጥዮስ የአማልክቶችህን አምልከሸ ይሽራል እኮን ሰዎችንም እያስተማረ ክርስቶስን ወደ ማመን ያስገባቸዋል"። በዚያንም ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "አግናጥዮስ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ የአማልክቶቼን አምልኮስ ለምን ሻርክ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ አስገብተሃቸዋልና" አለው።
አግናጥዮስም "ንጉሥ ሆይ ቢቻለኝስ ያክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ባስገባሁህ ነበር" አለው ንጉሡም "ይህን ነገር ትተህ ለአማልክቶቼ ሠዋ አለዚያ በታላቅ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። "በእኔ ላይ የምትሻውን አድርግ እኔ ግን ለረከሱ አማልክቶችህ አልሠዋም ሥቃይህንም እሳትም ቢሆን አንበሳንም ቢሆን አልፈራም ከሕያው ንጉሥ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው። ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ ተቆጣ ያሠቃዩትም ዘንድ አዘዘ በተለያዩ በብዙ ሥቃዮችም አሠቀሠዩት በእጆቹም ውስጥ እሳት አድርገወሰ ከእጆቹ ጋር በጉጠት ይዘው አቃጠሉት።
ከዚህም በኋላ በዲንና በቅባት እያነደዱ ጎኖቹን አቃጠሉ በሾተሎችም ሥጋውን ሠነጠቁ። ከማሠቃየትም በደከሙ ጊዜ የሚያደርጉበትን እስከመክሩ ድረስ ከወህኒ ቤት ጨመሩት ብዙ ቀኖችም በዚያ ኖረ።
ከዚህም በኋላ አስታውሱት ከወህኒቤትም አውጥተው በንጉሡ ፊት አቆሙት ንጉሡም "አግናጥዮስ ሆይ አማልክቶቼን ብታያቸው ውበታቸው ባማረህ ነበር" አለው። ቅዱሱም "ንጉሥ ሆይ አንተ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ብታምን ሙታኖችን የምታሥነሣቸው በሽተኞችንም የምትፈውሳቸው ባደረገህ ነበር"። ንጉሡም "ለፀሐይ ከመስገድ የተሻለ የለም" አለ የከበረ አግናጥዮስም "መንግሥቱ የማያልቀውን ፈጣሪ ትተህ ለተፈጠረ ፀሐይ ትሰግዳለህን?" ብሎ መለሰ ንጉሡም "ለራስህ መልካም አልክ ግን በመተላለፍ የአንጾኪያና የሶርያን ሰዎች ስበሕ ወደ ክርስቶስ አምልኮት አስገባሃቸው እንጂ" አለው። የከበረ አግናጥዮስም ተቆጥቶ "ንጉሥ ሆይ ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው።
በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"።
ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጤ አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት።
ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ቅፍሮንያ
በዚህች ቀን ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች ቅድስት ድንግልና መስተጋድልት ቅፍሮንያ ሰማዕት ሆነች።
እርሷም በደናግል ገዳም ቁጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች። የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው። ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት። በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያት የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት።
ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር። ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች። በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር።
ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ። እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ። እመ ምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች።
በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኞች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም። ቅድስት ቅፍሮንያም በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት አለቻቸው። እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው።
ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት።
ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦሪያናም አንተ ከሀዲ ይቺን ታናሽ ብላቴና እንዳጐሳቈልሃት እግዚአብሔር ያጐሳቍልህ ዘንድ አለው ብላ ጮኸች። መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህቺን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲያሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች።
ከዚህም በኋላ ደግሞ ምላሷንና ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ሕማም አስነሣት። መኰንኑም እሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች።
🙏1🕊1💯1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 07, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
Jul 07, 2026🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 07, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 07, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
Jul 06, 2026⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
የሁሉንም አባቶች ትምህርት ይፈልጋሉ❓️
--------------------------------------------------
✝️ ሰኔ 30
Jul 06, 2026✝️ ሰኔ 30
✝እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
❤1🥰1🕊1😘1
#ሰኔ_30 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአል…
Jul 06, 2026#ሰኔ_30 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአልዓዛር እህቶች #የቅዱሳን_ማርያ_እና_የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ…
❤1❤🔥1🥰1😘1
#ሰኔ_30 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአል…
Jul 06, 2026#ሰኔ_30 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአልዓዛር እህቶች #የቅዱሳን_ማርያ_እና_የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ…
በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::
ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: (ቅዳሴ ማርያም) ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች:: ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች::
=>ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
❤🔥1🕊1💯1🏆1
#ሰኔ_30
Jul 06, 2026#ሰኔ_30
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአልዓዛር እህቶች #የቅዱሳን_ማርያ_እና_የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።
በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።
ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ገድለኛው_አባ_ጌራን
በዚህችም ዕለት ደግሞ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ አባ ጌራን አረፈ። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራውና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።
ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ የነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጐራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው። የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ለአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ። እርሱም ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ አላት።
በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጐኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋር ተኝቶ ኃጢአት እንደሚሠራ ሆነ።
ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ። ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ደንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።
ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ሊቀሰቅሱት ጀመሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።
ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳት_ደናግል_ማርያ_እና_ማርታ (የአልዓዛር እህቶች)
በዚህችም ዕለት ከአራት ቀኖች በኋላ ጌታችን ከመቃብር ያስነሳው የአልዓዛር እህቶች የማርያ እና የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡ በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት ከኃጢአት የተመለሰች': 2ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር - በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል 12:1 ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: (ዮሐ.11)
ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: (ዮሐ. 12:1)
በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
❤🔥1🕊1💯1🏆1
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Jul 06, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 06, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 06, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
መልክዐ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት በግዕዝና በአማርኛ፡ገብረ ሥላሴ
Jul 06, 2026መልክዐ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት በግዕዝና በአማርኛ፡ገብረ ሥላሴ
🕊2💯2❤🔥1👏1
#ሰኔ_29 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቆና ገዳም #ሰባት_ቅዱሳን ሰማዕታት ሆኑ፣ #ቅዱሳን_አባ_ሖር_አባ_ብሶይና_እናታቸው_ይድራ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የንጉሥ ዳዊት ልጅ የኢትዮጵያ…
Jul 05, 2026#ሰኔ_29 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቆና ገዳም #ሰባት_ቅዱሳን ሰማዕታት ሆኑ፣ #ቅዱሳን_አባ_ሖር_አባ_ብሶይና_እናታቸው_ይድራ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የንጉሥ ዳዊት ልጅ የኢትዮጵያ ንጉሥ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ አረፈ፣ ጻድቅ የሆነ ለሮሜ ንጉሥ #ለቅዱስ_ማርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የወሎው #ሰማዕቱ_አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል ፍልሠተ ዐፅማቸው ነው። ✞✞…
ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው። (የዕረፍታቸውን ዕለት ኅዳር ሦስትን ይመለከቷል።) አቡነ ዓምደ ሚካኤል ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው። ወላጆቻቸው…
Jul 05, 2026ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው። (የዕረፍታቸውን ዕለት ኅዳር ሦስትን ይመለከቷል።) አቡነ ዓምደ ሚካኤል ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው። ወላጆቻቸው ገላውዲዮስና ኤልሳቤጥ ሁለቱም በሃይማኖትና በዓለም ገንዘብ የበለጸጉ ናቸው።
ይህንንም ጻድቅ ልጃቸውን የአርባዕቱ እንስሳ በዓል ዕለት ወለዱትና ስሙን ዓምደ ሚካኤል ብለው ጠሩት። ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ለዐፄ በእደ ማርያምና ለዐፄ እስክንድር የሠራዊት አለቃ የነበረ ጻድቅ ነው። በአንድ ዓመቱ ወላጆቹ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይዘውት እንደሄዱ ከወላጆቹ ተለይቶ ጠፍቶ ሳይገኝ ቀረ። መልአክም ከቤተ መቅደስ አግብቶ እየመገበው 3 ቀን አቆይቶታል። በ3ኛው ቀን ቄሱ ሊያጥን ሲገባ በከርሰ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን አገኘውና ወስዶ ለወላጆቹ ሰጣቸው። ባደገም ጊዜ በመመጽወትና አብያተ ክርስቲያናትን በማደስ የሚተጋ ሆነ። ለድኆችም በቅንነት በመፍረድ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ።
ለነገሥታም ገዥ ከሆነ በኋላ በጸሎቱና በበረከቱ በሀገራችን ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ። ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዝተው ይገብሩ ነበር። በበጎ ምግባሩ የቀኑ ዐመፀኞችም በክፋ ተነሡበት። ጻድቁ በመንፈስ አድጎ መንኩሶ በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ነገር ሠሪዎች በሐሰት ወንጅለው ከሰሱት። ንጉሡም እጅግ ስለሚወደው የራራለት ቢሆንም በነገራቸው ባስጨነቁት ጊዜ ወደ ሩቅ አገር አስሮ አጋዘው።
አባታችንም በግፍ ታስረው ሳሉ በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን ወረደላቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ሰማያዊ መና እያመጣ ይመግባቸው ነበር። የጌታችንንም ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ነበር። ነገረ ሠሪዎቹ ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት። በዓመፃቸውም ብዛት ወደ ፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሏቸው። አንድ ጻድቅ መነኩሴ የቅዱስ ዓምደ ሚካኤልን ሥጋ ሦስት ቅዱሳን መላእክት ሲያጥኑ አገኛቸውና ያየውን ለሕዝቡ ተናገረ። በሌላም ጊዜ የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድላቸው ብዙ ቀን የተመለከቱ ብዙ ቅዱሳን ምስክርነታቸውን ሰጡ።
ንጉሡም ይህንን ሁሉ ሲሰማ በአሳቾቹ ልበ ደንዳናነትና ክፋት እጅግ ተጸጽቶ በሞት ቀጣቸው። ቅዱስ ዓምደ ሚካኤልንም በአባቶች መቃብር በክብር አስቀበራቸው። ስማቸውንም በበጎ እንጂ በክፋ ማንም እንዳያነሳቸው በአዋጅ አስነገረ። መታሰቢያም አቆመላቸው። ከዚህም በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ የአባቱን የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው። ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋም ጻድቁ ሲያርፉ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተቀበሩ ቢሆንም ከብዙ ዘመን በኋላ ዐፅማቸውን አፍልሰው በተድባበ ማርያም እንደቀበሯቸው ጽፈዋል።
=>ሰኔ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ንጉሠ ሮም (ጻድቅ: ንጹሕና ገዳማዊ)
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ (ፍልሠቱ)
4."7ቱ" ቅዱሳን መስተጋድላን (አባ አብሲዳ: አባ ኮቶሎስ: አባ አርድማ: አባ ኒኮላስ: አባ ሙሴ: አባ እሴይ: አባ ብሶይ)
5.ቅዱሳን አባ ሖር: አባ ብሶይ: አባ ሖርሳና እናታቸው ቅድስት ይድራ (ሰማዕታት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤1
#ሰኔ_29
Jul 05, 2026#ሰኔ_29
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቆና ገዳም #ሰባት_ቅዱሳን ሰማዕታት ሆኑ፣ #ቅዱሳን_አባ_ሖር_አባ_ብሶይና_እናታቸው_ይድራ በሰማዕትነት ሞቱ፣ የንጉሥ ዳዊት ልጅ የኢትዮጵያ ንጉሥ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ አረፈ፣ ጻድቅ የሆነ ለሮሜ ንጉሥ #ለቅዱስ_ማርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የወሎው #ሰማዕቱ_አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል ፍልሠተ ዐፅማቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#7ቱ_ቅዱሳን
ሰኔ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቆና ገዳም ሰባት መስተጋድላን ሰማዕታት ሆኑ። እሊህም አባ አብሲዳ፣ አባ ኮቶሎስ፣ አባ አርድማ፣ አባ ሙሴ ፣ አባ እሴይ፣ አባ ኒኮላስና አባ ብሶይ ናቸው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጾ እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ግለጡ።
ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ሊሔዱ ተነሡ መርከብንም አገኙ በመርከቧም ውስጥ አምስቱን መስተጋድላን አገኙአቸውና ከእነርሱ ጋር ተስማሙ ወደ መኰንኑም ደርሰው በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመኑ።
መኰንኑም ከእርሳቸው አንዱን ስለ ሀገራቸው ጠየቀው እርሱም ቆና ከሚባል አገር እንደሆኑ አስረዳው መኰንኑም ያሥሩዋቸው ዘንድ አዘዘ። ከዚህም በኋላ ደግሞ ከእሥር ቤት አውጥተው ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩአቸው ዘንድ ደግሞም በአንገቶቻቸው ከባድ ደንጊያዎችን አንጠልጥለው እንዲአሥሩዋቸው አዘዘ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በውህኒ ቤት ውስጥ ተገለጠላቸው አጽናናቸውም ቃል ኪዳንም ገባላቸው። ከዚህ በኋላ ንጉሥ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላካቸው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው።
ከዚህም በኋላ ዝፍትና ድኝ በተመሉ ከሁለት የብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩአቸው ነበልባሉም ሃያ ክንድ ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ ከታች እሳትን አነደዱባቸው ከምጣዶችም ውስጥ አውጥተው በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩአቸው ጌታችንም ዳግመኛ ተገልጾ ያለ ምንም ጉዳት አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው መቶ ሠላሳ ሰዎች በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
ከዚህም በኋላ አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ እነርሱም አጵሎን የሚሉትን ጣዖት በወንበር እንደ ተቀመጠ አምጥቶ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው እነርሱ ግን በእግሮቻቸው ረገጡትና ከመንበሩ ወድቆ ተሰበረ። መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እግሮቻቸውንም እንዲቆርጡ አዘዘ የቅዱስ ቀሲስ አብሲዳንን ግን ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ምስክርነቱን ፈጸመ እንዲሁ ደግሞ እሊያ አምስቱንም ራሶቻቸውን ቆረጡ ቅዱስ ኮቶሎስን ግን በእሳት አቃጠሉት ሁሉም የሰማዕትነትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጁ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አባ_ሖር_አባ_ብሶይ_እናታቸው_ቅድስት_ይድራ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ደግሞ ቅዱሳን አባ ሖር፣ አባ ብሶይና እናታቸው ይድራ ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ የሆነ አባ ሖርሳም በሰማዕትነት ሞቱ። እሊህም ወደ እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታመኑ መኰንኑም አባ ብሶይን ይዘው ቀኝ እጁንም አሥረው በከተማዎች ሁሉ በበሬዎች እንዲጐትቱት አዘዘ።
ከዚህም በኋላ የተዘረጉ ብረቶችን በእሳት አግለው በሥጋው ውስጥ አደረጉ የግራ እጁንም ቆረጡ እርሳስም አቅልጠው በአፉ ጨመሩ ጊንጦችና እባቦች ወደ ተከማቹበት ውስጥ ጣሉት እነርሱ ግን ከቶ አልቀረቡትም።
ከዚህም በኋላ በብረት በትሮች ይደበድቡት ጀመር እርሱም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ ብሎ ጮኸ ጌታችንም አጸናው እንደቀድሞውም ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ አስነሣው።
ከዚህም በኋላ እናቱ ወደርሱ መጥታ አረጋጋችው በመጋደሉም ደስ ተሰኘችበት። ስለ እርሷም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ወደ እርሱ አስቀርቦ እያስፈራራ ለአማልክት ሠዊ አላት። እርሷ ግን አልፈራችውም ትእዛዙንም አልሰማችም የብረት በትሮችንም አግለው በጎኖቿ ውስጥ እንዲአደርጉ አዘዘ ይህንም በእርስዋ ላይ በአደረጉ ጊዜ ደስ ብሏት ዘመረች ስለ ቅዱስ ስሙም መከራ እንድትቀበል ያደረጋት እግዚአብሔርን አመሰገነችው ከዚህም በኋላ ነፍሷን ሰጠች የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀዳጀች።
ቅዱስ አባ ሖርንም ከቅባትና ከተቀመመ የነዳጅ ቅመም ጋራ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት እርሱም ያለ ሕማም ሁኖ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር ይህንንም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም እጅግ አደነቀ ደነገጠም። ንጉሡ ግን ተቆጣ በእጁም ጦር እንደያዘ ወደ ብረት ምጣዱ ሒዶ ቅዱስ ሖርን ወጋው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እንዲሁም ወንድሙ አባ ብሶይን ብዙ ሥቃይን ካሠቃዩት በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት። ሁሉም በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ጻድቅ
በዚችም ቀን የንጉሥ ዳዊት ልጅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቴዎድሮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ በዕውቀትና በተግሣጽ አደገ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የተማረ ደግሞም ቀስት ማፈናጠርንና ፈረስ ግልቢያን ተማረ ኃይል ያለውም ብርቱ ሰው ሆነ።
ከታናሽነቱም ጀምሮ በእግዚአብሔር ፍቅር ታሠረ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር። አብያተ ክርስቲያንንም እጅ መንሻ ከመያዝ ጋራ ይጐበኝ ነበረ በጸሎትና በጾምም ይጋደል ነበረ። ካንዲት ሴት በቀር አላገባም በማንም ላይ ዐመፅና ግፍ ከቶ አልሠራም።
ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ በአሰበ ጊዜ አባ ማርቆስን አማከረው እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ያውቅ ነበረና ክፍልህ አይደለም አለው። ከዚህም በኋላ ባረፈ ጊዜ በክረምት ወራት በድኑን ሲወስዱ ሞልቶ የነበረው ወንዝ ወዲያና ወዲህ ተከፍሎ ተሻገሩ በቀበሩበትም ቦታ ሕይወትነት ያለው ውኃ መነጨ እስከ ዛሬም አለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ማርቆስ_ንጉሠ_ሮም
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ንጹሕ ጻድቅ ለሆነ ለሮሜ ንጉሥ ለማርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ በድንግልናው አምስት ዓመት ነገሠ ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ።
እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስትን እንዲአገባ መኳንንቱ አስገደዱት እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቁሞ ጸለየ እመቤቴ ሆይ ላንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደ ምሔድበት ምሪኝ አላት። እርሷም ወደ ቶርማቅ ተራራ ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋራ ይኑር አለችው።
ከዚህም በኋላ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕር ወደብም በደረሰ ጊዜ ያለ መርከብ ተሻግሮ ወደ ቶርማቅ ተራራ ደረሰ ያም ቦታ ደረቅ ነበረ ከአጋንንት ጋራም እየተጋደለ በውስጡ ስልሳ ዓመት ኖረ። በአረፈ ጊዜም መላእክት በክብር ቀበሩት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው የነበሩት የወሎው ሰማዕቱ አቡነ ዓምደ ሚካኤል ፍልሠተ ዐፅማቸው ነው። ጻድቁ ኅዳር ሦስት በሰማዕትነት ካረፉ በኋላ መጀመሪያ በንጉሥ እስክንድር ዘመነ መንግሥት ወደ አባቶቹ መቃብር ዳግመኛም በንጉሥ ልብነ ድንግል ዘመን በዐረፉ በ40 ዓመታቸው ፈለሰ።
❤1
💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
Jul 04, 2026💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
✝ውዳሴ ይደሉ ለያዕቆብ እልበረዲ፤
Jul 04, 2026✝ውዳሴ ይደሉ ለያዕቆብ እልበረዲ፤
ዘመተረ መናፍቃነ ወአጋንንተ ሰዳዲ፤
አቄርብ አምኃ ለቴዎዶስዮስ ዓዲ፤
ምሥጢረ መጻሕፍት ዘከሠተ በቃሉ ዐዋዲ!
