August 03, 2026 ዜና (News)
  • 9
  • የብፁዕ አቡነ ቀሌምጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መግለጫ።

    የብፁዕ አቡነ ቀሌምጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መግለጫ።

    በጌታ የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ። ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸው ይከተላቸዋልና ። ራዕ ፲፫ ÷ ፲፬

    #በጻድቃኔ_ማርያም_የመሬት_መንሸራተት_አደጋ_ተከሰተ።
    በሰሜን ሸዋ ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።

    ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ መዝነብና የመባርቅት ድምፅ በታላቋ ገዳማችን በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ በድንገት በመከሰቱ ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ እጅግ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ኀዘን በመድረሱ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል ።

    በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ድንገተኛ አደጋም የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ሲያልፍ በ3 ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሁለት ወገኖቻችን ላይ መለስተኛ ጉዳት ደርሶብን በከፍተኛ የመርዶ ኀዘን ውስጥ እንገኛለን ።

    በዚህ ሰኣት የሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

    በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ መርዶ ሀገረ ስብከታችን የተሰማውን ጥልቅና መሪር ኀዘን እየገለጽን እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ለተጎዱት ፈውስን ላዘኑት መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ ከዕንባ ጭምር ጋር ከልባችን እንመኛለን።
    አባ ቀሌምንጦስ
    የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

    መረጃው የአቡቀለምሲስ ሚዲያ ነው።
    🥰1🙏1