July 16, 2026 ዜና (News)
  • 26
  • የሰ/ት/ቤቱ የ3 ዓመት የአገልግሎት ሪፖርት በጠቅላላ ጉባኤው ጸደቀ።

    የሰ/ት/ቤቱ የ3 ዓመት የአገልግሎት ሪፖርት በጠቅላላ ጉባኤው ጸደቀ።

    የደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና  መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤ/ክ የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት በ2016 የተመረጠው  ሥራ አመራር 3ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ  ያለፉትን 3 ዓመት የአገልግሎት ሪፖርት የሰ/ት/ቤቱ አባላት  በተገኙበት በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ለጠቅላላ ጉባኤው  አቅርቧል ።

    በጠቅላላ ጉባኤው ላይ በሰንበት ት/ቤቱ  ባለፉት 3 ዓመት  የተከናወኑ አገልግሎቶችን በተመለከተ ሪፖርት በሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ ዳግም ጌታቸው ቀርቧል።

    በአገልግሎት ሪፖርት ዙሪያ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመቀጠል የክፍላት ተጠሪዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ለ3 ዓመታት በአገልግሎት አብረዋቸው ለደከሙ ለሰንበት ት/ቤቱ  አባላት የምስጋና እና የይቅርታ መልእክት አስተላልፈዋል።

    በመጨረሻ የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት አመራሮች  ለአገልግሎቱ መሳካት የተባበሩ የአገልግሎት ሒደት በጥሩ መንገድ እንዲሳካ ላደረጉ  አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በአገልግሎት ሂደት የተከፉ አባላት ካሉ  አመራሩን በመወከል የይቅርታ መልእክት የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ጽጌረዳ ገ/ዮሐንስ አስተላልፋ በአንድነት በምስጋና መዝሙር መርሐ ግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል ።
    ❤1🙏1