❤2🥰2🕊2🙏1
#ሰኔ_28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ስምንት በዚች ቀን የእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው #ቅዱስ_አባ_ቴዎዶስዮስ አረፈ፣ የምሥራቁን ኮከብ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ መታቢያው ነው፡፡ ✞…
Jul 04, 2026#ሰኔ_28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ስምንት በዚች ቀን የእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው #ቅዱስ_አባ_ቴዎዶስዮስ አረፈ፣ የምሥራቁን ኮከብ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ መታቢያው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_ቴዎዶስዮስ ሰኔ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ የሆነው ቅዱስ አባ ቴዎዶስዮስ የእስክንድርያ…
❤2💯2🙏1🕊1
ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔዓለም አርመኖቹን ስቦ በ490ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ:: በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን : በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስን አስነስቷል:: ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ ንግሥት…
Jul 04, 2026ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔዓለም አርመኖቹን ስቦ በ490ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ:: በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን : በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስን አስነስቷል:: ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ ንግሥት ታኦድራን ማርኯል:: በእነዚህ ቅዱሳን ትጋት የለመለመችው ተዋሕዶ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ያለ አርበኛን ግን ያገኘችው በጭንቅ ቀን ነበር::
ሰው መሆን ሰው በጠፋባቸው ቀናት ነውና : በግብጽና በቁስጥንጥንያ በትምህርትና ምናኔ ላይ የነበረው ቅዱሱ ታጥቆ ለአገልግሎት የተሰለፈው በ530ዎቹ አካባቢ ነበር::
ጊዜው ወዲህ አንበሳው ቅዱስ ሳዊሮስ ከሶርያ ወደ ግብጽ እንደተሰደደ ያረፈበት ነበር:: ወዲያ ደግሞ ሊቁ አባ ቴዎዶስዮስ የግብጹ ለግዞት የተዳረገበት ነበርና የተዋሕዶ ምዕመናን ያለ እረኛ ተቅበዘበዙ:: የቤተ መንግስቱ ተጽዕኖ ደግሞ 2 ባሕርይ በማይሉት ላይ እሥራትና ግድያን ወደ ማወጅ ተሸጋግሯልና የምእመናን ቁጥር እጅጉን መመንመኑ ቀጠለ::
ይህ ዕረፍት የነሳው ቅዱስ ያዕቆብ በበኩሉ ነገሩን በዝምታ ሊያልፈው አልወደደምና አገልግሎቱን አሰፋ:: ሌሊቱን በጸሎት ያድራል:: ቀን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማስተማር ባይችል በየቦታው እየዞረ ያስተምር ነበር::
ከትምህርቱ ጣዕምና ከመልእክቱ ሥምረት የተነሳም ምእመናን እንደገና ተነቃቁ:: እርሱም ከግብጽ እስከ ሶርያ : አልፎም እስከ ቁስጥንጥንያ ድረስ ያለ ዕረፍት ሲሰብክ 40 ዘመናትን አሳለፈ:: በተለይ አዲስ አማኞችን ያጠምቅ ዘንድ በእሥረኛው ቅዱስ ቴዎዳስዮስ ኤዺስ ቆዾስነትን ተቀብሏል::
የሶርያ (አንጾኪያ) የፕትርክና መንበሩ ክፍት ሆኖ እርሱን ቢጠብቀውም እርሱ ግን የዚህ (የስልጣን) ፈላጊ አልነበረምና ሌሎች እንዲሾሙበት አድርጉዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ በስብከት አገልግሎት ምሥራቁን ዓለም ሲያበራ የተባበሩት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም ያሳለፈው ድካምና መከራ ግን ተወዳዳሪ አልነበረውም:: በተለይ የወቅቱ የአንጾኪያ ኃያላን መኩዋንንትና ሹመኛ መናፍቃን ብዙ አሳደውታል::
እርሱ ግን በጥበብና በፈሊጥ እዚያው ደጃቸው ላይ የነበሩ ምዕመናንን በእረኝነት ጠብቁአል:: ለዚህ ሲባልም ራሱን እየቀያየረ የመሣፍንቱን አጥሮችና ቅጥሮች አልፏል:: ለቤተ ክርስቲያን ክብርም እንደ እብድ : እንደ ሴትም መስሎ የወንጌልን ዘር ዘርቷል::
ከብዙ ፈተናና አገልግሎት በሁዋላም በተወለደ በ78 ዓመቱ (በ578 ዓ/ም) ዐርፎ በክብር ተቀብሯል:: ትልቁ መታሰቢያው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ምዕመኑ "ያዕቆባውያን" መባላቸው ሲሆን እኛ ደግሞ በአንገታችን ላይ እንድናስራት ባስተማረን ማዕተብ (ማኅተም) ዘወትር እናስበዋለን:: ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብን በአንገት ላይ ስለ ማሰር ያስተማረ እርሱ ነውና::
=>ሰኔ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ
3.ቅዱስ ባስልዮስ
4.ቅዱስ ባሊዲስ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ዲያቆን_ዮዳኖስ_አበበ)
❤🔥2🙏2💯2🕊1
#ሰኔ_28
Jul 04, 2026#ሰኔ_28
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ስምንት በዚች ቀን የእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው #ቅዱስ_አባ_ቴዎዶስዮስ አረፈ፣ የምሥራቁን ኮከብ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ መታቢያው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ቴዎዶስዮስ
ሰኔ ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ የሆነው ቅዱስ አባ ቴዎዶስዮስ የእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ። በዚህም ቅዱስ በስሙ በግብጽ ምድር ውስጥ ምእመናን ቴዎዶስዮሳውያን ተብለው ተጠርተውበታል።
ይህም የሆነው እንዲህ ነው ሊቀ ጵጵስና ከተሾመ በኋላ ክፉዎች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሥተው በንጉሥ ምክር ከመንበረ ሢመቱ አሳደዱት በእርሱ ፈንታም አስቀድሞ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዲያቆናት የነበረ ስሙ አቃቅያኖስ የሚባለውን አንድ ሰው ሾሙ እርሱም ለአባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ጵጵስና እንዲገባው ከፈረሙት ቁጥር ውስጥ ነበረ።
ይህም አባት ወደ ግርማኖስ አገር ሒዶ ሦስት ወሮች ኖረ በዚያም ወራት በግብጽ አገር ንቡረ እድ አባ ሳዊሮስ ነበረ እርሱም በአባቶቻችን ሐዋርያት እንዲሁም በአትናቴዎስና በዮሐንስ አፈወርቅ የደረሰባቸውን መከራ እያስታወሰ ያጽናናቸው ነበር።
ከዚያም ተነሥቶ መሊግ ወደሚባል አገር ሔደ በዚያም ሁለት ዓመት ተቀመጠ። የእስክንድርያ ከተማ ሰዎችም የጠባቂያቸው የቴዎዶስዮስን መመለስ ሽተው በእስክንድርያው መኰንን ላይ ተነሡበት መኰንኑም ወደ መንበረ ሢመቱ መለሰው አቃቅያኖስንም አባረሩት።
ይህም ነገር በንጉሥ ዮስጣቲያኖስና አምላክን በምትወድ በንግሥት ታዖድራ ዘንድ ተሰማ ንግሥቲቱም አስቀድሞ የተሾመው በሹመት ወንበሩ ይቀመጥ ብላ ጻፈች።
ሃምሳ ስምንት ካህናትም ጉባኤ አደረጉ አስቀድሞ የተሾመ አባ ቴዎዶስዮስ ነው ሲሉም ጻፉ። ያን ጊዜም አቃቅያኖስ በሕዝብ ፊት ቁሞ ክፉዎች ሰዎች ስለ አስገደዱኝ ይህን ሥራ ለመሥራት ሕግን ተላልፌአለሁ አለ። ከዚህም በኋላ አቃቅዮስን ከውግዘቱ እንዲፈታው ነገር ግን ክህነትም ሆነ ሊቀ ዲቁና ለዘለዓለሙ እንዳይኖረው ሕዝቡ አባ ቴዎዶስዮስን ለመኑት። አቃቅያኖስም አዎ እንዲሁ ይሁን አለ ይህም አባት ከግዝቱ ፈታው።
ሃይማኖቱን ያጠፋ ንጉሡ ግን በከፋች ሃይማኖቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ጋራ የሚስማማ መስሎት በእስክንድርያ ወዳሉ መኳንንቶቹ እንዲህ ብሎ ጻፈ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ በሃይማኖት ከእኛ ጋራ የሚስማማ ከሆነ ሹመት ይጨመርለታል። ለእስክንድርያ ከተማ ገዥ ይሆናል። ይህ ካልሆነ ግን ከሹመቱ ይሻር።
ይህም አባት ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ ሰይጣን በበረሀ ጌታችንን ብትሰግድልኝ የዓለም መንግሥታትንና ክብራቸውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ያን ጊዜም ይህ አባ ቴዎዶስዮስ ተነሥቶ ከእስክንድርያ ወጣ ወደ ላይኛው ግብጽም ሔደ በዚያም ሕዝቡን እያስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ጥቂት ቀኖች ኖረ።
ንጉሡም አባ ቴዎዶስዮስ ከእስክንድርያ ከተማ እንደ ወጣ በሰማ ጊዜ እየሸነገለው ወደ እርሱ መልእክት ላከ እንዲህም አለው እኔ ከአንተ ጋራ ልነጋገር ከአንተም ልባረክ እንድትመክረኝም እሻለሁ።
ከዚህም በኋላ ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ ሔደ የጳጳሳት አለቆችና ሕዝቡ ሁሉ ሠራዊቱም ተቀበሉት በከፍተኛ ወንበርም ላይ አስቀመጡት። እርስ በርሳቸውም ስለ ሃይማኖት ተከራከሩ ንጉሡም አብዝቶ ሲሸነግለውና ሲአባብለው ሰነበተ ቅዱስ አባት ቴዎዶስዮስም ከቅዱሳት መጻሕፍት በመጥቀስ ይረታው ነበረ።
ከእርሱም ጋራ ባልተስማማ ጊዜ ከመንበረ ሢመቱ ወደ ላይኛው ግብጽ አሳደደው። በእርሱም ፈንታ ጳውሎስ የሚባለውን ሰው ሾመው። ጳውሎስም ወደ እስክንድርያ ከተማ በመጣ ጊዜ ሕዝቡ አልተቀበሉትም ዓመት ሙሉም ኖረ በእጁም ማንም ቍርባንን አልተቀበለም።
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ ለመናፍቁ ጳውሎስ እስከሚታዘዙ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት እንደዘጉ አዘዘ። ምእመናንም ከእስክንድርያ በመውጣት ወደ ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቆዝሞስና ድምያኖስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዱ ነበር ካህናቱም በዚያ እየቀደሱ ያቈርቧቸው ነበር የአገር ልጆችንም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቋቸው ነበር።
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲከፍቱላቸው አዘዘ አባ ቴዎዶስዮስም ሰምቶ ንጉሡ እንዳያስታቸው ፈራ ማጽናኛ ቃልን የተመላች መልእክትም ጽፎ በቀናች ሃይማኖት እያበረታታቸው ወደ ምእመናን ላካት እንዲህም አላቸው ለዚያ ከሀዲ ጳውሎስ እንዳትታዘዙ ተጠበቁ። ይህም አባት ሃያ ስምንት ዓመት በስደት ኖረ። መላው የሹመቱ ዘመን ሠላሳ ሁለት ነበር። ይኸውም በእስክንድርያ አራት ዓመት በስደትም ሃያ ስምንት ዓመት ነው።
ይህም አባት ብዙ ድርሳናትን ደርሷል ምእመናንም በያዕቆብ ዘመን ያዕቆባውያን እንደ ተባሉ በስሙ ቴዎዶስዮሳውያን እየተባሉ ሲጠሩ ኖሩ። መልካም ጉዞውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ
በዚህችም ዕለት የምሥራቁን ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ መታሰቢያው ነው፡፡ "ያዕቆብ" ለሚል ስም ትርጉምን የሰጡ አበው በ2 መንገድ ያትቱታል::
1.አኃዜ ሰኮና:- ነገሩ ከወልደ ይስሐቅ ወርብቃው ርዕሰ አበው ያዕቆብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አበው ግን ለትህትና ይተረጉሙታል::
2.አእቃጺ / አሰናካይ:- ነገሩ ስድብ (አሉታዊ) ይምሰል እንጂ በዚህ ስም የተጠሩ አበው ሁሉ ለአጋንንትና ለመናፍቃን ትልቅ መሰናክል ሆነውባቸው ኑረዋልና አባባሉ ምስጋና እንጂ ነቀፋን አይወክልም::
የ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ምሥራቃዊ ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብም ለመለካዊ መናፍቃንና ለተዋሕዶ ተገዳዳሪዎች ትልቅ መሰናክል ሆኖባቸዋል:: የቀናችውን ቀርነ ሃይማኖትንም አጽንቷል::
ብዙ ጊዜ "ዘ"-እልበረዲ መባሉን ይዘው በ"ዘ" ምክንያት እልበረዲን እንደ ሃገር የቆጠሯት አልጠፉም:: በረከታቸው ይድረሰንና ትጉሑ ዻዻስ አቡነ ጐርጐርዮስ ካልዕ ግን ለዚሁ
መላምት "የለም!" ባይ ናቸው::
'የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ' በተሰኝ ተወዳጅ መጽሐፋቸው "እል-በረዲ" ማለትን በዓረብኛ ከሠጋር በቅሎ : ከሥሙር ሠረገላ ጋር አነጻጽረው አስቀምጠውታል:: ለምን ቢባል - እንደ ሠረገላ በተፋጠነ አገልግሎቱ ወዳጅንም ጠላትንም አስደምሟልና::
ቅዱስ ያዕቆብ የተወለደው በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ (በ500 አካባቢ) ሲሆን ያረፈው ደግሞ በ578 ዓ/ም እንደሆነ ይታመናል:: ነገሩን ልብ ስንለው ቅዱስ ማኅሌታይ ያሬድን - ወዲህ በዘመን : ወዲያ ደግሞ በአገልግሎት ይመስለዋል:: እርግጥ ነው ለውለታው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ስትባል የእኛዋስ ምናለ "ያሬዳዊት" ብትባል የሚል ቁጭትን ያመጣል::
ጊዜው (5ኛውና 6ኛው መቶ ክ/ዘመን) ወዲህ ወርቃማ : ወዲያ ደግሞ ጨለማ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ዘመን ነበር:: በብርሃንነቱ በተለይ በምሥራቁ ዓለም ያበሩ አበው እነ ያዕቆብ ዘስሩግ : ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ : ያዕቆብ ዘእልበረዲን የመሰሉ አበው ተገኝተውበታል:: ሲያልፍ ደግሞ ዘይኑንና አንስጣስዮስን የመሰሉ ደጋግ ነገሥታት በዘመኑ መነሳታቸውን እናስባለን::
