August 22, 2026 ዜና (News)
  • 8
  • በአጥቢያው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐ ግብር ተካሔደ።

    በአጥቢያው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐ ግብር ተካሔደ።

    የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ምግባረ ሰናይ ክፍል ከሚያከናውናቸው ዋና  ተግባራት  መካከል የአጥቢያውን ምእመናን  በማስተባበር  ነድያንን አቅመ ደካሞችን በተለያዩ መንገዶች የመደገፍ እና አጽዋማት ሲፈጸሙ የማስፈሰክ ተግባራት ይገኙበታል።

    ክፍሉም ከሚያከናውናቸው ከእነዚህ በጎ ተግባራት መካከል በዛሬው ዕለት  የፍልሰታ ጾም መፈጸሙን አስመልክቶ የአጥቢያውን ምዕመናን በማስተባበር  ከ800  በላይ ለሚሆኑ በአጥቢያው አካባቢ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያን  የማስፈሰክ መርሐ ግብር አከናውኗል።

    በመርሐ ግብሩ ላይ  የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ምክትል አስተዳዳሪ ሊቀ ሕሩያን ቀሲስ ምስራቅ ወግደረስ ፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ፣የደብሩ  አገልጋዮችና ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች ተገኝተዋል ።

    በመጨረሻም ይህን  በጎ ተግባር በማጠናከር እና በማስፋት ፍቁረ  እግዚእ  ሰንበት ት/ቤት  እየሰራ ያለውን ገዳማትና አድባራትን የመደገፍ እንዲሁም በየሳምንቱ በዕለተ ሰንበት እሐድ ከቅዳሴ በኃላ ነዳያንንና አቅመ ደካሞችን ቁርስ የማብላትና በዘላቂነት የማቋቋም ስራ ምእመናን በልዩ ልዩ መንገድ በመደገፍ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፏል።
    🙏2