August 16, 2026
ዜና (News)
6
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት መታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐት ተካሄደ።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት መታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐት ተካሄደ።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉበትን ፲፬ኛ ዓመት መታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐት ተካሄደ።
በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
@EOTC TV