በተቃራኒው ግን ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ለ2 የተከፈለችበት : መለካውያን የነገሥታቱ ደጀን አላቸውና ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከሥሯ ነቅሎ ለማጥፋት ብዙ የሞከሩበት ዘመን ነውና ጨለማነቱ ይጐላብናል::
በእርግጥም ከመርቅያን እስከ ዮስጢኖስ ዳግማዊ ዘመን ድረስ ለ100 ዓመታት መለካውያኑ የልዮን ልጆች 2 ባሕርይ ማለትን ሊያሰፉ : ተዋሕዶንም ሊያጠፉ የከፈቱት ዘመቻ ሊሳካ ጫፍ የደረሰ ይመስል ነበር::
❤🔥2🥰2💯2🙏1
ቅዱሳን (Saints)
Jul 03, 2026በዚህችም ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ልደቱ ነው፡፡ ዕረፍቱ ግን ሰኔ 7 ነው እየተባለም በሊቃውንት ይነገራል። የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሀገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት ሀገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ …
Jul 03, 2026በዚህችም ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ልደቱ ነው፡፡ ዕረፍቱ ግን ሰኔ 7 ነው እየተባለም በሊቃውንት ይነገራል። የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሀገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት ሀገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል ሀገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በሦስት ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። ይኸውም ‹‹ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ፣ ከጌታችን ጋር ስገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ›› እያለ ያለቅስ ነበር። አቡነ ያዕቆብ በ12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና ‹‹በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም›› አላቸው። ያንጊዜም ሕዝቡና ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹‹እግዚአብሔር በዚህ ሕጻን ላይ አድሮ ገሠጸን›› እያሉ ንስሓ ገብተዋል። ቅዱስ ያዕቆብ በነበረበት ዘመን በሮማው መናፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ ‹‹የውሾች ጉባኤ›› ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገዛቸውን ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኝ ብሎ ‹‹እኔን ምሰል›› በማለት ለቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። አቡነ ያዕቆብም ‹‹ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፣ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሙን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው›› በማለት መልሱን ጽፎለታል። ልዮንም እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበት አውግዞና እረግሞ ለይቶታል። ንጽሕናውና ቅድስናው ‹‹እንደ መላእክት ነው›› የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው።
† ሰኔ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት (ዘሰንደላት)
3.ቅዱስ አልዓዛር ነዳይ (በነዌ ደጅ የወደቀ : ቀጥሎ ደግሞ በአብርሃም እቅፍ ውስጥ የተገኘ ጻድቅ - ሉቃ. 16:19)
4.ቅዱስ ማማስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤1🥰1🕊1💯1
#ሰኔ_27
Jul 03, 2026#ሰኔ_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ሰባት በዚች ቀን ከተመረጡ አርድእት ውስጥ #ሐዋርያው_ሐናንያ አረፈ #ቅዱስ_ቶማስ_ሰንደላት በሰማዕትነት ሞተ፣ #የድሀው_አልዓዛር መታሰቢያው ነው፣ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘስሩግ ልደቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐናንያ_ሐዋርያ
ሰኔ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን ከተመረጡ አርድእት ውስጥ ሐዋርያው ሐናንያ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ሐዋርያት በደማስቆ ከተማ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በውስጧም ሕይወት ሰጭ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ዳግመኛም በቤተ ገብርኤል ውስጥ ሰብኮ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት ብዙዎቹን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው እውነተኛውንም የሃይማኖት ብርሃን አበራላቸው።
ይህም ሐናንያ ሐዋርያው ጳውሎስን ይቅር ባይ ጌታችን በቸርነቱ ከክህደቱ በጠራውና ምርጥ ዕቃ በአደረገው ጊዜ ያጠመቀው ነው እጁንም በራሱ ላይና በዐይኖቹ ላይ ጭኖ ያዳነው እርሱ ነው።
ጌታችንም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ በስብከቱም ብዙዎች አሕዛብ አመኑ ከአይሁድም ብዙዎቹን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸው።
ከዚህም በኋላ ዐመፀኛው መኰንን ሉክያኖስ ይዞ ታላቅና አስጨናቂ ሥቃይን አሠቃየው ጐኖቹንም ሠንጥቆ በእሳት መብራቶች አቃጠለው። ከዚህም በኋላ ከከተማው አውጥተው በደንጊያ እንዲወግሩት አዘዘ በዚያም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነፍሱን ሰጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ሰማዕት_ዘሰንደላት
በዚህችም ቀን ሰንደላት ከሚባል አገር ቅዱስ ቶማስ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱም ጋራ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ ።
ይህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ አንድ ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በበረሀ እሪያዎችን ሲጠብቅ ተገለጸለት ወደ መኰንኑ ሔዶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢያሱስ ክርስቶስ ስም ይታመን ዘንድ አዘዘው። ያን ጊዜም ተነሥቶ የገመድ አለንጋ ይዞ ብቻውን ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም ታመነ።
መኰንኑም ለአማልክት ሠዋ አለው ጸሐፊውም ሊያደርገው ቃል ኪዳን ገባለት ቅዱስ ቶማስም ተቆጥቶ ያቺን አለንጋ አውጥቶ መኰንኑን ብዙ ግርፋት ገረፈው የመኰንኑ ሎሌዎችም ይዘው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በብረት መጋዝ ሠነጠቁ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ርዳታን ለመነ ወዲያውኑም መልአኩን ልኮ አዳነው።
ከዚህ በኋላ በእሥር ቤት አሠሩት የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ስለ ታመመው ልጁ ለመነው እርሱም ያንን የገመድ አለንጋ ሰጠውና ይህን አለንጋ በልጅህ ላይ አኑር አለው እንዲሁም አደረገ። ያን ጊዜም ልጁ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ።
መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አቅርቦ ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱስ ቶማስም በፊትህ ዕሠዋ ዘንድ ና እንሒድ ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ዕውነት መስሎት ደስ አለው ወደ ጣዖቶቹ ቤትም ወሰደው ያን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ጣዖታቱን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ። ወዲያውኑ ሁሉም ጣዖታት ተሰባበረ ሰይጣኑም በመኰንኑ ላይ ተቀመጠ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ እስከሚታመን ድረስ አነቀው። አሕዛብም ይህንን ድንቅ ነገር አይተው እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉም ጮኹ በእርሱም አመኑ።
ያላመኑት ግን በጨለማ ቤት ውስጥ አሠሩት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ከብዙ ሥቃይም የተነሣ ከአፉ ደም እየፈሰሰ ዐሥራ አምስት ቀን በዚያ ተቀመጠ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ ፈወሰው።
አንዲት ሴት ዕውር ልጅ ነበራት ከዚያም ደም ወስዳ የልጅዋን ዐይን አስነካችው ወዲያውኑም አየ። ቅዱስ ቶማስንም ከወህኒ ቤት አውጥተው ሴት አንበሳ ሰደዱበት ወደርሱም በደረሰች ጊዜ እግሮቹን ላሰች ሰገደችለትም ።
ዳግመኛም በብረት መንደልቶ አፉ ላይ ደበደቡት በዚያን ጊዜ በሥቃይ ውስጥ ከእርሱ ጋራ ከበንደላ አገር ቅዱስ በብኑዳ ከበልኪም አገር ቅዱስ ሙሴ ነበሩ። እርስ በርሳቸው አንዱ አንዱን ያጽናናው ነበር።
ከዚህም በኋላ ቅባትና የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በቅዱስ ቶማስ ራስ ላይ ደፉት ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። እንደገናም አባለ ዘሩን ቈርጠው በአውድማ ውስጥ አበራዩት ደግመውም ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ ላይ ሰቅለው አሠቃዩት። ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመው ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ወደ እንዴናው ከተማ ሊወስደው ይዞት ተነሣ ጣው ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ የቅዱስ ቶማስን ራስ ቆረጡት በዚያም ምስክርነቱን ፈጸመ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ከእርሱ ጋራ መከራ ተቀብለው የሞቱ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶችም እርሱ ሥቃይ በተቀበለበት ወራት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ድሀው_አልዓዛር
በዚህች ቀን የድሀው አልዓዛር መታሰቢያው ነው፡፡ ይኸኛው አልዓዛር በሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተነገረው ባለጸጋው ነዌ ድሀው አልዓዛር በደጁ ወድቆ ትራፊውን ፍርፋሪ ይመኝ የነበረ ውሾች ቁስሉን እስኪልሱለት ድረስ በባጸጋው ዘንድ የተናቀና የወደቀ ነበር። ሁለቱም ሲሞቱ ግን ባለጸጋው ነዌ በሲኦል ሆኖ እየተሠቃየ ድሀው አልዓዛርን በአብርሃም እቅፍ አይቶታል። ቅዱስ አልዓዛር በዚህች ዕለት በዓመታዊ በዓሉ ታስቦ ይውላል። ሙሉ ታሪኩ በሉቃስ ወንጌል 16፡19-31 ላይ እንዲህ ተቀምጧል። ‹‹ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፣ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር። አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፣ ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፣ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር። ድሀውም ሞተ፣ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፣ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ። በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። እርሱም እየጮኸ አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ፣ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ። አብርሃም ግን (ልጄ ሆይ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሠቃያለህ። ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፣ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል› አለ። እርሱም ‹እንኪያስ አባት ሆይ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና። እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው› አለ። አብርሃም ግን ‹ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ› አለው። እርሱም አይደለም፣ አብርሃም አባት ሆይ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ› አለ። አብርሃምም ‹ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም› አለው።›› ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ።
🥰1🕊1💯1
💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
Jul 03, 2026💬 ይህን ያውቁ ኖሯል ❓️❓
🥰4😍1😘1
እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው በሰላም አሸጋገረን አሜን።
Jul 02, 2026እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው በሰላም አሸጋገረን አሜን።
🌺 እንኳን አደረሳችሁ!
💯1
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
Jul 02, 2026🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው
1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 02, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
ቅዱሳን (Saints)
Jul 02, 2026#ሰኔ_26
Jul 02, 2026#ሰኔ_26
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ #የመላእክት_አለቃ_የቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው፣ የታላቁ ነቢይና መስፍን የነዌ ልጅ #የቅዱስ_ኢያሱ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል
ሰኔ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው።
በውስጧም ከቤተ ክርስቲያንዋ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር። የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ_ወመስፍን
በዚህችም ቀን የታላቁ ነቢይና መስፍን የነቢያት አለቃ የሙሴ ደቀ መዝሙር የነዌ ልጅ የኢያሱ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ከታናሽነቱ ጀምሮ ለሙሴ አንገቱን ዝቅ አድርጎ የሚታዘዝ ፍጹም ትሑት ሆነ ስለዚህም በሙሴ ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ አደረበት። ነቢዩ ሙሴም ከአረፈ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤልን ሕዝብ ተረከባችው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው ከሙሴ ጋራ እንደኖርሁ ከአንተም ጋራ እኖራለሁ ጽና በርታ ለባለሟሌ ሙሴ ያዘዝሁትን ሕጌን ጠብቅ ከእርሱም ፈቀቅ አትበል ሕጉንም ትጠብቀውና በሱም ትጸና ዘንድ በውስጡም የተጻፈውን ታደርገው ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንደበትህ ማንበብን አያቋርጥ።
የኢያሱም ልቡ ጸና ሰላዮችንም ወደ ኢያሪኮ ላከ ሀገሪቱንም አይተው ሲመለሱ የኢያሪኮ ሰዎች አዩአቸው ሰላዮችም እንደሆኑ አውቀው ተከተሏቸው። እነርሱም ረዓብ በሚሏት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሸሸጉ እርሷም ሠወረቻቸው እነርሱም በሚመጡ ጊዜ ከቤተሰቦቿና ከዘመዶቿ ጋራ እንደሚያድኗት ቃል ገቡላት።
በደኅናም ሸኘቻቸው። ከዚህም በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገረ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ተሸክመው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ቆመው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እስከሚሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ እግዚአብሔር እንደ ግድግዳ አቁሞት ነበርና።
ከዚህም በኋላ ደግሞ በግንብ የተከበበች ኢያሪኮን ሰባት ቀን ዞራት ከእርሱም ጋራ የልዑል ታቦተ ሕጉ ነበረች ቅጽሮቿንም አፈረሰ በውስጧም የሚኖሩ አሕዛብን ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር ገደለ ሁሉንም አጠፋቸው።
አሕዛብ ሁሉ የእስራኤልን ልጆች ፈሩአቸው ከመፍራታቸውም ጽናት የተነሣ የገባዖን ሰዎች ተንኰል አደረጉ ስንቃቸውን ሰንቀውና አዘጋጅተው መጡ አሮጌ አቁማዶቻቸውን ያረጁና የተቀደዱ የተጠቀሙም የወይን ረዋቶችን በትክሻቸው ተሸከሙ። ጫማቸውም ያረጀና የተተበተበ ነበር ልብሳቸውም በላያቸው ያረጀ ነበር። ለስንቅም የያዙት እንጀራ የደረቀና የሻገተ ነበረ።
ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ወደ ገልገላ መጥተው እኛ ከሩቅ አገር መጥተናል አሁንም ለእኛ ማሉልን አሏቸው። የእስራኤልም ልጆች ኤዎያውያንን ከእናንተ ጋራ እንዴት መሐላን እንማማላለን አሁንም በአቅራቢያችን ትኖሩ እንደሆነ ተጠንቀቁ አሏቸው። ኢያሱንም እኛ ከሩቅ አገር የመጣን ባሮችህ ነን አሉት እርሱም ከወዴት ናችሁ ከወዴትስ አገር መጣችሁ አላቸው። እነርሱም እኛ ባሮችህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ አገር መጣን በግብጻውያን ያደረገውን ሁሉ በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥታትም ያደረገውን ሁሉ ሰምተን መጥተናል አሉት።
የአገራችን ሰዎች ሁሉና አለቆቻችን ለመንገድ ስንቅ ያዙ ትቀበሏቸውም ዘንድ ሒዱ እኛ ባሮቻችሁ ነን አሁንም ለእኛ ማሉልን በሉአቸው አሉን። እነሆ ወደእናንተ እንመጣ ዘንድ ከቤታችን በወጣንበት ቀን ይህ እንጀራችን ትኩስ ነበር አሁን ግን ሻግቷል ደርቋልም ይህም የወይን ረዋት አዲስ ሳለ መላንበት አሁን ግን ተራቁቷል አርጅቶም ተቀድዷል መንገዳችን እጅግ የራቀ ነውና ይህም ልብሳችን ይህም ጫማችን አርጅቷል አሏቸው።
መኳንንቱም ስንቃቸውን ተቀብለው አዩ የእግዚአብሔርንም ቃል አልጠየቁም ኢያሱም ከነሱ ጋራ ሰላምን አደረገ ሊያድናቸውም ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ የሕዝቡም አለቆች ማሉላቸው። ከሦስት ቀን በኋላም እስራኤል ከቅርብ እንደሆኑ ሰሙ። ኢያሱም በቅርብ እንደሆኑ በሰማ ጊዜ በሽንገላ ለምን ወደእኛ መጣችሁ አሁንም ለእግዚአብሔር ቤትና ለእኛ ባሮች ትሆናላችሁ አላቸው።
የአሞሬዎን ነገሥታትም የገባዖን ሰዎች ሔደው ለእስራኤልና ለኢያሱ እንደ ተገዙ በሰሙ ጊዜ እነዚህ አምስቱ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የኢያሪሞት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥ፣ የአዶላም ንጉሥ ተሰብስበው ዘመቱ መጥተውም ገባዖንን ከበቡአት ሊዋጉም ጀመሩ። የገባዖን ሰዎችም በገልገላ ውስጥ ወደ እስራኤል ሰፈር ወደ ኢያሱ ልከው ባሮችህን ለመርዳት እጅህ አትስነፍ ከተራሮች ላይ የሚኖሩ የአሞሬዎን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ወደ እኛ መጥተህ ርዳን ፈጥነህ አድነንም አሉ።
ኢያሱም ከገልገላ ወጣ ሰልፈኞችም የሆኑ ሕዝብ ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው በእጅህ እጥላቸዋለሁና በፊታችሁም አንድ ስንኳ የሚቀር የለምና አትፍሯቸው አለው ኢያሱም ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት በሌሊት ደረሰባቸው።
እግዚአብሔርም ከእስራኤል ፊት የተነሣ አስደነገጣቸው ኢያሱም ብርቱ ጥፋትን አጠፋቸው ከእነርሱም ወደ ቢቶሮን ቍልቍለት በሸሹትም እግዚአብሔር የበረድ ድንጋይ ከሰማይ አውርዶ ጨረሳቸው። የእስራኤል ልጆች በጦራቸው ከገደሏቸው በደንጊያ በረዶ የሞቱ በዙ።
ያንጊዜም እግዚአብሔር አሞሬዎንን በእስራኤል ልጆት እጅ አሳልፎ በሰጣቸው ጊዜ ኢያሱ ፀሐይ በገባዖን ጨረቃም በኤሎም ቈላ ትቁም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ ፀሐይና ጨረቃም ቆሙ። ጠላቶችንም ሁሉንም አጠፋቸው ከእነርሱም የቀረ የለም።
ከዚህም በኋላ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስትን አካፈላቸው ያለ ዕውቀት በስሕተት ሰው የገደለ በውስጡ ይማጠን ዘንድ ስባት መማጸኛ ከተሞችን እግዚአብሔር እንደ አዘዘው ሠራ። ዕድሜውም መቶ ሃያ በሆነው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሰበሰባቸው የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ በአምልኮተ እግዚአብሔርም እንዲጸኑ ትእዛዞቹንም እንዳይተላለፉ አዘዛቸው። እንዲህም አላቸው እርሱ ፈጣሪያችን ቀናተኛ ነውና ጣዖት ብታመልኩ ያጠፋችኋል ሕጉን ብትጠብቁ ግን የበረከት ልጆች ትሆናላችሁ።
ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ያዕቆብ ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች በገዛው ናብሎስ በሚባል ቦታም ተቀበረ ሠላሳ ቀኖችም ያህል ታላቅ ልቅሶ አለቀሱለት።
† ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤2🥰2💯2🕊1
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
Jul 02, 2026✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
😍3🥰2❤1
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Jul 02, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😘4❤3🥰2😍2
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 02, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
❤5🥰5😘3😍1
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jul 01, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jul 01, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
🥰5😘2😍1
#ሰኔ_25 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አምስት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ #ሐዋርያው_ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ጴጥሮስ አረፈ፣…
Jul 01, 2026#ሰኔ_25 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አምስት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ #ሐዋርያው_ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ጴጥሮስ አረፈ፣ ሰማዕቱ #መስፍኑ_ጲላጦስ መታሰቢያው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ይሁዳ_ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) ሰኔ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ከሰባ ሁለቱ…
❤2🥰2💯2🕊1
#ሰኔ_25
Jul 01, 2026#ሰኔ_25
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ አምስት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ #ሐዋርያው_ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ጴጥሮስ አረፈ፣ ሰማዕቱ #መስፍኑ_ጲላጦስ መታሰቢያው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ይሁዳ_ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
ሰኔ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ሐዋርያ በብዙ አገሮች ሰበከ ወደ አንዲት ደሴትም ገብቶ በውስጧም ሰበከ ሰዎቿንም በጌታ አሳመናቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው።
ከዚያም ወደ ሮሃ ሀገር ሒዶ የሮሃ ንጉሥ አውጋንዮስን ከደዌው ፈወሰው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ከዚያም ደግሞ ሐራፒ ወደሚባል አገር ሒዶ በውስጧ ሰበከ ከሰዎቿ ብዙዎቹን አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው።
የዚያችም አገር ገዥ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ችንካር ያለው ጫማ በእግሮቹ ውስጥ አድርጎ አንድ ምዕራፍ ያህል አስሮጠው ከዚህም በኋላ ሰቅሎ በፍላፃ ነደፈው ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ።
ከመከራውም አስቀድሞ ለምእመናን መልእክትን ጽፎ ላከ እርሷም ከሐዋርያት መልእክቶች ሰባተኛ የሆነች ምሥጢርን የተመላች ናት በእርሷም ብዙዎች አረማውያንን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አስገባቸው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ጴጥሮስ_ሊቀ_ጳጳሳት
ዳግመኛም በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጰሳት አርባ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ጴጥሮስ አረፈ። ይህም አባት ከመሾሙ በፊት የማርቆስ መንበር ያለ ሊቀ ጳጳሳት ለብዙ ዘመናት ኖረ የእስላሞች ንጉሥና መኳንንቶቹ አልፈቀዱላቸውም ነበርና።
ከዚህም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ መኰንን በእስክንድርያ ከተማ ላይ ተሾመ ያንጊዜም የአገር ሽማግሌዎች ወደ ርሱ ተሰብስበው ሊቀ ጳጳሳት እንደ ሌላቸው ኀዘናቸውን ነገሩት። እርሱም ደብረ ማሕው ወደሚባለው ወደ ደብረ ዝጋግ ወጥተው እንዲጸልዩ ለራሳቸውም ሊቀ ጳጳሳት እንዲሾሙ አዘዛቸው። በዚህም ነገር ደስ ብሏቸው ቀሲስ አባ ጴጥሮስን ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በእርሱም ደስ አላቸው።
በዚያም ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ሞተ የአንጾኪያ አገርም ያለ ሊቀ ጳጳሳት ትኖር ነበር የአንጾኪያ ምእመናንም ለእስክንድርያ ከተማ አባ ጴጥሮስ እንደ ተሾመ በስሙ ጊዜ እነርሱም የተማረ ደግ ሰው ለአንጾኪያ ሾሙ ስሙም ታውፋንዮስ ይባል ነበር ። እርሱም ከአባ ጴጥሮስ ጋራ ተስማማ እነርሱም ስለ ቀናች ሃይማኖት በመልእክቶቻቸው ይገናኙ ነበር።
ከእነርሱም እያንዳንዱ በባልንጀራው ምክር በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ይሰብክ ነበር ወደ አገራቸውም መግባት አልተቻላቸውም ነበርና አባ ጴጥሮስም በግብጽ ደቡብ በአንባንያ ገዳምና በዝጋግ ገዳም ይኖር ነበር አባ ታውፋንዮስም ከአንጾኪያ ከተማ ውጭ በአፍቆንያስ ገዳም ይኖር ነበር።
በዚያም ወራት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ሰባት መቶ ገዳማትና ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንም ያሉባቸው ሠላሳ ሁለት መንደሮች ነበሩ በግብጽ አውራጃ ሁሉና በላይኛው ግብጽ በአስቄጥስ ገዳማት የሚኖሩ መነኰሳት እንዲሁም ኖባና ኢትዮጵያ በዚህ በአባ ጴጥሮስ ስልጣን ሥር ነበሩ። እኒህ ሁሉ ሃይማኖታቸው የቀና ነበር። በትእዛዙም ጸንተው ይኖሩ ነበር። እርሱም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ወደእርሳቸው መልእክቶችን መጻፍ አያቋርጥም ነበር። የእስክንድርያን ገዳማት ሁሉና መንደሮችንም እየዞረ ያስተምራቸውና ይመክራቸው ያጽናናቸውም ነበር።
ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስና ዐዋቂ የሆነ ደቀ መዝሙር ነበረው እርሱም በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ሁሉ ይራዳው ነበረ። ይህም አባት ጴጥሮስ አንዳንድ ጊዜ ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ነበር የሰዎቿንም ሥራቸውን ተመልክቶ ያስተምራቸውና በሃይማኖት ያጸናቸው ነበር።
በዐሥራ ሁለቱ ዓመት የሹመቱ ዘመን እንደ ሐዋርያት መንጋዎቹን እየጠበቀ እንዲህ በሹመቱ ኑሮ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_ጲላጦስ_መስፍን
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሰማዕቱ ጲላጦስ እና የሚስቱ ቅደስት አብሮቅላም መታሰቢያ ነው፡፡ ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን። የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል። በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል።
ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው። ጌታችንን ተከትላ ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፋለች። ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ።
=> ሰኔ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን
3.ቅድስት አብሮቅላ (ሚስቱ)
4.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት
5.የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ
=> ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
🥰2💯2😘2🕊1
🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
Jul 01, 2026🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽
🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
❤1
👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
Jul 01, 2026👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መጽሐፍ 📕በPDF ታገኛላቹ።
1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open
2.ሕማማት......................Open
3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open
4.አባቶችህን እወቅ...........Open
5.ሃይማኖተ አበው............Open
7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open
8.የብርሃን እናት...............Open
9.ማህሌተ ፅጌ................Open
10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open
11.ተግባራዊ ክርስትና........Open
❤4🥰4😘2😍1
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
Jul 01, 2026💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
😍4❤3🥰3😘2
✝እንኳን አደረሰነ!
Jun 30, 2026✝እንኳን አደረሰነ!
=>አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ በረከት ይክፈለን።
😍10🥰5❤2💯2😘2
✝መነኮስ መስተጋድል አባ ሙሴ ጸሊም፤
Jun 30, 2026✝መነኮስ መስተጋድል አባ ሙሴ ጸሊም፤
ዘወጽአ ጣዕመ ዜናሁ ውስተ ኲሉ ዓለም፤
ኀዲጎ ወመኒኖ እከየ ሕይወቱ ዘቅድም፤
ዓምደ ብርሃን ኮነ ወአበ ሰላም!
✝ እንኳን አደረሰን !
😘9❤2🥰2😍2💯2
ቅዱሳን (Saints)
Jun 30, 2026#ሰኔ_24
Jun 30, 2026#ሰኔ_24
#ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም_ኢትዮጵያዊው
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ አራት በዚች ቀን አባ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት ሞተ። ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር።
አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል። እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር።
ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው። ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው። አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው። አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው።
እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሠህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ። ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ።
ሰይጣንም ቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብሉና በመጠጡ በዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽናንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር።
ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእነርሱ ሩቅ ነበረና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ።
ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ። ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ። እግዚአብሔርም ትዕግስቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበ ምኔት ሆነ።
ከዚህ በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ በአቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር አረጋውያኑንም ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት አላቸው እርሱም መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መልካም አደረጉብህ በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ።
በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህ በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጕድጓዶችን ሁሉ ሞላ። አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም እግዚአብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን አላቸው።
በአንዲትም ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋራ ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ አላቸው አባ ሙሴም አባቴ ሆይ ምናልባት እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና ብሎ መለሰ።
ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ አላቸው እነርሱም አባታችን አንተስ አትሸሽምን አሉት እርሱም በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለሚለው የእግዚአብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ አላቸው።
ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስለ አልፈለጉ ከእርሱ ጋራ ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መልአክ አየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም በአየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።
ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርስቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው የንስሐን ኃይሏን ተመልከቱ። ሥጋውም በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ።
❖ ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
2."7ቱ" ቅዱሳን መነኮሳት (ደቀ መዛሙርቱ)
3.አባ ኤስድሮስ ታላቁ
❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
2፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
4፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
5፡ ቅዱስ አብላርዮስ
6፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
7፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤10😘4🥰2💯2😍1
#ሰኔ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክ…
Jun 30, 2026#ሰኔ_21 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው፣ ከምስር አገር #ቅዱስ_ጢሞቴዎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ከላድያኖስ አረፈ፣ #ሐዋርያው_ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት…
😘12❤5😍4🥰3💯2
ጌታችንም ትዕግሥቱን አይቶ መልአኩን ልኮ ከሥቃዩ አድኖ ጤነኛ አደረገው ወደ መኰንኑም ቀርቦ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር አለው።
Jun 30, 2026ጌታችንም ትዕግሥቱን አይቶ መልአኩን ልኮ ከሥቃዩ አድኖ ጤነኛ አደረገው ወደ መኰንኑም ቀርቦ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር አለው።
ያን ጊዜም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በመጋዝም መግዞ ሰቀለው ከዚያም በኋላ ሥጋው እንደ ሰም ቀልጦ እንደ ውኃ እስቲፈስ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰለው ከከተማ ውጪም ጣሉት።
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለምንም ጉዳት አንሥቶ ጤነኛ አደረገው። ወደ መኰንኑም ተመልሶ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር ብሎ ጮኸ። ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
መኰንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የድል አድራጊነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ከላድያኖስ
በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አራተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ አረፈ። ይህም ቅዱስ በወንጌላዊው ማርቆስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ እርሱም ዲቁናን ሾመው ደግሞም ቅስናን ሾመው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርትና ሕግ ጠንቅቆ ተማረ።
አባ ሜልዮስም በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ዐሥራ አንድ ዓመት ያህል በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው በትምህርትና በምክር ሁሉ እንደሚገባ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። ልዑል እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ
በዚችም ቀን ሐዋርያው ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው።
አንድ ጎልማሳ በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ እጅ የተባረከ እንጀራን ከሕዝቡ ጋር ተቀብሎ ሊበላ ሲል እጆቹ ፈጽመው ደረቁ፡፡ እርሱንም ያዩት ሰዎች በዚህ ጎልማሳ ላይ የሆነውን ነገር ለሐዋርያው ነገሩት፡፡ ቅዱስ ቶማስም ልጁን ጠራውና ‹‹ልጄ ሆይ! የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ ዘልፎሃልና ያደረከውን ነገር ንገረኝ?›› አለው፡፡ ጎልማሳውም ከሐዋርያው እግር ሥር ወድቆ ሰገደና ‹‹መልካም ሥራ የሠራሁ መስሎኝ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁ፡፡ ይኸውም አስቀድሜ ወደ አንዲት የጠጅ አበዛ ሴት ልጅ እገባ ነበር፡፡ አንተም በንጽሕና እንድንኖር አስተማርኸን፤ ያችም ሴት አብሬያት እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ፡፡ ስለዚህም ሰይፍ አንሥቼ አረድኳት›› አለው፡፡ ሐዋርያውም ‹‹እንዴት እንዲህ ያለ ቁጣና የአውሬ ሥራን ትሠራለህ?›› ብሎ ከገሠጸው በኋላ ውኃ አስቀርቦ በላዩ ጸለየበትና ጎልማሳውን ‹‹በዚህ ታጠብ ትድናለህ›› አለው፡፡ ጎልማሳውም በውኃው በታጠበ ጊዜ የደረቁ እጆቹ ዳኑ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቶማስ ‹‹የዚያቸ ሴት በድን ወዳለበት ቦታ ምራኝ›› አለው፡፡ ጎልማሳውም መርቶ ከቦታው አደረሰው፡፡ ሐዋርያውም በድኗን ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ወደ ውጭ አውጥተው በአልጋ ላይ እንዲያኖሯት ካዘዘ በኋላ እጁን በላይዋ ጭኖ ጸለየ፡፡ ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጎልማሳውን ‹‹ሂድ እጇን ይዘህ ‹እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ፣ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ› በላት›› አለው፡፡ ጎልማሳውም ቅዱስ ቶማስ እንዳዘዘው ባደረገ ጊዜ ፈጥና ከሞት ተነሣች፡፡ ከአልጋዋም ፈጥና ወርዳ ከቅዱስ ቶማስ እግር ሥር ወድቃ ሰገደችለት፡፡
ቅዱስ ቶማስም ለሞተች በኋላ የት እንደነበረች ያችን በሕዝቡ ሁሉ ፊት ጠየቃት፡፡ እርሷም በሲኦል እንደነበረችና በዚያም ያሉትን ልዩ ልዩ የሆኑ እጅግ ጽኑ ሥቃዮችን ሁሉ በዝርዝር ለሕዝቡ አስረዳች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ከዚያ የነበሩትን ‹‹ይህች ሴት ሞታ እንደነበር አይታችኋል፣ አሁንም አይታ የምትመሰክረውን ሰማችሁን? በሲኦል ያለው ሥቃይ ብቻ አይደለም ነገር ግን ከዚህ የሚከፋ አለ፡፡ እናንተም የኃጢአትን ሥራና ክፉ ሀሳብን ትታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፡፡ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ፍቅርንና ንጽሕናን ጠብቁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋን ትቀበላላችሁ›› አላቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ በክብር ባለቤት በጌታችን አመኑ፡፡ ለድኆቸም ምጽዋትን ሊሰጡ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው አመጡ፡፡ ለድኆች ምጽዋት መስጠት ለሐዋርያው ልማዱ ነበርና፡፡ ወሬውም በሀገሩ ሁሉ ተሰማና ሕመምተኞችን ሁሉ ሰብስበው አምጥተው በፊቱ ጣሏቸው፡፡ ቅዱስ ቶማስም ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡
❖ ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
3.ቅዱሳን ሐዋርያት
4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
8.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)
9.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት
❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ አበው ጎርጎርዮሳት
2፡ አባ ምዕመነ ድንግል
3፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
4፡ አባ አሮን ሶርያዊ
5፡ አባ መርትያኖስ
6፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ ልመናዋ በረከቷም ወንዶችና ሴቶች ባሮቿ ከሆን ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር፣ በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)
❤14🥰7😍3💯2
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
Jun 30, 2026🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
😘5🥰4❤3😍3
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jun 30, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
😘5❤4🥰2😍2
✝ ቅዱስ አባ ኖብ
Jun 30, 2026✝ ቅዱስ አባ ኖብ
✨ገዳማዊ ጻድቅ።
✨ኃያል ሰማዕት።
✨ከ፸፪ቱ ከዋክብት አንዱ።
✨ሰማዕት ዘንበለ ደም።
✝️ በረከቱ ይደርብን። የበዓሉ በረከት ይደርብን 🌿
😍9❤8🥰4😘3💯2
✨ነቢየ_ጽድቅ
Jun 30, 2026✨ነቢየ_ጽድቅ
¤ መፍቀሬ_ጥበብ
✨ጠቢበ_ጠቢባን
¤ መስተሳልም_ወመስተፋቅር
✨ሐናጼ_መቅደስ
¤ ንጉሠ_እስራኤል
✨ወልደ_ዳዊት . . .
✨ቅዱስ ሰሎሞን
✨በእግዚአብሔር የተመረጠ ነው!
✨የክርስቶስ ምሳሌ ነው!
✨እግዚአብሔር ያከበረውን ማንም ሊያዋርደው አይችልም!
❀እኛም አባት ስንለው (በሁለቱም ተዘምዶ) የሚሰማን ደስታና ኩራት ብቻ ነው!
✨ለኢትዮዽያውያን ደግሞ በሃይማኖትም ሆነ በተዘምዶ አባታችን ነው::
✨ከንግሥተ ሳባ ምኒልክን (ቦይነ ሐኪምን) ወልዶ ተዛምዶናልና::
🌿 የበዓሉ በረከት ይደርብን 🌿
❤7🥰7😍3😘3💯2
#ሰኔ_23 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ #የጠቢቡ_ሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ #አባ_ኖብ አረፈ። ✞✞…
Jun 30, 2026#ሰኔ_23 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ #የጠቢቡ_ሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ #አባ_ኖብ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ነቢየ_ጽድቅ_ቅዱስ_ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) ሰኔ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን የዕረፍቱ…
🥰9❤7😘4😍2💯2
ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧ…
Jun 30, 2026ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧት አለችው ያቺ ሴት ግን አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእሷም አይሁን አለች። ንጉሡም መግደልስ አትግደሉት እሱን ለእሷ ስጧት ላለችው ለዚች ሴት ደኅነኛውን ሕፃን ስጧት እርስዋ…
ወደ ንጉሡም በገቡ ጊዜ ከእነርሱ ቡራኬ ተቀበለ ቁስላቸውንም ሳመ እጅግም አከበራቸው ብዙ ገንዘብም ሰጣቸው እነርሱ ግን ለቤተ ክርስቲያን ከሚሆን ንዋየ ቅድሳት በቀር ምንም ምን አልተቀበሉም ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶ ወደየሀገራቸው በሰላም አሰናበታቸው። አባ ኖብም ወደ ቦታው ተመልሶ አረፈና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ።
❖ ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ)
3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት)
❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
4፡ አባ ሳሙኤል
5፡ አባ ስምዖን
6፡ አባ ገብርኤል
7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
🥰7❤5😍5💯3😘2
ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧ…
Jun 30, 2026ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧት አለችው ያቺ ሴት ግን አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእሷም አይሁን አለች።
ንጉሡም መግደልስ አትግደሉት እሱን ለእሷ ስጧት ላለችው ለዚች ሴት ደኅነኛውን ሕፃን ስጧት እርስዋ እናቱ ናትና አለ። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ የፈረደውን ይህን ፍርድ ሰምተው ቅን ፍርድን ይፈርድ ዘንድ የእግዚአብሔር ጥበቡ በሱ ላይ እንዳለ አይተዋልና በንጉሡ ፊት ፈሩ።
ከዚህም በኋላ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዘመን በሆነ ጊዜ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሊያንፅ ጀመረ።
በዐሥራ አንደኛውም ዘመነ መንግሥቱ ወሩ ባዕድ በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱንና ሥርዓቱን ሁሉ ፈጸመ በሰባት ዓመትም ውስጥ ሠራው የራሱንም ቤት በዐሥራ ሦስት ዓመት ሠርቶ ጨረሰ። ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት በሃያ ዘመን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያመጣት ዘንድ ያን ጊዜ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆች የአባቶቻቸውንም ቤት አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው።
የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን በሰባተኛው ወር በጥቅምት ተሰበሰቡ። የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ ካህናቱም ታቦትዋንና የምስክሩን ድንኳን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያለ ንዋየ ቅድሳቱንም ሁሉ ተሸከሙ። ንጉሡና እስራኤል ሁሉ በታቦትዋ ፊት ሥፍር ቍጥር የሌላቸው በጎችና ላሞችን ይሠዉ ነበር። ካህናቱም ታቦቷን ከኪሩቤል ክንፎች በታች በቤቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ቦታዋ አገቧት።
ኪሩቤል በታቦትዋ ቦታ ላይ ክንፋቸውን ጋርደዋልና ኪሩቤልም በስተላይ በኩል በቅድስተ ቅዱሳን ላይ ታቦትዋን ጋርደዋት ነበር። ከቅድስተ ቅዱሳንም ጋራ የተያያዙ ነበሩ። ቅዱሳን ኪሩቤል ከፍ ብለው ከቅድስተ ቅዱሳኑ አንጻር ላይ ሁነው ያያሉ በውጭ ግን አይታይም ነበር። ከግብጽ አገር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ጋራ ቃል ኪዳን ከገባባቸው ሙሴም በዚያ በኮሬብ ከአኖራቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ አልነበረም።
ከዚህ በኋላ ካህናቱ ከቤተ መቅደስ በወጡ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ሁሉ ብርሃን መላው። የእግዚአብሔር ብርሃን በማደሪያው ቤተ መቅደስ መልቷልና ከብርሃኑ መገለጥ የተነሣ ካህናቱ ሥራቸውን መሥራትና ከፊቱ መቆም ተሳናቸው።
ያን ጊዜ ሰሎሞን እግዚአብሔር በደመና ውስጥ እኖራለሁ ብሏል። እኔም ለዘላለም የምትኖርበት ማደሪያህ ቤተ መቅደስን በእውነት ሠራሁልህ አለ። ንጉሡም ፊቱን መልሶ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መረቃቸው ወደ እግዚአብሔርም ረዥም ጸሎትን ጸለየ። ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ልመና ወደ እግዚአብሔር ለምኖ በጨረሰ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ከሰገደበት እጆቹንም ከዘረጋበት ከመሠዊያው ፊት ተነሣ።
ቆሞም የእስራኤልን ማኅበር እንደተናገረው ሁሉ ለወገኖቹ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጣቸው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ብሎ በታላቅ ቃል መረቃቸው። ከዚህ በኋላ ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕትን ሠዉ።
ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት የሠዋቸው ሃያ ሁለት ሽህ ላሞችና አንድ መቶ ሃያ ሽህ በጎች ናቸው ንጉሡ ሰሎሞንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ያንጊዜ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለቤተ መቅደስ ቅዳሴ ቤት አደረጉ።
ቀድሞ በገባዖን እንደታየው ዳግመኛ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ታየው በፊቴ የለመንኸኝ ልመናህንና ጸሎትህን ሰማሁ። እንደ ልመናህም ሁሉ አደረግሁልህ ስሜ በዚያ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖር ዘንድ የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ አከበርሁት ልቡናዬም ዐይኖቼም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ጸንተው ይኖራሉ አለው። ሰሎሞንም አርባ ዘመን ነገሠ ከመንገሡም በፊት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ መላ ዕድሜውም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነበር በሰላም አረፈ።
ይህም ጥበብ የተሰጠው ንጉሥ ሰሎሞን ጥቅም ያላቸው ብዙዎች መጻሕፍትን ደርሶአል። እሊህም ትንቢትና ትምህርት ያለባቸው ምሳሌዎችና መኃልዮች ናቸው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኖብ
በዚህችም ቀን ደግሞ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ አባ ኖብ አረፈ። ይህም ቅዱስ መነኰስ በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ የሚጋደል ጽሙድ ነበር።
ዲዮቅልጥያኖስም ብዙዎች ሰማዕታትን ሊአሠቃይና ደማቸውን ሊያፈስስ በጀመረ ጊዜ በአንዲት ቀን ሰማንያ ሰማዕታትን አቅርቦ ደማቸውን አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ አባ ኖብን አስታወሱት የእንዴናው ገዥ ወደሆነው ወደ አርያኖስ አቀረቡት። እርሱም ለአማልክት ዕጠን ሠዋ ይህንንም የምንኵስና ልብስ ከላይህ አውጥተህ ጣል አለው።
አባ ኖብም ይህ ሥራ ከቶ ከእኔ ዘንድ አይደረግም የክብር ባለቤት ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስንም አልተውም የረከሱ ጣዖታትንም አላመልክም አለ። መኰንኑም በየራሱ በሆነ ሥቃይ እጅግ አሠቃየው ያም አባ ኖብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ኃይል ታግሦ ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ ወደ አምስቱ አህጉር ሰደደው በዚያም በጉድጓድ ውስጥ ጣሉት በውስጡም ጌታችን ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍቶ ደግ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን እስከሾመው ድረስ ሰባት ዓመት ኖረ።
ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን ሁሉ ፈትተው ወደርሱ እንዲአቀርቧቸውና ከእርሳቸው እንዲባረክ ወደ አገሮች ሁሉ ደብዳቤዎችን ላከ። ለመልእክተኞችም እንዲህ አላቸው ሁሉንም ወደ እኔ ማድረስ ካልተቻላችሁ እጆቻቸውን በራሴ ላይ ጭነው ይባርኩኝ ዘንድ ክብር ያላቸውን ታላላቆችንና መምህራኑን አምጡአቸው።
ከእነርሱም ውስጥ የታወቁ አህናህ ከተባለ አገር አባ ዘካርያስ ከፍዩም መክሲሞስ ከሀገረ ድኂን አጋብዮስ ከሀገረ በላኦስ አባ ኖብ ናቸው የንጉሥ መልእክተኞችም በየአገሮች ሁሉ እየዞሩ የታሠሩ ቅዱሳንን ከእሥር ያወጡአቸው ነበር እነርሱም ደስ ይላቸው ነበር የተመሰገነ እግዚአብሔርንም ያመሰግኑት ነበር ይዘምሩለትም ነበር።
የንጉሥ መልእክተኛም አባ ኖብን ከአምስቱ አገሮች ፈልጎ የአገሩ አንጻር ወደ ሆነች ወደ ሀገረ በሰላ ወሰደው። በዚያም የብረት ልብስ ለብሶ ተቀምጦ ነበር የንጉሡ መልእከተኛም አገኘውና ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ እንዴናውም እስከ ደረሱ በመርከብ ተሳፈሩ ክርስቲያኖችም ተሰበሰቡ ከውስጣቸውም አራት ኤጲስቆጶሳት ነበሩ አባ ኖብንም ያለ ውዴታው ቅስና ሾሙትና የቊርባን ቅዳሴን ቀደሰ።
በቅዳሴውም ፍጻሜ ቅድሳት ለቅዱሳን ብሎ ጮኸ ይህም ማለት ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ከሥጋው ከደሙ ይቀበል ማለት ነው በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ ንስሐ የገቡትን ኃጢአታቸውን ይቅር ሲላቸው አየው ሥጋውንና ደሙንም ከአቀበላቸው በኋላ ወደ ንጉሡ ለመሔድ ተዘጋጁ ቍጥራቸውም ሰባ ሁለት ነበር ሠላሳ ሰባት ሠረገላም አዘጋጅተውላቸው እየአንዳንዳቸው በሠረገላው ተቀመጡ።
በአለፉም ጊዜ የደናግል ገዳማት ካሉበት ደረሱ ደናግሉም ወጥተው ተቀበሏቸው ቍጥራቸው ሰባት መቶ ነበር ከእነርሱ ጋራም እስከሚሰበሰቡ በቅዱሳን ፊት ይዘምሩ ነበር።
ወደ ንጉሡ ከተማም በደረሱ ጊዜ ወደ ንጉሡ ከመግባታቸው በፊት በውኃ ያጥቧቸውና አዳዲስ ልብሶችን ያለብሷቸው ጀመሩ እንዲሁም ለሁሉ አደረጉ ቅዱስ አባ ኖብ ግን አልታጠበም ልብሱንም አልለወጠም ።
❤8😘8🥰3😍3💯2
#ሰኔ_23
Jun 30, 2026#ሰኔ_23
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ #የጠቢቡ_ሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ #አባ_ኖብ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ነቢየ_ጽድቅ_ቅዱስ_ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
ሰኔ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
የዚህ የሰሎሞንም የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ነው ዳዊትም ሕግ ተላልፎ ከእሷ ጋራ ስለ መበደሉ ባሏንም ስለ ማስገደሉ ጌታ በገሠጸው ጊዜ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ጌታም ንጹሕ ስለሆነ ንስሓው ይቅር አለው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሷን አገባትና ሰሎሞንን ወለደችው ንጉሥ ዳዊትም ከእርሱ በኋላ ልጅዋ ሰሎሞን እንዲነግሥና በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ ቃል ገባላት።
እንዲህም ሆነ ሰሎሞን ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አዶንያስ እነግሣለሁ ብሎ ተነሣ ምክሩም ሁሉ ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ አብያታር ጋር ሆነ። እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት። አዶንያስም በሮጌል ምድር ምንጭ አጠገብ ባለ በኤልቲ ዘዘኤልቲ ላይ ፍየሎችን በጎችንና ላሞችን አርዶ የንጉሥ አሽከሮች የሆኑ የይሁዳ አርበኞችን ሁሉና የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ ጠራ።
ከዚህም በኋላ አዶንያስ ይህን እንዳደረገ ለቤርሳቤህ በነገሩዋት ጊዜ ወደ ንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ገብታ ለንጉሡ ሰገደች ንጉሥ ዳዊትም ምን ሆንሽ አላት። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል ብለህ ለእኔ ለባርያህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም አንተ ማልክልኝ እነሆ ዛሬ አዶንያስ ነገሠ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አንተ ግን አላወቅህም አለችው።
ከንጉሥም ጋራ ገና ስትነጋገር ነቢዩ ናታን መጣ ለንጉሡም ናታን መጣ ብለው ነገሩት። ወደ ንጉሡም ገባ በምድር ላይም በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ነቢዩ ናታንም ከእኔ ቀጥሎ አዶንያስ ይንገሥ በዙፋኔም ላይ ይቀመጥ ያልክ አንተ ነህን ዛሬ ወርዶ በጎችንና ብዙ ፍየሎችን አርዶ የሠራዊቱ አለቆችንና የንጉሥ አሽክሮችን ሁሉ ካህኑ አብያታርንም ጠርቷልና በፊቱም ይበላሉ ይጠጣሉ አንዶንያስ ሽህ ዓመት ያንግሥህ ይሉታል አለው።
ዳዊትም መልሶ ቤርሳቤህን ጥርዋት አለና ጠሩዋት ገብታም በንጉሡ ፊት ቆመች። በእግዚአብሔር ፊት እንደማልኩልሽ አሁንም በዚች ቀን እንደዚሁ እንዳደርግ ሰውነቴን ከመከራዬ ሁሉ ያዳናት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕያው ነው ብሎ ማለ። ቤርሳቤህም አንገቷን ደፍታ በግምባርዋ በመሬት ወድቃ ለንጉሡ ሰገደች ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ኑር አለች።
ንጉሥ ዳዊትም የዮዳሄ ልጅ ብንያስንና ካህኑ ሳዶቅን ነቢዩ ናታንንም ግራዝማቹንና ቀኝ አዝማቹን ጥሩልኝ አለ። ንጉሡም ከእናንተ ጋራ የጌታችሁ አሽከሮችን ይዛችሁ ልጄ ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን አውርዱት። በዚያም ነቢዩ ናታንና ካህኑ ሳዶቅ ቀብታችሁ በእስራኤል ላይ አንግሡት አላቸው።
ቀንደ መለከት ንፉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ በሉ። ተከትላችሁትም ውጡ ገብቶም በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ እርሱም ስለ እኔ ፈንታ ይንገሥ በሁለቱ ነገድና በዐሥሩ ነገድ ይነግሥ ዘንድ እኔ አዝዣለሁ። ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ ቀርነ ቅብዑን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው ቀንደ መለከትንም ነፉ ሕዝቡም ሁሉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ አሉ ሕዝቡም ሁሉ ተከትለውት ወጡ ከበሮም መቱ ታላቅ ደስታም አደረጉ ከድምፃቸውም የተነሣ ምድሪቱ ተናወጸች።
ሰሎሞንም በመንግሥት ዙፋን ተቀመጠ። የንጉሡም አሽከሮች ጌታቸው ንጉሡ ዳዊትን ሊአመሰግኑ ገቡ። እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርገው ዙፋኑንም ከዙፋንህ ይልቅ የበለጠ ያድርገው አሉት። ንጉሡም በዐልጋው ሆኖ ሰገደ። እንዲህም አለ ዐይኖቼ ሲያዩ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ልጅን ለኔ ለባርያው ዛሬ የሰጠ የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አለ። ዳዊትም የሚሞትበት ወራት በደረሰ ጊዜ ልጁ ሰሎሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው። እኔ ሰው ሁሉ በሚሔድበት በሞት ጐዳና እሔዳለሁ አንተ ግን ጽና ብልህ ሰውም ሁን።
በሕጉ ጸንተህ ትኖር ዘንድ የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ትእዛዙን ጠብቅ እኔ እንዳዘዝሁህ እንዴት እንደምታደርግ ታውቅ ዘንድ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ትእዛዙንና ሕጉን ፍርዱንም ጠብቅ ልጆችህ ሕጌን ቢጠብቁ በፊቴም በፍጹም ልቡናቸው በፍጹም ሰውነታቸው በዕውነት ጸንተው ቢኖሩ ከእስራኤል ዙፋን ላይ ሰው አይጠፋብህም ብሎ እግዚአብሔር ለእኔ የነገረኝ ቃሉን ያጸና ዘንድ ጠብቅ ብሎ አዘዘው።
ዳግመኛም በኢዮአብና በሳሚ ወልደ ጌራ ላይ በቀል እንዲአደርግ አዘዘው እነርሱ እጅግ የከፉና ብዙ ክፋት የሠሩ ነበሩና። ከዳዊት ዕረፍትም በኋላ ሰሎሞን በዚያ መሥዋዕትን ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ወደ ገባዖን ሔደ ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና ሰሎሞንም በገባዖን በዚያው መሠዊያ ውስጥ ሽህ መሥዋዕትን ሠዋ። እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት በሕልም ተገለጠለት ለአንተ እሰጥህ ዘንድ ልብህ ያሰበውን ልመናን ለምን አለው።
ሰሎሞንም በቅንነትና በእውነት በንጹሕ ልቡናም ከአንተ ጋራ በፊትህ ጸንቶ እንደኖረ ከአባቴ ከዳዊት ጋራ ታላቅ ቸርነትን አድርገሃል በዚችም ቀን ልጁን በዙፋኑ ላይ ታስቀምጠው ዘንድ ይህን ታላቁን ቸርነት አጽንተህለታል አለው። አሁንም አቤቱ አንተ ፈጣሪዬ ስለ አባቴ ስለ ዳዊት ፈንታ እኔን ባሪያህን አነገሥኸኝ እኔም መግቢያዬንና መውጫዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።
እኔ ባሪያህ ግን የማይቈጠር ብዙ ሕዝብ በሆነ በመረጥከው ወገንህ መካከል አለሁ። ለዚህ ለብዙ ወገንህ መፍረድ የሚችል የለምና ሰምቶ ለወገኖችህ በእውነት ፍርድን ይፈርድ ዘንድ ከክፉ ነገርም ለይቶ በጎውን ነገር ያውቅ ዘንድ ለባሪያህ ዕውቀትን ስጠው። ሰሎሞን ይህንን ነገር ለምኖታልና ይህ ነገር እግዚአብሔርን በፊቱ ደስ አሰኘው። እግዚአብሔርም ይህንን ነገር ከእኔ ለምነሃልና ለአንተም ብዙ ዘመንንና ባለጸግነትን አልለመንህምና ጠላቶችህንም አጥፋልኝ ብለህ አልለመንህምና ነገር ግን ፍርድ መስማትን ታውቅ ዘንድ ለምነሃልና እነሆ እንዳልህ አደረግሁልህ።
እነሆ ከአንተ አስቀድሞ እንዳልነበረ ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ እንዳይነሣ አድርጌ ብልህና አስተዋይ ልቡናን ሰጠሁህ። ሰው በመንግሥቱ እንዳንተ እንዳልሆነ አድርጌ ያልለመንኸኝን ባለጠግነትንና ክብርንም በዘመንህ ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
ሰሎሞንም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እውነተኛ ሕልም እንደ ሆነ ዐወቀ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በጽዮንም በእግዚአብሔር ታቦተ ሕግ አንጻር ባለ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የሰላም መሥዋዕትን አቀረበ ለሰዎቹና ለሱም ታላቅ ግብዣ አደረገ።
በዚያን ጊዜም ሁለት አመንዝራ ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው በፊቱ ቆሙ አንዲቱም ሴት ጌታዬ ስማኝ እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን በአንድ ቦታም ወለድን እኔ በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች በአንድነትም እንኖራለን በዚያም ቤት ከሁለታችን በቀር ከኛ ጋራ ማንም አልነበረም። በላዩ ላይ ተጭናዋለችና የዚያች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ።
በሌሊት እኩሌታም ተነሥታ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወስዳ በብብቷ አስተኛችው። የሞተውን ልጅዋንም በአጠገቤ አስተኛችው። ልጄን አጠባ ዘንድ በጧት በነቃሁ ጊዜም ያንን የሞተ ልጅ አገኘሁ በነጋም ጊዜ አየሁት እነሆ የወለድሁት ልጄ አይደለም አለች።
ያቺ ሁለተኛዋ ሴትም አይደለም ይህ ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው እንጂ ያንቺ ልጅ አይደለም ያንቺስ የሞተው ነው አለች። በንጉሡም ፊት እንዲህ ተባባሉ።
❤12😍4🥰3😘3💯2
"ዑራኤል ሆይ የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለ ሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ ፤ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድነናልና። "
Jun 30, 2026"ዑራኤል ሆይ የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለ ሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ ፤ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድነናልና። "
መልክአ ዑራኤል
🥰24❤20😍4😘3👏2
✝ጳውሎስ የዋህ ረድአ እንጦንዮስ ቡሩክ፤
Jun 30, 2026✝ጳውሎስ የዋህ ረድአ እንጦንዮስ ቡሩክ፤
ዘመነነ ዓለመ ወተጋደለ በሠርክ፤
ቴዎዳዳ ወውሉዳ ሠዓርያነ ሀከክ ወሀውክ፤
ቆዝሞስ ወድምያኖስ አግብርተ ሔር አምላክ!
❤16😍5🥰2💯2😘2
#ሰኔ_22 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ሁለት በዚች ቀን የከበሩ #ቅዱሳን_የቆዝሞስና_የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው ቤተ ክርስቲያናቸውም የከበረችበት ነው፣ ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበ…
Jun 30, 2026#ሰኔ_22 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ሁለት በዚች ቀን የከበሩ #ቅዱሳን_የቆዝሞስና_የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው ቤተ ክርስቲያናቸውም የከበረችበት ነው፣ ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ የነበረው #የዋህ_ጳውሎስ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_ቆዝሞስ_ወድምያኖስ ሰኔ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን የከበሩ ቅዱሳን የቆዝሞስና…
❤14😘5🥰3😍2💯2
#ሰኔ_22
Jun 30, 2026#ሰኔ_22
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ሁለት በዚች ቀን የከበሩ #ቅዱሳን_የቆዝሞስና_የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው ቤተ ክርስቲያናቸውም የከበረችበት ነው፣ ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ የነበረው #የዋህ_ጳውሎስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ቆዝሞስ_ወድምያኖስ
ሰኔ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን የከበሩ ቅዱሳን የቆዝሞስና የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው የበዓላቸው መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያናቸውም የከበረችበት ተአምራታቸውም የተገለጠበት ነው።
እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዎዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ዶኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ።
ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ። ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምእመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም የንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው አጋግዩስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ።
ቆዝሞስና ድምያኖስ በሀገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደርሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበትም ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ አስመጣቸውና አምስቱንም በመኰራኲር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው።
መኰንኑም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች።
በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትንት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብሎ ጮኸ የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት።
ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ጳውሊ_የዋሕ
በዚህችም ዕለት ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ የነበረው የዋህ ጳውሎስ አረፈ። ይህም ጳውሎስ በረኸኛና እጅግ የዋህ ነበረ ደም ግባቷ ውብ ሥራዋ ግን ክፉ የሆነ ሚስት አገባ ከእርሱም ልጆችን ወለደች።
በአንዲትም ቀን ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ከሎሌው ጋራ ስታመነዝር አገኛት በአያቸውም ጊዜ ሣቀ ያንን ሎሌውንም ከልጆቿ ከቤቷና ከንብረቷ ጋራ ውሰዳት እኔ ምንም አላዝንም እግዚአብሔርም ወደ ፈቀደልኝ እሔዳለሁ አለው።
ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አባ እንጦንስ ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ የአባ እንጦንስንም ሥራ ተከተለ። በደዌያትና በሰይጣናት ላይ ጸጋና ኃይል እስከተሰጠው ድረስ በጾምና በጸሎት ተጋደለ።
በአንዲት ዕለትም ጋኔን የያዘውን ሰው ያድነው ዘንድ ወደ አባ እንጦንስ አመጡ። አባ እንጦንስም ይፈውሰው ዘንድ ረድኡ ጳውሊን አዘዘው ጳውሊም ጋኔናሙን ሰው ወስዶ አባቴ እንጦንስ ውጣ ይልሃል አለው ሰይጣኑ ግን መውጣትን እምቢ አለ። እርሱንም እንጦንስንም ተሳደበ። ጳውሊም ካልወጣህስ ለእንጦንስ እነግረዋለሁ እንደሚቀጣህም ታያለህ አለ።
ይህንንም ብሎ በቀትር ጊዜ ወጥቶ ፀሐይ በአጋለው ደንጊያ ላይ ቁሞ ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው እስኪድን ድረስ ከዚህ አለት እንዳልወርድ እንዳልበላና እንዳልጠጣ ሕያው እግዚአብሔርን አለ።
በዚያንም ጊዜ ጋኔኑ ጮኸ በታላቅ ዘንዶ አምሳልም ከሰውዬው ላይ ወጥቶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ገባ። ይህም የዋህ ጳውሊ የሰዎችን ሥራ ሁሉ እያየ ስለ ኃጥአን ያለቅስ ነበር ስለ እነርሱም ይማልድ ነበር። በመልካም እርጅናም በሰላም አረፈ።
† ሰኔ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ
2.ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ (ሰማዕታት)
3.ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት (እናታቸው)
4.አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ (ሰማዕታት)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
††† አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን: በጐነትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: †††
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_22)
❤14🥰5😍4😘4💯2
🌷ማርያም ድንግል🌷
Jun 30, 2026🌷ማርያም ድንግል🌷
•✨እኅቶሙ ለመላእክት፣
•✨ወለቶሙ ለነቢያት፣
•✨ሞገሶሙ ለሐዋርያት፣
•✨እሞሙ ለሰማዕት፣
•✨ተስፋ መነኮሳት፣
•✨ደብተራ ፍጽምት
•✨አክሊል ንጹሕ ለካህናት፣
•✨ወላዲተ አምላክ ንጽሕት፣
°✨መጽደቂቶሙ ለኀጥአን፣
°✨ናዛዚቶሙ ለኅዙናን፣
°✨ፈዋሲቶሙ ለሕሙማን!
✝ እንኳን አደረሳችሁ !
🥰18❤15😍7😘5💯4👏1
=>በዚችም ሰኔ21ቀን ሐዋርያው ቅዱስቶማስ በመሸታ ቤት (ቤተ መያሲ) ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
Jun 30, 2026=>በዚችም ሰኔ21ቀን ሐዋርያው ቅዱስቶማስ በመሸታ ቤት (ቤተ መያሲ) ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
"ከቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን ከበደላችን ያንጻን::"
😍9❤8🥰2💯2😘2
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
Jun 23, 2026✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳 █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
🥰5❤3😍3😘2
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
Jun 23, 2026🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇
👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
👤ዘማሪ አቤል መክብብ
👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ
👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው
👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
👤 ዘማሪት ወርቅነሽ
👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ
👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
🥰4😍4😘3❤2
✝ በዚህች ቀን (ሰኔ ፲፮) ✝
Jun 23, 2026✝ በዚህች ቀን (ሰኔ ፲፮) ✝
✝ " ✝ ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ።
የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።
በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ::
በነቢያት 'ናዝራዊ ይባላል' የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ። ✝" ✝
(የማቴዎስ ወንጌል 2:19)
✝ተዝካረ ሚጠታ ለእምነ ማርያም ድንግል፤
በከመ አብሠራ መልአክ ፍሡሐ ገጽ ገብርኤል፤
ባሕታውያን ክቡራን እለ ውስተ ኲሉ ደወል፤
ወእምኔሆሙ አሐዱ አቡናፍር ብእሴ ኃይል!
✝እንኳን አደረሰን !
✝️ ከጻማ ንግደታ በረከት ይክፈለን::
🥰9❤8😘6🙏5💯3😍2🕊1
✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝
Jun 23, 2026✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝
ሰኔ16
✝✝✝ ዛሬ የሁሉም #ቅዱሳን_ባሕታውያን (በተለይም የስውራኑ) ዓመታዊ በዓል ነው:: ✝✝✝
✝ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው
¤ንጽሕ ጠብቀው
✝ዕጸበ ገዳሙን
¤ድምጸ አራዊቱን
✝ግርማ ሌሊቱን
¤የሌሊቱን ቁር
✝የመዓልቱን ሐሩር
¤ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ ስለ #ፍቅረ_ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና::
☞ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን የሚማጸኑ አሉ::
✝️ አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን
❤10🥰6😍3❤🔥2🙏2💯2😘2🕊1
#ሰኔ_16 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ስድስት በዚች ዕለት የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ አዘዘው፣ የከበረ በገዳም የሚኖር…
Jun 23, 2026#ሰኔ_16 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ስድስት በዚች ዕለት የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ አዘዘው፣ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት የላይኛው ግብጽ ሰው #አባ_አቡናፍር አረፈ፣ #የቅዱሳን_አበው_ባሕታውያን መታሠቢያ ናት:: ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ተዝካረ_…
😍8🥰5😘5❤3👏2🕊2🙏1
#ሰኔ_16
Jun 23, 2026#ሰኔ_16
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ ስድስት በዚች ዕለት የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ አዘዘው፣ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት የላይኛው ግብጽ ሰው #አባ_አቡናፍር አረፈ፣ #የቅዱሳን_አበው_ባሕታውያን መታሠቢያ ናት::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ተዝካረ_ሚጠታ_ለእግዝእትነ_ማርያም
ሰኔ ዐሥራ ስድስት በዚች ዕለት የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ አዘዘው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_አቡናፍር_ገዳማዊ
በዚች ዕለት መልካም ሽምግልና ያለው ስም አጠራሩ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት የላይኛው ግብጽ ሰው አባ አቡናፍር አረፈ። የዚህንም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቁጥሩ ከገዳማውያን ነውና።
አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ።
በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጉሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስንም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያትን ጸለየ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው አለው ይህንንም በማለቱ ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት።
ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ። ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ ከዚያም በረሀ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው።
አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኰሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን አልኳቸው እነርሱም አዎን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው አሉኝ።
ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ። ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳማውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ።
ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔርም ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚች ምንጭ እጠጣለሁ በዚችም በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም አለኝ።
ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው። ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገብን። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔርም ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ። ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው።
ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ። ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አበው_ቅዱሳን_ባሕታውያን
ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱሳን አበው ባሕታውያን መታሠቢያ ናት። ከሰው (ከዓለም) ርቀው፣ ንጽሕ ጠብቀው፣ ዕጸበ ገዳሙን፣ ግርማ አራዊቱን፣ ጸብዐ አጋንንትን ታግሠው የኖሩ ስማቸውን የምናውቀውንም ሆነ የማናውቃቸውን እንድናከብራቸው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና በዓል ሠርታለች።
=>ሰኔ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አቡናፍር ገዳማዊ (ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናው ያማረ አባት)
2.አበው ቅዱሳን ባሕታውያን ( ዛሬ የሁሉም ቅዱሳን_ባሕታውያን (በተለይም የስውራኑ) ዓመታዊ በዓል ነው::
¤ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው
¤ንጽሕ ጠብቀው
¤ዕጸበ ገዳሙን
¤ድምጸ አራዊቱን
¤ግርማ ሌሊቱን
¤የሌሊቱን ቁር
¤የመዓልቱን ሐሩር
¤ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ
ስለ ፍቅረ_ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና::
<< ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን የሚማጸኑ አሉ:: >>
<< አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን >>
3.የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ከግብጽ
እንዲመለስ የነገረበት (ተዝካረ ሚጠታ ለእግዝእትነ
ማርያም)
4.አፄ ይኩኖ አምላክ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ ኪዳነ ምሕረት ማርያም
2፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ
3፡ አባ ዳንኤል ገዳማዊ
4፡ ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሠ ሮሜ
5፡ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
6፡ ቅዱስ ሐርቤ ንጉሠ ኢትዮጵያ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይህን እኛንም ስለ እናቱ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መከራና ስደት ይቅር ይበለን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤12🥰4🙏4❤🔥3🕊3😍3😘2
✝ሐራ ሰማይ ሔር ሚናስ ሰማዕት፤
Jun 23, 2026✝ሐራ ሰማይ ሔር ሚናስ ሰማዕት፤
ገባሬ መንክራት ፥ ወፍጡነ ረድኤት፤
ለኃጥአን አግብርቲከ አውጽአነ እምአዘቅት፤
ወአድኅነነ እምዳግም ሞት!
❤21🥰5😘3😍2🙏1
#ሰኔ_15 #ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የሰማይ ጭፍራ የተባለ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው። የዚህም ቅዱስ አባቱ …
Jun 23, 2026#ሰኔ_15 #ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የሰማይ ጭፍራ የተባለ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው። የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና…
😍13❤8😘4🥰3🙏1
#ሰኔ_15
Jun 23, 2026#ሰኔ_15
#ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የሰማይ ጭፍራ የተባለ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው። የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና።
እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያንም ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።
ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን አለ ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል ሚናስ ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት ። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ አረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ አረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ።
መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።
ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ ። በዚያንም ጊዜ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊሎችን ሲያቀዳጇቸው አየ። ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና።
መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።
የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈፀም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።
በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት።
እነርሱም በባሕር ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱስ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጠለቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።
ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በግመል ላይ በጫኑት ጊዜ ግመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ግመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እምቢ አለ። አብዝተውም ደበደቡት ግመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው በዚያ ቀበሩት።
ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ፡፡ ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ፥ የቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበቀ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጉድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ። እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ።
ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ፡ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋር አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ። ለንጉሡም የቁስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው። ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ በዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አላት።
ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች። የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ሰሟም መርዩጥ ተባለች።
እግዚአብሔርም ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቁጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋራ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ።
=>ሰኔ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅድስት እንባ መሪና
4.ቅድስት ክርስጢና
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ_እና_ዘወርኀ_ኅዳር_15)
❤21😘6😍4🥰3❤🔥1🙏1
✝ብእሲ ሔር አባ አክራ ሐዲስ፤
Jun 23, 2026✝ብእሲ ሔር አባ አክራ ሐዲስ፤
ወማኅበሩ ክቡራን አብጥልማ ወዮሐንስ፤
ወእኁኁ ሰማዕት ዘይብልዎ ፊልጶስ፤
እለ አድምኡ ጸጋ በሥጋ ወነፍስ!
🥰13❤9😘3😍2💯2🙏1
ቅዱሳን (Saints)
Jun 23, 2026#ሰኔ_14
Jun 23, 2026#ሰኔ_14
#ቅዱሳን_አባ_አክራና_ዮሐንስ_አብጥልማና_ፊልጶስ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ አራት በዚች ቀን ቅዱሳን አባ አክራና፣ ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና፣ አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ።
መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አድረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም።
ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧችው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ቆረጡአቸው። ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጡ። እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዳሳን የፊልጶስን፣ ለአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገነዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቁጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ።
=>ሰኔ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን አበው ሰማዕታት (አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ
አብጥልማ: አባ ፊልዾስ)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤18🥰4😍2💯2😘2🙏1
ስንክሳር ዘተዋሕዶ pinned a photo
Jun 23, 2026ስንክሳር ዘተዋሕዶ pinned a photo
📢 ማስታወቂያ 📢
Jun 23, 2026📢 ማስታወቂያ 📢
👋 ሰላም የቻናላችን ውድ ቤተሰቦች
📢 ምን ማስተዋወቅ ይሻሉ? መንፈሳዊ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ብቻ ቻናሉ ላይ ለማስተናገድ እንፈልጋለን። የምታቀርቡት ማስታወቂያ ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ከሆነ ያናግሩን። እንዲሁም CHANNEL መግዛት የምፈልጉ አናግሩን።
👇🏾
👇🏾
👇🏾
➡️ @Top_Faye
🥰4❤3😍3😘3
✝ገብርኤል ሊቅ ዜናዌ ፍስሐ ሐዲስ፤
Jun 23, 2026✝ገብርኤል ሊቅ ዜናዌ ፍስሐ ሐዲስ፤
ወቃይናን ጻድቅ ወልደ ነቢይ ኄኖስ፤
ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ቢጸ ዐቢይ ኤጲፋንዮስ፤
ሰማዕታት ወአቡላግ ወስዱድ ማትያስ!
😘13❤9🥰4😍2🙏1
† ሰኔ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
Jun 17, 2026† ሰኔ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (ሕይወቱ መላእክትን የመሰለ)
2.አንድ ሺ ሰማንያ ስምንት ሰማዕታት (የቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበር)
3.አባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት
4.እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮጵያዊት (የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እህት)
5.የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤቱ (ግብጽ)
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
††† አምላካችን የቅዱሱን መንኖ ጥሪት: ትዕግስት: ጸጋና በረከት ያሳድርብን:: አሜን::
🥰12❤9😍4😘4
#ሰኔ_11
Jun 17, 2026#ሰኔ_11
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ አንድ በዚችው ቀን የመላእክት አርአያ ያለው የከበረ #ሰማዕት_ገላውዴዎስ የተጋድሎው ፍጻሜ ነው፣ ኢትዮጵያዊው ታላቅ ጻድቅ #አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
#ማር_ገላውዴዎስ_ሰማዕት
ሰኔ ዐሥራ አንድ በዚችው ቀን በጦርነት ድል አድራጊው ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነ የመላእክት አርአያ ያለው የከበረ ሰማዕት ገላውዴዎስ የተጋድሎው ፍጻሜ ነው። ይህ ቅዱስ ምድራዊ መንግሥትንና የዚህን ዓለም ክብር የናቀ ነበረ መልካም ገድልንም ተጋደለ።
የማይጠፋ ሰማያዊ መንግሥትንና የማያልቅ ክብርንም ወረሰ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብጥልዎስ ነው እርሱም ለሮም ንጉሥ ለኑማርያኖስ ወንድሙ ነው መልኩም እንደ እስራኤል ያዕቆብ ልጅ እንደ ዮሴፍ እጅግ ውብ ነበር።
እርሱም በጦርነት ላይ የበረታ ነበር የአንጾኪያ ተወላጆችም ይመኩበት ነበር። ስለ ደም ግባቱና ጽናቱ በሁሉ ዘንድ የተወደደ ነበር። እርሱንም ከመውደዳቸው ብዛት የተነሣ ጠላቶችን ድል እንዳደረጋቸው እነርሱም ድል ሁነው በውርደትና በብዙ ድንጋጤ ከፊቱ እንደሸሹ አድርገው ሥዕሉን ሥለው በከተማው መግቢያ በር ላይ ያኖሩት ነበር።
ቅዱስ ገላውዴዎስም የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር። የሮም ንጉሥም ዜናውን ሰምቶ ሊያየው ወደደ ልጁ ገላውዴዎስንም ይልክለት ዘንድ ወደ አባቱ ላከ እርሱም ላከለት። በደረሰም ጊዜ በደስታ ሊቀበለው ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋራ ወጣ በአየውም ጊዜ ደስ ተሰኘበት የሮሜ ከተማ ሰዎች ሁሉም ደስ አላቸው።
ከእነዚያ ወራቶችም በኋላ ከቍዝ አገር ሰዎችና ከአርማንያ ታላቅ ጸብ ተነሣ ይህም ቅዱስ ገላውዴዎስ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታምኖ ወደ እነርሱ ወጣ ድልም አደረጋቸው ንጉሣቸውንም ያዘው ጣዖቶቻቸውንም ሰበራቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን በአጸና ጊዜ እጅግ አዘነ ፊቅጦር የሚባል የኀርማኖስ ልጅ ወዳጅ ነበረው ሁልጊዜም የመጻሕፍትን ቃል ይሰሙ ነበር ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ያነቡ ነበር።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ ተስማሙ። በዚያ ጊዜም ሰይጣን በሽማግሌ አምሳል ታያቸው ያዘነላቸውም መስሎ እንዲህ አላቸው ልጆቼ ሆይ መልካሞች ጎልማሶች ናችሁ የነገሥታት ልጆችም ናችሁ። ስለ እናንተ እፈራለሁ አዝንላችኋለሁም እኔም ከንጉሡ ጋር ትስማሙ ዘንድ ለአማልክትም ታጥኑ ዘንድ እመክራችኋችለሁ ሲአዝዛችሁም ትእዛዙን አትተላለፉ እናንተም ክርስቶስን በቤታችሁ አምልኩት ይህ ንጉሥ ኃይለኛ ርኅራኄም የሌለው ጨካኝ ነውና አላቸው።
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገራቸው ሰይጣን እንደሆነ አስገነዘባቸው ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሐሰት አባት ሆይ ከእኛ ራቅ አንተ ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግ ትቃረናለህና አሉት። ያን ጊዜም መልኩን ለውጦ እንደ ጥቁር ባሪያ ሆነ እንዲህም አላቸው እነሆ ከንጉሥ አጣልቼ ደማችሁን እንዲአፈሰስ አደርገዋለሁ ሰይጣኑም ይህንን ብሎ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ሔዶ ፊቅጦርንና ገላውዴዎስን ካልገደልካቸው በአንተ ላይ ይነሣሉ አንተንም ገድለው መንግሥትህን ይወስዳሉ እነርሱም የመንግሥት ልጆች ናቸውና አለው።
ስለዚህም ንጉሡ ወደ ቅዱስ ገላውዴዎስ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ለጣዖታቱም እንዲሠዋ ለመነው የአባቱንም ሹመት ይሾመው ዘንድ ቃል ገባለት ሰምቶም አልታዘዘለትም። ንጉሡም ክፉ ቃልን ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን በድፍረት ይናገረው ነበር ያለ መፍራትም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ሰደበ።
ኀርማኖስም ቅዱስ ገላውዴዎስን ወደ ግብጽ እንዲልከውና በዚያ እንዲገድሉት ንጉሡን መከረው እርሱ እንደ ልጄ እንደ ፊቅጦር ዐመፀኛ ነውና። ንጉሡም ወደ እንዴናው ገዥ እንዲህ ብሎ ጻፈ ገላውዴዎስ ትእዛዛችንን አልተቀበለም ቃላችንንም አልሰማም አንተም ወደ ትእዛዛችን ይመለስ እንደሆነ በብዙ ድካም ሸንግለው ይህ ካልሆነ ራሱን በሰይፍ ቁረጥ።
ቅዱስ ገላውዴዎስም ወደ እስክንድርያ ይወስዱት ዘንድ ንጉሡ እንደ አዘዘ በአወቀ ጊዜ የእኅቱ ባል የሆነ ሲድራማኮስን ጠርቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን በማመን እንዲጸና ወገኖቹንም እንዲያጸናቸው አደራ አለውና በሰላምታ ተሰናበተው።
ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም በደረሰ ጊዜ አርያኖስ አይቶ ደነገጠ ተነሥቶም እጁን ሳመው እንዲህም ብሎ ለመነው። ጌታዬ ገላውዴዎስ ሆይ ይህን ሥራ አትሥራ የንጉሥንም ትዕዛዝ አትተላለፍ።
ቅዱስ ገላውዴዎስም እንዲህ ሲል መለሰለት ንጉሥ ያዘዘህን ልትፈፅም እንጂ በነገርህ ልታስተኝ አልተላክሁም አለው። መኰንኑም እስከሚቆጣ ድረስ እንዲህ እርስበርሳቸው ይነጋገሩ ነበር በመኰንኑም እጅ ጦር ነበረ ቅዱስ ገላውዴዎስንም ወጋው ነፍሱንም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ሰጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
ምእመናንም መጥተው የቅዱስ ገላውዴዎስን ሥጋ ወሰዱ በመልካም አገናነዝም ገነዙት ከቅዱስ ፊቅጦር ሥጋ ጋርም በሣጥን ውስጥ አኖሩት። የስደቱም ዘመን እስከሚፈጸም ጠበቁት። ከዚህ በኋላም የቅዱስ ፊቅጦር እናት ቅድስት ሶፍያ ወደ እንዴናው አገር መጣች የቅዱሳን ገላውዴዎስንና የፊቅጦርን ሥጋቸውንም ወስዳ ወደ አንጾኪያ አደረሰች።
የቅዱስ ገላውዴዎስ ሥጋ አስዩጥ በሚባል አገር ይኖራል የሚልም አለ።
#አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ
ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ለግብፃውያን አባቶች ትንቢት ይነግሯቸው የነበሩት ኢትዮጵያዊው ታላቅ ጻድቅ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ በሀገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌልን ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብፅ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብፅ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ፡፡ ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ፡፡ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብፃውያኑ ይቀኑባቸው ነበር፡፡
66ኛው የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ፡፡ በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ ለአቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው ‹‹ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባ ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ›› በላቸው ብሎ ነገራቸው፡፡ አቡነ ገብረ ኢየሱስም ‹‹ከመካከላችሁ ስሙ ገአርጊ የሚባል ጻድቅ አለና እርሱን ሹሙት›› ብለው መልአኩ የነገራቸውን መልአክት ነግረዋቸው አባ ገአርጊን በማርቆስ መንበር ላይ 67ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡
አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሸሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል፡፡ በወቅቱ የነበረው የግብፃውያኑ ንጉስ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል፡፡ የጻድቁ አባታችን ገድላቸው በጣና ይገኛል፡፡ ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብፅ በቁስቋም ገዳም ነው፡፡ ግብፃውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
😘11❤5🥰3😍2💯2
ቅዱሳን (Saints)
Jun 17, 2026#ሰኔ_10
Jun 17, 2026#ሰኔ_10
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥር በዚህች ዕለት ለክርስቲያን ወገኖች በዓለሙ ሁሉ ታላቅ ደስታ ሆነ መላእክትም በሰማያት ደስ ተሰኙባት፣ #ቅዱሳት_ደናግል_ደባሞንና_ብስጣሞን_እናታቸውም_ሶፍያ በሰማዕትነት ሞቱ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን
ሰኔ ዐሥር በዚህች ዕለት ለክርስቲያን ወገኖች በዓለሙ ሁሉ ታላቅ ደስታ ሆነ መላእክትም በሰማያት ደስ ተሰኙባት። በዚች ቀን ዕውነተኛ ምእመን ከሆነ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ የጣዖት ቤቶች እንዲዘጉ አብያተ ክርስቲያናትም እንዲከፈቱ ትእዛዝ ወጥቷልና። ደስታን የተመላች ያች መልእክት ወደ እስክንድርያ ከተማ እንደ ዛሬዋ ቀን በደረሰች ጊዜ ፈጽሞ ደስ ተሰኙ ወደ ግብጽ አውራጃዎችም ሁሉ ላኳት ምእመናን ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብር ከፍ ከፍ ማለት ደስ አላቸው። የጣዖታት ቤቶችንም ዘጓቸው አብያተ ክርስቲያናትንም ከፈቱአቸው እንደ ዛሬም በዚች ዕለት በዓል አደረጉ ይኸውም ቈስጠንጢኖስ በነገሠ በዐሥራ አንድ ዓመቱ ነበር እለእስክንድሮስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያ ዓመት ነበር።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሶፍያ_እና_ደናግል_ልጆቿ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱሳት ደናግል ደባሞንና ብስጣሞን እናታቸውም ሶፍያ በሰማዕትነት ሞቱ። እንዲህም ሆነ ስሙ ዋርስኖፍ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በወደዱ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ናባ አውራጃ እሊህ ደናግል ወዳሉበት ወደ ግሕሙን ደርሶ በዚያ አደረ።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጦለት ከዚህ ለምን ትተኛለህ ተነሥተህ ተጋደል ለአንተና ሰማዕት መሆን ለሚሹ ሁሉ አክሊል ተዘጋጅቷልና አሁንም ተነሥተህ ወደ መኰንኑ ሒድ በፊቱም ቆመህ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመን አለው።
ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ራእይን እንዳየ ለቅዱሳት ደናግል ነገራቸው። ሲነጋም ተነሥተው ከእርሱ ጋራ ወደ መኰንኑ ሔዱ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ታመኑ። መኰንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸውና ወደ ወህኒ ቤት ጨመራቸው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ከዚያ አውጥቶ ከቅዱስ ዋርስኖፍ ጋራ ወደ ስንሑር ላካቸው እናታቸውም ትከትላቸው ነበር።
መኰንኑም ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ አጸናቸው ቊስላቸውንም ፈወሰ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከእርሱ ጋር ወደ ሀገረ ፃ ይዞአቸው ሔደ። የጣዖታቱ ካህናትም ጣዖታቱን እንደምትረግም ስለ ቅድስት ደባሞን ነገሩት እንዲሁም ባልጀራዋ ዮና የምትባል ሴት አንዳለች ነገሩት እነርሱም ኀብራቸው በየራሱ የሆኑ መልካም ልብሶችን እየሠሩ ለምግባቸው ይሸጡ ነበር የተረፋቸውንም ይመጸውቱ ነበር። መኰንኑም የዮናን ዜና ሰምቶ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጥ ባለሰይፉን ላከው የሰያፊውም ስም አውሎጊስ ነው።
ወደርሷም በቀረበ ጊዜ ፊትዋ እንደ መላእክት ፊት ብርሃንን ተመልቶ አየና ፈራ እርሷንም ወደ መኰንኑ እንዲወስዳት እንጂ እንዳይገድላት የእግዚአብሔር ጸጋ አስገነዘበችው ቤተ ሰቦቿም ተሰነባብተዋት ጸንፋ ከሚባል አገር ወጣች ወደ ሀገረ ፃ ደርሳም መኰንኑን ተገናኘችው ከቅዱስ ወርስኖፍና ከባልንጀሮቹ ጋራ እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ።
ሰያፊው አውሎጊስም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነና ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ እንዲሁም እሊያን ቅዱሳት ደናግልንም ራሳቸውን ቈረጧቸው ገድላቸውንም ፈጽመው የድል አክሊልን ተቀበሉ።
ቅድስት ደባሞንን ግን ጽኑዕ ሥቃይ ያሠቃዩአት ዘንድ በመንኰራኵር ላይ ሰቀሉአት። በዚህ ሥቃይም ውስጥ ለብዙ ቀኖች ኖረች የእግዚአብሔር መልአክም ያጸናት ያስችላትና ቊስሎቿን ይፈውሳት ነበር መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገባት በዚያም ጥቂት ቀን ኖረች ወደ ፍርድ ሸንጎም አስቀርቦ ለአማልክት ሠዊ አላት ባልሰማችውም ጊዜ ራሷን እንዲቆርጡ አዘዘ።
ራስዋንም ሊቆርጡ ከከተማ ወደ ውጭ በአወጧት ጊዜ ሴቶች ሁሉ እያለቀሱ ከብበዋት ነበር እርሷ ግን ፈጽማ ደስ ይላት ነበር። ራስዋንም በሰይፍ ቆረጥዋት እንዲሁም እናቷንና እኅቷን በሰይፍ ቆረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የድል አክሊልን ተቀበሉ።
† ሰኔ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
2.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት (ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት)
4.ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን (የቅድስት ሶፍያ ልጆች)
5.ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት
† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤23😍9😘5💯4🥰3
#ሰኔ_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ #ነቢይ_ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞…
Jun 17, 2026#ሰኔ_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ #ነቢይ_ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሳሙኤል ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ ነቢይ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና ነው። እነርሱም…
🥰16❤11😘3😍2
#ሰኔ_9
Jun 17, 2026#ሰኔ_9
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ #ነቢይ_ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ነቢዩ_ቅዱስ_ሳሙኤል
ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ ነቢይ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና ነው። እነርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው። ሐናም መካን ነበረች ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለደች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት በቤቷም ሦስት ዓመት አሳደገችው።
ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ። የካህኑ የኤሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር የሚታይ ራእይም አልነበረም።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ሌሊት እንዲህ ሆነ ኤሊ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ዐይኖቹም መፍዘዝ ጀምረው ነበር ማየትም አይችልም ነበር። የእግዚአብሔርንም መብራት አብርቶ ለማሳደር ገና አላዘጋጁም ነበር ሳሙኤል ግን በቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት አጠገብ ተኝቶ ነበር።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው እነሆ እኔ አለሁ አለ። ወደ ኤሊም ፈጥኖ ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ እኔ መጣሁ አለው ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰኽ ተኛ አለው ሔዶም ተኛ።
እግዚአብሔርም ዳግመኛ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ኤሊ ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ መጣሁ አለው። ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ አለው። ሳሙኤልም ከዚህ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በራእይ ገና አላወቀውም ነበር ቃለ እግዚአብሔርም አልተገለጠለትም ነበር።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሦስተኛ ጊዜ ጠራው ተነሥቶም ወደ ኤሊ ሔደ ስለጠራኸኝ እንሆ መጣሁ አለው ኤሊም ያንን ልጅ እግዚአብሔር እንደጠራው አሰበ። ልጄ ተመልሰህ ተኛ የሚጠራህ ካለ እኔ ባርያህ እሰማለሁና ጌታዬ ተናገር በለው አለው ሳሙኤልም ሒዶ በመኝታው ተኛ።
እግዚአብሔርም መጥቶ እንደ መጀመሪያው በፊቱ ቁሞ ጠራው። ሳሙኤልም እኔ ባሪያህ እሰማሃለሁና ጌታዬ በል ተናገር አለው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን የሰማው ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ይይዝ ዘንድ እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ የተናገርሁት ቃሌን አደርጋለሁ።
በዚያችም ቀን በኤሊና በወገኑ ላይ የተናገርኹትን ሁሉ አጸናለሁ እጀምራለሁ እፈጽማለሁም። ልጆቹ የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለዋልና እርሱም አልገሠጻቸውምና በልጆቹ ኃጢአት እኔ ወገኑን ለዘላለም እንደምበቀለው ነገርሁት። ስለዚህም ነገር በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም ቢሆን የኤሊ የወገኑ ኃጢአት እስከ ዘላለሙ ድረስ እንዳይሠረይ ራሴ እንዲህ ብዬ ማልሁ። በኤሊ ወገኖችና ልጆች ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ።
ከዚህም በኋላ የቂስ ልጅ ሳኦልን ቀብቶ ለእስራኤል ልጆች ያነግሠው ዘንድ እግዚአብሔር ሳሙኤልን አዘዘው እንዲአነግሥላቸው ለምነዋልና። ሳኦልም የልዑልን ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ዳግመኛ ለእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የዕሴይ ልጅ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ይህን ነቢይ ሳሙኤልን ዳግመኛ አዘዘው። ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሉክያኖስ
በዚህችም ዕለት ቅዱስ ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበረ የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በአየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ አደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና።
ዳግመኛም እንዲህ አለ ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ አምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው። ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ አምናለሁ ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባላት።
እርሱ ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ እንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ።
ከዚህ በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው።
ቅዱስ ሉክዮስን ግን እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እነዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
† ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
2.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ
† ወርኀዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ)
3. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤24🥰5❤🔥2😍2😘2
🌷#ሰኔ_8 #የእመቤታችን_ማርያም_ቅዳሴ_ቤት አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የ…
Jun 17, 2026🌷#ሰኔ_8 #የእመቤታችን_ማርያም_ቅዳሴ_ቤት አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው። ይህም እንዲህ…
❤18🥰5💯4😍3😘3
🌷#ሰኔ_8
Jun 17, 2026🌷#ሰኔ_8
#የእመቤታችን_ማርያም_ቅዳሴ_ቤት
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው።
ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ።
ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው። በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።
† ሰኔ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
2.የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ
3.ቅድስት ትምዳ እናታችን
4.ቅዱስ አውሎጊስ
5.አባ አትካሮን
† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)
እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
❤22😍4🥰3😘3💯2🙏1
#ሰኔ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ እረፍቱ ነው፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው #አባ_አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞…
Jun 17, 2026#ሰኔ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ እረፍቱ ነው፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው #አባ_አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እረፍቱ ነው። ይህም ቅዱስ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው…
😍12❤11🥰10😘5🕊3
#ሰኔ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ እረፍቱ ነው፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው #አባ_አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞…
Jun 17, 2026#ሰኔ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ እረፍቱ ነው፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው #አባ_አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እረፍቱ ነው። ይህም ቅዱስ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው…
የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ።
† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው)
3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ)
4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ)
† ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
❤16🥰3😍2😘2❤🔥1💯1
#ሰኔ_7
Jun 17, 2026#ሰኔ_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ እረፍቱ ነው፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው #አባ_አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ
ሰኔ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እረፍቱ ነው። ይህም ቅዱስ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ነው።
ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::
አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ጳጳሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው።
የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ። ጳጳሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት። እርሱም:- ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ፣ ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ እንዲሁም ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው። ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ጳጳሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል።
ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት። በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል። በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን። አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት። እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው። "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል። ፈጣሪንም አመስግነዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን፣ ዕጸበ ገዳምን፣ ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል። በድንግልናው ጸንቶ ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል። በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል::
ቅዱስ ያዕቆብ በዘመኑም የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል፣ ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል፣ በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል፣ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::
በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚህች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_አበስኪሮን
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው አባ አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ።
ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዙ በደረሰች ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ ቅዱስ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት።
መኰንኑም ወደ ሀገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስ፣ ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮን ጋራ ተስማሙ።
በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ።
የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ ይህንም ሁሉ አደረጉበት።
ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር።
ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም።
ያም መሠርይ የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ።
ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለቤት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል አንተን ይቀጣሃል አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ።
በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን አንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ከፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞቱ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ አላቸው እነርሱም ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራችው።
እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላዕላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅድሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት።
🥰13❤9😍2🕊1💯1😘1
#ሰኔ_6 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ስድስት በዚች ዕለት ከእስክንድርያ ከተማ የሆነ #መነኰስ_አባ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱሳን_አውሳብዮስ_ታማን_ሐርዋግና_ባኮስ የተባሉ የሀገረ እስና አራት መኳ…
Jun 17, 2026#ሰኔ_6 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ስድስት በዚች ዕለት ከእስክንድርያ ከተማ የሆነ #መነኰስ_አባ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ሞተ፣ #ቅዱሳን_አውሳብዮስ_ታማን_ሐርዋግና_ባኮስ የተባሉ የሀገረ እስና አራት መኳንንት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #መነኰስ_አባ_ቴዎድሮስ ሰኔ ስድስት በዚች ዕለት ከእስክንድርያ ከተማ የሆነ መነኰስ አባ ቴዎድሮስ…
❤21🥰9😍8🕊2😘2
ለማንበብ ከዝርዝሩ ውስጥ አንድ ርዕስ ይምረጡ